በተክሌ (መስከረም 27/ 2002) – መስከረም 25 መሆኑ ነው? እኛ ተናጋሪዎቹ፡ እኛ እንግዶቹ ወደ ውስጥ ስንገባ፡ የዳላስ ክራውን ፕላዛ ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከግማሽ በላይ ሞልቷል። ስብሰባው ከተጠራበት ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በላይ ዘግይተን መጀመር ግን አልፈለግንም። ዶ/ር ብርሀኑ መሀል ቁጭ አለ። አቶ ዘነበ ሀይለማሪያም ገነሜ በስተግራ፡ ልጅ ተክሌ ደግሞ በስተቀኝ ተቀመጠ። የመድረኩ መሪና ሰብሳቢው አቶ አበበ እንግዶቹን አስተዋወቀ። ስብሰባው ተጀመረ። አቶ ዘነበ ተናገረ መጀመሪያ። ከአ.አ.ዩ. ስድስት ኪሎ ግቢ እስከ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፡ ከውጭ ጉዳይ እስከ የመን፡ ከየመን አሜሪካ እስኪደርስ ላለፉት ስድስት ሰባት አመታት ያለፈበትን የፖለቲካ ሰቆቃና ፈተና ተረከልን። በነገራችን ላይ ዘነበ ገነሜ ስድስት ኪሎ እያለን መግባባት አይኑረን እንጂ አንድ ላይ ነበርን። ዘነበ ገነሜ ራሱ ነው በተለምዶ ባባቱ ስም ሳይሆን፡ ዘነበ ሀይለማሪያም፡ ባያቱ ስም እንደሚጠራ ያወሳው፡ ዘነበ ገነሜ። ደግሞም ያያትን ስም ማንሳት መልካም ነው። በራሳችንና ባባታችን ስም ማንነታችን የተደበቀ ሰዎች ባያታችን ማንነታችን ይገለጣልና ለኛ ለአንድነት ሀይሎች የአማራ ስብስቦች ብቻ ሳንሆን የሌሎች ብሄሮች ተወላጆችም እንዳለንበት ያሳያል። ለዚህ ነው እኔም ባለፈው ሰሞን አባቴን ያሳደጉትን ሳይሆን አባቴን የወለዱትን፡ ያያቴን ስምና ደም የጻፍኩላችሁ።
ዘነበ ቁጥብ ነው። አፈ ጮሌ አይደለም። የዋህም ይመስላል። በቁጥብነትና በየዋህነት ግን መናገር ያለበትን ሁሉ ተናገረ። ጥያቄ ስለጠየቀ፡ የኢትዮጵያን ጥቅም ይጎዳል ብሎ ስለተናገረ፡ ስለባለሙያዎችና ካድሬዎች ስብጥር ስለጠየቀ፡ በብሄራቸው እንጂ በችሎታቸው ስላልተቀጠሩ ሰዎች ስለመረመረ “የአመለካከት ችግር ያለበት” እየተባለ የደረሰበትን መከራ አወሳን። ግን ለምንድነው የትግራይ ተወላጆች ለዚያውም በብቃታቸው ሳይሆን በካድሬነታቸው ወይም በታጋይነታቸው ብቻ በየኤምባሲው በብዛት የተሰገሰጉት? አንዱ ጥያቄ ነው። “አንተ ችግር አለበህ እንዴ በዚያ?” የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ሰዎች በችሎታቸውና በኢትዮጵያዊነታቸው ሳይሆን፡ ጥቂት ባለሙያዎችን ከፊት አድርጎ የተቀረውን በሙሉ ግን በቀድሞ የህወሀት ወታደሮች የተሞላ መስሪያ ቤት መሆኑንና በተለይ በኢትዮጵያ ጎረቤት አገሮች በሚገኙ ኤምባሲዎች ውስጥ የሚሰራው ስራ ሁሉ እንዴት ኢትዮጵያን ይጠቅማል ሳይሆን እንዴት ለሕወሀት ስጋት የማይፈጥሩ ሁኔታዎችን በነዚያ አገራት ውስጥ መፍጠር ይቻላል በሚል ላይ ያተኮረ መሆኑን ተናገረ። ጥቂት ጥያቄዎች ቀረቡለት፡ እነሱንም አስተናገደ። ምሳሌዎችም ሰጠ።
ከዚያ ልጅ ተክሌ ቀጠለ። እኔ ማለት ነች፡ ዘጋቢው። እኔ ጋዜጠኛው ብል ደግሞ፡ የቀድሞዎቹ የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች፡ እነ ክንፉ ሊቀየሙኝ ነው። ስላለንበት ፖለቲካዊ ሁኔታ ዳስሼ፡ ስለኤርትራ መንገድ (መቼም የኤርትራ መንገድ ምን ያህል እንደናፈቀኝ ታውቁታላችሁ) እንዲሁም ስለግንቦት 7 አስፈላጊነት፡ እንደገናም ደግሞ ስለ ኦሮሞና መሰል ብሄርተኞች እና አንድነት ሀይሎች፡ ከነሱ ጋር ያለንን ግንኙነትም እንዴት ብናደርግ መልካም እንደሆነ አስሼ፡ ኦው ሌላ የረሳሁት ነገር፡ “እንዴት ሕወሀት የማንንቀውና በቀላሉ የማይሸነፍ ሀይል” እንደሆነም ጭምር ተናግሬ ተቀመጥኩ። ዶ/ር ብርሀኑ ስለደርግና ኢህአዴግ፡ (ኢህአዴግ የሚባል ነገር የለም ሕወሀት ብሏል ገብሬ/ገብረመድህን አርአያ)፡ አገዛዝ፡ የኢህአዴግ፡ ማለቴ ሕወሀት አገዛዝ እንዴት ከደርግ የበሰ እንደሆነ፡ በፍርድቤት፡ በመከላከያ እንዲሁም በሌሎችም ዘርፍ፡ የሕወሀትን ከደርግ የተለየ አይን ያወጣ ዝርፊያና ቅጥፈት አትቶ አበቃ። ከዚያ ጥያቄና መልስ ሆነ። ሰዉ አስተያየት ሰጠ፡ ጥያቄም ጠየቀ። እኛም መለስን። አንዳንዶቹ ጥያቄዎች ተደጋጋሚ ናቸው። ስለሰላማዊ ትግልና ምርጫ። እኔና ዶ/ር ብርሀኑ እንለያያለን በዚህ ላይ። ልዩነታችንን በሌላ ቀጣይ ጽሁፍ ላይ እገልጻለሁ። እስከዚያው ግን እነዚህ ሰዎች፡ “ጉዶች” ይላቸዋል ደ/ር ብርሀኑ፡ በምንም መልኩ ስልጣናቸውን ለመጠበቅ ምንም ነገር ከማድረግ ወደኋላ የማይሉና በሰላም ለመውረድ ያልተዘጋጁ መሆናቸውን አሰመረበት።
