ወያኔ የትግራይ ህዝብ ተወካይ አይደለም (ባይሳ ዋቅወያ)

ክፍል ሁለት (ካለፈው የቀጠለ)
(ለውይይት መነሻ)

ባይሳ ዋቅ-ወያ right

ባለፈው ጽሁፌ ባጭሩ ለማስቀመጥ የሞከርኩት የወያኔ መንግሥት በታሪካችን ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በወገኖቻችን ላይ እየፈጸመ ያለው ግፍ ከልክ ያለፈና መደረግ ያልነበረበት ወንጀል መሆኑን እያወቅን፣ ደጋግሞ ስለተነገረን፣ ደጋግመን ስላየነውና ስለሰማነው ብቻ፣ መሆን የነበረበት ነው ብለን መቀበላችን የህሊናችንን መደንዘዝ ያመለክታል ብዬ ነበር። በመሆኑም ከዚህ የህሊና መደነዝ ተላቅቀን ባንድነት በመቆም ህገ መንግሥታዊ መብታችንን ለማስከበር ድምጻችንን እናሰማ ብዬ ነበር የደመደምኩት። በጽሁፉ ውስጥ የወያኔ ገራፊዎች አሰቃዮችና ገዳዮች እንዴት ቢሰለጥኑ ነው እንደዚህ በወገኖቻቸው ላይ ሊጨክኑ የቻሉት የሚል ጥያቄ አንስቼ ነበር። መልስ ጠብቄ ሳይሆን የጭካኔው ደረጃና የግፉ ብዛት ቀሪው የኢትዮጵያ  ህዝብ ወያኔን እንደውጭ ወራሪና ርህራሄ ቢስ አካል አድርጎ ከመቁጠር አልፎ፣ ሀ) ጠቅላላውን የትግራይን ህዝብ እንደ ወያኔ ጨካኝና ርህራሄ ቢስ አድርጎ በመቁጠሩና፣ ለ) ወያኔንም የትግራይ ህዝብ ተወካይ አድርጎ በመፈረጁ፣ አዝማሚያው ወዳልተፈለገ የርስ በርስ ግጭት ማምራት ብቻ ሳይሆን ