
ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 9/2009 –ቅዱስ ሲኖዶሱ ያረቀቀውን ቃለ ጉባዔ ሳያጸድቅ፣ የጀመረውን አጀንዳ ሰይቋጭ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱን ሜዳ ላይ ጥሎ ወደ ቤቱ ገብቷል። ከስምምነት ላይ የተደረሰበት ውሳኔ በፊርማ እንዳይጸድቅ ብፁዓን አበው እስጢፋኖስ፣ ኤጲፋንዮስና ጎርጎርዮስ የሞት ሽረት ትግል አድርገው፣ አባቶችን በጥብጠው ውሳኔው እንዲከሽፍ አድርገዋል። በተለይም በምዕራብ ኢትዮጵያ በጀመሩት መልካም አገልግሎት በሕዝቡ እየተመሰገኑ የነበሩት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ይህንን ገዳይ አቋም እንዴት ሊይዙ እንደበቁ እንቆቅልሽ ሆኗል። ገሚሱ በገንዘብ ተገዝተው ነው ሲል ሌላው ደግሞ ውስጠ ዘ በሆነ ማስፈራሪያ ሊሆን ይችላል እያለ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ወደ አሸናፊነቱ እየመጡ ያሉት ፓትርያርኩ የበቀል በትራቸውን እንደሚመዙ እየተጠበቀ ነው። የመጀመሪያ ተጠቂዎች የሚሆኑት በአዲስ አበባ የሚገኙ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ሲሆኑ ባለፈው ሳምንት በብፁዕ አቡነ ሳሙኤል መሪነት ስብሰባ ካደረጉ በሁዋላ የፓትርያርኩን ድርጊት የሚቃወም መግለጫ ማውጣታቸው ይታወሳል። ከዚህም ባሻገር ይህንን ሁሉ ሕዝብ ያስተባብርብኛል ያሉት ማህበረ ቅዱሳንም ላይ ጥርሳቸውን ነክሰዋል ተብሏል።
የቤተ ክህነቱ ድራማ ዛሬ ሲተወን ጠዋት በማለዳው ስብሰባ እንዳይገቡ የታገቱት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ለምን እንደታገቱ ፌዴራል ፖሊስ ራሱ አያውቅም። የደህንነት ክፍሉ ደግሞ ለደህንነታቸው ብዬ ነው ብሏል። ድራማው ሊቀ ጳጳሱን ከስብሰባው በማስቀረት ውሳኔውን ማክሸፍ ከሆነ በርግጥም ዘዴው ሰርቷል ማለት ይቻላል።መንግሥት በበኩሉ ጉዳዩን እያጠናው እንደሆነ ውስጥ አዋቂዎች ገልጸዋል።
በተያያዘ ዜና ፓትርያርኩ የተነሣባቸውን ተቃውሞ ለመስበርና አባቶችን አንገት ለማስደፋት የሚሆን ገንዘብ ራሳቸው በግላቸው ከሚያዙበት ከቁልቢ ገብርኤል ካዝና ወጪ መደረጉ ታውቋል። የብሩ መጠን ለጊዜው ባይታወቅም ገንዘቡ ለአንዳንድ የፖሊስ ሃላፊዎች፣ ደህንነቶችና ጉልበት ላላቸው ሰዎች መበተኑ ሲታወቅ መንግሥት በውስጡ ሌላ መንግሥት ያለበት አስመስሎታል። እስከ ዛሬም በመንግሥት ስም ቤተ ክርስቲያኒቱን እግርተወርች አስረው ሲበሏት፣ ሲግጧትና ሲያዋርዷት የነበሩ ሰዎች የፓትርያርኩ ዘመዶችና ወዳጆች ብቻ ሳይሆኑ በመንግሥት ሥልጣን ላይ የተንፈራጠጡ ሰዎችም መሆናቸው እየተገለጸ መጥቷል። መንግሥት ጉዳዩን አጣርቶ ሕገ ወጦቹ እጃቸውን ከቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ እንዲያነሱ ያደርጋል ተብሎ ይገመታል።
ነገሩ በዚህ ከቀጠለ ቤተ ክርስቲያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ አላት ለማለት እንደማያስደፍር አንድ ሊቀ ጳጳስ ተናግረዋል። ከዋሺንግተን ዲሲ ተጠርተው የተሾሙት የሲዳሞ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስና የሥራ አስፈጻሚው አባል ብፁዕ አቡነ ፋኑኤልም በበኩላቸው “ሀ/ስብከቴን ተረከቡኝ” ማለታቸው ተሰምቷል።
በርግጥም ሊቀ ጳጳሱ እንዲህ ካደረጉ ጳጳሳት የሥራ መልቀቂያ የሚያስገቡበት፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ሳይሆን በፓትርያርክና በሴት ወይዘሮዎች ብቻ የሚመራ ቤተ ክህነት ይፈጠራል ማለት ነው።
አንድ አስተያየት ሰጪ እንደተናገሩት የፊታችን ሰኞ ስብሰባ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ስብሰባው የተጠራው በቅዱስ ፓትርያርኩ ከመሆኑ አንጻር ምንም ተለየ ነገር አይጠበቅም። ቅዱስነታቸው የፊታችን እሑድ በዓለ ሲመታቸውን እንደሚያከብሩ ይታወቃል።
ለማንኛውም ደጀ ሰላም በበኩሏ “ተስፋ አንቁረጥ፣ እግዚአብሔር ሥራው ድንቅ ነውና” ትላለች።
ቅ/ሲኖዶስ በአቡነ ጳውሎስ ቦታ “እንደራሴ” ሾመ
(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 9/2009) [PDF]- ትናንት ማታ የተጠናቀቀው የቅዱስ ሲኖዶስ ታሪካዊ ስብሰባ በእምቢተኝነታቸው የጸኑትን ፓትርያርክ ሥልጣን በመግፈፍ እንደራሴ ሾመባቸው። ትናንት የስብሰባው ቃለ ጉባዔ በተነበበበት ጊዜ እንደተገለጸው አቡነ ጳውሎስ ከአስተዳደራዊ ጉዳዮች በሙሉ ተገልለው፣ በጸሎት ብቻ ተወስነው እንዲኖሩ፣ ለዚህም አስፈላጊው ነገር ሁሉ እንዲሟላላቸው፣ በእንደራሴነት ደግሞ ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ እንዲሰየሙ ወስኗል።
ቅዱስ ሲኖዶስ ሰሞኑን ባደረገው ሙከራ አቡነ ጳውሎስ ነገሮችን በጥሙና እንዲመለከቱና በሕገ ቤተ ክርስቲያን እንዲመሩ አባቶች በእንባ ጭምር የለመኗቸው ቢሆንም ፓትርያርኩ ግን ማንንም ለመስማት ሳይችሉ ቀርተዋል። በርግጥም ቃለ ጉባዔው በሚፈረምበት ቀን ማለትም ሐሙስ ጁላይ 9 ጠዋት ውሳኔው ቀድሞ እንደተነበበው ሆኖ ካለፈ አቡነ ጳውሎስ በሕይወት እያሉ ሥራው በእንደራሴው ይመራል ማለት ነው። ይህ ማለት ግን እንደ ቀድሞ ፓትርያርክ ከሥልጣናቸው ወርደዋል ማለት እንዳልሆነ አንድ አባት ለደጀ ሰላም አብራርተዋል። ምናልባት ግን ቅዱስነታቸው በተለመደው ጠባያቸው (የነ ወ/ሮ እጅጋየሁን ምክር ተከትለው) ከሄዱ የአቡነ መርቆርዮስ ዓይነት መጨረሻ ይገጥማቸው ይሆናል ተብሎ ተሰግቷል።
ከእንደራሴው ሹመት በተጨማሪ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ሹም ሽር የሚደረግ ሲሆን በተዋረድም በቅዱስነታቸው ቤተ ሰቦች ተይዘው የነበሩ ታላላቅ የአገልግሎት መምሪያዎች ሃላፊነቶች በሙሉ ለቦታው በሚመጥኑ ሊቃውንት ይሰጣሉ ተብሏል። ይህንኑ አጠቃላይ ሒደት የተመለከቱ አንድ አባት “እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሥራውን እየሠራ ነው” ብለዋል።
እንደራሴነት ምን ማለት ነው የሚለው ጉዳይ ከሕገ ቤተ ክርስቲያን ጋር ተመሳክሮ ማብራሪያ መሰጠት እንዳለበት እያመንን ለጊዜው ግን ከዚህ ቀደም የነበረ አንድ ታሪክ ለማስታወስ እንወዳለን። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ (የመጀመሪያው ፓትርያርክ) በዕድሜና ጤና ምክንያት ሥራቸውን መሥራት ባልቻሉባቸው የመጨረሻ ዓመታት ሁዋላ 2ኛ ፓትርያርክ የሆኑት ሰማዕቱ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ “እንደራሴ” ሆነው ቤተ ክርስቲያንን ሲመሩ ቆይተዋል። መንበሩ ግን የፓትርያርኩ እንደሆነ ዘልቋል። በቅዳሴ ወቅት የሚነሣውም የእንደራሴው ስም ሳይሆን የፓትርያርኩ ስም ነበር።


July 9th, 2009 at 8:35 am
Corrupted so called spritual leaders. Haha. Maferiawoch
July 9th, 2009 at 8:40 am
Dont try to make a big buzz out of it. still the church remain to be held hostage by the tigray mafias! hagos meta kiros yaw nachew!
July 9th, 2009 at 8:41 am
አልሸሹም ዞር አለ ነው ነገሩ በየገድማቱ በየቤተክርስትያኑ የጳጳሱ አቡነ ጳውሎስ ስም የሚቀደስበት ከሆነ ምንም ሳይሰሩ ፓትራክይነታቸው እብዳለ ከሆነ ሳይሰሩ ቁጭ ብለው መክበር ከሳቸው መንግስተ ሰማይ ነው መታደል ይሉችሁአል ይህ ነው
እንደራሴው በ ውጭ ያሉትን ፓትራያክ መንበራቸውን እስካልመለሰ ደረስ አልሸሹም ዞር አሉ ነው ነገሩ
አይይይይይይይይይ ………… አለመታደል
July 9th, 2009 at 9:27 am
እግዚአብሔር ይመስገን::
ቅዱስ ሲኖዶሱን ያነሳሳ እግዚአብሔር ነው:: እስከመጨረሻው ያበርታቸው::
የሚቀጥለው ሥራቸው ደግሞ በው ጭ አገር ለሚገኙት ስደተኛ ጳጳሳት ይቅርታ አድርገው የቀድሞውን ፓትርያርክ አንድ ገዳም ሰጥቶ እሳቸውም በጸሎት እንዲኖሩ … ሌሎቹን ደግሞ እንደ እውቀታቸው ሃገረ ስብከት ሰጥቶ ቤተክርስቲያናቸውን እንዲያገለግሉ ማድረግ ነው:: ይህ ታዲያ በቅርብ ጊዜ “ተሾሙ” የተባሉትን አይደለም:: እነሱማ ያለ ዕውቀት - እንዲሁ በፉክክር የተሰጣቸው ማ ዕረግ በመሆኑ .. እነሱም ቆቡ እንደከበዳቸው ያስታወቃል:: ስለዚህ ወደ ቀድሞው የአጥቢያ አስተዳዳሪነት ተመልሰው እንደገና ለሹመቱ እንዲበቁ ጊዜ መስጠት ነው::
ለሁሉም ግን እንጸልይ
July 9th, 2009 at 9:31 am
The Church needs more than this. It has to transform itself - it needs reformation - it has to get ready to cope up with the 21st century. One area of reformation is the church has to come completely OUT of politics. Church leaders and priests have to preach the truth and stand for justice. We need to see church leaders to speak against dictatorship, tyranny, injustice and racial discrimination. We need more Abune Petros - the great spiritual leader who stood against injustice and tyranny even at the expense of his life.
July 9th, 2009 at 9:34 am
Selam Selam
By the way, one of the bishops in the America “fake” synod, abune Zena markos, was ENDERASE , after patriarch Merkorios was ousted in his own will.
It is surprising that Abune zena markos, after he tried to be the next Patriarch, now he acts like the supporter of Abune Merkorios.
ENDERASE, means he acts as a patriarch, but doesn’t be called patriarch. So this is a victory from GOD.
We , all in the diaspora has no reason now, not to support our synod in Ethiopia.
With prayer and love
Meron
July 9th, 2009 at 9:39 am
ere pls be pdfffffff aderegut manbeb alechalnem thahnk you
July 9th, 2009 at 9:41 am
it sounds good
July 9th, 2009 at 10:06 am
We said it before and we are saying it now too. This Mahibere Kidusan, (which created by foreign, supported by republican fake Christian) never stops until destroy the old Ethiopian Orthodox. እነዚህ የማህበረ ቅዱሳን መሪዎችም ሆነ ሰልጣኞች የውጪ የትምህርት እድል ተሰጥዋቸው ይህንን ጉዳይ ሊፈጽሙ የታዘዙ ናቸው(ለጥቅም የተገዙ ማለት ነው);; አሁንም ቢሆን በየሃገሩ ተበትነው የነበሩ በተክርስቲያንን አምሰው በትንሹም የተሳካላቸው ስለመሰላቸው አሁን ደግሞ የአገርቤቱን ልክ አገቡት:: ድሮም ፓትሪያክ ጳውሎስ ማህበረ ቅዱሳን የዲያስፖራ አጌንስት ናቸው እና ወዳጅ ላርጋቸው ብሎ እነሱንም ሰሩላቸው:: አይ አድዋ ሃማሴን አገሩንም ሃይማኖቱንም አምሱት! ለሃይማኖታችን ከአዜብ አመራር ጋር ወደፊት ነው! ተምች!
ማጠቃለያ ለህዝባችንም ሆነ ለኦርቶዶክስ ሃይማኖት በጭራሽ ይሄ ማህበረ ቅዱሳን የሚባለው ግብስብስ አደገኛ ነው ወደ ጥሩም አይወስደን ልክ እንደነ 700 ወይም ቤኒ የሚባለው እና ሌሎች ፌክ ሃይማኖት ነው:: እንዲየውም ሁለቱም ለኢትዮጲያ የማይበጁ ቢሆንም እንደሚመስለኝ በፓትሪያኩ ያለው ግሩፕ ሳይሻል አይቀርም:: የእነዚህ ግን እስከትውልድ ድረስ የሚሄድ ነው:: አፍሪካን በሃይማኖት ድሮ እንዳታለሉት አሁን ይሄው በነዚህ ጉግማንጉጎች ተከልለው መጡ:: አዬ
July 9th, 2009 at 10:23 am
Is the new person a tigrian?
July 9th, 2009 at 10:32 am
Thank you Emf le fetan melashachehu be pdf madregachehu manbeb chelenal egziabher ewnetega meri yesetat le zehech bete kerseteyan tiruna melkam zena new beretu
July 9th, 2009 at 10:42 am
It is a good initiative and we should appreciate the motive.Now the church has begun waking up and the people will follow soon.Do not criminalize the bishops fighting in Addis.They are better than those staying in Washington.During the ceremony of anointment,the bishops promised to sacrifice themselves.But they turned down and left the country.The people suffered,killed and thrown to jail.No bishops stood behind them.These bishops are responsible for the lost sheep.We should start appreciating and recognizing the people who stand to the truth.We salute the Synodos!!!!
July 9th, 2009 at 11:04 am
Is this another example of Mengistu H/Mariam famous proverb:
“Thieves fight when they share the proceeds of their crime’?
‘Adeneneh k’ematu’! Hallelujah!
July 9th, 2009 at 11:14 am
Dear Admin
My track record with you is replete with furnishing EMF netters with nothing but the truth especially so with news from EOTC.
I am now able to confirm to you that the attempted coup d’etat has been foiled by the makings of the dissidents themselves as one Archbishop after another Archbishop started dessering the coup leader Aba Samuel. All is quite at the Patriachate and the Patriarch has brushed the “News” as nothing more than children’s bed time story.
In the unlikely event that I am proven wrong, I pledge to post a public apology with my picture on all Ethiopian websites. Thanks
July 9th, 2009 at 11:16 am
Kassay Says:
July 9th, 2009 at 10:42 am
It is a good initiative and we should appreciate the motive.Now the church has begun waking up……”!!!
July 9th, 2009 at 12:09 pm
Atleast a news better than nothing. But still these corrupt church leaders and corrupt government officials should be exposed to the public and punished.
God will show his power and mercy to Ethiopia and its people. Do you think God forgets Ethiopia? I am telling you he doesn’t and he won’t. You will see more miracles soon…the whole country is shaking and the End will come to the cry of the people …the time is coming ….look where to hide..but no one will escape.
