
- ፓትርያርኩ በቅ/ሲኖዶስ የተሠየመውን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አገዱ (አዲስ ነገር ጋዜጣ)
- የሐገረ ስብከቱ የባንክ ሒሳብ ታግዷል (ሪፖርተር ጋዜጣ)
(አዲስ ነገር ጋዜጣ፤ አብርሃም በጊዜው):- [PDF] ግንቦት 26/2001 ዓ.ም በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ን በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባዔ የተቋቋመውና ሰባት ሊቃ ነጳጳሳት የሚገኙበት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በብፁዕወቅዱስ ቡነ ጳውሎስ በተጻፈ ደብዳቤ ታገደ።
ፓትርያርኩ በፊርማቸው ሐሙስ ዕለት (June 25/2009) ያወጡት የእግድ ደብዳቤ በአድራሻ ለኮሚቴው ሰብሳቢ ለብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የተጻፈ ቢሆንም የኮሚቴው አባላት ለሆኑት ጳጳሳት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፣ ለፌዴራል ጉዳዮች ሚ/ር፣ ለብሔራዊ ደህንነት መረጃ አገልግሎት፣ ለፌዴራል እና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽኖች በግልባጭ እንዲደርሳቸው መደረጉን የአዲስ ነገር ምንኞች አረጋግጠዋል። ፓትርያርኩበዚህ ደብዳቤ “ግንቦት 26 ቀን 2001 ዓ.ም የተሰየመው ኮሚቴ ከዛሬ ሰኔ 18 ቀን 2001 ዓ.ም ጀምሮ ከሥራ አስፈጻሚነቱ ተግባር ታግዷል” ሲሉ አሳውቀዋል።
በደብዳበኔ ቁጥር ል/ጽ/637/2001 የተበተነው የፓትርያርኩ የእግድ ትእዛዝ ውሳኔው የተላለፈው ረቡዕ ዕለት በተካሄደው “የጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ጉባዔ” መሆኑን ይገልጻል። በዚህ ጉባኤ ላይ ውሳኔ የተላለፈባቸው የኮሚቴው አባላትም ሆኑ በርካቶች የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አለመገኘታቸውን በስብሰባ የተሳተፉ ታዛቢዎች ለአዲስ ነገር ገልጸዋል። በጉባኤው የተሳተፉት የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች መሆናቸው ቢታወቅም ትክክለኛ ቁጥራቸውን ለማረጋገጥ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
የቅዱስ ፓትርያርኩ ደብዳቤ ኮሚቴው የተቋቋመው “የቤተ ክርስቲያንን ማዕከላዊ አስተዳደር የማስፈጸም አቅም ለማጎለበት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንዲሠራ” እና እስከ ሐምሌ ወር ውስጠ ደንብ እንዲዘጋጅለት፤ እስከዚያው ግን “በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤና በቋሚ ሲኖዶስ ደንብ እንዲዘጋጅለት፤ እስከዚያው ግን “በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤና በቋሚ ሲኖዶስ ተወስነው የተጓተቱ ጉዳዮችን እየተከታተለ” እንዲያስፈጽም እንደነበር ይገልጻል። ይሁንና ኮሚቴው “ቤተ ክርስቲያኒቱ ከምትደዳርባቸው ከሕገ ቤተ ክርስቲያን፤ ከቃለ ዓዋዲውና ከሠራተኞች አስተዳደር ሕጎች ውጭ የሆነ አሠራር በመፈጸም ያልተጠበቀ ችግር በመፍጠር አላስፈላጊ ጽሑፎችን ያስተላልፋል ብለን አልገመትንም ነበር” ሲል ለእግዱ ምክንያት የሆኑተርን ችግሮች ይዘረዝራል።
ለዚህም በቀዳሚነት የሚነሣው ኮሚቴው ባለፈው ሳምንት የፓትርያርኩን የጣልያን ጉዞ፣ የሠራተኞች ዝውውርና ድልድል እንዲሁም አዲስ ሹመት በተመለከተ ማብራሪያዎች እንዲሰጡትና እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ ያጻፋቸውን ደብዳቤዎች ነው። ይኸው ደብዳቤ የሥራ አስፈጻሚውን ተግባር “የሥልጣን ተዋረዱን ያልጠበቀ” ነው ብሎታል። “የሥራ አስፈጻሚው ተግባር የተጓተቱ ጉዳዮችን እንዲያስፈጽም እንጂ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላኢ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ የተሰጠውን ሐላፊነት ድርሻ በመጋፋት ወይም የበላይነቱን ሥልጣን በመያዝ ቤተ ክህነቱን ተክቶ እንዲሠራ ኤኢደለም” ሲል ከሷል።
በዚህ ተግባሩ “የአስተዳደር ጉባኤው” ስድስት ውሳኔዎችን በማስተላለፍ እንዲፈጸሙ አዟል። በውሳኔው መሠረትም ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የከፈተው ጽሕፈት ቤት በአስቸኳይ እንዲዘጋ፣ ኮሚቴው ያሳተማቸው ክብ ማህተም፣ ቴተርና ሄዲንግ ማዘዣ ወረቀቶች የቤተ ክርስቲያኒቱን ቃለ ዓዋዲ እና ሕገ ቤተ ክርሲያኑን የጣሱ በመሆኑ በሥራ ላይ እንዳይውሉ ይላል።