ስለግንቦት ሰባት ስልትና ስለኤርትራም ተጠየቀ፡ ዶ/ር ብርሀኑ። አብራራ። በጣም ግልጽ ነን ብለን የምናስብበት ጉዳይ በማናቸውም መንገድ ሕወሀትን እንታገላለን፡ እንነቅላለንም የሚለው ስልታችን ሆኖ ሳለ፡ ይሄ የስልት ጉዳይ ዘወትር በየስብሰባው ጥያቄ ሆኖ መነሳቱ ግርም እንደሚለው ገለጸ። በማናቸውም መንገድ፡ ጠቃሚ ሆኖ ከተገኘ፡ እንኩዋንስ ከኤርትራ ከጋኔንም ጋር ቢሆን፡ አብሮ ከመስራት ወደኋላ እንደማይል ተናገረ። በዚህን ግዜ እኛ የኤርትራ መንገድ የሚናፍቀን ሰዎች በደስታ ዘለልን። ግን፡ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ የመረጠው ብቻ እንጂ ማንም ኢትዮጵያን ወክሎ መደራደር እንደማይችልና ግንቦት ሰባትም የህዝብ ውክልና ስለሌለው ኢትዮጵያን ወክሎ ከኤርትራም ይሁን ከሌሎች መንግስታት ጋር መነጋገርና መደራደርም እንደማይችል ተናገረ። ግን ኢትዮጵያን ወክሎ እንጂ እንደ ግንቦት ሰባት የሚያደርጉትን እያደረጉ እንደሆነ ተናግሯል። ስብሰባው ከ3፡30 እስከ 8፡30 ቀጠለ። አምስት ሰዓት ላይ መቀመጫ ወንበር አልነበረም። የተሰወሰኑ ሰዎችና የስብሰባው አስተባባሪዎች ቆመው ማዳመጥ ነበረባቸው። እጅግ በጣም የገረመኝ ነገር፡ ባለቤቱ በሷም ይሁን በልጆቿ ላይ ጉዳት ያላደረሰ መኪና ግጭት ደርሶባት፡ ተጠርቶ ከሄደው የስብሰባው ሊቀመንበር በስተቀር፡ የሆነ ቦታ ላይ መቆም ስለነበረበት በግድ ስብሰባው እስኪቆም ድረስ፡ ሰዉ ሁሉ በተመስጦና በንቃት ይከታተል ነበር። ይሄንን ስብሰባ ከመናፈቃቸው የተነሳ፡ ድክም ብሏቸው ከስራ መጥተው ሁሉ እስከመጨረሻው ስብሰባውን የተከታተሉ ሰዎችን አግኝቻለሁ። የተሳታፊው ሰዉ ስብጥር በእድሜ ረገድ የተለያየ ሲሆን፡ የሴቶች ተሳትፎ ግን አናሳ ነበር።
ከሁለት መቶ ሀምሳ ሰው ውስጥ ከአምስት ያልበለጡ ሴቶች ብቻ ነበሩበት። ስብሰባው መጀመሪያ ላይ፡ ለሰብአዊ መብት መከበርና ለዴሞክራሲ መምታት መስዋእትነት ለከፈሉና ለሚከፍሉ ሁሉ የህሊና ጸሎት ተደርጓል። በዚህ ውይይት ከመደሰቱ የተነሳ፡ አንድ በእለቱ ወይም በዚያው ሰሞን ልደቱን ያከብር የነበረ ወጣት፡ “በቃ የልደት ስጦታዬን አገኘሁ” ብሏል።
የረሳሁት ነገር፡ ስለቤተክርስቲያንና በየከተማዎቹ ስለሚገኙ የኢትዮጵያ ማህበረሰባት ሚናዎችምተነስቶ ነበር። ይሄን ጉዳይ እኔ እንድመልሰው እድል ተሰጥቶኝ፡ የማይክ ጥማቴ እስኪወጣልኝ ድረስ ሃሳብ ሰጥቼበታለሁ። በእለቱ ጠዋት በዳላስ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ተገኝቼ፡ የየትኛው ቅዱስ ወይም ጻድቅ እንደሆነ ያልጠየቅኩትና ያላወቅኩት በዓለ ንግስ ተሳትፌያለሁ። በግንቦት ሰባት ስብሰባና ከዶ/ር ብርሀኑ ጋር በነበረን ቆይታ ብደሰትም ግን፡ የዳላስ ቆይታዬ፡ በቤተክርስቲአንና በፓትሪያርክ ጉዳይ በአገር ልጅነትና በመሰል ጉዳዮች ላይ የነበረኝን ጭንቀትና ሀዘን አብሶብኝ ተመልሻለሁ። እንደውም በአሜሪካን አየርመንገድ ላይ ሆኜ ነገሮችን ሳሰላስል፡ ትግሉ ከእጃችን እያመለጠን ነው እንዴ የሚል ጥያቄ ወጥሮኝ ነው ሲያትል የደረስኩት። በሸዋና በጎንደር ሰዎች መካከል ስላለ ሽኩቻ ትግሉን እንዴት እየጎዳው እንደሆነ፡ የዚህ የማህበረ ቅዱሳንና የፓትሪያርክን ጉዳይ፡ የቤ/ክንን ሚናና ቀጣዩን አካሄዳችንን የተመለከተውን ዘገባዬን፡ በዳላሱ ስብሰባ ላይ ካቀረብኩት ወረቀት ጋር አያይዤ በዚሁ ሳምንት አቀርብላችኋለሁ። እስከዚያው ግን መልካም ሳምንት።
ፊታውራሪ ተክሌ ነኝ። በነገራችን ላይ እዚያ ዳላስ በቆየሁበት ወቅት ዳላሶች በቫንኩቨርና አካባቢው ላይ ፊታውራሪ አድርገው ሾመውናል። እኔ እንኩዋን ደጃዝማችነትን ነበር የተመኘሁት።
ከዳላስ መልስ፡ መስከረም 27/ 2002, ወይም October 7, 2009፡ ቫንኩቨር ካናዳ


October 7th, 2009 at 9:28 am
viva G7 we support!!! good job Dr berhanu
October 7th, 2009 at 12:38 pm
ይህች ከሰይጣንና ከኤርትራ (ሻእቢያ) ጋር መሞዳሞድ እኔ እንጃ:: ወያኔም “መንግስት አይደለንም ከማንም ጋር በድንበር ይሁን በሌላ አንደራደርም” ይሉ ነበር ስልጣን ከመያዛቸው በፊት:: ስልጣን ከያዙ በሓላ ኤርትራን አስገነጠሉ;አሰብ, ባድሜ, ኢሮፕን አስረከቡ:: ይባስ በለው አሁን የምእራቡ አዋሳኝ ሰፊ መሬት ለሱዳን ለመስጠት ዝግጅቱ አልቓል::
ስለዚህ G-7 ምን ማረጋገጫ ሊሰጠን ይችላል? ስልጣን ላይ እስኪወጣኮ ሁሉም ነገር ባላል:: ሻእቢያ ወያኔ ሁለቱ የኢትዮጵያ ጠላቶች ናቸው::
October 7th, 2009 at 2:04 pm
አቶ ተክሌ ዝም ብለህ አዲስ ትግልና አዲስ ሜዳ መፍጠር ትክክል አይደለም። እንደዚህ እንዳንተ እይተነሱ ነዉ ነገርን በመሳጥ ልዩነትን መፍጠር የሚያካሂዱት። በጎንደርና በሸዋ የምትለዉ አፈ ታሪክህን አቁም ምክንያቱም በጎንደርና በሸዋ መሃከል ምንም ልዩነት የለም። ጥቂት አቅማርኛ የሚናገሩ ትግሬዎች ጎንደሬ ነን ብለዉ የሚያጭበረብሩ ከሆነ ማጋለጥ ስራህ ይሁን፤ ጋዜጠኛ ነኝ ብለሃልና። ከዚያ በተረፈ ግን አማራዉን ካማርዉ ለመለየት መሞከር የዋህነት ይሆናል። ለመሆኑ አላማህ ወያኔን መታገል ነዉ ወይስ ሽዋና ጎንደርን መለያየት? በጣም ያሳዝናል፤ ይህን አይነት መከፋፈል ብታቆሙ ጥሩ ይመስለኛል ወያኔ እየከሸፈበት ሲመታ በናንተ በኩል ጎንደር ከሸዋ እያላችሁ እሳት መጫር ጀመራችሁ። እባክህ መረጃህን አቅርብልን፤ በየቦታዉ አማሮችን ከምዉጋትም ተቆጠብ። የቄስ ሚስት አወቅሽ ቢሏት መጽሃፍ አጥባ ቆየች እንዳይሆን።
Good luck with your struggle from asmara but please stop dividing our people.
