FBI ስለቦስተን ፍንዳታ ተጠርጣሪዎች መግለጫ በሰጠ ማግስት አንደኛው ተጠርጣሪ ተገደለ፤ ወንድሙም እጁን ሰጠ!

(EMF) ክጥቂት ደቂቃዎች በፊት የደረሰው ዘገባ እንደሚያመለከተው ሁለተኛው ተጠርጣሪ ጃሃር፤ ከቦስተን ትንሽ ራቅ ብሎ በሚገኘው ዋተር ታውን ውስጥ ቆይቶ ነበር። ከዚያም ተደብቆበት የነበረውን የቆመ ሞተር ጀልባ ፖሊሶች ሲከቡ ቆይተው በመጨረሻ እጁን መስጠቱ ተዘግቧል።

ዛሬ ጠዋት አቅርበነው የነበረው ዘገባ ከዚህ የሚከተለው ነው።

(EMF) በትላንትናው እለት F.B.I. የሁለቱን ተጠርጣሪዎች ፎቶ ይፋ ካደረገ በኋላ፤ ለሊቱን ሌላ ዜና ተከትሎ መጥቷል። የቦስተኑ ፍንዳታ ተጠርጣሪዎች መሰረታቸው ቺችንያ (ሩሲያዊ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ) የሆኑ ሁለት ወንድማማቾች ናቸው ተብሏል። ምሽቱን ሁለቱ ወንድማማቾች ወደ 7/11 ሰቨን ኢለቨን ገብተው ዘረፋ ካደረጉ በኋላ በሌላ መኪና ለማምለጥ ሙከራ ማድረጋቸውን ፖሊስ ገልጿል። በዚህ መሃል ክትትል ያደረጉባችወ ፖሊሶች ላይ በመተኮስ አንድ ፖሊስ ሲገድሉ፤ ሌላኛው ፖሊስ ከፍተኛ የመቁሰል አደጋ ደርሶበት በህክምና ላይ ነው።

ንጋት ላይ ከፖሊስ ጋር የተደረገው የተኩስ ልውውጥ እንዳበቃ፤ ታላቅ ወንድምየው ታመርላን ዛርናኤቭ ህይወቱ ማለፉ ተገልጿል። በሚዲያ ላይ በተደጋጋሚ እንደተገለጸው ታላቅየው ታመርላንድ የእስልምና አክራሪነት ባህሪ እንደነበረው የሚያውቁትን ሰዎች በመጠየቅ ሲዘግቡ ነበር የቆዩት። በሌላ በኩል ደግሞ የ19 አመት እድሜ ያለው ታናሽ ወንድሙ የዛሬ 5 አመት ወደ አሜሪካ መምጣቱንና ረጋ ያለ፤ እንዲህ ያለ ወንጀል ለመፈጸም ብቃት የሌለው ወጣት ነው፤ ሲሉ በተደጋጋሚ ተደምጧል። እህታቸውም ጭምር ቦስተን ውስጥ በተደረገው ፍንዳታ ማዘኗን እና አንደኛው ወንድሟ በመሞቱ ማዘኗን ለጋዜጠኞች ገልጻለች።

ሜሪላንድ የሚገኘው የተጠርጣሪዎቹ አጎት፤ “አሳፋሪ ጉዳይ ነው። በጣም አፍረናል።” ካለ በኋላ ጉዳዩ ከእስልምና ጋር መያያዝ እንደሌለበት ከገለጸ በኋላ ያልተያዘው ወጣት እጁን ለፖሊስ እንዲሰጥ ተማጽኖታል። በሩስያ የሚገኘው የተጠርጣሪዎቹ አባት በበኩሉ፤ “ለኔ እንደመልአክ የማየው ልጄ ነበር” ብሏል።
ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት የመጨረሻ ሰአት ድረስ ሁለተኛው ተጠርጣሪ አልተያዘም ወይም እጁን አልሰጠም ነበር። በቦስተን ከተማ የሚገኙ ንግድ ቤቶችም ሆኑ መስሪያ ቤቶች ተዘግተዋል። ሰዎች ከቤታቸው እንዳይወጡ ተደርጓል። የቦስተን ፖሊስ ሄሊኮተር በሰማይ እያንዣበበ ነው። የቦንብ አክሻፊዎች በስፍራው ተገኝተዋል። ሁለተኛው ተጠርጣሪ ጃሃር ግን አልተያዘም።

በተያያዘ ዜና የትላንቱ ዘገባ
(EMF) የቦስተን ማራቶን ከተጠናቀቀ ጥቂት ቀናት ተቆጠሩ። በዚህ ውድድር ላይ የኢትዮጵያ እና የኬንያ አትሌቶች በወንድም ሆነ በሴት በማሸነፋቸው የወርቅ፣ የብር እና የነሃስ አሸናፊዎች ሆነዋል። ሆኖም የአሜሪካ ሚዲያዎች ስለነዚህ አሸናፊዎች ሳይሆን በእለቱ ስለፈነዳው ቦንብ መዘገባቸውን ቀጥለዋል። በእርግጥም በቦስተን የደረሰው አደጋ የብዙዎችን ትኩረት የሳበ ሆኖ ነው የሰነበተው።
Wanted
ዛሬ April 18, 2013 ዓ.ም. የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ከባለቤታቸው ጋር በቦስተን ከተማ በተደረገው የመታሰቢያ በዓል ላይ ተገኝተው፤ “ሩጫችን ይቀጥላል!” የሚል ተደጋጋሚ ቃል ያለው ንግግር ካደረጉ ጥቂት ሰዓታት በኋላ፤ FBI የሁለቱን ተጠርጣሪዎችን ፎቶ ይፋ አድርጓል። እነዚህን ተጠርጣሪዎች የሚያውቅ ሰው ጥቆማ እንዲያደርግ ማሳሰቢያ ሰጥቷል። ለበለጠ መረጃ Click here http://www.youtube.com/watch?v=G0wDb4jVwbo&feature=youtu.be !

ይህ ሁሉ ሆኖ ግን የአሜሪካ መንግስት፤ ድርጊቱን “የአሸባሪዎች ተግባር ነው” ብሎ አልኮነነም። ምናልባት እነ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት አለሙን እና ሌሎች ንጹህ ኢትዮጵያዊያንን በማሰር “አሸባሪ” የሚል ስም የሰጣቸው የኢህአዴግ አስተዳደር፤ ሽብር እና አሸባሪነት ትክክለኛ ትርጉማቸውን እንደገና ቢመለከታቸው መልካም ነው በሚል ማሳሰቢያ የዛሬ ዘገባችንን እናበቃለን።

የከዚህ ቀደም ዘገባ

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 18, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.