በተጨማሪም ሥራ አስፈጻሚው “በሚያከናውነው ሕገ ወጥ ተግባር” ከጀርባው “የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕግና ደንብ መዋቅርንም ጭምር ለማፍረስ የተዘጋጀ አካል እንዳለ ስለሚያመለክት አስፈላጊ ክትትል እንዲደረግበት” ይላል። በአራተኛው ውሣኔው ላይ በሥራ አስፈጻሚው የተላለፉት “ሕገ ወጥና ፀረ ሰላም ጽሑፎች” በኢንተርኔት እና በአዲስ ነገር ጋዜጣ በመውጣታቸው የኮሚቴው አባላት እንዲጠየቁ እና የአዲስ ነገር አዘጋጅም በሕግ እንዲጠየው ሲል ጠይቋል።
በማያያዝም ሥራ አስፈጻሚው ባለፈው ሳምንት ማብራሪያ የጠየቀበትና ከሕግ ውጭ ተካሄደ ያለው የፓትርያርኩ የውጭ አገር ጉዞ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ዕውቅና የሚጠቅም በመሆኑ “ቀጣይነት እንዲኖረው የአስተዳደር ጉባኤው አምኖበታል” ሲል የኮሚቴውን ውሳኔ ተቃውሟል። በመጨረሻም የኮሚቴው አባላት ላሳዩት እንቅስቃሴና ለፈጠሩት ውዥንብር “በሕግ ፊት እንዲቀርቡና እንዲጠየቁ” መወሰኑን አስታውቋል። የኮሚቴው አባላት የሆኑ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ይህንኑ በመረዳት በአስቸኳይ በተመደቡበት ሀገረ ስብከት ተገኝተው መደበኛ ሥራቸውን እንዲያከናውኑ ሲል ደብዳቤው ትእዛዝ አስተላልፏል።
እርምጃው በፓትርያርኩ እና በኮሚቴው መካከል ሲብላላ የቆየው ሽኩቻ ከፍተኛ መገለጫ ተደርጎ ተወስዷል። ቀደም ሲል ባቀረብናቸው ተከታታይ ዘገባዎች ቅዱስ ሲኖዶስ ያቋቋመው አዲስ የ ራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ፓትርያርኩን በአስተዳደራዊ ሥራዎች የሚኖራቸውን ሥልጣን ይገድባል የሚል ግምት መኖሩን መግለጻችን ይታወሳል።
የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀጳጳስ አቡነ ሣሙኤል እና አቡነ ጢሞቲዎስ ከኃላፊነታቸው ታገዱየሐገረ ስብከቱ የባንክ ሒሳብ ታግዷልበታምሩ ጽጌ - ሪፖርተር ጋዜጣ –በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀጳጳስ አቡነ ሣሙኤል እና የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ጠባቂ አቡነ ጢሞቲዎስ ከሰኔ 17 ቀን 2001 ዓ.ም. ጀምሮ ከኃላፊነታቸውና ከሥራቸው መታገዳቸውን ምንጮች ለሪፖርተር ጋዜጣ ገለፁ፡፡በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚገኙ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ከቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔና ከሊቃውንት ጉባኤ ዕውቅና ውጭ መንፈሳዊ አገልግሎትን ስለማስተላለፍ የተሰራጨው ትምህርተ ቀኖና፤ ቤተ ክርስቲያንን የሚያፋልስና በቤተ ክርስቲያን ላይ የተሰነዘረ የድፍረት ድርጊት መፈፀማቸውን በመግለፅ፣ ጉባኤው ተጠንቶ በቅዱስ ሲኖዶስ እርማት እስከሚሰጥበት ድረስ ረዳት ሊቀ ጳጳሱ ከኃላፊነታቸውና ከሥራቸው ታግደው እንዲቆዩ በሚል ባስተላለፉት ጥሪ መሠረት መታገዳቸውን ምንጮቹ አረጋግጠዋል፡፡በብፅዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ሰኔ 18 ቀን 2001 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ፀሐፊዎች ለአንድ ቀን ባደረጉት ስብሰባ፣ ለቤተ ክርስቲያኗ ሠራተኞች እየተላለፈ ያለ ህገወጥ ደብዳቤ በመኖሩ ከፍተኛ ችግር እየፈጠረ መሆኑን፣ በሐገረ ስብከቱ በኩል ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ የእምቢተኛነት መንፈስ ከመታየቱም በተጨማሪ፣ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የሚተላለፉ መመሪያዎችም ሆኑ ውሳኔዎች ምላሽ በማይሰጥባቸው ደረጃ ላይ መደረሱን መግለፃቸውን ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡የቅዱስ ሲኖዶሱ ምልአተ ጉባኤና በቋሚ ሲኖዶስ ተወስነው ያልተፈፀሙ ጉዳዮችን እየተከታተለ የሚያስፈፅም አንድ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ቢቋቋምም የሐገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በኮሚቴው ስም ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ፣ ለመምሪያዎች፣ ድርጅቶችና ለሠራተኞች ባስተላለፏቸው ተደጋጋሚ ደብዳቤዎች፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ ቃለ ዓዋዲ ሕገ ቤተ ክርስቲያኑና የመሥሪያ ቤቱ መዋቅር እንዲጣስ መደረጉን በስብሰባው ወቅት ትኩረት የተሰጣቸው ነጥቦች መሆናቸውን ምንጮቹ ገልፀዋል፡፡
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ረዳት ሊቀ ጳጳስ በኩል እየታየ ያለው ችግር በቅርብ የተከሰተ አለመሆኑን የገለፁት የጉባኤው ተሳታፊዎች፣ ድርጊቱ የቆየና የኖረ መሆኑን፣ ከላይ የመጣ መመሪያን ያለመቀበል ብቻ ሳይሆን ከታችም መመሪያን ተቀብሎ ማስተናገድ ባለመቻሉ፤ የአብያተ ክርስቲያናቱ አገልጋዮች ኑሮአቸው የሰቀቀንና “ነገ ምን ይገጥመን ይሆን?” የሚል የሥጋት ኑሮ መሆኑ በምሬት መወሳቱን ምንጮቹ አረጋግጠዋል፡፡
የጉባኤው ተሳታፊዎች ጨምረው እንዳስረዱት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ሀገረ ስብከት መሆኑ በሕግ መደንገጉን አስታውሰው “ፓትርያርኩም ሆኑ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ቢጠሯችሁ፣ መመሪያ ቢሰጣችሁም እንዳትቀበሉ” በማለት ከሐገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ሕገ ወጥ ደብዳቤ ቢተላለፍላቸውም፤ ትዕዛዙን ጥሰው በጉባኤው ላይ ሊገኙ መቻላቸውን መግለፃቸውን ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡
በሀገረ ስብከቱ በየአብያተ ቤተ ክርስቲያናቱ የተመደቡ ሠራተኞች፤ ለመዳቢዎቻቸው ጥቅም አሰባሳቢ ሆነው ካልተገኙ አኗኗራቸው አደጋ ላይ የወደቀ መሆኑን እንደሚገለፅላቸው የተናገሩት የስብሰባው ተሳታዎች፣ በሀገረ ስብከቱ የሕንፃ ግንባታና በሌሎችም ሙስና በተካሄደባቸው ዘርፎች ጥያቄ እንዳላቸው በመግለፅ ቅዱስ ሲኖዶሱ የመጨረሻ ውሳኔ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸውን ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡
የጉባኤው ተሳታፊዎች በሀገረ ስብከቱ እየተከናወነ ያለውንና የእምነቱ ተከታዮች ምዕመናንን ያሳዘነ በርካታ አሳፋሪ ተግባራትና የስነ ምግባር ጉድለት በተለይም የጥንታዊ ቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት በሚቃረን መልኩ ቅዳሴን፣ ፀሎትና ትምህርት በኢንተርኔት መረብ መከታተልና መፈጸም እንደሚቻል ያስተላለፉትን መልዕክት አበክረው እንደሚቃወሙት መግለፃቸውን ምንጮቹ ገልፀዋል፡፡
በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ፣ በብፁዕ አቡነ ይስሐቅ እና ንቡረዕድ አብርሃ የመክፈቻ ንግግር የተጀመረው የአንድ ቀን ውይይት ሰባት ነጥብ ያለው የአቋም መግለጫ በማውጣት መጠናቀቁን ምንጮች ገልፀዋል፡፡
ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ጋር የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ጠባቂ አቡነ ጢሞቲዎስም የታገዱ መሆናቸውን፣ ነገር ግን ሰኔ 19 ቀን 2001 ዓ.ም. ወደ ቅዱስ ፓትርያርኩ በመመለስ ይቅርታ ጠይቀው በመታረቃቸው ምናልባት እግዱ ሊነሳላቸው እንደሚችል ምንጮቹ ግምታቸውን ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሣሙኤልን አግኝተን ለማነጋገር በተደጋጋሚ በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ላይ ብንደውልም ሊያነሱልን ባለመቻላቸው ሳይሳካልን ቀርቷል፡፡


June 30th, 2009 at 2:35 am
አቡነ ጳውሎስ Spokes Person “Parrot Ben” Editor of Ethiopia First (Alamoudi First) website will come up with his photographs and forgid documents to tell us that there is nothing going on in the Ethiopian Orthodox church. (Keep watching the parrot is about to bark) heheeee
People like Ben Keep liying and work for individual.
June 30th, 2009 at 4:45 am
Will it be possible to post pdf version of the document?
