ኢትዮጵያውያን (በተለይ አማሮች) ቢኖሩ አይጠቅሙንም፡ ቢጠፉም አይጎዱንም፡ (1975፡ ሕወሀት)
እየተጓዝኩ ነበር። ከቦታ ቦታ። ከቢሲ እስከ ዲሲ የታዘብኩትን፡ የከነከነኝን፡ ሆዴን የበላውን እጽፋለሁ እያልኩ ስዘገጃጅ፡ በዚህ መሀል ነው ገብሬን ሲናገር የሰማሁት። ገብረመድህን አርአያ። የሱ ወግ ጊዜ አልሰጠኝም። ሌላው ይቆይ። የቀድሞ የህወሀት አባልና ገንዘብ ቤትን ወግ ላወጋችሁ ፈቀድኩ። ሙያዬ ምስክር፡ ወይም ብዙ ወንድማገኘሁ አንዳንደዬ ልብ ሰቃይ ቅጽበቶች ላይ እየገባች ብስጭት ብታደርገኝም፡ እየጎረጎረች፡ እየሰረሰረች፡ ደግሞም እየፈለፈለች የምታወጣቸውና የምታናዝዛቸው ሰዎች ያስደስቱኛል። ባለፈው ቅዳሜ፡ ገብረመድህን አርአያ አስደሰተኝ። አስደመመኝ። አሳቀኝ። አሳዘነኝ። እንደወረደ ይናገራል። እንደመጣ ይሰይማል። ጣጣ የለውም። አብርሀም ያየህ እሱንም አበሳጭቶት ኖሮ ፡ “ዋይ፡ እሱ እኮ ጭልፊት ነው፡ ጭልፊት ታውቃላችሁ? ጭልፊት። ቆሻሻ ነው። ሌባ ነው። የማይረባ።” ለብቻዬ ነበር የምሰማው። ቤቴ እስኪታዘበኝ ሳቅኩኝ። ተንከተከትኩኝ። ሁለት ሶስት አራት በሳቅ የሚያንፈቀፍቁ ቅጽበቶች ነበሩ፤ በዚያ ባለፈው እሁድ፡ ኦገስት 23 ቀን በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች መወያያ መድረክ እንግዳ ሆኖ የቀረበው አቶ ገብረመድህን አርአያ በሰጠው ቃለ ምልልስ ላይ።
ገብሬ ማነው? ገብረመድህን አርአያ የዛሬ 36 ዓመት ኣካባቢ ነው መንገድ ላይ ሲሄድ ወይንም እርሻውን ከሚያርስበት መጥተው የማገብት ሰዎች የያዙት። ማህበረ ገስግስቲ ብሄረ ትግራይ። ምንም የፖለቲካ እውቀት አልነበረኝም ይላል። ብሄር፡ ብሄረሰብ፡ ብሄርተኝነት፡ የብሄር ጭቆና ምናምን የሚባል ነገር አያውቅም ነበር። በዚያ ምንም በማላውቅበት ጭንቅላቴ ገብተው የነሱ ተከታይ አደረጉኝ አለ ገብረመድህን። በወቅቱ ማገብት በኋላም ተሀህት ከዚያም ህወሀት፡ እስካሁንም ድረስ ትግላቸው በሶስት ዋና ዋና መርሆች ላይ የተመሰረተ ነበር። ኤርትራን ማስገንጠል ወይንም የኤርትራን ቅኝ ግዛትነት መቀበል። የቀይ ባህር የኢትዮጵያ አካል አለመሆን መቀበልና አማራውን ጠላት አድርጎ መቀበል። ሶስተኛውን ረሳሁት። ስለዚህ ከመጀመሪያውም ሕወሀት ኢትዮጵያን ለመበታተን ኤርትራን ለማስገንጠል የተፈጠረ ቅጥረኛ ድርጅት ነው ይለናል ይህ ሰው። ከኢትዮ ሚድያው አብረሀ በላይ ጋር ይስማማሉ እዚህ ጋር። አብርሀም ይሄንን ነው የሚለው http://ecadforum.com/ECADF_VIDEO.html።
ስለኢኮኖሚ ምንጫቸው ስለዓላማቸው ተጠየቀ።
ገብረመድህን አርአያ እንዳስቀመጠው፤ ባጭሩ የሕወሀት የኢኮኖሚ ምንጭ ዘረፋ ነው። ሕወሀት መጀመሪያ የትግራይ ዜጎችን አስሮ እየገረፈ ይዘርፍ ነበር። ጎን ለጎን አማራው የትግራይ ህዝብ ጠላት ነው ብሎ ተነሳ። ኤርትራም ቀይ ባህርም የኢትዮጵያ አካል አይደለችም ብሎ ተዋጋ። በዚህና በሌሎችም ምክንያት ሕወሀት በትግራይ ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት አልነበረውም። በዚህም ምክንያት ብዙ የትግራይ ኢትዮጵያዊያን ተገድለዋል። አቶ ገብረመድህን ብዙ ስም ጠራ፡ እነ ክቡር ፊታውራሪ ምናምን። እነ ደጃዝማች እከሌ። እነ ክቡር ደጃዝማች እንቶኔ። ብዙ የላይኛውን አማራውን ጠላት አድርጎ የመነሳትና ኤርትራን የማስገንጠል የህወሀት አላማ የተቃወሙ የትግራይ ኢትዮጵያዊያን ተገድለዋል። መቼም ታሪክ ስለሆነና አቶ ገብረመድህን ስላለው ላንሳው እንጂ፡ ዛሬ የኤርትራ እጅ እንደሚያስፈልገን የማምነው ሰው ይሄንን መዘገብ አልነበረብኝም። ግን እሱ አቶ ገብሬ አለ።