Ethiopia shall stretches her hands out unto God
July 9th, 2009 at 12:44 pm
ትልቅ ለውጥ ነው:: ለቤተ-ክርስቲያኒቱ አንድ እድምጃ ወደፊት :የሚያስኬድ ነው::ሠውዬው ስልጣን ከተገፈፉ ስማቸው ተጠራ አልተጠራ የሚያመጣው ለውጥ የለም:: ዋናው ትልቁ ጉዳይ ግን ነፈሰ በላው ወያኔ እጅህን ከቤተክርስቲያናችን ላይ ያንሳ::በፊትም ችግር ሆኖ ያለው ወያኔ በጉልበት የ አምላክ ሳይሆን ቅድሚያ የ ስር-አቱ አገልጋዮች እንዲሆኑ ስለሚያደርግ ነው:: የወያኔ ጉልበተኝነት በቤተ-ክርስቲያኒቱ ላይ ካላቆመ ግን መጪዎቹም እንደበፊተኞቹ እንዳይሆኑ ያስፈራል::ግራ የገባው ወያኔና ቤተሰቡ መውደቂያህ እስኪደርስ ድረስ እዚያው ራስህን ቻል::
July 9th, 2009 at 1:06 pm
ስማ ጃ ነኝ ብልህ የጻፍከዉ … ዲያብሎስ ወይም ጴንጤ መሆን አለብህ.
July 9th, 2009 at 1:17 pm
ሰላም ለሁላችሁ
እባካችሁ ይህን ጥያቄ መልሱልኝ
የማህበረ ቅዱሳን ጥፋት ብዙ ጊዜ ሲነገር እሰማለሁ ግን ምን እንደሆነ በዝርዝር አላውቀውም: እስኪ እገሌ እገሌን ይደግፋል ወይም እገሌ የእገሌ ቡድን ነው የሚለውን ሳይሆን በቀኖና ላይ ያለውን ጥፋይ አስረዱኝ:
ሁላችንም እንደምናውቀው ቀኖና (Dogma) የማይቀየር፣ የማይለወጥ የእምነት መሰረት ነው: ስርአት፣ (የአምልኮ ዘዴ ለማለት ፈልጌ ነው) እንደ ጊዜው ሁኔታና አመቺነት የሚቀየር ነው: ደግሞ እምነት አይደለም: ለእግዚአብሄር ክብር መግለጫ ሽብሸባ፣ ቅዳሴ፣ ውዳሴ ሰለሆነ:
ከዚህ በመነሳት ማህበረ ቅዱሳንና በሌላው መሃከል ያለውን ይጸብ መነሻና የዶክትሪን ልዩነት ብታስረዱኝ በጣም አመሰግናለሁ
July 9th, 2009 at 1:37 pm
አነተ Ja ብለህ ስምህን የለጠፍከው አዛውንት .. መጀመሪያ ስለ ክርስትና ወይም ደግሞ ስለ ቤተ-ክርስቲያን ከመናገር :በፊት ቅድሚያ ውስጡን እና ህጉን ማወቅ አልያም ትንሽ እንክዋ ደጅዋ ላይ መድረስ መቻል ያስፈልጋል::በህይወትህ ስንት ግዜ ቤተክርስቲያን ሄደህ ታውቃለህ?አለበለዚያ እዚህ ላይ በዘልማድ የፖለቲካ ድህረ ገጽ ወይም መጽሄትና ጋዜጣ እያያችሁ ወይንም ደግሞ የሌላ እምነት እየተከተላችሁ ቤተክርስቲያንን ለማጥቃት የምትሞክሩና የመሸታ ቤት ወሬ ያለ እውቀት የምትናገሩ ሁሉ ራሳችሁን ባታዋርዱ ጥሩ ነው::አሁን ማህበረ ቅዱሳንና ወያኔ ምን አያያዘው?ስለተላለፈው ውሳኔስ የሰንበት መሃበሩ እንዴት እንዴት ሆኖ ነው ለ ጳጳስ ስልጣን ሰጪ የሚሆነው? የማህበሩ መኖር የሚያንገበግባችሁ እና የ እግር እሳት የሆነባችሁ የግብረ ስዶማዊያን እምነት ተከታዮች :ላያችሁ ወንጌላዊ ውስጣችሁ ደግሞ መናፍቃዊ የሆናችሁ የሃሰታዊው መሲህ መንገድ ጠራጊዎች ጦራችሁን ስትሰብቁ እና መርዛችሁን በየግዜው ስትረጩ ዛሬ አዲሳችሁ ባይሆንም :እኛ ግን ዘወትር ያለውንና የነበረውን እውነት ከመናገር ወደህዋላ አንልም:: እመን የፈለከውን ::ነጮቹ አጎቶችህም በየወቅቱ እምነት ያወጡሉሃል :ይፈለስፉልሃል : እድሜ ለዲሞክራሲ:: እነሱ የሚሰጡህን ብጣሽ ዶላር እየጨበጥክ የሚሉህን እየተቀበልክ እየመጣህ :እነደ ገደል ማሚቱ አስተጋባ በየ ድህረ ገጹና ሻይ መጠጫው :: በየ አዳራሹም በጌታ ስም አላዝን ጩህ ተንፈራገጥ ተንከባለል ::እዚህም እየመጣህ አግዋራ አላዝን :: መርከቢትዋ እንደሆነ ትናወጣለች እንጂ አትሰምጥም :: ባለቤትዋ ማእበሉን ጸጥ ያሰኛል:: ምናልባት ፓስተራዊው ቶሎሳ ትላንት ማታ መንፈሱን ጭኖብህ ይሆናል ትላንት ማታ ምን ይታወቃል:: እንዲያውም እንደ ማሀበረ ቅዱሳን አይነት አንድ ሺ ይፈጠራል ገና::የ አውሮፓውያንም ዶላርም ሆነ ሽቀጥ የማያቆመው: አንተ ብቻ እሱን ጸባይ አሳምረህ ዋጥ:: የቤትህም ጣሪያ በየግዜው እየተከፈተ በአናትህ ሰዶማዊው መንፈሳቸው ይሰርጽልሃል:: አሜን በል:: ይሁንልኝ ይደረግልኝ በል:: ለሁለተኛው ከድህረ ገጽ በፊት መጽሃፉን ግለጠው:: ጀርመን ወይንም አሜሪካ ያተመውን ሳይሆን :የራስህን ::የአገርህን ካደለህ ቆዳ ላይ የተቀረጸውን:: እስከዚያው ግን ልብ ይስጥህ ::
July 9th, 2009 at 1:40 pm
Dear ja,
Why you simply opened your mouth on issue which you don’t know. Please say what you know rather” zim bileh afikin kemitikefit”. I am not mahiber-kidusan, but I know what they ar doing. they are real childrens of the church who gave their life, time and money to God and the oerthodox church.
God Bless our church and bring peace with true leader, not Derg Abune Merkorios or Woyane Abune paulos.
July 9th, 2009 at 1:44 pm
Ewunetu Wushetu, you are back again to try to twist people’s mind. Are you a spokesperson for EOTC or you are feeding us with your usual Woyane propaganda? Who cares whether Aba Diabilos goes or not with his Colt-45 Pistol? And who wants you to tell us, deny or confirm too? Leave this to the media and don’t forget that we all know what is going on in your backyard in Ethiopia let alone this openly spoken thing. We know when you sneak in the dark like a hyenas, drag people from their sleep and take them away to unknown forests and kill them too? Hence just get out of this site because you would make it smell like a rotten fish which is the known smell of Woyanes. Get lost you blood sucker! Go to hell you child killer! We don’t need you anywhere. Bastards and murderers!
July 9th, 2009 at 2:09 pm
Listen people
All this is a game. How in the world good things come in the presence of TPLF? Why are you fulled a million times?
July 9th, 2009 at 2:47 pm
እኔ የምገርመኝ. What do we call this, religion? Spiritual leader? unless the church itself repents and confesses its last sins, still there are so many “gannen” in that church, the devils should be cleaned out of the church, and then only the Spirit of God works. Let us all pray that may the Truth, Love and Justice prevail. God bless ETH.
Hadi,
July 9th, 2009 at 3:01 pm
Dear Admin
I have proved right once again. In the last hour deje selam has issued with yet another story informing us that majority members of the Holy Synod have refused to endorse the proposal of the Abuna Samuel renegade group. Good news for the unity of EOTC.
July 9th, 2009 at 3:48 pm
Ewnetu Says:
July 9th, 2009 at 11:14 am
Dear Admin
My track record with you is replete with furnishing EMF netters with nothing but the truth…
ha, ha,you locust blood sucker that is how you earn your frifari. If the truth was a snake it will bite you.
burn in the hottest crevices of hell with Gebremedhin!!
