[Read in PDF] ጋዜጠኛ ሀብታም፡ መዝሙር ደስታ ትባላለች፡፡ የአዲስ አበባ መስተዳድር የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ እንዲሁም የዜና አገልግሎት ድርጅቱ ሪፖርተር በመሆን አገልግላለች፡፡ ጋዜጠኛ ሀብታም: በዴንማርክ ኮፐን ሀገን ከዲሴምበር 5 እስከ 19 ድረስ ሲካሄድ የነበረውን አለም አቀፍ የአየር ልቀትን መጠን ለመወሰን በተደረገው ጉባኤ ላይ ለመዘገብ ነበር ወደ አውሮፓ የተጓዘችው፡፡ ጋዜጠኛዋ ስራዋን በመሃል በማቋረጥ ለስራዋ የያዘቻቸውን መሳርያዎች በመያዝ የአቶ መለስን መምጣት ይቃወሙ ከነበሩት ወገኖች ጋር ተቀላቅላለች፡፡ ከስካንዲኒቭያ ባልደረባችን አነጋግሯት እንደሚከተለው አቅርቦታል::
በመጀመሪያ ራስሽን ብታስተዋውቂን?
ሀብታም:- ስሜ ሀብታም፡ መዝሙር ደስታ እባላለሁ፡፡ የተወለድኩት በጎንደር ክፍለ ሀገር ሲሆን፣ ሥራዬ የቴለቢዥንና ራዴዮ ጋዜጠኛ ስሆን አገለግልበት የነበረውም መሥርያ ቤት፣በአዲስ አበባ መስተዳድር፣ የቴሌብዥንና ራድዮ ጋዜጠኝነት ነበር፡፡
እዚህ ለምን መጣሽ?
ሀብታም:- የመጣሁት በዴንማርክ ኮፐን ሀገን ከዲሴምበር 5 እስከ 19 ድረስ ሲካሄድ የነበረውን አለም አቀፍ የአየር ልቀትን መጠን ለመወሰን በተደረገው ጉባኤ ላይ ለመዘገብ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ በተለያየ ወቅት ይደረጉ የነበሩትን የየእለቱን ውሎ ስዘግብና ሳስተላልፍ ከርሜ፣በተለይ በመጨረሻዎቹ ሳምንታት ውስጥ ረቡዕ የጠቅላይ ሚንስትሩን ውሎ ከዘገብኩ በኋላ፣ሀሙስ ጠቅላይ ሚንስትሩን የሚቃወሙትን ኢትዮጵያዊ ወገኖች ተቃውሞ ዘግቤ፣በማስተላለፌ፣ሀይለኛ ተግሳጽና ማስፈራራት አገር ቤት ካሉት አለቆቼና፣ጠቅላይ ሚንስትሩን ካጀቡት ደህንነቶች ስለደረሰብኝ፣አርብ እለት የተረከብኳቸውን መቅረጫ ድምጽና የመሳሰሉትን መሳርያዎቼን በመያዝ ካገሬ ልጆች ከሆኑት የአቶ መለስን መምጣት ከተቃወሙት ወገኖች ጋር ተቀላቀልኩ፡፡
ከጋዜጠኝንት ሞያሽ ጋር ተያይዞ በሃገሪቱ የፕሬስ ነጻነት አለ ትያለሽ?
ሀብታም:- በአገሪቱ ሀሳብን በነጻነት መግለጽና፥መጻፍ የሚሉት መሠረታዊ መብቶች በወረቀት ላይ የሰፈሩ ቢሆንም፣እነኝህ መብቶች ለአፍ ፍጆታና ፈረንጅን ለማጭበርበርያ የወጡ ህግጋት እንጂ በመስክ ላይ ማንኛውም የመንግሥት ጋዜጠኛም ሆነ የነጻ ጋዜጠኛ፣ሀሳቡንና እምነቱን በነጻነት የማይገልጽበት፣ለመዘገብም ወጥተን ያሰባሰብነውን የህዝብ ድምጽና፣የታዘብነውን ሁኔታ ለመግለጽ ስንሞክር በመንግሥት ሃይሎች ሥራዎቻችን ተውስደው እንደገና ባዲስ መልክ ከውነታው ውጭ ተቀባብተው የሚቀርቡበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ በዚህ የተሳሳተ ዘገባ፣ህብረተሰቡ በኛ የመንግሥት ጋዜጦች ላይ ከፍተኛ ጥላቻ ያለው ሲሆን፣ባጠቃላይ ለመንግስቱ የግሉ ውሾች፣በህዝቡ ደግሞ ክፉኛ የምንጠላ ሆነናል፡፡
ይህንን የበለጠ ታብራሪልኛለሽ?