ስዬ መጣብኝ። ስዬ አብርሀና ገብረመድህን አርአያን በሁለት የተለያዩ ቅርንጫፎች ላይ የሚያስቀምጥ ነገር ብዙ ነው ከዚህ ቃለ ምልልስ እንደተረዳሁት። የዛሬ ዓመት ከምናምን አቶ ስዬ ከእስር እንደተፈታ ከዚያም በኋላ በተካፈለባቸው ስብሰባዎች ላይ ሲናገር አደምጫለሁ። ሌሎች ስለሱ የጻፉትንም ተመልክቻለሁ። ስዬ ፍንክች አላለም። ምንም ሀጢያት ሰራን አይልም። ግበሬ ግን እኔ ሀጢያተኛ እያለ ንስሀ ይገባል። አሁንም ስዬ በመድረክ በኩል ከአንድነት ጋር ወግኖ በመስራት ሕወሀትን ለመደምሰስ ይረዳናል ብዬ ብመኝም ለክ እንደኤርትራው ጉዳይ፡ የተባለውን እንደተባለ ከማቅረብ አልቦዝንም። ለነገሩ ይሄ አቶ ስዬን ምላሽ እንዲሰጡ ያነሳሳ ይሆናል እንጂ አይጎዳም።
ዌል፡ ገብረመድህን አርአያና ስየ አብርሀ በሁለት ዓለም ውስጥ ያሉ፡ አንዱ ባውሮፓ አንዲ በኢትዮጵያ፡ በተለያየ ምክንያት ከህወሀት የተገለሉ ወይንም የወጡ ሰዎች ናቸውና፡ ባንድ አይነት ቋንቋ እንዲነጋገሩ ወይንም እንዲመሰክሩ መጠበቅ የለብንም። ግን ልዩነታቸው እጅግ በጣም የተለያየና የሰማይና የምድር ያህል የሰፋ ሆነ። አንዱ ሕወሀትን በሀጢያት ተጸንሶ በሀጢያት ያደገ በሀጢያትም ህይወቱን የሚገፋ የመርገምት ድርጅት ያደርገዋል። አንዱ ደግሞ፡ አቶ ስዬ፡ ሕወሀትን በርግጥም ለቅድስና የቆመ፡ ነገር ግን በሀጥአን የተነጠቀ የቅድስና ድርጅት ያደርገዋል። ለስዬ ሕወሀት ጥቂት ሰዎች ከተወገዱ መታደስ የሚችል ምንም ወንጀል ያልፈጠመ ድርጅት ነው። ለግረመድህን ደግሞ ወያኔ፡ ለፍርድ መሰቀል ያለበት የጥፋት ድርጅት ነው። አንዳንዱ የአቶ ገብረመድህን ምስክርነት ለኔ ራሱ የሚዘገንን ነው። አገር የወጉ። አገር የሸጡ። ህዝብ ያስጨረሱ። ህዝብ ያደሙ። ወገን በረሀብና በመሳሪያ የፈጁ ያደርጋቸዋል ገና ሲፈጠሩም።
የጋሽ ገብሬ ምስክርነት ይመች ነበር። ማንም ሊያደምጠው ይገባል።፡የምግባረ ሰናይ ድርጅት ያቋቋምነው በ1975 ነው አለ። ከዚያ በፊትም በኋላም ግን እንዘርፍ ነበር። እስኪ አቶ ገብረመድህን ሲናገር እንስማው። “እኔ ያኔ ሱዳን ውስጥ እርዳታ የመቀበሉንና ገንዘብ የመቀበሉን ስራ እሰራ ነበር። ብዙ ፈረንጆች ይመጡ ነበር። እርዳታ ለመስጠት። ኋላ ላይ አለቃዬ ስብሀት ነጋ ጠራኝና ገበሬ ወይንም ነጋዴ መስየ እንድቀርብ አደረገኝ። አንዴ ሀኪም እንድሆንም ተደረግኩ። እኔ ገብረመድህን አርአያ ሀኪም መሀመድ እንድሆን ተደረግኩ። ቁርአንና መቁጠሪያ እንዲሁም ጥምጣም ተሰጠኝ። አንድ ታጋይ ሚስትም ተመርቆልኛል አለ ገብረመድህን። እንግሊዘኛ በፍጹም እንዳልናገር አስጠነቀቁኝ።” ማሽላ መሸጥ ነው የሱ ስራ። “ግን የቀረበው የእርዳታ ገንዘብ መጠንና የማሽላው ብዛት አይገናኝም። ስለዚህስ? ከተከዜ አሸዋ እየተጫነ መጣና ማሽላ እንዲመስል ተደረገ። ከፊት ከፊት ማሽላ በጆንያ። ከኋላ አሸዋ የተሞላ ጆንያ ተቀምጦ፡ አንድ ግዜ ሰላሳ ሁለት ሚሊዮን ሌላ ጊዜ አርባ ስድስት ሚሊዮን ዶላር ሸጥን” አለ። ይህቺ ናት ጨዋታ። ይህቺ ናት ብልጠት። ብሩን ስብሀትና መለስ ወሰዱት አለ። ከዚህ ምን እንማራለን? ብዙ ነገር። ለምሳሌም።