July 9th, 2009 at 3:57 pm
Ewnetu is quite correct Aba Paulos has won this round. As much as I despise this so called Patriarch, I am happy he survived this ordeal just enough to eradicate the poisonous organization called Mahebere Kidusan which only he can do. The traitors who knowingly helped this man must first face the consequence of their treachery against all Ethiopians by selflessly empowering him for the last 18 years. As for Aba Paulos, there is no doubt that he will vaporize into thin air along with Woyanne tribal gangs, first he just need to undo the damage he unleashed on Ethiopia for his temporary survival .
For all you faithful who adhered to the Canon of our true church, the change you hope to come can only begotten from Christ the Lord and not from men. All those complicit so called archbishops are political appointee of woyanne and Aba Paulos, and their council shall not yield the salivation you seek for your church.
Therefore, regarding your church the Lord has spoken:
11 “O afflicted city, lashed by storms and not comforted,
I will build you with stones of turquoise, [a]
your foundations with sapphires. [b]
12 I will make your battlements of rubies,
your gates of sparkling jewels,
and all your walls of precious stones.
13 All your sons will be taught by the LORD,
and great will be your children’s peace.
14 In righteousness you will be established:
Tyranny will be far from you;
you will have nothing to fear.
Terror will be far removed;
it will not come near you.
15 If anyone does attack you, it will not be my doing;
whoever attacks you will surrender to you.
16 “See, it is I who created the blacksmith
who fans the coals into flame
and forges a weapon fit for its work.
And it is I who have created the destroyer to work havoc;
17 no weapon forged against you will prevail,
and you will refute every tongue that accuses you.
This is the heritage of the servants of the LORD,
and this is their vindication from me,”
declares the LORD.
Isahia 54:11-17
God Save Ethiopia and her Church, Amen.
July 9th, 2009 at 4:11 pm
ለጉዳዩ ቅርበት ካለው ሰው ስለሁኔታው እውቀት ማግኘት አለብን:: የመለስ መንግስት እዚህ ጉዳይ ላይ ገለልተኛ መሆኑ ግራ ገብቶኛል:: ፓውሎስ ለመንግስቱ ካደረገው ታላቅ አስተዋጾ በኋላ የማይመስል ነገር አለ:: ለምን አንዱን ትግሬ ከስልጣን አንስቶ በሌላ መተካት አስፈለገ:: ከጀርባ ያለው ጫወታ ምንድን ነው:: ትንቢቱ ሊፈጸምና ፓውሎስ እራሱን ሊያጠፋ መለስም ወደውጪ ሊወጣ ከሆነ መልካም የምናየው ይሆናል::
July 9th, 2009 at 4:11 pm
Ja,
Forget those weyane and confused ethiopians who dont know the dirty work of Mahbere kidusan..
thanks so much for reavling the truth, you have entirely exposed the basic reality of the Mahebere Kudusan anti Ethiopian orthodox destruction along with their legislative proposal that was written and approved by Tagay Paulos of the weyane appointed person.
What is the difference between Addis legesse, tefera walwa, aba dula, Junedien, Lidetu , Maherbere kidusan members and other weayene servants that carries out weyane’s crime everyday. To me they all are the same that carries out weyane’s daily crime against human beings in Ethiopia. So the Ethiopian people have to fight back all these weyane hodam servants everywhere by any means possible to stop their daily destructive agenda.
Mahbere kidusan is well known in Ethiopia with their name Mahebere Irkusan, since the Ethiopian people have clearly seen their destructive actions in orothodox churches, as side from their destruction duties in side orothodox churches, the so called Mahbere Irkusan have taken the order of Tagay Paulos to stop the public from praying for those hundreds Ethiopians civilians who died aftermath 2005 election that were shot and dead in the street of Addis by the weyane agazi forces. These so called Mahebere Irkusan members have announced in every church to stop praying for those individuals who died with merciless weyane agazi forces. So, the Ethiopian people in Ethiopia exactly know the undercover dirty duties of Maheber Irkusan and have always try to isolate them by any means possible in the society.
The other part of Mahbere Irkusan is appointed to Diaspora with the command in chief of Tagay Paulos all over the world to accomplish their dirty destructive duties inside orothodox churches. They restlessly working to divert the attention of the orothodox followers using many falsified and machine fabricated reasons that are provided by the weyane major cadres in Diaspora. They own so much medias including radio shows, websites, paltalk rooms and so many other means to distribute their destruction agendas.
Actually, the so called Mahberhe Irkusan are very knowing in opening a new churches in the name of orothodox religion in so many cities in Diaspora, particullrly they focus on cities that there is no orothodox church to ultimately accomplish their destructive agenda. Moreover they stricktly target college students that do not have enough awareness about their religion but believers of the orothodox religion. As a result they have been dividing the followers of the orthodox religion in a few places, At the same time they have been exposed by brave Ethiopians who are very concerned about their religion and who are opposing the coming of Tagay Paulos by breaking all the rules and regulations of the Ethiopian orothox. In some places the members of Mahbere Irkusan have been facing angery Ethiopians who are disappointed by the insider agents and elements of Tagay Paulos and dissatisfied by the daily gross human rights disrespect of Weyane.
the weyane mafia groups supported by Aba Gebermedihin( tagay G/medhin). I wish other churches around Washington, dc and other states cleansed them selves from weyane supporter religious people. Especially, the so called weyane new cadre members who are organized them selves with the name MAHEBERE KIDUSAN are playing a magnificent role for weyane in dividing the orthodox followers through out the world. Since they are financially supported by weyane government they have all things including medias that are surrounded by radio show and website in order to preach the orthodox followers to accept the Patriarch Abune paulos and to silent the public from asking and discussing the major Ethiopian people proplems such as famine, lack of democracy, increase of inflation which comes from bad governance and bad policy of weyane that is organized by highly corrupted officials and members of weyane. In stead they consistently preach the people all the resolution can only comes from God, while God gives us the resolution on our hands to fight weyane and bring all justice and democracy for our people, so that our people can gradually illuminate our complex problems with the help of god.
Lets all be aware of the bad role of Mabere Irkusan and lets all aware those ethiopians around our area about the dirty duties of Mabere Irkusan who are working for the weyane criminal party. lets at least say enough is enough…
Lets not wait some resoultion would come from the sky and lets step up to contribute our part. Lets all stop the dirty duties of mahberhe kidusan everywhere by any means possible.
Together we win!!!
God Bless Ethiopia!!!
July 9th, 2009 at 4:12 pm
ትግረን ትግረ ቢበላው ጥሩ ነገር ነው እኮ! ለእኛስ አልዋጥ ብለውናል:: አዞን አዞ እንደሚበላ: ትግረን ትግረ ቢበላው አገራችን ስላም ታገኛለች:: የኢትዮጵያ አምላክ የሚባለው ያለ ምክንያት እንዳይመስላችሁ!!
July 9th, 2009 at 4:41 pm
በ”አቡነ” ጳውሎስ ዘመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ምእመናን አጥታለች:: በስንት እንባ እና በስንት መስዋእትነት እዚህ ደረጃ ላይ የደረሰቸው ቤ/ክርስቲን እንደዚህ ስትጠፋ ያሳዝናል::
ስለምን እያወራ ነው ብሎ ለሚጠይቅ ሰው ይህን መረጃ ላቅርብ:-
በ1994- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተከታዮች የአገሪቱ 50.2% ነበሩ
በ2007- የህዝብ ቆጠራ ይህ ቁጥር ወደ 43% ዝቅ ብሎ እናየዋለን::
የ7%, ወይም የ5.6 ሚልዮን ምእመን ቅነሳ ደርሶዋል:: እንደዚህ ያለ የቤ/ክርስቲያን ጥፋት ካለ”ግራኝ አህመድ ወረራ” ታይቶ አይታወቅም:: ለዚህም አላፊነቱን መውሰድ ያለበቻው, ያለችሎታቸው, በወያኔ የተሾሙት አባ ጳውሎስ ናቸው:: ይህ ሃቅ ነው::
July 9th, 2009 at 4:55 pm
Meron, tell that tert tert to your weyane buddies. ETOC is controlled by weyane. Aba samuel or aba paulos aka aba dablilos are one and the same. Both are working for weyane. So Ethiopians do not see any difference between the two.