Thank you
October 7th, 2009 at 2:27 pm
ከጌታቸዉ ረዳ www.Ethiopiansemay.blogspot.com
የካዉ ቦይ መንደርተኞች “ቴክሳሶች” የወያኔዉ ፕረዚዳንት የመቶአለቃ ግርማን “የካዉ ቦይ” ቆብ እንደሸለሙዋቸዉ አንተኑም በወጣት ነፃ አዉጪ ጓድነትህ “ፊታዉራሪ” ሲሸልሙህ ፊታዉራሪነቱን አላረካህም እና አንተ በመረጥከዉ “የደጃዝማችነት” ማዕረግ “ደጃማች ተክሌ” ልበልህ እና “መቼም የኤርትራ መንገድ ምን ያህል እንደናፈቀኝ ታውቁታላችሁ” ስትል “የኤርትራ መንገድ ምን ያህል እንደናፈቀህ እኔ ስለማላዉቅ “ታዉቃላችሁ” ስትል እኔን አይጨምርም እና የሚያዉቁልህን እንጂ እኔንም ከሚያዉቁህ ጋር ባትጨምረኝ ጥሩ ነዉ እላለሁ፤፤ ካልሆነ እንዴት እንደናፈቀህ ብትገልጽልን ጥሩ ነዉ፤፤ ኮምብሽታቶን አያለሁ ስትል “ዊዓ” ወይንም ሳዋ ወስደዉ “የሻዕብያ” አሰልጣን ሳህን አጣቢ እንዳያደርጉህ “ጠንቅቅ ማለት ጥሩ ነዉ። ወጣት ነህ እና ከአረጋዊያን ምክር ማዳመጥ፤ ረዢሙን ጉዞ ሳይደርሱት ጥድፍያዉ ባጭር ጉዞ እንዳይሟሽሽ “ረጋ” ማለቱ ጥሩ ነዉ ብየ ነዉ፤፤ በቤተክርስትያን ምዕመናን በኩል ስለ በሸዋ እና በጎንደር መካከል ያለዉ ያለዉ ጥላቻም እንዳሳሰበህ ገልጸሃል። አይ ደጃማች ተክሌ፤ እያደግክ በሄድህ ቁጥር ብዙ ትማራለህ ፤ ይሀ ጉድ የቆየ ነዉ አዲስ ሆኖብህ እንጂ፤፤ ለመሆኑ ካናዳ ዉስጥ እንዲህ ያለ ነገር የለም?
October 7th, 2009 at 3:16 pm
is that all the meeting about only jokes?
October 7th, 2009 at 6:36 pm
ተክሌ አፈርኩብህ ዲያቆን ነበርኩ ስትል የሰማሁ መስሎኝ ነበረ 318ቱ ሊቃውንት ከ1600 አመታት በፊት የጌታን አምላክነት የካደ አርዮስን ያወገዙበትን ታላቅ ቀን, ለሀገራችንና ለቤተክርስቲያናችን ኩራት የሆነው ጌታ ሲሰቀል ቀኝ እጁ ያረፈበት ግማደ መስቀል በግሸን ያረፈበትን, እንዲሁም የጌታ እናት የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን መታሰቢያ ታላቅ በአል የግሸን ማርያምን ንግስ ”ምን እንደሆነ ያላወቅኩት” ትላለህ ማፈሪያ ነህ መንፈሳዊ ስሜት ቢጎልህ እንኩዋን ለአንባቢዎችህ ያህል ከመጻፍህ በፊት መረጃ ሊኖርህ ይገባል ለካ ያው እንደነዚዎቹ ሚዲያንና ፖለቲካን ለብሰህ በቤተክርስቲያን በኩል የሚገኝ ሰው አሰሳ ብቻ ነህ ለካ: ጎበዝ መስከረም 21 ግሸን ነበር እኮ…..እባካችሁ ለህዝብ ለሀገር ቆመናል የምትሉ ወንድሞቼ ለነገ የተለየ ጥቅም ቤተክርስቲያንን አትታከኩ ወደ ቤተክርስቲያን ስታስቡ ለእግዚአብሔር ለመገዛት ብቻ ይሁን የግልና የቡድን ሃሳባቸውን አራማጆች እጃቸውን ከቤተክርስቲያን ሲሰበስቡ ቤተክርስቲያን ዳግም በንጹህ የነፍስ አዳሪ አገልጋዮች ስትከበብ ተዋህዶ ታብባላች ያኔ የኢትዮጵያም ጥያቄ ይመለሳል:: ተክሌ ምንም ባንዲራ ቢሆን ቤተክርስትያን ውስጥ ስትገባ ሻሽህን አውልቅ ያው ኮፍያ መሆኑ አይደል አዳራሹ ውስጥ ይበቃል የቅድስት ቤተክርስቲያንን ስርአት ማክበር በቅዱስ መንፈስ ተመርተው ስራቱን ያወጡትን አባቶች ማክበር ነው :እነሱን ያጸና ቅዱሱን መንፈስም ማክበር ነው : በየዘመኑ ያሉ የቤተክርስቲያንን ስርአት ጠባቂ ምእመናንንም ማክበር ነው:: በተረፈ የጎደሉህን እስማርትነትና የጽሁፎችህን አለመብሰል እያሻሻልክ በርታ ሀሳቦችህ ጥሩ ናቸው ብዙ ዋዛ ፈዛዛ አይብዛበት እንጂ: በሀይማኖት ዙሪያ አደራ ሲሪየስ ሁን የማይሆንልህ ከሆነ ተው አትንካ ደህና ሁን ትችት ጉዳት የለውም ብዬ ነው:: ከዳላስ ነዋሪ::
October 7th, 2009 at 6:55 pm
አይ ግንቦት ሰባት !! እንዲያው ወሬና ገንዘብ መዋጮ ሆኖ ቀረ?
ተክሌ - እንኳን ደጃዝማችነትና ፊታውራሪነት ልጅነቱም ይበዛብሃል ባይ ነኝ:: ለምን ብትለኝ እንደለሌቹ ወሬ ብቻ ሰለሆንክ:: እኔና ጓደኞቼ ግንቦት ሰባት 2001 ሳያበቃ አዲስ አበባ ይገባል ብለን ሰንጠብቅ ቀስ በቀስ እስከወሬውም ጠፋ:: አሁን አሁንማ እንደ አሸን የፈሉት ድረ ገጾችም ወደጎን እያሉት ነው:: አበጁ ያሰኛል:: ብሎ ብሎ ደግሞ ተሰብሳቢውም ጠፋ:: የሴቶቹማ አይነሳ::
እንዲህ የምታቆላምጠው የዳላሱ ሰበሰባ ለምን ባለፈው አመት ግንቦት ሰባት ምን እንደሰራ አልተወያየም? አሁን ማን ይሙት የሃገራችንን ሁኔታ የማያውቅ ሰው ኖሮ ነው ስለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወያኔነት - ሰለኤርትራ - ሰለብሄሮች - ሰለአንድነት - ሰለደርግና ወያኔ ወዘተ. ስታወሩ የዋላችሁት? ያበደው እናንተ ሳትሆኑ ሰብሰባው ላይ የተገኘው ነው እላለሁ:: ምን እንደሰራችሁ እንደማትነግሩት እያወቀ ማን መሰስ በል አለው? ይቅመሳት::
የግንቦት ሰባትና የኤርትራ ግንኙነት ዋና ጥያቄ ነው:: ወያኔን ለመጣል ከማንም ጋር አብረን እንሰራለን የሚለው የማታለያ አባባል የስልት ፈሬ ከርስኪ ብትለው ይሻላል:: በዚህ ጉዳይ ስልትና ግብ የሚለያዩ አይደሉም:: መተንተን ካስፈለገ እመለስበታለሁ:: አለበለዚያ ግን እናንተ ተታላችሁ ሌሎችን ልታታልሉ አትሞክሩ::
ደግነቱ ግን ግንቦት ሰባትም ኤርትራም ዝም ናቸው::
ቻው::
October 7th, 2009 at 7:53 pm
via G7 pls sign http://www.gopetition.com/petitions/stop-illegal-child-trafficking-of-ethiopian-children.html
October 7th, 2009 at 10:20 pm
Will Ginbot 7 supports two national languages, Amharic and Oromiffa.