ሀብታም:- ለምሳሌ በዘገባ ወቅት የመስክ ስራ ላይ ሆኜ ያየሁትንና የታዘብኩትን የህብረተሰቡን ችግር አጠናቅሬ ወደቢሮ በምመለስበት ወቅት የላይኛው የምንግስት አካል ዘገባዎቼን ወስዶ እንደገና በመከለስ፣ 50 ሰው ተገኝቷል ያልኩትን መላው ህዝብ በመደገፍ ክ500 በላይ ሰው ተገኝቷል በሚል ፈጠራ ዜናው ተለውጦ የሚቀርብ ሲሆን፣ በተለይ የሪፖሩቱን ዘገባ ለነርሱ በሚያስደስት ሁኔታ ካላቀረብኩት፣ በግምገማ ወቅት፣ የነፍጠኞችን አቋም ነው የምታስተጋቢው በሚል ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ደርሶኝ ነበር፡፡
በግሉ ብቻ ሳይሆን በመንግስትም ጋዜጠኞች በነጻነት የመስራት መብት የለም ነው የምትይው?
ሀብታም:- ምንም አይነት ነጻነት የለም ከላይ እንደገለጹት፣ያልተገነባውን ተገነባ፣ያላደገውን ኢኮኖሚ በዚህ ቁጥር አድጓል ማለት የተሰጠንን ዘገባ ብቻ ነበር የምንሠራው በቲዎሪ መብት እንዳለን መብት ተሰጥቶን ዘግበን ስንመጣ ግን ያው የሚገጥመን ያው የተለመደ አሰራር ነው፡፡
አሁን በአኢትዮጵያ ያሉትን የነጻ ፕሬስ ውጤቶች እንዴት ታይያቸዋለሽ?
ሀብታም:- ነጻው ፕሬስ በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት አለ ማለት ውሸት ነው፡፡ ለአለም ህብረተሰብ ማታለያ ሲባል በጣት የሚቆጠሩ እንዲንቃሳቀሱ ከመደረጉ ውጭ በተግባር ሲታይ ጋዜጠኞቹን በክፍታኛ ቅጣት በማስፈራራት ተሸማቀው እንዲሰሩ እየተደረገ ነው፡፡ የፕሬስ ፈቃድ የተከለከሉም አሉ፡፡ ማህበሩ በስም እንጂ በእንቅስቃሴ ሲታይ ምንም በጉልህ የሚታይ ስራ አይሰራም፡፡ ባጠቃላይ የወያኔው ተለጣፊ ማህበር ብቻ ነው በነጻ ጋዜጠኞች ማህበር ስም የሚንቀሳቀሰው፡፡
በመንግስትና በህዝብ መሀከል ያለው ክፍተት እንዴት ነው?
ሀብታም:- በመንግስትና በህዝብ መሀከል ያለው ክፍተት የትዬ ሌሌ ነው፡፡ ህዝብ መንግስትን አያምንም፣መንግስትም ህዝብን አያምንም፡፡ መንግስት በህዝብ ላይ ከፍተኛ ፍርሀት ስላለበት ባጠቃላይ ሲታይ ባህር ላይ ያለ ብቸኛ ደሴት ነው የሚመስለው፡፡ በተለይ አሁን ደግሞ የምርጫው ወቅት በመድረሱ፣ ህዝብን በማሸማቀቅ፣ማስፈራራት በሚል ዘዴ ሚዲያውን በከፍተኛ ሁኔታ እየተጠቀመበት የማይፈልጋቸውን የሚያስደነብርበት አሰራር ነው እየተከተለ ያለው፡፡ ለዚህም ምሳሌ አዲስ ነገርን ማስታወስ ይበቃል፡፡


December 28th, 2009 at 7:47 am
Given the opportunity this is something everybody who went through the corrupt system of Woyane would obviously say. We need to make a systematic resistance any time any where possible to expose the atrocities perpetuated by Woyane narrow ethnicists.
December 28th, 2009 at 10:40 am
Dear; Habtam
WELL COME TO THE FREE WORLD!