ሁለት ነገር ታየኝ እዚህ ጋር። ዋናው ነገር ወያኔዎች እየዘረፉና እያጭበረበሩ እያምታቱ ሀብት መሰብሰባቸው ነው። ግን ትንሽም ቢሆን ጠላትን ማድነቅና ከጠላትም መማር አለብን። እንደው ጥሎብን ከጠላት መማር አልለመደብንም እንጂ፡ በዚያን ዘመን ጭንቅላታቸው ይሄንን ያህል ብልጠት ከሰሩ፡ እንደው መድሀኔዓለምን ነው የምላችሁ ትንሽም አደነቅኳቸው። ። በዚያ መልኩ ነው ማለት ነው ጄኔራሉንና አገሩን ሁሉ እየገዙ እዚህ የደረሱት ያስብላል። ያ ብቻ አይደለም፡ እኛም እነሱ የደረሱበት ለመድረስ ይሄንን ያህል መጓዝ ይጠበቅብናል ማለትም ይመስላል። አሸዋ እንደ ስንዴ መሸጥ አለብን አይነት ነገር። በሚቀጥሉት ቀናት ስለገብረመድህን አርአያ ሌሎች ምስክርነቶች እጽፍላችኋለሁ። ለምሳሌ እሱን ስለዘገነነውና አሁንም ድረስ ቋቅ ስለሚለው ያልተለወጠ የ1975 የሕወሀት መፈክር። እሱ እንዳለው፡ “To keep the Ethiopians is not benefit, to kill them is not loss” አባባል። ይሄንን እሱ እንዳለው ነው ያሰፈርኩት። ኢትዮጵያውያን በተለይ አማሮቹ ብናቆያቸው አይጠቅሙንም፡ ብናጠፋቸውም አይጎዱንም። “አፈር ያርገኝ” ትላለች እናቴ ስትምል። እኔል ልበላችሁ። እንደወረደ፡ ገብረመድህን አርአያ እንዳለው ነው ያሰፈርኩላችሁ። በዚህ ፖሊሲ እጅግ ከማዘኑና አሁንም ድረስ ከመጸጸቱ የተነሳ፡ ገብረመድህን ይሄ በዓለም ላይ በየትም የሌለ እንደው በካምቦዲያም ያለጠፈጸመ ጸያፍ ፖሊሲ ነው ይለናል ደግሞ ደጋግሞ።
ስለገብሬና ቃለምልልሱ የምለው ይቀጥላል። እስከዚያው ግን ሙሉ ቃለ ምልልሱን http://www.ecadforum.comላይ መጠበቅና ማዳመጥ አለባችሁ። ያልተናገረበት ርእስ የለም። ከሀውዜን እስከ ሱዳን ከአዜብ ጎላ እስከ አብርሀም ያየህ፡ ከዚህ በኋላስ እንዴት መጓዝ አለብን በሚለው ርእስ ላይ ጥሩ ተናግሯል። እንደው ምንም አላውቅም ይላል እንጂ፡ ብዙ ያውቃል፡ ሰውዬው።


August 26th, 2009 at 4:30 am
i don’t understand the merite of this article. We know gebremedihen gave simillar interview in Ethiopian radio and tv during mengistu hailemariam era. And it is obvious that woyane is thief and ruthless killers and ignorant s. There is nothing new in this article except mentioning again about how intelligent woyanes are ” selling sand instead of wheat” this breach of trust not intelligence and Gebremedhin is telling us to do the same and it looks like the so called Tekle is agreed to his point. In conclusion woyane knows that they are ignorant and they also believe that it is too late for them to get the education since they spent their youth in the cave however they envy the groups of Ethiopians with most intellectuals and i believe they fell inferior towards them. This is the main agenda that unites all previous and current members of woyane IGNORANCE; the funny thing is that they want to get out it by giving interview or campaign at different level and situation.I will give some example:
1)Azeb Mesfin(Gola) she gave interview abut her husband intelligence including many woyane cadres
2) As we have just read it the uneducated gebremdihin told us how intelligent woyanes for breaching their trust not knowing even monkeys in the amazon used camouflages to protect their craked nuts. By the way they crack their nuts with two rocks too.
3) there was an article titled Meles’s thesis that was the funny one and so on.
ባጪሩ አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል ነው
August 26th, 2009 at 6:57 am
ባልሳሳት አቶ ገብረመድህን በደርግ ጊዜ ነው እሕአዴግን የከዳው (ሞክሼ ካልሆነ): ያኔም የተናገረው ብዙ ነገር ነበር:: ያም ሆነ ይህ ኢሕአዴግ ምን እንደነበረ ማውራት ብዙም ጥቅም ያለው አይመስለኝም:: ደርግም የወደቀው የወያኔን ማንነት መረዳት ስላቃተው አይደለም:: አንዱ የከዳ ወያኔ በተናገረ ቁጥር እየተነሳን መጨፈር ምንም አይጠቅምም: እነሱ ስለነገሩን ምናደርገው ነገር የለም: ባይነግሩንም የሚቀርብን ነገር የለም: ጉዛችንንም አንድ እርምጃ ወደፊት አያንቀሳቅሰውም:: ለነጻነትና ለዲሞክራሲ የሚታገል አላማውን ያውቃል: ምን ማድረግ እንዳለበትም ማወቅ አለበት: ወዴት መሄድ እንዳላበተም ማወቅ አለበት:: የእነ ገብረመድህን ወሬ ለጊዜው ግርምት ይፈጥርብን እንደሆን እንጂ ምንም ጥቅም የለውም::
August 26th, 2009 at 8:19 am
ተክሌ ስለ ገብረመዲህን ጥሩ መጣጥፍ ነው ያቀረብከው ማን ያርዳ የቀበረ ማን ያርዳ የነበረ ነውና.በርግጥም ስዬ እና ገብሬ የተለያዩ ex ወያኔዎች ናቸው::
August 26th, 2009 at 8:29 am
ልጅ ተክሌ ተባርክ..አንተ ደግሞ ……አዬ…
እሱ መናገር ያውቃል..አንተ ደግሞ ..ማጣፈጥ ስትችል!!!!ለዚያውም
ካለ ቁዋንቁዋችን በእንግሊዝኛው ላይ ዘለው ከሚንፈራጠጡት ተለይተህ
ጥሩ አቀናጅተህልናልና…ይልመድብህ…
ፋሲል
August 26th, 2009 at 9:16 am
አባኪያ በጣም አመሰግንሃለሁ: ያልተረዳ እንዲረዳ ያቀረብከው ትንተና: ላልገባው እንዲገባው የሚያብራራና ጥልቅ የሆነ ማሳሰቢያ ያለው ስለሆነ ለማወቅም ለመገንዘብም በትግሉ ጎራ ያለውን ህብረተሰብም ምን ያህል ሃላፊነት እንዲሰማውና በተለይም በትግራይ ክፍለሃገር ያለውን እኔስ ከወዴት ነኝ የሚል “መልእክተ ኢትዮጵያውያንን የሚወክል በመሆኑ “የኢትዮጵያ አምላክ ይባርክህ ይልመድብህ” እላለሁ::
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
August 26th, 2009 at 11:40 am
ፍስሀ: we were not all born or grown ups or adult during the Dergue regime and when Gebremedihin spoke on the TV and radio. Do u know that the Ethiopian population has almost doubled since 1988. Therefore, for us the young generation, what Gebremedihin said is new and important. Lelaw ነገር: we are human and we forget quick and do not hate that Gebremedihin’s interview was repeated ….