June 30th, 2009 at 5:00 am
ሰሞኑንን በውጪ አቡነ ፓውሎስ የሰጡትን መግለጫ ቆይተው ከሰጡት ማስተባበያ ጨምሮ ላነበበ አንድ ነገር መረዳት ይቻላል:: አባታችን የእምነት ሰው አይደሉም:: ቢያምኑም የኦርቶዶክስ አማኝ አይደሉም:: በሳቸው አባባል ቅዱስ እግዚአብሂእር የሚያድርበት ጽላት አክሱም ላይ ንግስቲቷ በሚያሰሩት ሙዚየም ይቀመጥና ጆንና እስቲቭን እየጎበኙት አብረው ፎቶ ይነሳሉ:: እኔ ሙዚዬሙ ስሄድ ጫማ አወልቃለው በር ላይ እሰግዳለው እንዲታየኝ ሆኜ አልጠጋምም:: መቼም አያድርገው እንጂ ካደረጉት እንሱ ስላላከበሩት የኦርቶዶክስ አማኞች ከነጆኒ ጋር ፎቶ አብረው ለመነሳት እንዲሰለፉ አይጠብቁ። ሊዳፈሩትም እምነታቸው አይፈቅድም። የገረመኝ ደግሞ ማስተባበያው ነው:: የሳቸው ሲገርም ምኑ ላይ ነው ሲኖዶሱ እንዲወስን የፈለጉት:: እስከዛሬ የምታመልኩት …..ነው እንደሚሉን ጴምጤዎች ትክክል ነበሩ እንዲሉ ነው።
ይህቺ አገር ምኑን ጉድ ታስተናግድ ህዝቡንና አገሩን እየጠላ የሚመራ፤ የማያምን የእምነት መሪ……./።
አንድ ነገር ግልጽ ብሎ ወቷል። እዚህ ጉዳይ ላይ የተሰጡ እውቀት ያለባቸው ብዙ አስተያየቶችን ሳነብ አቅጣጫ ላማስቀየር ለማድበስበስ በዘመቻ መልክ እየተሰራ እንዳለ ያሳያል። ጠንቀቅ ነው።
June 30th, 2009 at 5:06 am
Will it be possible to post pdf version of the document?
June 30th, 2009 at 5:36 am
በውጭ ሃገር ቲኦሎጂ ተምረን መጣን የሚሉ አብዛኛዎቹ ቀሳውስት በጳጳስነት አይደለም በዲያቆንነት በየቤተክርስቲያናችን ቦታ ካገኙ በውጭ በሚገኙት በባዕድ ሃይማኖት ተጽዕኖ መሳባቸውንና በጥበብ እድገት መታለላቸውና በማናውቀውም ሆነ በምናውቀው መንገድ የኦርቶዶክሳዊት ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንችንን ዶክትሪን ለመለወጥ “ቀኖናዊ” ነው በማለት በሊቃዊንቶቻችን የተወገዘውን ጽሁፍ አባ ጳውሎስ ምን ያህል ፈተና ውስጥ እንደከተቱን የቅርብ ጊዜ ትዝታና አሁንም የሚያምሱበትን ዐእምሮዋቸውን እግዚአብሔር ያግድልን:: ነፍሳቸውን ይማርልን!!! አለቃ አያሌው አባ ጳውሎስን የተከተለ ውጉዝ ብለዋል: ምክንያቱም “ቀኖና” በሚል ምክንያት ከሃይማኖታችን ጋር የማይሄድ ጽሁፍ በማሰራጨታቸው:: በወያኔ አባልነታቸው የሚያስፈራሩበት አለማዊ ሃይል በእግዚአብሔር ሃይል ይገረሰሳል: “ሃይል የእግዚአብሔር ነውና”
June 30th, 2009 at 5:53 am
ሲኖዶስ በምላተ ጉባኤየወሰነውን በአንድ ሁገረ ስብከት የአስተዳደር ጉባኤ መሻር ስራተ አልባነት ነው. የቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይ ባለስልጣን ሲኖዶሱ ነው. ፓትርያርኩ የሲኖዶሱ ውሳኔ ካልተስምማማቸው ,ሲኖዶሱን በምላት ሰብስበው አለኝ በሚሉት የግድፈት ማስረጃ ውሳኔውን ማስቀየር ይችላሉ. ከዚህ ውጭ በማን አለብኝነት በየደብሩ የሰገስጉዋቸውን የአራዳ ሆዳሞች ሰብስበው በአንባገነንነት የሚበትኑት ደብዳቤ ችግሩን በምላት ፓትርያርኩን ማንሳት ይችላሉ.
የዚህ ሁሉ ችግር ምንጩ,
1. የሲኖዶሱ አባላት አባ ጳውሎስን ከህግ ውጭ በፕትርያርክ መርቆርዮስ ላይ የመንግስት መሳሪያ ሁነው መሾማቸው.
2 ከትሾሙ በሁዋላ ባስተዳደሩ ስራ እየገቡ ፈላጭ ቆራጭ በመሆን ከቅድስናቸው ውጭ በሙስና ሲዘፈቁ ዝም ብለው መቆየታቸው. (በቅዱሳን ፓትርያርኮች አቡነ ባስልዮስ, አቡነ ቴዎፍሎስ, አቡነ ተክለሃይማኖትና አቡነ መርቆርዮስ ጊዜ ፕትርያርክ በአስተዳደር ስራ ትዘፍቆ አያውቅም. ከባዱን የአስተዳደር ስራ የሚጋፈጠው የጠቅላይ ቤት-ክህነት ስራ አስኪይጅ ነበር. ለዝህም ነው እነዚያ ቅዱሳን አባቶች በሙስና ስማቸው ተነስቶ የማያውቀው.)
3. አሁንም እንደሚታየው የጳጳሳቱ መከፋፈል ነው ለቤተ ክርስቲያኒቱ ክብር መደፈር
ጠንቅ ሆኖ የኖረውና የሚኖረው. ከእውነተኛ ምንጭ እንደሚሰማው የአራዳ ቅሬ ሴትዎይዘሮዎች ሳይቀር በቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደር አዛዥና ናዛዥ ሁነዋልይባላል.