December 28th, 2009 at 11:07 am
Kudos Habtame,
You did what anybody who was serving the genocidal Meles’s regime should do when there is an opportunity. Now it is time for you to put together all the information that was available to you because of the nature of your jouranlist profession, the systematic killing and detention of all Ethiopians that raise their voice against the mother’s breast biting wild animal Woyane, and expose it generally to the whole world and particularly to the governments that are supporting the murderer regime. These will help these governments that are pouring their money to the Woyane regime in the name of coopertation for development but rather fatten the pockets of Meles and his cronies to come to their senses. If they don’t, it will be one of the evidences that will show glarely that they were knowingly helping and collaborating with a murderous government when a democratic government replaces the Meles regime and bring him to justice.
December 28th, 2009 at 11:27 am
If so why about 40,000 people are subjected to run even near the government palace as a great run every year by the government of Ethiopia if there is a fear from the people.
I think politics is stopped now do something else!!!!!
December 28th, 2009 at 12:43 pm
Demil
get a life. It does not seem you know what you are talking about or you are out of touch and do not read, listen or are willing to accept what you are seeing with your own eyes. I am sure you are not blind as you were able to put your fingers on the keyboard and were able to type your meaning less sentences.
Did you not hear or read on almost all Ethiopian prodemcracy sites the runners were denouncing the genocidal Meles government and asking for the release of the Heroine Birtukan Mideksa and other political prisoners or are your eyes and ears covered by a fat tissue that was the result of the blood money you get from your creator and boss Woyane. Let us know.
December 28th, 2009 at 12:52 pm
……ወንድ ተኩል ..የሴት ወንድ…መለስ እና አገዛዙ ማለት ይሄ ነው በቃ:: በውሸት ያለ እና በውሸት የሚኖር…viva ginbot 7
December 28th, 2009 at 1:02 pm
ደምል; ምነው የካድሬ ስራህ ቢበቃህና ፕሮቶጋንዳህን ብታቆም:: ለነገሩ ነጻ ሃገር ለሚኖር ካድሬ ድንጋይ ራስ ብትሆን ነው እንጂ እስካሁን ይገባህ ነበር:: እስቲ ጋዜጣ አንሳና አንብብ ምናልባት ይገለጽልህ ይሆናል::
የሚቀጥለው የካድሬዎች ስብሰባ ላይ ደግሞ ለለውጥ ጥያቄ ጠይቅ እንደበግ ትእዛዝ ከምትቀበል:: አሁን የቀረህ ቀንድ አብቅለህ በአራት እግርህ መሄድ ነው::
ብለህ ብለህ የአራባ ሺህ እሯጭ የወያኔን ጥሩነት ይገልጻል ትላለህ? አልፈህ ወገኖች አገራቸው ጥለው የማይሰደዱት ወያኔን ወደው ነው ልትል ነው:: እያደር መግማት ሆነ ኑሮህ::
December 28th, 2009 at 1:30 pm
ጋዚጠኛ ቅድስት ሀብታም እንኻን ከመከራ ከጭንቅ አወጣሽ በደረሰብሽ ሕሊናዊ ጫና የገባሽበት ግዲታና በሞያሽ(ፕሮፊሽናል)ልትውጭ ባለመቻልሽ ለዚህ ስደት በቅተሻል ሁሉም ግዲታውን ለመውጣት ሃላፊነት መውሰድ የማንኛውም ፍጡር ተገቢ ብሂራዊ ተግባሩ ማድረግ አለበት እንግዲህ ወደዋናው የጋዚጠኛ ሞያና ተግባር ግዲታ ብን መለከት እውነትን የሚነግር በቦታው የነበረ ሕዝብን የሚያነቃ አይምሮን የሚያሰፊ የሕዝቦች መድረክ የችግሮች መፍቻ ማቀራረቢይ መሆኑ ግልጽ የሆን መረጃ ያለው የሰለጠኑት ዓለማት ያደጉበት ለመሆኑ ሁሉም ይስማማል
በተለይ በሃገራችን ጋዚጠኛ ማለት የገዥውን መደብ የውሸት የተንኮል የመለያየት የመደንቆር እውነትን በመደበቅ ጊዚያዊ ሕይወትን በሚሰጠው መሃያ ተገዥ በመሆን ሕሊናን መሽጥ በመሆኑ የስርዓቱን ማመጎስ በሕዝብ ማሾፍ በመሆኑ እንዲያስቡበት እንዲነቁ ዛሪ ነገ እንዳል ሆነ ያለው የሚቀየር መሆኑን መገንዘብ አስፈላጊ ነው
ጋዚጠኛ ማስተማር ያለበት ግዲታ ሁሉም ዚጎች በፍትሕግና በርትእ መገዛት አለባቸው ትንሾችም ይሁኑ ትልቆች የሕብረተሰብ አባሎች ሙሉ በሙሉ የመብት ነጻነት መጎንጸፍ እንዳለባቸው ሓሳባቸውን የመግለጽ የመጻፍ የመናገር የመሰብሰብ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ የመደራጀት ነጻንት ዋስትና ያስፈልጋችዋል