Sami
August 26th, 2009 at 12:19 pm
They hate us simply because we are amara. We didn’t choose to be amara. We happed to be and we can not trade our blood – we are amara and Ethiopian.
August 26th, 2009 at 12:53 pm
ተክሌ እድሉንና ጊዘውን አግኝተን ላላዳመጥነው እንድተለመደው በቆንጆ አማርኛ ከስነህ ስላደረስከን ምስጋናችን የላቀ ነው: ይደግ ይመንደግ ነው የምለው!!!
August 26th, 2009 at 1:19 pm
ሰላም ተክሌ ሁል ጊዜ በሚታደርገው ጥረትህ እኮራለሁ ወጣት ነህ, በቂ እውቀት አለህ; ሃገርህን ታወዳለህ,የ ሰነ ጽሁፍ ብቃት አለህ ,ትክኖሎጂን የመጠቀም አቅም አለህ ሰለዚህ ፈቃደኝነትህ ካለ ሁሉም በ እጅህ, ሁሉም በደጅህ ነው በርታልን የኢትዮዽያ አምላክ ይጠብቅህ ::
አባትህ ሀገሩን ጠብቅዋል ብጦር;
አንተም ተዋጋላት በብዕር::
አሰንቲ ሳና!!!
August 26th, 2009 at 2:50 pm
Dear Sami i respect your point of view but since woyane come in power it is 18 years and if you are younger than that i will appreciate your concern for the current Ethiopian situation by visiting this site. Saying that; what gebremedihen said was obvious and you would probably experienced it during the past election and a federal police might have struck you unless and otherwise you are to the other of the addis ketema ,menen tikuranbesa ,shimeles habte high school students.Or gebremedin is not an eloquent speaker nor bright his interview is a living proof for my comment on him. In conclusion; we don’t want this kind good for nothing ppls in here rather it is better to invite intellectuals or peoples with extra ordinary life experience from other walk of life not from woyane. Woyanes could write on their aiga forum and in their tigree only parties.
August 26th, 2009 at 3:14 pm
አበበ , ፍስሃ…..እና……
ወያኔ..18 አመት ሙሉ ትንሽዋን ነገር እ የ ደ ጋ ገ መ ህዝብ ግራ ሲያጋባ ሲያስርና ሲገድል ተደጋግመብን ብላችሁዋል?
የአቶ ገ.መድህን ቃል አይደለም ሁልቴ ገና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ጆሮ እስኪገባ ይደመጣል , የጻፋል, በፊልም የጠነጠናል. የሚያመው ሰው አለማንበብ , አለማየት…መብቱ ነው.ለብዙዎች አዲስ ሊሆን ይችላልና
ክፉ ነገር አይመስለኝም.በዚያ ላይ የ17 ዓመት የሕወአት የትግል ውጤት ስለሆነው ስለ ቀለበት መንገድና ….ትርኪ ምርኪ ውሸቶች ጠዋት ማት ዜና ይሄ ባይሻል ነው?