OR NO?????????????
US, British Diplomats to mediate between EPRDF and Medrek-FDD
Published 10/07/2009 - 3:51 a.m. GMT Credit - reuters (By Simegnish Yekoye/SSI) Foreign diplomats have started to broker negotiations between the ruling party, Ethiopian People Revolutionary Front (EPRDF) and a forum of opposition parties, MEDREK/FDD, on issues concerning the upcoming Ethiopian election to be held next year.
Diplomats from the British and US embassies have started consultations with both parties so that they can come to a round table discussion and settle their differences.
Merara Gudina, member of one of the eight parties that formed the Forum for Democratic Dialogue (FDD) says the diplomats have talked to them and asked them to have discussions with EPRDF, which he says is also the request of the forum.
The Forum which boycotted parties discussions with the ruling party and other “opposition parties” over a disagreement on agendas of negotiation sent a letter to EPRDF asking for the need of bilateral negotiations with the ruling party on issues concerning media usage, election observers, rules and regulations and other issues. However, the ruling party agreed to discuss only on the code of conduct for the election.
The ruling party gave a response in letter saying the forum can take part in the progressing discussions with the other opposition parties but will not hold any separate negotiation with the forum. Representatives of the eight parties in the forum are to hold a meeting on how to respond to the letter and what their next step would be. “EPRDF has given us a letter that doesn’t clearly say whether they don’t want the discussion or need to sit with us and talk on issues. So members of the forum need to come together and decide what to do next,” says Merara.
Dr. Hailu Araya, Public Relation Officer of Andenet party which is also member party of the forum, says leaders of the forum are already in a meeting and will reach on a decision in the coming few days. With only a few months away to the upcoming election, eight parties that formed the coalition with two other individuals haven’t decided yet whether they are to take part in the election or not.
The forum has come up with their own manifesto, however, that would help them get ready for the election. However, the National Board of Election (NBE) hasn’t given them approval yet. Their manifesto mainly states they will find any means where Ethiopia will be able to use the Port of Assab – located in Eritrea and the country will have two national languages, Amharic and Oromiffa.
October 7th, 2009 at 10:27 pm
I have seen on the web that G7 is having meeting in different parts of Europe and North America, what about other places like Australia?
I think you as a party (G7) have to work in here, there is large number of Ethiopians in Australia, and have public meeting to address all the problems and look for a solution as one.
Tesfaye,
Melbourne, Australia
October 8th, 2009 at 12:18 am
በአሁኑ ሰዓት ግንቦት 7ትን የሚደግፈው ሕዝብ እየበዛ ነው።
ግንቦት 7ት የሰው ልጆችን መብት እኩልነት ይደግፋል።
ግንቦት 7ት እንባገነንነትን ይቃወማል።
ግንቦት 7ት ዲሞክራሲን ይደግፋል።
ግንቦት 7ት የኢትዮጵያ ጥቅሞችን ያስጠብቃል።
ግንቦት 7ት ሉአላዊነትን ያስከብራል።
ግንቦት 7ት እኩልነትን ያራምዳን።
ግንቦት 7ት ፍትሕን ለሁሉም ያጎናስጽፋል።
ግንቦት 7ት አገር ድንበርን ያስከብራል።
የወያኔ አንባገነንትን ይታገላል።
ግንቦት 7ትን የምንደግፈው ሌላ ተጨማሪ ደም ለማፍሰስ ሳይሆን የወያኔ ስራዓተ-አልበኝነት ማብቃት ስላለበት ነው።
ዛሬ መሬታችን ለሱዳን ሊሰጥ ነው። ተነስ እንነሳ!!!
ኢትዮጵያ የሁላችንም ናት ያንተ ያንቺ የኛ የናንተ!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!
October 8th, 2009 at 2:02 am
Ft. Tekle, I am waiting for your next article. (Sile patriaku ena sile mehiberkidusan yebete kirstan minna)
October 8th, 2009 at 5:25 am
Hi Guys,
What ever any one says any thing, as to my understanding, G7 is the greatest movement so far in Ethiopian history. It is a movement that has progressively improving and sharpening itself for an effective struggle.
Viva G7! Keep it up!
October 8th, 2009 at 5:27 am
ለ Semaglew
ኣንተ ቁጭ ብለህ ሌላዉ የሚሰራውን አንቁዋሽሽ:: ለመሆኑ አንተ ምን ያደረከው ነገር አለ ? ከጉዋደኞችህ ጋር ቁጭ ብለህ ግንቦት ሰባት አዲስ አበባ እንዲገባ ትጠብቃለህ መቸስ ሌላው በደከመበት ቀድመህ ለመገኘት ማንም አያክልህም::
ግንቦት 7 አንተ እንደተመኘህው ዝም ያለ ድርጅት አይደለም:: የሚችለውን እየሰራ ነው::አንተ ግን ቁች ብለህ አውራ::ወሬኛ ነገር ነህ::ደግሞ ለትንተና እመለሳለሁ ስትል አታፍርም ? ሂድና እዝያ የለመድክበትና የሚያዳምጥህን ፈልግና ቅደድ::
ወሬኛ ነህ::
ተክሌ በርታ:: ስራህ አሪፍ ነው አንተም ጥሩ ልጅ ነህ:: ግንቦት 7 በተፈለገ ጊዜ የተፈጠረ ድርጅት ነው! የዝህን የማድ ቤት ወሬኛ ስው ፍሬ ከርስኪ ነገር ከቁም ነገር አትቁጠረዉ::
ሞት ለወያኔ! ድል ለግለሰቦች መብት መከበር ለሚታገሉ ሁሉ::
October 8th, 2009 at 7:20 am
Lij Tekle,
I think you are very fresh in reporting public events specially for a political parties which have a number of opponents. It is not good to mention the exact number of participants of the meeting rather it is better to say- the meeting hall was packed or over packed etc. Don do it again. 250 is not a big number; if you say the hall was full or packed one can imagine that it could be 400, 500, etc.
October 8th, 2009 at 7:48 am
To Yehuala, GETACHEW REDA (Getachew EPRP), gonafir, solomon and Semaglew negn ,
You all are either the elements of Weyane or the distructive elements of EPRP/AEUP or simply a navie and moron individuals who are the will of Ginbot 7.
If someone who is concerned to Ethiopia is either supports the idea of Ginbot 7 or find another alternative to get rid of weyane….otherwise singing gossips against G7 is a sign of weyane or eprp/aeup or naive and moron people…..
Go g7 …go
ከዳር ቆመህ አትይ …..ግባና ታገል…….