ሰውየውም ጤና አጥተዋል. ሮም ሂደው የሚቀብጥሩት የጠነኛሰው አይደለም. የሲኖዶሱ አባላት በምላት የወስኑት ቢዘገይም እንኩዋን ትክክል ነው. አንድነታቸውን ማጽናት አለባቸው. ውሳነያቸው አስተዳደሩን ብቻ ሳይሆን ከገባቸው ሰውየውንም የሚታደግ ነው.
June 30th, 2009 at 9:38 am
WHY DO YOU WRITE THE NAME OF BIN HERE, HE IS JUST A RUBBISH AND HOD AMILAKU. DOES HE REALLY HAVE BRAIN IN THE FIRST PLACE? I DOUBT. HOW ABOUT THAT ABIY TEKLEMARIAM WHO WROTE A DIFFRENT STORY FEW WEEKS AGO. WHAT IS HE GOING TO SAY NOW? GOBEZ, PLEASE READ FROM THIS LINK http://www.worldnetdaily.com/index.php?fa=PAGE.view&pageId=102532. THERE IS A VERY SHOCKING NEWS ABOUT THE ARK OF THE COVENANT. ONE GUY BOLDY ARGUED THAT THE ARK WAS STOLEN BY ISRAEL’S COMMANDOS IN 1991, AND IS KEPT THERE TILL GOD LEADS WHERE THE TEMPLE SHOULD REST. I THINK WOYANE COULD HAVE SOLD IT IN 1991 WHEN IT CONTROLLED ETHIOPIA. PLEASE TELL ME WHAT YOU KNOW, I AM SHOCKED BY THE NEWS.
June 30th, 2009 at 9:40 am
ማህበረ ቅዱሳን ወይም ማህበረ ርኩሳን የሚባለው (ኦርቶ ጴንጤ) ገና ብዙ ያሳየናል:: ትላንት በየውጪ አገር ያሉትን ቤተክርስቲያኖችን ሲያምስ ውሎ አሁን ደግሞ የአገርቤቱን ኩዴታ ለማረግ ሳይሆን አይቀርም:: በዚህ አጋጣሚ በውጪ ስደት ላይ ያለው ሲኖዶስ “ክፉ ነገር አታውሩ ቢናገሩዋችሁም ስራችሁን መስራት እንጂ ክፉ አትመላለሱ” ይሉ ነበር:: ወደፊትም ድሮም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አትጠፋም ብለውምም ነበር:; እውነትም የሚጣላቸው ሲጠፋ እራስ በራሳቸው ይናጩ ጀመር:: ከማህበረ ቅዱሳን(ርኩሳን) ሰውረን!
June 30th, 2009 at 11:14 am
ja
አንተ ጂል መናፍቅ ማህበረ ቅዱሳን ምን ያድርግህ ? ባንተ ቢት ማጃጃልህ ነው . ማህበረ ቅዱሳን እውነትን ይዞ ያለ የታመነ ነው .
June 30th, 2009 at 11:56 am
ወይ አገሬ ምን ሀጥያት ሰራሽ ዳብልዮሱን ያመጣብሽ? ልብ በሉ ወገኖች እኝህ ሰውዬ አቤት ድረሱልኝ የሚሉት ለወያኔ ፌደራል ፖሊስና ደህንነት ነው:: ወያኔ ሀይማኖት የሌለው ከጛጥ የመጣ ቡድን ነው; እስቲ ተመልከቱ የትኛው የወያኔ ባልስልጣን ነው ቤተ ክርስትያን የሚያስቀድስ? ታምራት ላይኔ እንኻን ማሩኝ ሳይል እየሱስን ተቀበልኩ ብሎ ጰንጤ ኮስጣል ሆነ:: ያጠፋው ነፍስ የኦርቶደኩስን ነው; ማሩኝ የሚለው ሌላ ነው::
ይህ ግልጽ ሊያደርግልን የሚገባው የወያኔን ህገራችንንና ህይማኖታችንን ጥላቻና ሊያጠፉ የቆሙ መሆናቸውን ነው::
ወደ ውጭ ሀገር ስንሄድ ደግሞ ህይማኖት የሌላቸው የወያኔ ካድሬዎች ቤተክርስቲያኖቻችንን ሊያጠፉ ስራቸው መፅለይ ሳይሆን ለመከፋፈልና አስተዳደሪዎችን ለማስወገድ የካድሬ መናሄራ ሊያደርጉ ያላመሱትና ያልቆፈሩት ጉድጛድ የለም::
የሸጡት ቅርጻ ቅርጽንም እግዚህብሄር ይወቀው:: የኢኮኖሚው ዘረፋ አልበቃ ብሎ: የህገር መሬት መሸጥም አልፎ; ግድያው እስሩም ዘረኛነቱም ቀርቶ ህይማኖታችንን እንኻን አልተውም ያሉት እነኚህ ጉጠኞች ኢትዮጵያኖች ናቸው ወይስ ወራሪዎች?
ያገር ሰው ሆይ መልካቸው እኛን ይመስላሉ ብለን ተታለልን እንጂ የሙሶሎኒ ልጆች ናቸው; አልያ በህገር;በወገንና በህይማኖት ሲመጡብንና ሲያተራምሱን እንዴት አንድ የአብርሃም ደቦጭ አይነት ጀግና አውራውን ባንዳ በጎራዴ አንገቱን የሚል ከማሃላቸው ጠፋ?
እኔ በቅቶኛል;አገሬ በወራሪ ተይዛለች ፌዙን ትተን ወራሪን ወራሪ እንበልና እንደ አባቶቻችን አገራችንን ነጻ እናውጣ:: ሆዳሞችንም ባንዳ እንበላቸው:: ዘንድሮ ወይ አገራችን ወይ ወያኔ ሆኖአል ምርጫው::
ለወያኔ ለአደሩ ሁሉ ግልጽ ማድረጉ የሁላችንም ሃላፊነት ነው; በበኩሌ ወያኔ ኢትዮጲያዊ ነው የሚል የታመመ አልያም አገር ሊያጠፋ የተነሳ ብቻ ነው::
ወገን አባ መላ;የወያኔ አፈ ቀላጭ ቤን እያወቀ የሚያጠፋ ወያኔ ነው; የሚጸዳም አይደለም አትድክም እንደማንኛውም ባንዳ የሚያስፈልገውን ማድረግ ነው
አገራችንን ክወያኔና ከጎጦቹ እንጠብቅ ብዙ ግዜም የለንም
June 30th, 2009 at 1:57 pm
Aba g/medhin seems to be out of his mind it can be that he has sold the arc i pray for allah that this guy pay the price .we have to have this guy alive and bring him to justice as tegadaly not as priest
June 30th, 2009 at 3:27 pm
MAY GOD BLESS ETHIOPIA if we join Eritreans, Woyannes have no where to hide! We will squeese them from every corner and grab them!
http://www.ethiopianreview.com/content/10213
http://www.eastafro.com/Amharic/
June 30th, 2009 at 9:08 pm
MAY GOD BLESS ETHIOPIA if we join Eritreans, Woyannes have no where to hide! We will squeese them from every corner and grab them!
http://www.eppfonline.org/
June 30th, 2009 at 11:50 pm
My Ethiopian friends,
The arc of covenant is in Ethiopia. First of all, if the Levi tribe or what ever the commando it was the white guy claimes, to have had it, then let them show us. What are they waiting for? Ethiopia would never allow to unveil it, because it is the holiest object in our religion it has been there unveiled for thousands of years, hence no reason to unveil it this time.
July 1st, 2009 at 1:49 am
ጃ ! የማታውቅውን አታውራ ማህበረ ቅዱሳን ከሲኖዶሱ ጋር አይገናኝም :የወጣቶች ማህበር ነው ሌላ አይደለም::እንደኔና እንዳንተ ::ማህበረ ቅዱሳን ባይኖር ኖሮ…..የየትኛው የ እምነት ሰው ነው መንጋውን የሚጠብቀው ?መጀመሪያ እወቅ ከዚያ ነው መጻፍ እንዲሁ ኮምፒውተር አገኘሁ ብለህ እየገባህ አትዘባርቅ :ጠጋ በልና መጀመሪያ አላማቸውን ጠይቅ:አሉባልታ ወሬ ምንም አይጠቅምም
July 1st, 2009 at 9:49 am
አንተ የዋህ ጃ! በማህበረ ቅዱሳን ላይ የጻፍኸው ምን ዓይተህ ነው? መጀመሪያ ዓላማቸውን ተረዳ፣ ጠይቅ፣ መርምር ማህበሩን በከንቱ አትማ ከሲኖዶሱ ጋር ምንም አገናኘው ይልቅስ በአባቶቻችን መካከል የተፈጠረው አለመግባባት እግዚአብሔር በሰላም እንዲፈታው ፀልይ ክርስቲያን ከሆንክ
July 1st, 2009 at 10:15 am
በእምነት እያስመሰላችሁ ቤተክርሰቲያናችንን አትበጥብጣት ይቺ ቅድስት የሆነች ቤተክርስቲያን ብዙ የቅዱሳን አባቶች ደም ፈሶባት ለዚህ የበቃች ነች ስለዚህ እርስ በእርስ ከመተቻቸት ይልቅ በጋራ መስራት ይሻላል ጊዜው የሚወራበት ሳይሆን የመሰራበት ነው አማኙ ልቡን ወደ አምላኩ በመለሰበት ጊዜ ከቤተክርስቲያን አባቶች እንደዚህ አሳፋሪ የሆነ የስላጣን ጥማት ማንሳት የጌታን ትልቅ ሀላፊነት ከተቀበለ አባት የሚጠበቅ አይደለም ስለዚህ ሰለዚች ቅድስት ሀገር እና ሰለቀደሙ አባቶች ታሪክ መለስ ብሎ ማሰብ ተገቢ ነው ይሁንና ሀይል ሁሉ የእግዚአብሄርና ነገር ሁሉ ለበጎ መሆኑን በመገንዘብና የተጠራችሁበትን ዓላማ በማሰብ ሁሉን ነገር በበጎ ጎኑ ብቻ በመየት ለእምነታችን ከራሳችን በላይ ቅድሚያ በመስጠት ገመናችንን በውይይት መፍታት ልማዳችን ቢሆን በአውደምህረት ላይ ከምንናገረው ትንሽ እንካ ብንሰራ መልካም ነው ያለዚያ ግን ጌታ በማቴዎስ 23 የተናገረው ተፈጻሚዎች መሆናችንን መዘንጋት አይኖርብንም በመጨረሻ መመካታችን ሁሉ በእግዚአብሄር ላይ ይሁን
July 1st, 2009 at 11:23 am
ማሀብር ቅዱሳን ከሲኖዶስ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም ለምትሉ ሁሉ ይህንን አንብቡ
www.ethiopianreview.com/2008/mahebere_kidusan_empowerrment_by_synod.pdf
የወያኒ ጥቅም አስተባቂ ሁሉ!