እነኝህን መብቶች መንግስት በምንም አይነት መንገድ የመጻፍ የመናገር መብቶች መቆጣጠርና ማገድ ካደረገ መንግስት በጠና ታማል ማልት ነው ሕብረተሰቡም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባታል ማለት ነው ዲሞክራሲ ብለን ስንለፍፍ ሕዝቦች ያለመፍራት ሓሳባቸውንና ስሚታቸውን ሲገልጹ ጠናማ ሊሆኑና ሊያድጉ የሚቻለው ለምሳሊ ያህል በነጻ አስተሳሰብ ያደጉ ሕጻናት ያላቸው ያስተሳሰብ በራስ መተማመን በነጻ ካላደገው ማለት እንደኛው ሕብረተሰብ በዩልኝታ በፍራቻ ተውጦ ሲረገጥ ሲለገጥበት ይኖራል ስለዚህ መብትን ማስከበር የያንዳንዱ ስው
December 28th, 2009 at 1:52 pm
Thanks EMF for the news, it was very informative
December 28th, 2009 at 2:16 pm
This is another opportunist.She has been abroad many times and now suddenly she is against the democratic government EPRDF.I have to tell you hat this girl is fool and she was forced to seek asylum by the vocal diaspora.Mark my word,she is going to regret her decision.If she had self confidence like the great Teddy Afro,she would have said to vocal diaspora to go to hell.
December 28th, 2009 at 2:25 pm
That is right. People dont believe government. but I still doubt your intenstion to defect my sister. You just want to get better life. that is all. anyways hodam goes another hodam will replace. The word hodam should not refer only to people who are serving to the rulling party though. Look in your selves. how many of us are willing to stand for our freedom up to the last point? very few! people are like birtukan not like these journalists.
December 28th, 2009 at 2:38 pm
You are hero!
What is hero? fighting for the truth!
The ethiopian professionals, especially lier economists and journalists work to get bread from the government. You have chosen the truth and one step to improve the lives of the people.
Unity First
December 28th, 2009 at 3:14 pm
Welcome to your new home Habtam Mezmur , we hope your fight for freedom and equality will be contnue . This TPLF Govt. clearly in the business of high jacking the minds of free thinking society and changed into the mind of a Zombie society.
December 28th, 2009 at 4:07 pm
I don’t trust her. I don’t trust anybody who would just jump of the wagon suddenly. Interview her, get info from her, but don’t even dare to include her in any real political activities.
I don’t even trust the adisneger group,let alone this one, who is part of the meles entrouge.
December 28th, 2009 at 5:23 pm
What a decision. What a gallant woman. I am proud of her. I am proud not of her being an Ethiopian but a female as well. We are having a lot of Burtukan and a lot of Taitus NOW. Iranian protest demonstrated how women are by far organized to boldly fight their ruthless enemies.
You Ethiopian males, Go G7 or to EPPF and die with your brothers in Arms. Peaceful struggle is a fiasco. Do not chicken here. Either you shape out or ship out. You are dying any way.
The bravery comes from a female at times when we are devoid to see heroic men like Belay Zeleke and Balcha Aba Nefeso.
Go and fight the fight. The mountains are wanting you. Either you go or contribute with what you have.
I know the mere action of a simple individual woman surprises everyone. if this action is united, guess what change it will bring about.
As I said, let us at least organize and do something to this girl in her sustainance and raise money to pay her rent till she picks up.
Let us tell her that help is on the way. Donot gossip take action.
December 28th, 2009 at 5:27 pm
@Demil. Your comment is like your name. Tire. Tinish mebsel yikerehal. do not expose your stupidity dude..
December 28th, 2009 at 6:34 pm
you are so wise. you did it on right place and on right time.
as you know they are killer. you are the icon for the rest of journalist that are serving woyanie.