October 8th, 2009 at 8:42 am
Ato Getachaw ,KKKKKKKKKKKK you Kill ME.pls,write down matured advice.G7 is one years old movemant, then they have done a good things instead of 40 years party. don’t expect every thing do with in one year, you have to ask your self, what i have to do to defeat the woyane? particpatie anti woyane demostration, help money for organization,help them to diplomacy to cut woyane income, don’t send money fro your family by woyane contrlo money trasfar. Teklay we support you and we like you.
God bless Ethiopia.
October 8th, 2009 at 10:02 am
የሻዕብያ የኤርትራና የጉንበት 7 ስም ሲነሱ መቸም ምድረ ዎያኔ ያአማርኛ ካባቸውን ደርበው አካኪ ዘራፍ ኢትዮጵያ ወይ ሞት !!! (የኢትዮጲያ መሬት ለባዕድ እየሸነሸኑ ) ማለት የቆየ ባህርያቸው ነው ታድያ አሁን እንደ አይጥ ተጠራርተው ልጅ ተክሌ ጋ መርባረባቸው አዲስ ነገር አይደለም ድሮም የደደቢት አይጦች ልዩ መታወቅያቸው እሱ ነው :: ግን እኔ ግርም የሚለኝ ነገር ቢኖር ዎያኔዎች የሻዕቢያን ስም ሲሰሙ መስቀል እንዳየ ሰይጣን መበርገጋቸው ነው :: ውስጥ ለውስጥ ኢንተርናሽናል ኮሚኒቲውን ከሻዕቢያ ካላስታረቃችሁን ጥቅማችሁን በደንብ መጠበቅ አንችልም ለህልውናችንም አስጊ ነው ሲሉ የመዕራቡን ዓለም ደጅ ሲጠኑ እንድማይውሉ ሁሌ እዚህ እሳይበሩ አለም ደሞ አካኪ ዘራፍ ሲሉ መሰማታቸው በጣም የሚገርም ትዕይንት ነው:: ወያኔን አትመኑ ምክንያቱም 17 ልብ ነው ያለው 16ቱን አስቀምጦ በአንድ ልቡ ነው የሚሸውዳችሁ::
October 8th, 2009 at 4:25 pm
Tekle,
you are trying to impress us with your amateur writing skill.
Do sth better for a living and dont waste your time in this. Go to school and finish what you started in 6 killo.
I know Zenebe and he was not a true professional in the first place. He didn’t have a strong moral ground to asses professionalism.Its even the generosity of the Foregn Minsitry to assign him as a diplomat. He was not competent at all. It should be shame for him to generalize that there are no professionals working in Foreign office. He knew there are plenty of them with high caliber and skill though i dont deny that there are some who joined by thier party membership.
October 8th, 2009 at 4:52 pm
ኪብረት,
ኣንተ ደግሞ ከየት ነህ? ‘ጉንበት’ ክወደ ዎያነው ሰፈር የሚንሰማት ነገር ነች!
ለማስታወስ ያሂል ነው!
ወንዲሚህ አሉላ
October 8th, 2009 at 5:07 pm
Nunu, are you saying that Lij Tekle should lie or exaggerate or are you suggesting that we should build false impression in the people’s mind. I do not think Tekle suggested that 250 is a big number. That is only your perception. Secondly, even if Teklay stated that 250 was a big number, that is true when we only less than a hundred people in a public demonstration in cities with big Ethiopian population like D.C. Therefore, your comment is fresh and like jumping to criticizing.
Kassa
October 8th, 2009 at 5:34 pm
I have been using the nick name Sami for a while on this web site. Now, I noticed that some one used it to comment under this article about G7. I thought the system is Nick name sensetive here and I am kind of suspecious about why now someone choose to use my nike name? Kiffe Assefa did you involve in this?
October 8th, 2009 at 6:41 pm
G7 IS A FAST GROWING MOVEMENT,NO DOUBT ABOUT THAT. IT HAS BECOME THE HOPE OF ETHIOPIA; MANY PEOPLE ARE EAGERLY WAITING FOR THE COMING OF G7. THAT IS THE INFO I HAVE FROM ETHIOPIA.
BUT FOR TEKELE, PLEASE STOP YOUR CHILDISH STYLE OF WRITING. KNOW YOUR READERS. YOU ARE TOO VERBOSE, AND TOO ARROGANT. SOMETIMES YOU ARE WRITE- LIJ TEKELE NEGN. WHO IS LEJ TEKELE? WHO GAVE YOU THE TITLE OF LIJ; YOU ALSO CALL YOUR SELF FITAWRERAI BLABLA…THIS IS REALLY CHILDISH. IF YOU WANT TO WRITE ARTICLES JUST BE FORMAL. YOU MENTION NAMES LIKE KINFU. WHO IS KINFU? WE DON’T KNOW. I AM SORRY FOR G7 INVITING CHILDISH PEOPLE LIKE TEKLE. PLEASE FOR SAKE OF GOD DON’T EVER INVITE THIS KIND OF BABIES.
October 8th, 2009 at 7:41 pm
As I do not have the program to translate the the artice in Amharic, I can not help but respond to the comments about US and British officials to mediate between Medrek/FDD, which is the two sides of the same coin with TPLF?eprdf, rather than than pressure TPLF/eprdf to implement the 8-point preconditions. This is like mediating disputes between two brothers over distribution of an inheritance.
Now Medrek/FDD, with ethnic agenda is pandering to the seccessionist movemnts by including Affan OROMO as one of the Official language with Amharic, hoping it is going to satisfy their demand of Affan Oromo as the Official language, in addition to their entitlement of Ethnic right and seccionis right upto self-determination. What is going to happen to Amharic which abandoned from Tigrai by Gebru Asrat, now Cahairman of Medrek/FDD, with ethnic Patform. What supperficial arrangements were made for Ethiopians in 1991 and for 2010 by western donor countries, and TPLF/eprdf and Tigrai Harena/Medrek for the silent majority of Ethiopians. All the people want is individual freedom from the multi-layered, hierachical political model of TPLF/eprdf and its alter ego, in order to use use their unfettered right to elect a party with national agenda to power to restore private ownership of land, individual right, development of the country in a free market driven economy by empowered individuals, and perhaps for the government of federated states to promote develpent by ecological regions, instead of saying the ill defined ethnic boundries belong to ethnicities, rather to all Ethiopians, and the current well develped language of Amharic, pending to be an African language as the official language. These parties want just assume power and maintain stability at the power of the gun, because nothing is new of what is in their manifesto or in the manifesto of TPLF/eprdf, when it statrted.