የወያኔ ሚስጥር ወጥቶ ሺ ግዜ ተደጋግሞ ቢነገር ቅሬታ ሊሰማን አይገባምና ጥቅም የለውም ብሎ ማጣጣሉ ለበጎ አይመስልም.
ብትችሉ በተለያየ ሜድያም እስር ቤት ላለው መላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ልናደርስለት አንጣር.
ከሁሉም በላይ በ ገ.መድሕን ቃል ውስጥ አሸዋ በጤፍ ያመለውጥ ብልጥና ብቻ ሳይሆን ..ሌሎች አይናችሁ ተገልጾ ሊያየው የሚገባ አደገኛ ነገሮች አሉት.
ፋሲል
August 26th, 2009 at 3:40 pm
ከጌታቸዉ ረዳ
የኔ አስተያየት አቶ ክንፉ የተባለዉ ዚህ ድረገጽ አዘጋጅ የኔን ጽሁፍ እንደ መብረቅ ይፈራዋል እና ኣያትመዉም እንጂ -ቢያትመዉ ኖሮ አንተ ባልከዉ በዚህ የገብረመድህን ኣርኣያ ጽሁፍ ብዙ ባልኩ። ሆኖም አስኪ ለናሙና “ገብረመድህን አርአያ” (ባንተ አጠራር “ገብሬ”) ተናገራት ያልካትን ስህተትህን ወይንም ስህተቱን ላርመዉ/ላርምህ።
ልጥቀስ፦
“ገብሬ ማነው? ገብረመድህን አርአያ የዛሬ 36 ዓመት ኣካባቢ ነው መንገድ ላይ ሲሄድ ወይንም እርሻውን ከሚያርስበት መጥተው የማገብት ሰዎች የያዙት።”
ዉሸት!!!!!! ግበረመድህን አርኣያ እኔ መቀሌ እሱ ማይጨዉ በአንድ የምኒስቴር መስርያቤት ተቀጣሪዎች ነበርን እና በደምብ ስለማዉቀዉ፤- አንተ የጠቀስከዉ ወይንም እሱ ገበሬ ነበርኩ የሚለዉን ዉሸት መሆኑን ላንባቢዎችህ ሳዝገነዝብልህ የኛ “ወጣት” ቅር እንደማይልህ ባለሙሉ ተስፋ ነኝ። ጌታቸዉ ረዳ www.Ethiopiansemay.blogspot.com
August 26th, 2009 at 5:12 pm
ልጅ ተክሌ ዛሬም እንደትናንቱ ተባረክ:: ትናንት “ተስፋዬ ገብረአብ ይሰቀል ወይስ ይመስገን?” ብለህ ግሩም የትዝብት መጣጥፍህን አስነብበህን ረክተንብህ ነበር:: ዛሬም ደሞ በነካ እጅህ ገብሬን ደገምክልን:: ቀለም አጣጣልህ አይነ ንባብን ይማርካል:: የምታነሳቸው ነጥቦች ደርዛቸውን እንደጠበቁ ግባታቸውን ይፈጽማሉ:: እናም ድንቁን የገብሬን ወግ ባይነ ብእር እይታህ ስላስኮመኮምከን ብሩክ ሁን ወንድም ዓለም::
ያገር ልጅ
የማር ጠጅ
August 26th, 2009 at 5:39 pm
http://www.ethiotube.net/video/5312/Revolution
we ethiopian have to get those thugs.
August 26th, 2009 at 6:05 pm
I have a big respect for Mr. G/ medhin Araya . Since his escaping from TPLF, he was consistent by exposing the TPLF mafia narrow minded group . He is different from Abraham Yayeh who is a lier, unprincipled and talkative person .
August 26th, 2009 at 7:18 pm
What is Aite Gebremedihin’s vision for Ethiopia? The pre-Weyane form of Ethiopian unity or the post-Weyane form which may be the following?
A new Ethiopia with Afaan Oromo as the National Language
It is clear that only Amhara elites and few Amharanized elites from other nations are against “ethnic” federalism and self-determination of nations. Genuine “ethnic” federalism is the compromise solution for all nations in the region to live together - achieving both national independence and regional integration. The position of Amhara elites regarding the federalism and self-determination made them to be not suitable to cooperate with the elites of other nations against TPLF regime. Amhara elites do prefer unconditional Ethiopian unity rather than self-determination as a precondition for the possible alliance to be forged between Amhara democratic forces and Oromo freedom fighters. Oromos tend to accept this precondition, only if Amhara elites also accept Oromos’ precondition aka making Afaan Oromo the only working language of the federation instead of Amharinya. Oromo elites make such a demand to make Amhara elites to notice how wrong is their cry for unity with Amharinya as the only federal language. Then, in a common house aka “NEW Ethiopia” they suggest to build, the working language must be only Afaan Oromo. Will they then stay to be pro Ethiopian unity and anti ethnicity, even if Amharinya will be demoted to only local language of Amhara region and if Afaan Oromo will be promoted to be the only working language of the Ethiopian federation? I am sure they will not! In case they will stay further to be pro-Ethiopianity and pro-unity as they seem to believe now, let’s then try this NEW version of Ethiopianity with Afaan Oromo instead of with Amharinya.
Read more:
http://www.ethioplanet.com/medrek
In short, the best instrument to compel Amhara elites so that they accept and respect the compromise solution aka genuine “ethnic” federalism and to make them recognize the right of nations to self-determination is to demote Amharinya to be the local language and promote Afaan Oromo to be the federal language, i.e a transformation of the empire to a NEW Ethiopia with Afaan Oromo as the National Language!
August 27th, 2009 at 5:44 am
አቶ ጌታቸው ረዳ! አቶ ገብረመድህን ገበሬም ነበሩ ወይም የሚንስቴር መስሪያቤት ሠራተኛ: ዋናው ነገር:- ፍሬ ነገሩን ወይም ሃቁን መናገራቸውና:- “በትግራይ የተወለዱ ሁሉ የአቶ ገብረመድህንን ፈለግ በመከተል ማለትም ከልብ: ከመላው ኢትዮጵያዊ ህብረተሰብ ጋር በተግባር በመተባበር የፋሽስቱን የወያኔ ጨካኝ ዘረኛ አገዛዝ በመደምሰስ:- “አንድ ሃገር አንድ ህዝብ አንዲት ኢትዮጵያ” አንድነቷ ነጻነቷና የህዝቧ ዲሞክራሲያዊ መብቱ የተከበረባት የፍቅር ሃገር እንድትሆን ሃላፊነት አለባቸው::
ትግራይ ሃረና ወይም ከወያኔ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ዘረኛ ቡድን መፍጠርና ህዝብን ከሌላው ወገን ጋር ማንቆር ለትግራይ ህዝብ የሌላው ክፍለሃገር ተወላጅ ብሄረስብ ሁሉ የመጨረሻ ጥያቄ ማቅረቡ የማይቀር ጉዳይ ነውና ይታሰብበት:: የትግራይ ክፍለሃገር ተወላጅ ሁሉ የወያኔዎች የደገሱለትን የጥፋት ተልእኮ: እያንዳንዱ በፊት ለፊት መቃወምና እንደአቶ ገብረመድህን ይናገር:: ዘረኝነት የትም አያደርስም:: በቁጭት የሚኖሩና ምነው በቀረብን የሚሉትን ባይናችን እያየን ነውና::
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
August 27th, 2009 at 6:41 am
ogina you are living in an endless fantasy world to say the least after saying that ethiopia is not your kid or wife to tell us to change the language from your dining room , let us say even to make your wishful dream true you have to struggle to bring down woyanne firist and then democracy and then the majority ethiopians decide the language the system and all Ethiopia is not a bannana republic like you imagine rather it is land of 3-5 years history
August 27th, 2009 at 6:42 am
sorry 3-5 thousand years history
August 27th, 2009 at 7:34 am
ልጅ ተክሌ- ያለህን ስታበረክት ለሀገርህና ለህዝብህ የምትችለውን ያህል ልትሰጥ ስትሞክር ለዚህም ጊዜህንና ገንዘብህን መስዋህት ስታደርግ መቼም ታውቀዋለህ-አንዳንዶች ለሃገር ሃሳቢ የሚመስሉ ነገር ግን ከሂስ በስተቀር ምንም የሌላችው ስላሉ ከዓላማህ እንዳትዘናጋ:: በተረፈ በጽሁፉ ተደስቻልሁ ሙሉውን ቃለ ምልልስ እጠብቃለሁ::
በርታ!!!!!!