GOD BELESS ETHIOPIA
December 28th, 2009 at 9:59 pm
When the Temprature of Diaspora politics diminish the case of Biirtukan raises on keyboard.
But who are these people(politicians)?
December 28th, 2009 at 11:45 pm
መለሰ ዜና ዊ ! ከኮፕን ሃገን ሲመለስ ወደ ኢትዮጵያ ቤተመንግስቱ ውስጥ የሚጠብቁት ቆሌዎቹን ሰብስቦ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጥ..የተከበራችሁ እንግዶች ምንም ጉዟችን ያሰብነውን ያህል እንኳ ባናገኝም,የተመኘነውን አልነሳንም…
ካለ በኋላ ረጋ ባለ ድምጽ ቀና በማለት የግምባሩ ፈገግታ እያስታወቀበት…ኢህአዴግ ከመቸውም በላይ በዚህ ኩሩ ነው ::..ካለ በኋላ ጭብጨባ በጉጉት ይጠብቁ የነበሩቱ ፈጠጤ ዓይኖቹ አዳራሹን ረዘም ባለ ጭብጨባ ሞሉት:: በጣም ረጅም ለዲክታተሮች ብቻ የሚደረግ ጭብጨባ:ጭብጨባው ሊበርድና ሊቆም የቻለው በጁ እንዲቀመጡ ምልክት ከሰጠ በኋላ ነው ::
ምንይላል ባትሉኝ በዚያቹ ምሽት ትልቅ ድግስ ተደግሷል : ዙርባ ዙርባ ጫት ተግዟል ,ሰንጋም ተጥሏል ,ውስኪም ፈሷል:: የድሉን ወቅታዊ ምሽት ለማዳመቅ በጥንቃቄ ተመርጠው የተጠሩቱ ተወዛዋዥና አቀንቃኞች ሆይ- በሌያቸውን ሲያተራምሱት አድረዋል::ሊነጋጋ አካባቢ የስራ ቀን መሆኑ ትዝ ያላቸው እኝህ ታታሪ የስራ አርበኛ, ብቸኛ ጭብጨባ ..ጨብ..ጨብ!ጨብ! እንዳደረጉ ያ ሁሉ ሁካታ ዕሩምታ ባንድ ጊዜ ጸጥ!ለጥ!ዕርጭ ! አለ
“..የተከበራችሁ እንግዶች ሁላችንንም አመስግናችኋለች..” ከማለታቸው ..ጭብጨባው ፉጨት በተቀላቀለበት መልክ ተናጋ..ክቡር ጠቅላይ አጠገባቸው ባገኙት ባዶ የኮኛክ ጠርሙስ ጠረጰዛውን ተም !ተም!በማድረግ እንደገና ያ ሁሉ ሁካታ ከመቅጽበት ጸጥ አለ..ከጥቂት ዝምታ በኋላም ምንም ድምጽ አይሰማም ነበር:
ክቡር ጠቅላይ ከመቸውም ምሽቶች ይህች ምሽት ነፍሳቸው እንደአራስ ነፍስ የፈነደቀችበት ምሽት ከመሆኗም በላይ እንደብረት የጋለውና ከመቸውም ወቅቶች የሚያበራው ከአንገታቸው በላይ ያለው ገጽታ ብቸኛ የሁኔታዎች ተቆጣጣሪ አስመስሎዋቸዋል::
በዚያ ሁሉ ዳንኪራና ሁካታ ጭንቅላቱን ሲያደክምና ሲወቅጥ ያነጋ ባለስልጣን ሁሉ አሁን ደግሞ ምን ሊለን ይሆን? ብለው ሲጠባበቁ..ጠቅላይ ክራባታቸውን በደንብ ማላላቱ ስላላረካቸው ይሄን ጊዜ ጭራሹኑ አውልቀው ክራባቱን በመጣል ጠጋ በማለት ወደ ጊዜያዊው ማይክራፎን…ከመጠጋታቸው ድንገተኛ ከባድ ግሳት አንድ ጊዜ ቤቱን በድምጽ
ሞላው..አ..!አ…!አ…! ብዙዎቹ ባለስልጣናት ሰምተው እንዳልሰሙ መሆን ፈልገው ይሁን ወይም የለም ይህ የጠቅላይ ሚ/ር አይደለም የማለት ይሆን..እርስ በርስ በመተያየት አንተ ነህ..የለም አንተነህ..የሚባባሉ ነበር የሚመስሉት…ጠቅላይ ሊያፍሩ ነው እንዲያውም ይህ ድንገተኛ የራሳቸው ግሳት ያስቆጣቸውም ይመስላል, ድንገት ዞር በማለት ጎናቸው ተቀምጦ በሙቀቱ ምክንያት ከወገቡ በላይ ልብሱን ገፎ በካኒቴራ ብቻ ሆኖ ..በአንድ እጁ በድልህ የተለወሰ ክርክም ያለች ቀይ ጥሬ ሥጋ በሌላ እጁ ደግሞ የውስኪ ብልቃጥ ጥርቅም አድርጎ የያዘውን ኃይሉ ሻውልን ቆይ ነገ እንተያያለን የሚሉት ነበር የሚመስለው …ልክ ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ የቆጠሩት ጠቅላይ.. እንደገና ቀረብ በማለት ወደማይክራፎኑ አ….ከማለታቸው..ይህን ጊዜ ደግሞ ያልታሰበች አንዲት ብቸኛ ስቅታ
ከጉሮሮአቸው ህቅ!.. የዚህን ጊዜ ከጠቅላይ ጉያ የማይጠፉት ኃይሉና ልደቱ ውሃ! ውሃ ! ሲሉ ይሰሙ ነበር : በዚህ ውድቅት ምሽት ምን ሊል ይሆን ብለው ባለስልጣኖች በግልጽ የሚነበብባቸው ነበሩ::