July 9th, 2009 at 4:58 pm
“ማህበረ ቅዱሳን” ጸረ ወንጌል ጸረ ኢየሱስ ናቸው, ህይወት የሌለው ወግ እና ተረት ብቻ ይሰብካሉ:: ኦርቶዶክስነት በነጠላ, መዝሙር በከበሮ… ብቻ (ከዛ ውጭ እ/ር አይቀበለወም ይላሉ), ብሉይ ኪዳን ቆመው አዲስ ኪዳንን ክደዋል (ሴቶች በወር አበባ ወቅት እንደ ኦሪቱ ረክሰዋል, ሰው በምግብ ይረክሳል ይላሉ), በገድላት እና በታምራት ያሉት ተራ ተረቶች እንደ እ/ር ቃል ይቀበላሉ:: ኢየሱስ ማለት በመርኅ ደረጃ ችግር እንደሌለበት ያውጃሉ በተግባር ግን የሉበትም አይሰብኩትም:: ለምሳሌ የኢየሱስ ክርስቶስ ሊቀ ካህናትነቱ እንዴት ነው ብለህ ጠይቃቸው, አይቀበሉትም:: በአጠቃላይ ዘጽአት ላይ ቆመው ገላትያን አይሰብኩም, ዘሌዋውያን ቆመው ዕብራውያንን አይሰብኩም::
July 9th, 2009 at 5:10 pm
Addis Neger reporter Abraham Begizew was today gang-beaten by Aba Paulos’ men. He was beaten by hooligans who claimed that they were the patriarch’s supporters. Abraham went to the EOC’s main office today to attend a press conference which was called by the synod. But the press conference was cancelled. He was beaten while he was heading to the newspaper’s office at Hayahulet after he learnt the cancellation of the conference. Since last year, Abraham has consistently reported the power squabbles and abuses of power within the Ethiopian Orthodox Church.
July 9th, 2009 at 5:18 pm
አባ ሳሙኤልም ሆኑ አባ ጳውሎስ አንድ ናቸው::
July 9th, 2009 at 6:28 pm
Religion is no morethan an institution…what always matters is your pure conscience….am not an atheist as it would rather seem, but am just a realist who believe on the vision of radica inclusiveness. Therefore, forget about all universal religious based institutions and follow your instinct!!
July 9th, 2009 at 7:16 pm
I say to all of you, there will be a serious solution for the problem that winds right in this movement. God is near to Ethiopia. But for those of you who are talking an irrelevant issue about Mehaber Kidusan , Addis kidan Bluye Kidan , please please come to your minds . It is completily different from the current issue under discussion. You have to find a better place to insult others or/and go to your church to Preach . Specially ” WELETE MARIAM” you dont even know the meaning of it. But you call it Welete mariam.
Please call your self shamful Ethiopian . Clear your mind not to insult others. Respect others.
WHEN YOU SAY SOMETHING FOR SUCH KIND OF ISSUE DONT BE PART OF THE PROBLEM BE PART OF THE SOLUTION.
God ke kifu neger yitebikish
July 9th, 2009 at 7:21 pm
Ewunetu Wushetu, wants us to give him a Nobel Prize for telling us utter lies and the life and death of his Aba Paulos known as Aba Diablos by 80 million Ethiopians. Who cares for Saitan Paulos or Diablos Ewunetu Wushetu? Go to hell with your Aba Diablos who was a womanizer in LA for many years. He is a Paedophile who raped many young girls and used married women for sex. He conned the church as well and then declared that he is a luck prist to have a Tigrian government. In fact, he wanted Qidase to be in Tigrigna but could not succeed hence begun destroying the Orthodox churches not only in Ethiopia but also around the world. But Ye-Ethiopia Amlak Alfeqedeletm, Ayifeqdletmim. Now, Ersberasachew Endibalu Eyaderegachew New. Soon TPLF would fight each other as well.
July 9th, 2009 at 8:51 pm
Instead of dealing with narrow minded and biased and do not seek the truth individuals, MK and the rest of Tewahedo people has to focus on how to reach out and help those fellow Christians across the country’s border, in village and remote areas, in monasteries and traditional schools (ye abinet timirt betoch). We have to focus on improving the church administration while maintain the doctrine and canon.
Let those opponents do the trash things (finger pointing, blaming, ….), which is the easiest work in the world. Those are who have NEVER asked themselves for a minute ‘what have I personally contributed to the church and country’. Just talk talk talk and never gets changed even while residing in a developed country.
Please, check out the following message that I have read from other site.
Any one of you, who are against Mahibere Kidusan, do you know this: Assume if there was no MK, almost our Church would have been completely taken by Menafikan. I could be an example, if there was no MK, just now I had been menafik (as when when I was in University).
Do you know how many monasteries are assisted, how many books are published, how many Ye Abinet Timihirt Betoch are redeemed from closing, how many people come to pay Asirat Bekurat, how many educated people who used to be distant from church are now embraced by our Holly Church, how many Guba’et are operating through out the country, how many educated young are fighting for the church, how many educated young are becoming priests and deacons, how many from ‘forgotten’ in remote areas are getting the words of God, how many kids from non-believers are becoming deacons, how many Ethiopians oversees are getting the words of the Holly Bible. These are some of the accounts done by MK. God bless MK and its effort. Please come to your sense and think once what they have been doing, and weigh your contribution to the Church, too. Have you done something like MK that makes difference to the Church rather than throwing words of hatred with out any roots of truth?
The people who hate MK must be the following: Menafikan, who are losers but had been trying their best to dismantle the Church; Enemies of the Church; Hidden burglars who are looting the treasures of the Church for their personal use or hired by third parties.
But MK: go and work, walk the walk, stride out the stride and we are with you forever! Gobs bless Ethiopia and its Children! But we should know this - the blessing would only comes through our Holly Church. There is no way for blessing other than our Holly Church.
ጣት ከመቀሰራችን በፊት በግሌ ለሀገሬና ለቤተ ክርስቲያን ምን አስተዋጥሆ አደረኩ???????????????? ብለን አራስችን አንጠይቅ::
በጎ ሂልና ይኑረን:: ቸር ሰንብቱ::
July 9th, 2009 at 8:54 pm
Instead of dealing with narrow minded and biased and dኦ-not-seek-the-truth individuals, MK and the rest of Tewahedo people has to focus on how to reach out and help those fellow Christians across the country’s border, in village and remote areas, in monasteries and traditional schools (ye abinet timirt betoch). We have to focus on improving the church administration while maintaining the doctrine and canon.
Let those opponents do the trash things (finger pointing, blaming, ….), which is the easiest work in the world. Those are who have NEVER asked themselves for a minute ‘what have I personally contributed to the church and country’. Just talk talk talk and never gets changed even while residing in a developed country.
Please, check out the following message that I have read from other site.
Any one of you, who are against Mahibere Kidusan, do you know this: Assume if there was no MK, almost our Church would have been completely taken by Menafikan. I could be an example, if there was no MK, just now I had been menafik (as when when I was in University).
Do you know how many monasteries are assisted, how many books are published, how many Ye Abinet Timihirt Betoch are redeemed from closing, how many people come to pay Asirat Bekurat, how many educated people who used to be distant from church are now embraced by our Holly Church, how many Guba’et are operating through out the country, how many educated young are fighting for the church, how many educated young are becoming priests and deacons, how many from ‘forgotten’ in remote areas are getting the words of God, how many kids from non-believers are becoming deacons, how many Ethiopians oversees are getting the words of the Holly Bible. These are some of the accounts done by MK. God bless MK and its effort. Please come to your sense and think once what they have been doing, and weigh your contribution to the Church, too. Have you done something like MK that makes difference to the Church rather than throwing words of hatred with out any roots of truth?
The people who hate MK must be the following: Menafikan, who are losers but had been trying their best to dismantle the Church; Enemies of the Church; Hidden burglars who are looting the treasures of the Church for their personal use or hired by third parties.
But MK: go and work, walk the walk, stride out the stride and we are with you forever! Gobs bless Ethiopia and its Children! But we should know this - the blessing would only comes through our Holly Church. There is no way for blessing other than our Holly Church.