October 8th, 2009 at 7:46 pm
አይ ሽማግሊ አይዞህ ተክሊ አንደሁ አንደፈራህው ደጃዝማችነት አይደለም ፊታውራሪነት ጀነራልም መሆኑ የማይቀር ነው :: ይብላኝልህ ላንተ አንጂ ሺማግሊውነኝ ስምህም አንደ መንግስትህ ጠማማ ነው ያንተ ደሞ አንደመንግስትህም ሽምግለህል መስለኝ ማስብ አቃትህ ግንቦት 7 ባዶ ነው ትላልህ አንጂ አንደ አጎቶችህ 17ና 30 አመት የሚፈጅበት ዝባተሎ አይምስልህ በአንድ አመት ውስጥ የስራውንማ አንተም በሾርኒ ተናግረህዋል አኮ ለምን በስብስባ መናገር ያስፈልጋል ብለህ ነው ሞኞ ‘ባዶ ያልክውም ፍርህትህን ለመግለጥ የተጠቀምክበት አንጂ በአንድ አመት ውስጥ አንደ ግንቦት 7 የስራ ድርጅት አንካን አንት ጊቶችህም ቢሆኑ አንድ ድርጅት አንካን አይጠቅሱም ያለፈውን አመትማ የትስራውን አንተም ጠቀስክው አኮ አንደው ለመሽፋፈን በ2001 አልክው እንጂ መንግስትህ አዲስ አበባ ውስጥ አለም ጉድ እስክሚል ቅዘንበቅዘን እንዳደረገውማ አንተም ሁነኛው ምስክር ትሆነኛለህ:: ያበድክውስ አንተ ተስብሳቢውማ በዳላስ የስብስባ ታርክ ውስጥ የሚመዘገ ስብሰባ ክመሆኑም በላይ በመጨረሻ ያጎረፈውን የገንዘብና የእርካታ መግለጫ ውኪልህን ብትጠይቅው አንተው እራስህ እንዳበድክ ይነግርህ ነበር በተስብሳቢው ላይ ያረረውን ጨጎራህን የባስ የሚመልጥ አንድ ነገር ልበልና ላብቃ ወይ ሸማግሌ እነዛ ነጫጭ ጠጉርህ በቃ መጥቆሩ ነው ይውጣልህ የኤርትራ መንግስትማ ህውሀትን እጁን ይዞ አዲስ አበባ ያስገባ እሱ መሆኑን እንደማናቅ ልታታልለን አትቃጣ እሺ ስለዚህ የኤርትራ መንግስት የአንድነት ሀይሎችንም በምደገፍ አጎቶችህን ክ4 ኪሎ ከሚያባርረው ግንቦት 7 ጎን ይቆማል ፈንዳ እንግዲህ ሽንፈት ለእናንተ ድል ለኢትዮጵያ ሕዥብ
October 8th, 2009 at 8:41 pm
Furthermore Ethiopians want a democratic government that derives its power from the the consent of the governed, not the the status quo, which is manifested in Medrek/FDD.
October 9th, 2009 at 5:24 am
Tekle,
Frankly, I don’t trust you. Judging by the style and content of your writing, you sound like trouble — a pretentious, self-seeking, and quarrelsome traditional highlander.
Ethiopia needs a new generation and quality of public figures — young, but also modern, nimble, humble, and cosmopolitan.
The traditional Ethiopian personality, whether Tigre, Amhara, Oromo, or any other ethnic group, is a useless one in our day and age. The traditional Ethiopian personality is selfish and egomanaical, has a tunnel vision and only knows how to scavenge his own.
Tekle, sorry for saying it so blatantly, but you strike me as being one such type.
October 9th, 2009 at 6:35 am
ጎበዝ! ፋሽስት የወያኔ ቡድን ከምድረ ኢትዮጵያ ተጠራርጎ እስኪጠፋ:-
የግንቦት7 የአንድነት የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በፍጹም የትግል ጽናት ይቀጥላል::ለአዘናጊዎችና ለወሬኞች ቦታ የለውም!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
October 9th, 2009 at 9:01 am
Some illitrate woyanne diasspora cadres like semaglew were the first once to comment on this article. G7 is the way to join the civilized world that is why the woyanne camp shakes when ever they hear this real ethiopian like they are acting the last 18 years when ever they listen something ethiopian. One of the cadres previous comment reads as of G7 tells them the other way after being told it is the duty of the government to make dialogue with the neighbouring countries like eritrea is taken as lies only because tekle says that he missed eritrea that shows woyanne is only there for such village politic as the former woyanne diplomat tells us some of the embassys personal even cant read and write and they represent ethiopia as diplomats and the skeptic approach over everything that is ethiopian.
October 9th, 2009 at 9:02 am
ተክሌ አትቀልድ ስቲጽፍ እባክህ ምንም ጥቅም የለውም በተረፈ በርታ የበሰለ ታጋይ ሁን
October 9th, 2009 at 9:13 am
Alemayehu
not a single ethiopian wants to impress you either in amateur or professional writing you are an enemy you must be wiped out from this proud nation which will come to the reallity in the near future (You are part of different insects bleeding our motherland to its bone) the only thing what we need is you (small woyanne paid cadre)and your bosses to bring to justice for the last 19+ years crimes and attrocities you were practising against ethiopians
October 9th, 2009 at 10:21 am
aha
in this artical doesn’t mention about Medrek. but why you menation? I am’t supporter and anti MEDREK. Ethiopia has multi ethnic. i don’t like ethnice base organition and only the name in Natinalist but in side is ethnic like AEUP. if we need to solve our problem , we have to talk with other not rigid. Medrek at time doing good job.this mention the 8 pre conditon that kinijt was rais.i have no problem to speak to languge. In USA Engliesh and spanish are common languge. why spaish is the second languge ? ther are a lot of spanish speaker are living in the country. Medrek are metion a bout Assab port, to get by any means. i know Gberu , saye and so on were struggle to give asab for Eritra, but now they are compromise taht is good. we Build rule of law all criminal like Derg, Miasion and soon will be trial on court. at this time Mederk is better than AEUPthat lead by Eng. Hailu , EDP that lead by kidetu and Ayale Chamiso.
October 9th, 2009 at 10:26 am
Ethiopia is for all Ethiopian , Oromo, Ahmare, Gurage, Tigrie Woliyte , Ethio somalia and so on, not for only Melese, Eng. Hailu and Iyassu Alemayu.
October 9th, 2009 at 10:47 am
ተክለሚካኤል ? ስለግለሰቦች ማንነት ትችትህ ብቻ ሳይሆን በቤተክርስቲያንም ጭምር በዓለ ንግሡ ምን እንደሆነ ሳላውቅ ተሳትፌያለሁ ብለሃል::
የጻፍከው ነገር ሁሉ ራስህን እንደገና እንድትመረምር ይገፋፋሃልና አስብበት:: ስለፋሽስቱ ወያኔ ወቅታዊ ተግባርና ቀጣይ ትግል የምትለውን ነበር የጠበቅሁት: ለወያኔ የሚመቹ ዝብዝብ በመጻፍህ ተክሌ ራስህን መርምር እልሃልሁ:: ወጥመዱ ውስጥ ከገባህ እናወጣሃለን::
ተክሌ! ትግሉ ይቀጥላል::
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
October 9th, 2009 at 10:58 am
ምን ይዘላብዳል ይሀ ሰውየ::
የኤርትራ መረት እንደዚህ የሚናፍቅህ ከሆነ ለምን አመሪካ መጣህ? ኤርትራ አይቀርብህም ነበር:: የማነህ አስቀያሚ:: ያልሆንከውን ለመሆን አይከጅልህ::
October 9th, 2009 at 11:17 am
I think it’s very wrong that Gebru Asrat Siye Abraha are active in Ethiopian politics. They have participated in giving away of Erittrea, human rights violations and massacres of innocent Ethiopians. Closer studies of their activities will reveal both treason and human rights charges.
Before they are cleared by a nationally commissioned organ, they should have refrained themselves from seeking public office again.
October 9th, 2009 at 12:21 pm
ወንድሜ አሉላ ጥሩ አስተውለሃል ሆኖም ” ጉንበት ” ከወደ ዎያኔ ሳትሆን ከወደ ሰሜን ናት ለማረም ያህል ነው:: በዛ ላይ ኪ ቦርድ ሲጫኑት በስህተት አንዳንዴ የለተፈለጉ ቃላት መጻፋቸው አይቀሬ ነው :: ለምሳሌ አንተ እንደጻፍከው ” ለማስታወስ ያሂል ነው! ” እና ” ወንዲሚህ አሉላ ” ብለህ ጽፈሃል እንግዲህ ” ያሂል እና ወንድሚህ ” የሚሉት በአማርኛ ቋንቋ የቃላት ስህተት አጻጻፍ ውንድሜ አሉላን ከወደ ኦነግ የሚገፉት ከሆነ ፍርዱን ለወንድሜ አሉላ እተወዋልሁኝ ::
October 9th, 2009 at 1:38 pm
Aha ! ( read before comment on something)
Why do you bark before you see the program of mederek.. they have already stated that they will work under the unity of Ethiopia with federal system and abandaning article 39 of ethiopia. Honerable Bulcha has said it in Voa, why have already heared. What do you want more aha.. except if you don’t have a hate for the oromo people.what is wrong if they prefer self-determination. Do you think that you are going to hold the oromo under ethiopia if they don’t want to live with the rest of the Ethiopian people. You can demand and work all the process of self determination to go in free and democratic way alas. If you want to struggle for the unity of ethiopia you should argue your points how unity is good Ethiopia. Otherwise barking unity unity leade you any where..