July 1st, 2009 at 3:52 pm
ይህ ሁሉ ትርምስ ዐቡነ ሳሙእልን ለማንገስ ነው ::
ኣትጃጃሉ ::
July 1st, 2009 at 4:57 pm
እንዴት ነው ነገሩ ወጣቱ ማህበር:: እስቲ ተርጉምልኝ ማህበረ ቅዱሳን ማለት ምን ማለት ነው? የቅዱሳኖች ማህበር ማለት አደል እንዴ? ወይስ የድሮ ቅዱሳን አባቶች ማህበር ነው ልትል ይሆን? ቅዱስነታችው ወይም ቅዱስነታቸውን ማን ነገረህ? ጌታ! እባካችው በተለይ በነ ክለብ 700 እና በመሳሰሉት ስኮላር ሽፕ እያገኛችው ድሮ አፍሪካን እንደ ዘረፉት በሃይማኖት ጥቁርን ህዝብ ለማፍዘዝ ለማጭበርበር እና እናንተም ለዚች 70 አመት ለማትሞላ እድሜ አፍሪካንም ሆነ ኢትዮጵያን ለማበላሸት የተፈጠራችው ጉግማንጉግ ናችው:: ከየት የመጣ ነው አዲስ ያልነበረ ማህበር የምትፈጥረው? ደግሞ እናንተን ብሉ ቅዱስ መጀመሪያ አፋችሁ ይጽዳ:: በአንድ ወቅት የኬኒያ መሪ ጆሞ ለ እኛ መጽሃፍ ቅዱስ አሲዘውን ስናጎነብስ ዘረፉን ብሎዋል አሁንም እያየነው ነው ስንቱን አፍሪካ ውስጥ በእንደናንተ አይነት ኤጀንት በውሸት መጤ ሃይማኖት የምታፈዙት::
እስቲ አሰታውስ በሃረርና ስላሞች ያሉበት አካባቢ ታረጉ የነበራችሁትን እናንተ ማህበረ ርኩሳኖች? ጠበል ኤድስን ያድናል የሚያድነውም ወይም የሚሰራው ለዕስላም ብቻ ነው እያላችው ስታጭበረብሩ:: ሰላም የነበረችን የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ዋናዎቹ ለመበተንና (እናንተ ቅዱስ ነን ባዮች ጉግማንጉግ)በምትፈልጉት መንገድ ለመቅረጽ የምትሩዋሩዋጡ:: ሌቦች!
ከ እናንተ አፍ ምን ጥሩ ነገር ይወጣል እከሌ ተሃድሶ ሆነ (እንታደስ ባዮች እናንተ ሃይማኖትን ፍራሽ ይመስል ለማደስ):: ሆድህን (ኪስህን) አሰፋለው ብለህ አዳሜ ያንተንም የአገርህንም እድሜ አታሳጥር:: ሰው ለካ ካለ ነገር ሰውን ጭባ አይልም “ጭባ”
July 1st, 2009 at 5:14 pm
በዚህ አጋጣሚ የረሳሁት:- ከዚህ በፊት አንዱ “ቅዱስ ያሬድ ነኝ” አለ እያላችው ስታሙት ነበር እሱስ አንድ ነው እናንተ ይሄው እራሳችሁን ቅዱስ የቅዱሶች ማህበር እያላችው አይደል እንዴ ወይም ያለፉት አባቶች ቅዱስ ናቸው ለ እነሱ ብለን ነውም ካላችው እናንተ ናችው እንዴ ማን ቅዱስ የሆነናን ያልሆነ የምትመድቡት? እንዴው ለምሆኑ ሰዉ ወይም የኦርቶዶክስ ሃይማኖት እንዲህ ብጥብጥ ያለችው እነዚህ ማህበረ ርኩሳን ከመጡ አይደል እንዴ ርብሽ ብሹዋ የጠፋው ሰዉም ጥሎ የጠፋው:: አሁን አባ ሳሙኤልን ወደራሳችው ከታችው ልክ የተጣሉ አባቶችን ለማስታረቅ አስመስላችው የህዝብን ድጋፍ ለማግኘት እና የምንግስትንም ታካችው ኩዴታ ልታካሂዱ ነበር ተነቃባችው:: እዚህ ላይ ግን አባ ጳውሎስን መደገፌ አይደለም በዚህኛው ሰአት ላይ ግን ከማህበረ ቅዱሳን ዝርጠጣ ወይም ከመጤ ሃይማኖት ሳያድኑዋት የቀሩ አይመስለኝም::
July 1st, 2009 at 7:31 pm
God keep our church from this bad time .I belive that God will give them thier hand in the near future.One thing we have to see that all the pops live like us not like pop who devoted to God.Being a pop, even a monk is a dead person but they are not that is the problem thier in back home.
July 1st, 2009 at 9:47 pm
gulto, Martha, Lettamo, Michael, aklilu, Bube, Haku, rahel you are tigrain under cover. you are here to confuse ethiopian.
we are comming after you soon.
promise
weyane TPLF will be put to death soon for next 200000 years
http://www.eppfonline.org/
http://www.eastafro.com/
http://www.eastafro.com/Amharic/
July 2nd, 2009 at 7:17 am
ማህበረ ቅዱሳንም ሆነ ሌላው ምእመናን ሁሉ ሃገራችንን ከፋሽስት ወያኔ መንጋጋ ነጻ ለማውጣት በማንኛውም የትግል ስልት: ከልብ እንንነሳ::
አንዳንድ ምዕመናን ሲያዘናጉን እንዲህ ይላሉ:- ወያኔ የሚወድቀው በጸሎት ብቻ ነው የሚል መልስ ሲሰጡኝ: በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ያገኘሁት ግን ማለትም ወያኔን ለማንበርከክ: ልበ አምላክ ዳዊት ከልጅነቱ ጀምሮ መጀመሪያ “በወታደርነት” ሲያገለግል ጎልያድን የሚያክል ሰው በአንዲት ድንጋይና ወንጭፍ አሸንፏል:: ብዙ የጦር አውድማዎች ላይም ተሰልፏል እንጂ በጸሎት ብቻ ተቀምጦ አልነበረም ያሸነፈው:: ከዚያም እግዚአብሔር ለመሪነት መረጠው በውጊያም ወቅት በመጀመሪያ “ጸሎት” ከዚያም በጀግንነት እየተዋጋ ነው ድል ያደረገው:: ንጉስ ዳዊት ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርን አምነውና ከውጊያ በፊት ጸልየው ድል ሲያደርጉ የነበሩ ነቢያትና ነገስታት በመጽሃፍ ቅዱስ የተገለጸው ብዙ ናቸውና እንደቀድሞዎቹ ምዕመናን ኢትዮጵያን ለማዳን ከልባችን እንንነሳ::
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
July 2nd, 2009 at 7:17 am
ማህበረ ቅዱሳንም ሆነ ሌላው ምእመናን ሁሉ ሃገራችንን ከፋሽስት ወያኔ መንጋጋ ነጻ ለማውጣት በማንኛውም የትግል ስልት: ከልብ እንንነሳ::
አንዳንድ ምዕመናን ሲያዘናጉን እንዲህ ይላሉ:- ወያኔ የሚወድቀው በጸሎት ብቻ ነው የሚል መልስ ሲሰጡኝ: በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ያገኘሁት ግን ማለትም ወያኔን ለማንበርከክ: ልበ አምላክ ዳዊት ከልጅነቱ ጀምሮ መጀመሪያ “በወታደርነት” ሲያገለግል ጎልያድን የሚያክል ሰው በአንዲት ድንጋይና ወንጭፍ አሸንፏል:: ብዙ የጦር አውድማዎች ላይም ተሰልፏል እንጂ በጸሎት ብቻ ተቀምጦ አልነበረም ያሸነፈው:: ከዚያም እግዚአብሔር ለመሪነት መረጠው በውጊያም ወቅት በመጀመሪያ “ጸሎት” ከዚያም በጀግንነት እየተዋጋ ነው ድል ያደረገው:: ንጉስ ዳዊት ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርን አምነውና ከውጊያ በፊት ጸልየው ድል ሲያደርጉ የነበሩ ነቢያትና ነገስታት በመጽሃፍ ቅዱስ የተገለጸው ብዙ ናቸውና እንደቀድሞዎቹ ምዕመናን ኢትዮጵያን ለማዳን ከልባችን እንንነሳ::
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
July 2nd, 2009 at 1:22 pm
What have we, followers of the Ethiopian Orthodox Tewahido Church, done lately for our church besides name calling and finger pointing. As followers of the church, we should take an active stand and tell the church leaders to shape up. They can’t keep acting like a bunch of children while the church is losing followers and falling apart at the seams.
God save our church
July 3rd, 2009 at 2:30 pm
http://www.eppfonline.org/
Michael, GETACHEW REDA ,Lettamo, rahel,gulto, Martha, Lettamo, Michael, aklilu, Bube, Haku, Agazi , rahel mikeZ you are tigrain under cover. weyane cyber warrior.
you try to divide amhara against oromo acting as one of us.
oromo against amhara.
amhara against oromo
we know who you are.
we ethiopian are not as stupid as you thing you are
you are here to confuse ethiopian.
we are comming after you soon.
promise
weyane TPLF will be put to death soon for next 200000 years
Lets get those thigrain thugs & cadre
July 16th, 2009 at 3:29 pm
እባካቹ እንጸለይ እናልቅስ … እስኪ ጠዋት ጠዋት 12 እግዚዮታ እናድርስ መድሃኔዐለም ቢታርቀን … ያ ስምንተኛው ሺህ አልቀረም ደረሰ … እየጎሸ እምቢ አለኝ እየደፈረሰ