ጣት ከመቀሰራችን በፊት በግሌ ለሀገሬና ለቤተ ክርስቲያን ምን አስተዋጥሆ አደረኩ???????????????? ብለን አራስችን አንጠይቅ::
በጎ ሂልና ይኑረን:: ቸር ሰንብቱ::
July 9th, 2009 at 9:25 pm
ወለተ ምርያም አምላክ ይባርክሽ ስለ ማህበረ ቅዱሳን ጥሩ ግንዛቤ አለሽ ማህበረ ቅዱሳን ማለት የኤትዬጵያ ኦርቶዶክስ ተላቶች ናቸው ሳያውቁ ያወቁ የሜመስላቸው አገር አጥፍውች ናችው::የኤትዮጵያ አምላክ ይፋረዳቸው አባቶችን የሜሳደቡ የአዉሬው መንፈስ ያለባችው የዳቤሎስ ልጆች ናቸው
አምላክ ኤትዮጵያን ይባርክ አሜን
ገረምው
July 9th, 2009 at 10:23 pm
NEXT AGMIWE MELIS .GOGOGOGOGO EPPF
July 9th, 2009 at 10:45 pm
አቶ ወለተ ማርያም ስለ ወንገል የተሰበከው ታዲያ የት ነው? ቀበሌ 666 አዳራሽ ወይስ የት? ጀርመን ፈረንሳይ? ስለ ማህበሩ መኖር ግብረ ሰዶማውያን መናፍቅ ዘወትር እንደሚቃጠሉ የታወቀ ነው:: ማህበረ ቅዱሳን ወንጌልን ከ ሃ እስከ ፐ ድረስ የሚተነትኑ አባላት ያሉበት ስብስብ ነው:: ስለ ሌላ ከማውራት እና ከመቃወም በፊት መጀመሪያ ራስን ማወቅ::ማነው እሱ ቅዱስ መጽሃፍን እየቀየረናና እየቀደደ ሰዎች ዘንድ ለክስርክር የሚቀርበው?መርግጠኛ ነኝ ከአንድ ሰዶማዊ መናፍቅ ሚሲዮናዊ ፓስተር ብላ ብላ : አንድ የሰንበት ት/ቤት ተማሪ የተሻለ የቅዱስ መጽሃፍ እውቀት እንዳለው:: ወይም ፓስተር ብሎ ሆዱን አሹሎ መንፈስ አወርዳለሁኝ ከሚለው ሆዳም ሁሉ :: በዚህ ሆዱን ይሞላል ለአንተና ለምስኪኖቹ መንፈስን እንደ ፓስታ ጠቅሎ ያጎርሳል::ሞኝ :: እውነትን ፈልግ::
July 10th, 2009 at 1:52 am
Can we have a Pdf version of the news.
many thanks
July 10th, 2009 at 2:59 am
The power struggle within the establishment of ethnofascism seems to have ended with the victory of the Adwans. The Adwan cadre and Tegaday Gebremedhin enjoys the full backing and support of the ethnofascist Meles Zenawi and is expected to emerge as the winner.
So the weyanne using the name ewnetu has nothing new to tell us. Ofcourse as the member of the club of ethnofascism, ewnetu can
have access to information on the power struggle. The sad thing is that the Ethiopian Orthodox Church is now fully under the control of the ethnofascists and looting the country.
July 10th, 2009 at 4:13 am
እጅጋየሁ ማለት ምን አይነት ሰው ነች? ማንነትዋን የሚገልጽ ድህረ ገጽ ካለ እባካችሁ ጠቁሙን!
July 10th, 2009 at 5:19 am
Tesfaye
Either your education is incomplete or your cognition has gone haywire. One gets the Noble Peace Price for - among other fields - brokering peace, and not for brokering the truth.
July 10th, 2009 at 7:59 am
ያ ይምትባለው ማሂበረ ኪዱሳንን አታዉከም ለማለት ዪከብደናል ከማሂበረኪዱሳን ጋር ግን ኪም አለህ ብል ጊን አልሳሳትም:እግዛሄር አዪንህን ያብያልህ እና እዉነቱን ዪግለትለህ.
July 10th, 2009 at 8:00 am
በተፈጠረው ብጥብጥ ባዝንም ይህን ሁሉ ችግር ያባባሰው በ1984 በመንፈሳዊ ማህበር ሺፋን የተዋቀረው ማህበረ ቅሉሳን የተባለው የፓለቲካ ድርጅት መሆኑን ህዝቡ ባለመገንዘቡ በእጅጉ ተነክቻልለሁ። አሁንም ችግሩ ተባብሶ ሲኖዶሱ ለሁለተችኛ ጊዚ እንዳይክፈልና ጥፈት እንዳይከተል፡ ምንግስትም ሆነ በተክህነት ማህበረ ቅሉሳን የተባለውን ነብሰ በላ ድርጅት በህግ እንዲያግደው በአጽንኦ እናሳስባለን
በትየሰ ቢተ ጸሎት ትሰመይ
July 10th, 2009 at 9:03 am
I am writting this from Kenya. Just I arrived today in Nairobi. You all know we can not open such website and chat like you. But I was so shoked not by the breaking news but the commnets. Most of us write not the truth but our emotions.
Those who wrote negative about Mahiber kidusa, one thry do know it or they deliberetly doing it.
They are either form the Menafikan or woyane.
Woaye has an agenda to disolve Mahiber Kidusa. They are making all the preparation. This could one of the conspirecy. I have friends who are memeber of the EPRDF and they told me the mission they are given by Woyane this year.
1. To follow every MK memebr and make record
2. All new EPRDF memebers form University are told not to go to MK
3. Organize a Drama like they did in Awassa Univeristy and make the bleam to MK
What makes me lough is the commnet saying that MK is geeting money from Woayne.
Please write only the truth. And use such media for the betetr of our country.
July 10th, 2009 at 9:06 am
አቤት ሰው ሲታወር — ፓትርያርኩ ቤ/ክቱን ገደሉዋት ይሉና ቤ/ክቱን “ገደሉ” የሚሏቸውን አባት ቅዱስነትዎ ይላሉ:: ዘረፉ, አስተዳደር በደሉ, ዘረኝነት አለበዎት ወ.ዘ.ተ ይሉና የእርኩሰት ስራ ሰረተዋል ብለው ወዲያው ቅዱስነታቸው - አባታችን ይላሉ:: አይ ማህበረ ቅዱሳን ድራማ ነው ሰውች:: ከጠንቋይ ጋር ችግር የለባቸውም, ከወንጌል ሰባኪያን ጋር ግን ጦርነት - ስማቸው የጠፋ አባቶች እንባ ገና ገና ገና እ/ር ይበቀልላቸዋል::
http://www.thetruthfighter.net/index.html
July 10th, 2009 at 12:18 pm
እንጽልይ
SO FRUSTRATING GOVERNMENT, AND POPE. PRAY FOR THE HOLY FATHER’S SO GOD WILL GIVE THEM THE STRENGTH TO STAND WITH TRUTH.
July 10th, 2009 at 4:23 pm
What makes me so annoyed is the way you are reporting this news. Does it really matter if Aba Paulos is replaced by the so called Aba Samuel? All of ther are the same and they don’t deserve no attention and respect from us. Aba Paulos is not a legitimate patriarch and every one who was appointed by him are not legitimate. We should underscore that and reject them outrightly. They are a bunch of mafias who are fighting for power. Where were Aba Samuel when highly respected learned men like Aleqa Ayalew were dismissed from his position or denied even to have a tomb on his grave by inhuman Aba Paulos? All of them are criminals and traitors. Hope they burn in hell.
July 10th, 2009 at 8:51 pm
በወለተ ማርያም ስም”የገባሀው የትግና ያለህ “ውስጥህ ቂም የተሞላ ነው::ትችትና ውግዘት ራስህን አዋቂ አያስብለውም ::የትም ነበርክ እና የት አሁንስ የት አለህ::መጽሃፍም ቸከቸክ ወረቀት አሁን ግን እንደዚህ የሚያደርግህ እውነት አይደለም ::ጥላቻ ነው::ራስህን ከ ጌታ ጋር ካደረክ ወደ ዝባዝንኬ ስም ማጥፋት ምን አስወሰደህ? ስልጣኔ ?አውቃለሁኝ ባይነት ወይስ ቂም ? ዞሮ ዞሮ አብደሃል::አሁንም መናፍቅ ነህ::ትንሽ የምትጥመው ገንዘባቸው ነካክቶሃል::በህዋላ ደግሞ የሰዶማዊው መንፈሳቸው::እንዲህ ነበርኩ እንዲያ ነበርኩ አይሰራም::አልሰራምም :ዋናው ሆኖ መገኘት ነው::በክርስትናው ህይወት ሰዎች ከተሙለጨለጩ መጥፎ ነው::ለነፍሳቸው ሳይሆን ለስጋቸው ይሆናል::ምናልባት ፈረንጅ አገር ብትቀመጥና ብርጭቆ የማጠብ ስራ ተሰማርተህ ላንተም የሰለጠንክ መስሎህ ይሆናል::ለወገንህ ግን የጠቀምከውና የሰራሀውን እስቲ አንድ ነገር ንገረን::የጻፍከውን መጽሃፍ ምናምን ነገር ለሽንት ቤት ተጠቀምበት::ዞሮ ዞሮ ለጠፊ ገንዘብ ነው::ለሌላ አይደለም::ብጹእ ፓስተር የአለም ሰባኪ የገባሀው የትግና እስቲ አንድ ነገር ስራና አሳየን::ወያነም ሁን ፓስተር የዘመኑ የሰለጠነው እንግሊዘኛ ሰባብሮ የሚናገር :ከፈለክ እንደ ጥላሁን ጉግሳ በዚህ ፓስተር ነኝ እያልክ ሚሊየን ብር አጋብስ :ግን እስቲ የሻይ ቤት ወሬ ትተህ አንድ ነገር አሳየን!!!