October 9th, 2009 at 11:47 pm
Anga! It is a drama played out by the oblivious elites in the Diaspora against the silent majority of Ethiopians, who have been under the controll by the multi-layered, hierarchical poitical model of TPLF/eprdf, ever more tightening its grip, which is now sustained by its alterego Medrek/FDD with ethnic agenda with conlomerates of loyalist opposition parties with ethnic agenda as their entitlement from TPLF/eprdf gearing up for election without an ultimatum of seeing the the 8-point preconditions implemented. Nor have they any chance of winning to take over the Government, other than to garner a few more seats, depending on political space, while are complaining of imprisonement of their potential candidates, eventhough such incidences have been going on in the past elections. Whether they win or not what is concoted for the majority of Ethiopians is a bicameral chamber of TPLF/eprdf on one side and Tigrai harena/Medrek on the other side, to say the least whether the ledars in Mederk qualify for the position or not.
October 10th, 2009 at 10:13 am
The Woyane cadres inside and outside the country talk ad nauseam about the astounding development achieved under the Woyane rule. Don’t believe a thing of it. These are either mercenary liars or delusional. The much bragged about infrastructure development is anything but impressive. There is some road construction for sure. And for some one who hasn’t seen much in their lives, even the little is a lot. It is the perception that is hoodwinked. Even some of the people I talked to in Ethiopian tend to compare the little with the nothing and betray a slight sign of contentment. But, I asked, why compare the little with the nothing? Why not compare the little with what could have been had?
October 10th, 2009 at 1:23 pm
ለተክሌ:- የተለያዩ አስተያየቶች እንደሚያሳዩት ተክሌ ጽሁፎችህን በደንብ ኤዲት ማድረግ እንዳለብህ የሚጠቁሙ ይመስሉኛል አየህ የዚህ መድረክ ዋና አላማ ሀገራችን ስላለችበት አንባገነናዊ አገዛዝ መወያየት ትግሉን ስለሚደግፉ ድርጅቶች ሀሳብ መስጠት ድካምና ጥንካሬያቸው መመካከር ነው እንጂ ስለግለሰቦች የእለት ሪፖርት የአጻጻፍ ብስለት መሆን የለበትም ለዚህም መነሻው የአንተ የተክሌ ጽሁፎችህን በደንብ አለመመልከት ነው እኔ እንደሚታየኝ ግን ጽሁፎችህን ለተመልካች ከማውጣትህ በፊት የበሰለ የጽሁፍ ሰው ማሳየት ያለብህ ይመስለኛል ጣጣው እዛው ይለቅና እኛ ስለትግሉ ብቻ እናውራ ጽሁፎች ሲወጡ ሁሉም አይነት ዜጋ እንደሚያነበው ሳትገምት አትቀርም መቼም ምሁሩም ጨዋውም ….. ደሞ እኮ ጽሁፋቸውን እንከን የለሽ ለማድረግ የአለም መሪዎችም ደራሲያንም…… ለንባብ ከማብቃታቸው በፊት ያስመረምራሉ አንተም ይሄንን ዘዴ የማትጠቀም ከሆነ አስብበት ቅንንነትና ሆነስቲ ውስጥህ ይታያሉ ነገሩ ስለኢትዮጵያ ነውና ጽሁፎችህን እያስመረመርክ የበሰሉ ፎርማል የሆኑ ጽሁፎች ይዘህ ውጣ: ጠንካራ የበሰለ ታጋይ እንዲወጣህ ምኞቴ ነው ደህና ሁን ትችት ጉዳት የለውም ብዬ ነው::ከዳላስ ነዋሪ
October 10th, 2009 at 4:57 pm
ethiopians in usa. are you so dysfunctional?? tamrat layne, ermias legesse and all former murderers all are now in usa. why dont you take them to court? why you bark in the internet?? where are the so called kinjit support groups?
October 10th, 2009 at 7:31 pm
ለአለማየሁ
? አንተ እንዳልከዉ እዉነትም ኢትዮጵያ ምርጥ ዲፕሎማቶች አሉዋት ለዝህም አይደል በደምና በአጥንት የተገኘዉን መሬት አሳልፋችሁ የሰታችሁት ??? ቂቂቂቂቅ… ግሩም ነው:;
መለስ ጋር አልጀርስ አብረህ የሄድክ አንዱ አንተ ነህ አይደል ? ሳምሶናይቱን ተሽክመህ ?ከዚያ አበልህን ስታሰላ ውለህ ይሁን ወይም ኢንግሊዘኝኛ ካለመቻል የተነሳ የተባልዉን ትተህ ያልተባለውን ሪፖርት አቅርበህ ያችን አምባሳደር ቖንጅትን አሳስተህ አልነበረም እንዴ ?
እሰኪ ከምርጦቹ ዲፕሎማቶች ትቀስልኝ ብልህ መቸስ ያንተ ነገር እኔ ትል ይሆናል ከዚያም ተክላይ:ገብራይ:ሃጎስ: መሃሪ :ስዩም:አሰግዶም;ሃዱሽ እያልክ መዘርዘርህ አይቀርም ያሉት እነዚሁ ናቸዉና::
ስለውች ጉዳይ ካነሳህ አለቃህ ስዩም ከቀረጥ ነጻ እያስገባ የሚቸረችርዉን በቅርብ ጊዜ ሥለሚወጣ ታነበዋለህ::እሱ ነው የናንተ ድፕሎማሲ::ሌብነት!ዘነበ ግን ይህን ዝርፊያ ነው የተቃወመው ለዚህም ችሎታ ይጠይቃል:: የውሳኔ ስው መሆንን ይጠይቓል!አንተ ግን ክነዚህ ወንጀለኞች ጋር ምን እንደምታርግ ቆም ብለህ አስብ::
የኢትዮጵያን ህዝብ እያገለገልኩ ነኝ ብለህ ራስህን አታታልል::ከወያኔ ጋር ሆነህ የኢትዮጵያን ህዝብ እየገደልከዉ እንደሆነ አሁን አስታውስሃለሁ:;ህግ በይጤይቅህ ነግ ሂሊናህ እንደሚጠይቅህ አትዘንጋ!ትንሽ እግዛብሄር በውስጥህ ካለ ማሌቴ ነው::
ደግሞ ልጅ ተክሌን ሂድና ትምህርትን ጬርስ ትለዋለህ ?አንተ የምታገለግለው ወያኔ አይደለም እንዴ ካገር ያስወጣው እንዳይማር በገሩ እንዳይኖር:ዝ ዘረኝነትን ደግፎ ከወያኔ ጋር ባለመተባበሩ::ምንም እፍረት የሌለህ ነገር ነህ:;
ለግለሰቦች እኩልነት የሚታገል መንፈስ ይደርብህ::አሜን
October 11th, 2009 at 8:27 am
ወያኔዎች አዲስ አበባ የገቡት ሁሉንም ይዘው ተረድተው መሆኑን አንርሳ: ዋናው ሻቢያና ኦነግ ሌሎችም ጭምር::
ጸረ ወያኔ የሆነውን ሁሉ ይዘን ወያኔን ከምድረ ኢትዮጵያ ማስወገድ ቀዳሚ አላማችን መሆን አለበት እላለሁ::
ምንም ምንም ተባለ መጻኢው መንግስትን ለመመስረት መላው ኢትዮጵያዊ አንድነቱን ለመጠበቅ እንጂ እንደወያኔ አይነት በምንም በምንም አይነት እንገንጠል የሚል ህዝባችን አያስተናግድም አያስብም::
ቀዳሚ ተግባራችን ወያኔን ማስወገድና የአንድነት ትግልን ለማጠናከር እንጂ በትግሉ ጎራ በእሳት የተፈተኑትን እውነተኛ ኢትዮጵያውያንን እንደተክሌ በጭፍን መተቸት ያለመብሰል ነውና: ቅሬታ ካለ በግል መወያየት ትልቅነት ነውና: ለወያኔ በር አንክፈት::
October 11th, 2009 at 9:42 am
Girma,
I can tell you the names of competent Diplomats in the Foreign Ministry which will be a long list. But Zenebe can never join that list. Never. It was even a surprise for most when he was assigned as a diplomat. he was on the border of being fired cause he didnt deliver anything. Foreign Ministry is the best Government institution in ethiopia. It has professionals and committed ones from junior to senior and knowledgeable servants.