ጠቅላይ ከትንሽ ለዘብታ በኋላ ….”ክቡራት ኩቡርትና…ህቅ!…አመስግናችኋለች እኔና ባለበቴ ስም …ህቅ!..
ወደ ደንማርካዊት በከንቱ …ህቅ! አላስላኪሽንም :በቲቭኢም እንዳያችሁኝ ከፈረሱላዊ..ህቅ! ፕሬዝዳንት ሰርቆዚ
ጋራ እጅ በጅ በመያያዝ…ህቅ! አንድ እህታማቾች ኃጎራዊት መሆናችንን አረጋግ..ህቅ!.ጠናል:: እናም እንደምታውቁት በነገዊቷ ዕለት ..ህቅ!.. የሥራ ቀን ናትና ሆኖም ስለደከመችኋት..ህቅ!..አትምጽኡ ዕረፍት አርጉ ህቅ! ክቡርነታቸው ይህንን ብለው ሲጨርሱ…ፉጨቱ..ሁካታው..ጭብጨባው ..ያካባቢውን የጸጥታ ጠባቂዎች በመጠኑ አደናብሯችዋል ..እንዲያውም አንዳዶቹ ጠመንጃ ሲያቀባብሉ ታይተዋል::
December 29th, 2009 at 4:10 am
Dear habtamu: It is good decession and bright action. You will go back to our home and when we get freedom.
December 29th, 2009 at 3:14 pm
We have seen list of so many jounalists and other woyane officials who have defected to teh west. Most of them have not come forward to expose woyanes. why not??? I believe they are cowards or opportunists! I request EMF to find these individuals to present themselves. The rest of us have also the responsibility to tell EMF the names and where abouts of these people.
December 29th, 2009 at 6:18 pm
Deriba (hagos or sold out)
When the Temprature of Diaspora politics diminish the case of Biirtukan raises on keyboard.
But who are these people(politicians)?
Where do yo live ? Or is it because of the frustration in you that you are trying to empower your commrades or paid cadres to keep on their
day to day life producing lies after lies and defend the barbarian woyanne
The second part of the whole issue is it is your trade mark even in your dying days (like that of iraq former propaganda chief ali) you are
misinforming the woyanne symptheisers which is completely absurd for Ethiopians you are simply a joke living in the woyanne village with no clue to forsee what your future will be, each woyanne activist is in the
Ethiopian least for your information .Thirdly your secret plan of attacking Eritrea shows that you are in the verge of collapse and that i advice you to stay tuned .woyannes days are numbered 2010 is there to make woyanne history
December 30th, 2009 at 9:19 am
ጎበዝ ተረጋጉ……….አትችኩሉ.
ብስለት…………..አይጉደለን
በዚህ አስተሳስብ…..መለስን ማውረድ ይከብዳል
ለማውረድ ከሚወርደው በላይ ማሰብ አለብን
ለተቀላቀለ ሁሉ በመዝፍን……..ለውጥ አይመጣም