July 10th, 2009 at 11:04 pm
ወለተ ማርያም በርች እነዝህ ማህበር ሰይታን እስክተፉ ድረስ መታገል አለብን አምላክ ቤተክርስትያንን ይተብቅ
ገረመው
July 11th, 2009 at 7:06 am
ገረመው ወይም ወለተ ማርያም አንድ አይነት ሰው ቂቂቂቂቅ ለምን ታዲያ ፈረንጅ አገር ሮጠህ ሰሃን አጥበህ ዶላር ፍለጋ ከመምጣት ወንጌልን አልሰበክም:: መጽሃፍ ጽፌያለሁ ምናምን ከምትል አገርህ ግባና ፍልስፍናህን አንግበህ ወንጌልን አስተምር :;ቁጭ ብሎ እንደ ሴትናፍ ማሞጥሞጥ ምን ይሰራል?ወይም የሚሰራን ከመቦጬቅና ከማማት ስራና አሳየን ወሬ::አገሪትዋ እንዳንተ አይነቱ ወሬኛ ነው ያስቸገራት::ዘወትር የ የሰው እየናፈቀ የራሱን የሚጥል::ከንቱ::በአንተ ቤት አሁን መሰልጠንህ ነው::በቃ የነጮችን እምነት ተከተልክ::ቂቂቂቂቂ ወሬ ወሬ ወሬ የ ኢንተርኔት ጀግና ፓስተር ቂቂቂቂ
July 11th, 2009 at 10:35 am
የሚቀጥለው ፓትርያርክ አባይ ፀሐይ ሳይሆኑ አይቀሩም እየተባለ ነው:: አቡነ አባይ የአባ ጳውሎስን ዋና ዋና ተቃዋሚዎች እንዲታገቱ ካደረጉ በኋላ የሲኖዶሱን ስብሰባ መርተዋል:: አቡነ ጳውሎስ የለቦታቸው በፖለቲካ ቦታውን እንዲይዙ ያደረጋቸው መንግሥት በቤተክርስቲያኒቱ ባጋጠማቸው ተቃውሞ በከፍተኛ ቅሌት ከሥልጣናቸው ሊባረሩ አፋፍ ሲደርሱ ነፍስ ሊዘራባቸው እየታገለ ነው:: በዚሕ አስገራሚ ድራማ ቤተክርስቲያኒቱ በታሪኳ አይታው የማታውቀውን ቀጥተኛ የመንግሥት ጣልቃ ገብነትን እያስተናገደች ትገኛለች:: እነ አባ አባይ ፀሐይ ጳጳስ ከሚሆኑ ወደድሮው የምስር ጳጳሳት መመለሱ ይሻላል::
July 11th, 2009 at 4:46 pm
ወለተ ማርያም አግዚአብሂር ያብረታሀ እንዳንተ 50 ስማእታት ቢገኙ ኖሮ ማሀብረ ቅዱሳን አዚሀ ድርጃ ባለደረሱ ነበር
ይህንንም ማስርጃ ተጠቀምበት
www.ethiopianreview.com/2008/mahebere_kidusan_empowerrment_by_synod.pdf
ወስብሃት ለአግዚአብሂር
July 11th, 2009 at 5:00 pm
I recently came across this fasciniating reading posted: Must Read:
1. The current members of this organization may not even be aware of the history of this hideous organization, as they were not even born when the organization was first formed.
It all began as opposition group of the late Abuna Tewoflos as “Atekalye Gubaye” for three primary reasons.
1) Abuna Tewoflos began in earnest the ground work for making the church to be economically self sufficient especially from the grips of dictatorial regimes. This Gubaye opposed this plan from the start and in 1975 they used the Arat Kilo Property as falls evidence to bring a drummed charges of corruption against the patriarch which was used by the Derg for the massacre of the Holy Father. Ironically today almost 40 years later these properties are providing the intended benefit to the church proving the Abuna Tewoflos insightful vision
2) In order to forever curb the influence of menafekan and “Atekalye Gubaye”, the patriarch in acted the formation of “Sebeka Gubaye” allowing every member of the parish to participate in the daily activity of the church till this very day.
3) Unlike today’s state of the church “Teneshewa Mekele”, The Holy father was a staunch Ethiopian who vehemently opposed to ethnic preferences in order to serve the body of Christ which ran to the contrary of “Atekalye Gubaye” main goal.
After its successful role in the assassination of the Holy Father, in 1981 the organization had a nerve to submit application to the Holy Synod to freely organize within the Church without any kind of accountibility. The Late Abuna TekleHaimanot sealed its fate by denying its request and later on its ultimate refugee in Zewaye region where it adopted the current infamous name “Mahebere Kidusan”. This coincided with the invasion of Woyane in 1991 who perfectly knew the history of the organization to successfully used it as a readymade tool to infiltrate the Church for its own agenda. From that time forward “Mahebere Kidusan” was allowed to organize for the first time free from the church’s authority in every parish throughout Ethiopia except Tigray region.
In 2001 the division within Woyane’s rank gave a new golden opportunity to “Mahebere Kidusan” when the surviving woyane entity (Melese’s flank) who moved to seek alliance with other nationalities as its lost a significant Tigray base. In this endeavor Aba Geberemedhene was quickly summoned to give a legal authority to “Mahebere Kidusan” to legalize its activity for the purpose of recruiting Woyane’s support as well as purge anyone who remain against woyane in the church. This 36 pages proclamation which was signed by 15 archbishops of Aba GebreMedhin on Ethiopian Calander Nehase 12/11/1994 (EC August 2002) with Synod doc # 187/275/94 gave “Mahebere Kidusan” unprecedented authority to destroy the Ethiopian Orthodox Church from within.
Since that time (till most recently) a high level delegate led by Daniel Kebret have been given limitless financial and diplomatic latitude with double mission to infiltrate the Diaspora Church’s primarily to reject the legitimate patriarch of Abuna Merkorios. If this initial plan fails, to campaign for the Diaspora church’s in proclaiming neutrality which of course is unheard of in the Orthodox Christian Faith for the last 2000 years. This clever tactic if successful provides the dilemma of an “Orthodox Church without Archbishops” a misnomer as it will create “Wefe Zerash” generation that forever excommunicate itself from its mother church. Anyone who calls for ‘neutrality’ knowingly or otherwise is practicing from the playbook of “Mahebere Kidusan” ultimately Aba Gebgremedhin and Woyanne. One can simply refers the truism of the 700 million strong orthodox family worldwide which phrases, ‘if one cannot recite his/her baptismal and archbishop’s name one cannot call himself/herself an Orthodox Christian”. (But this should be left for a later date for broader discussion.)
Seeing and calling for what it is, there is a contract on Ethiopia and the Orthodox Tewahedo Church as this priceless institution which defines the country we know staggers to behold. As Abuna Gorgorios once defined it, ‘the church that gave Ethiopia its faith, its language with Fidel, its existence with freedom …….is unlike any other in the world’ Therefore, to all of us the church and the country is the two faces of the same coin. For anyone to argue to restrain from exposing the sinister contract to destroy the church (and their by dismembering the nation of Ethiopia) is simply asking all of us to standby within the limit of artificial boundary and surrender everything that define us.
Now the inevitable has come to roost. The dragon net planted to enslave the Ethiopian people is turning its venomous fang against its master. ማቅ (ማሀብረ ቅዱሳን ) the adoring nickname given to MK by the Ethiopian faithful has now suffered a mortal blow when it lost all its material holding to the church and exiled its pseudo patriarch Daniel Kibret who in his recent article compared Jesus Christ with Prophet Mohammed. http://deje-selam.blogspot.com/2009/03/blog-post_28.html. This is the sad end of Mahebere Kidusan, and glory to the divine God of Aba Tekelhaimanot who did it.