Zenebe Just talked about one Embassy. You cannot generalize like that. Well, Yes Tekle was a student in 6 killo. I agree he left the country cause he had to save himself. But, i still maintain he better persue his study rather than writing amateurish paper.
October 12th, 2009 at 7:28 am
Weyane-alemayew, You can tell us there are none educated Dedebit-Tegadaly bunches in everywhere as a Diplomat &……
It is ridiculous & shamefull that, you are saying proffesionals. In the Weyane Minstry of Foreign, everyone recognized that 99% of the workers are an extrimist, Nationalist & racist Tigray Tegadalays spying in the diaspopra Ethiopian communities.
The Weyane racist top Leaders are given to their workers, The Civil service college certificate or forged Addis Abeba University degree.
We are confirm this practicaly one of the Weyane member Hodam had a forged degree of the Addis Abeba University, but He do not have any kind of knowledge to do, He is working or barking in one of the weyane Internet Radio-Station for nothing.
Zenebe has mentioned about, all of the Weyane Embassies, The Majority of the spying Tegadalay workers are from Tigray.
-Weyane alemayew! All Ethiopian enemies never exist forever. The truth Ethiopian are struggling against your brutal racists for JUstice, Freedom & Democracy; They all are on the way.
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
አንድነት ኃይል ነው!!!
October 12th, 2009 at 11:01 am
This is a day that equally frustrated me as June and Nov 2005 mass murders. This guy is another Lidetu. I am frustrated because the Party I was aspirying for Ethiopian freedom has such self seeking, woyane oriented individual in its leadership. First of all what he wants is to tell advertise himself as he went to AAU by mentioning about Zenebe’s school history. Then he proceeded to Eirtrea which all Ethiopians are afriad of to be a secret allay of woyane even if they pretend to be enemies and he is pushing the struggle to be directed that side. Thirdly he started to preach us the same old woyane strategy of ethinic and religious conflict biases. Dr Birhanu is such a linient person that he is hurting the struggle by allowing the inclusion if such individuals. he did the same thing with lidetu. He knew that Lidetu was woyanes security person but could not take any action until Kinijit was finally dismantled because of him. He also made the biggest mistakes ever by taking the major part of blocking the “meskerem 22, 2005″ public demonstration with Beyene Petros who later got his reward by crowned Professor by woyane. Only for the sake of making the leadership multi ethinic, we don’t have to include such distructive individuals. Mark my words, you will see every secret meetings and plans will land to woyanes office after the event like lidetu used to do. And finally you will find him collaborating with woyane officially. He is both woyane and shabia bloods. I am flattered today may God Save our loved Nation.
October 13th, 2009 at 6:38 pm
ለታጋይ አለማየሁ…..
እስቲ ጎበዝ ከሆንክና በራስህ የምትተማመን ከሆነ እውነትኛ ስምህን ተናገርና ይውጣልህ::ሆኖም ግን በራስህ ስለማትተማመን ስምህን አትናገርም::ዘነበ ግን በራሱ የሚተማመን ስለሆነ የሚያምነውን ተናግሮ ወጥቶአል::ለሂልና መታመን ማለት እንዲህ ነው!
በተረፈ ውጭ ጉዳይ ችሎታ ባላቸው ባለሙያዎች የተሞላ ነው ያልከው እውነት አይደለም::ያሉት ሆዳሞችና “opportunists” ናቸው::ከዝህ ቀደም ጎበዝ ተማሪዎች ከየዩንቨርስቲው እየተመረጡ ይቀጠሩ ነበር አሁን እንርሱ በሙሉ ተባረዋል::የቀሩት አንተና መስሎችህ አነ ገብሩ; ሀዱሽ;መሃሪ;ገብራይ;ስዩም;አረጋዊን የመሳስሉት ናችሁ::ምንም የኔ የምትሉት ነገር የሌላችሁና እውነት የሚባል ነገር ውስጣችሁ ያልተፈጠረላችሁ:: ሁሉንም እሺ ብላችሁ በልታችሁና ሆዳችሁን ሞልታችህ የምትኖሩ::
አሁንም ተክሌን በተመለከተ ዝም ብትል ይሻልሃል::እርሱ ለሂሊናው የሚኖር ስው ነው:: እንዳንተ የደብተራ ትምህርት ተምሮ ጨርሻለሁ ከማለት ሳይማሩ ለነጻነት መኖር እጅግ የተሻለ ነው::የአንተ ትምህርት መጨረስ ምን የፈየደው ነገር አለ ? ነጻነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንኩዋን ገና አልገባህም:: ነጻነት የማያውቁ ወያኔዎችን ወግነህ የሚወረውሩልህን ትርፍራፊ እየለቀምክ ትኖር የለ ?በዚያ በውጭ ጉዳይ የሚፈጸሙ ዝርፊያዎችን እንኩዋን ለመቃወም አቅም አጥተህ እየኖርክ ችሎታ አለኝ ብለህ ማውራትህ ሂሊና ቢስነትህን የሚያመለክት ነው::
እኔ አስከማውቀው ድረስ አለማየሁ የሚባል ውጭ ጉዳይ የሚሰራ የለም:: እስቲ ወኔው ካለህና የምትናገረውን ታምነው እንደሆነ እውነተኛ ስምህን ተናገር;;ከዚያም የበለጠ እንግርሃለሁ::ምደባህ እንዲራዘምልህም ምክንያት ይሆንልሃል:;
በመጨረሻም አንተን ከዘነበ ጋር ሳወዳድርህ እርሱ በራሱ የሚተማመን አንተ ደግሞ አድር ባይ ደብተራ ነገር ነህ::ምናልባትም ከትግራይ ደናቁርት ካድሬዎች አንዱ ነህ:: አሁን ሂድና አንዳርጋቸው ጽጌ የጻፈዉን ነጻነትን የማያውቁ ነጻ አውጭ የሚለውን መጽሃፍ አንብብና ራስህን ፈትሽ:: ዝም ብለህ አውቂ ንኝ ብለህ ራስህን እዚያ ላይ አትስቀል::
ለግለሰቦች መብት እኩልነት የሚያታግል መንፈስ ያሳድርበህ!አሜን;;