My heart goes out to those young members of “Mahebere Kidusan” who unknowingly are complicit with the most evil alien ever to occupy our nation. Christ the Lord has given all of us the passage of repentance to join the everlasting mercy of his kingdom, and we shall pray for that day to come upon them. Today however, I am more concerned with millions of faithful of the church and the people of Ethiopia to make sure the agent of nation-killers are not left without measure.
Long Live Ethiopia and her Church
July 11th, 2009 at 6:49 pm
ወይ ማህበረ ቅዱሳን Guys just look at them how they play flip flap? They were so pro weyane, now they are pretending against them. You see, we can tell how the division b/n Ertro weyane and Tigro weyane. Ertro weyane who is always divisive wants to create fight among united Ethiopians and its religion, Tigro weyane who are fantasized but doesn’t have nothing power or wealth and controlled and used (on the name of tigray ppl) by ertro weyane.
አሁን እስቲ እግዜር ያሳያችው ከመቼው እንደተገለባበጡ? በየአገሩ እየዞራችው የውሸት ሃይማኖት ቅዱስ ነን እያላችው የስንቱ በተክርስቲያን ስትበጠብጡ ከርማችው አሁን ደግሞ ልክ ለተከፈለው ኦርቶዶክስ ተቆርቁዋሪ መስላችው ቁጭ! ትላንት ያላወራችሁትን የመቀሌ የትግራይ የምናምን እያላችው ሌላውን ለመሳብ ልታጭበረብሩ መጣችው:: እረ እናንተ ጉግማንጉግ ተዉ ህዝብን አትረብሹ ለምን እራሳችሁን ችላችው የፈለጋችሁን ሆናችው በሴጣን አታመልኩም? ተመሳስሎ ገብታችው መርዛችሁን አትርጩ!
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ በፓትሪያክ ጳውሎስና በብጹዕ አቡነ ፓትሪያክ መርቆሪዮስ ያለው ልዩነት አንድ ብቻ ነው ያው ፓትሪያክ ሳይሞት ፓትሪያክ አይሾምም በሚለው:: እናንተ ጉግማንጉግ ግን የተከፈተውን ልዩነት አይታችው በመሃል ገብታችው መርዛችሁን ትረጫላችው:: እናንተ ወደ ዲያስፖራ ሳትመጡ በፊት ሁሉም የየራሱን ቤተክርስቲያን ይዞ ወደሚፈልገው ይሄድ ነበር ይሄ ማህበረ ርኩሳናችው መጥቶ ግን ተመሳስሎ ገብቶ አተረማመሰው:: አሁንም ይህቺ ነገር በነአዜብ መስፍን (ኤርትሮ ወያኔ) ግሩፕ አቴንሽንም ድጋፍም ስላላት አንዴ የትግሬ አንዴ የሸዋ አንዴ የጎንደር እረ ስንቱን ያላላችሁት አለ? አሁን ደግሞ ከናንተም ብሶ ግብረሰዶም ማለት ጀመራችው (ሆሞሳዊያን):: አዬ እነ ዶክተር መስፍን የካናዳው እነክብረት የካናዳው እነ ዳዊት አኩዋሃናቸውን እየው:: አንተው እየው ማን ሰዶማዊ እንደሚመስል:: አሁን ደግሞ ጢሞቲዎስ በዚች ስለከሸፈበት ሌላውን አፋግጥኦ ፓትሪያኩን ይቅርታ ብሎ ገባ: ነገ ሌላ ሊዘይድ! ገና ገና ብዙ ትቀባጥራላችው
July 12th, 2009 at 4:06 pm
Yohannes,
From your long post it is obvious that you know nothing about Mahibere kidusan. It is a very long conspiracy theory you put in here. Membere’s of MK and many christians in Ethiopia know the nature of the organization and its achievement. And don’t feel sorry for the young members of MK. They are very capable and intellegent kids who love their church and their country. If you go to Ethiopia and try to associate MK with woyane everybody will lough at you. MK is always with Ethiopian people. MK never kept quite when the gov’t shoot people on the street. Read their magazine and monthly paper. In America and Europe, Ethiopian are opening ‘churchs’ in every corner and pay morgage in millions every year when churchs in the countryside are closing due to lack of finance. It is only MK and few churchs in exaile who are keeping the churchs in countryside open and support our church scholars (ye Abenet memeheran).
I am planning to join this great association, and advice you to study the association before writting such long, biased accusation.
July 12th, 2009 at 7:24 pm
ወንደም ja:- እንዲያዉ ስለቤተክርስቲያን አለማወቅህ ነው እንጂ የቀድሞው ፓትሪያክ ብጹዕ አቡነ መርቆሪዮስም ቢሆኑ ከሳቸው በፊት የነበሩት ፓትሪያክ ብጹዕ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሳይሞቱ ነው የተሾሙት:: ከዚያም በላይ በደርግ ጊዜ የነበሩት የቀድሞው ፓትሪያክ ብጹዕ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሲሞቱ እንካ ፍትሐት አላደረጉላቸውም ነበር:: በፓትሪያክ ጳውሎስ ጊዜ ነው ፍትሐት የተደረገላቸው:: ታዲያ ማንም ቢሆን ንጡህ የለምና አንድ ወደሚያደርገን ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን በንሰሐ ብንመለስ ለራሳችንም ሆነ ለቤተክርስቲያን ይጠቅማል::የቤተክርስቲያን ልጅ ካልሆንክ ደግሞ stay away. It is non of your business.
ስለዚህ ስለቤተክርስቲያን ከማውራትህ በፊት ስለቤተክርስቲያን ስርዓት እና ታርክ ማወቅ አለብህ: አለብን:: በጎ ሂሊና ይኑርህ::
ማህበረ ቅዱሳኖችን በተመለከተ ግን ማንንም ሳይሆን ሀገር ቤት ያሉትን የሰ/ት/ቤት ተማሪዎችንና በገጠርና በገዳማት ያሉትን ካሀናትንና ምህመናንን ጠይቅ:: If you are residing in a developed country, think like a developed people. Otherwise, Ethiopia has plenty of people who are agianst posetive things.
July 13th, 2009 at 5:01 am
ብሉስማ(pilusumma) አንተ የትህትና መንፈስ የጎደልህ በስድብ የተሞላህ ያውሪው መንፈስ ይደረብህ ሰው ነህ ከመሳደብ በስተቀር ቁም ነገር የለህም:: በቅዱሳን ስም አትነግድ:: ቅዱሳን ራሳቸውን ዝቅ ዝቅ ነው የሚያደርጉት እናንተ ቢተክርስትያንን ለማፍረስ ታትቃችሁ የተነሳችሁ የዳቢሎስ ልጆች ናችሁ:: ራሳችሁን እየገደላችሁ አገርንም ለማትፋት ዘመቻ ከከፈታችሁ ቆይታችዋል አምላክ ይፋረዳችሁ
አምላክ ሕዝባችንን ይባርክ
ወስብሃት ለአግዚአብሂር
ገረመው
July 13th, 2009 at 5:47 am
Senai በቁምህ መዋሸትህ ሳያንስህ የአቡነ መርቆርዮስን ማጥፋትህና ድፍረትህ: የሥራህን ይስጥህ ከማለት ውጭ የምለው ነገር የለኝም:: አቡነ መርቆርዮስ በፓትርያርክነት የተሾሙት ከጥቂት ቀናት በኋላ እንጂ አንተ እንደምትለው አይደለም:: በስርአተ ቀብራቸው ላይ መላው የአዲስ አበባ ምዕመናንና ከየክፍለሃገሩ የተሰባሰበው ህዝበ ክርስቲያን ነው የቀበራቸውና ጸሎተ ፍትሃት የተደረገውና በጎ ህሊና እንዳለው ሰው አትመጻደቅ አትዋሽ (በሃሰት አትናገር) ተብሎ ተጽፏልና::
“ስብሃት ለእግዚአብሔር”
July 14th, 2009 at 8:22 pm
Senai እውነት መናገር የክርስትያን ተግባር ነው እባክህ ወንድሚ አምላክን ፍራ ሰውን ማታለል ብትችልም አምላክን ግን አትችልም:: ስለዝህ ያለፈው ያጥፋሃው ዘመን ይብቃህ ቢተክርስትያንን ክማውጋት ታቅብ::
አምላክ ይተብቀን
ገረመው
October 10th, 2009 at 1:02 pm
ንስሃ ግቡ መንግስተስማያት ከርባለች እና!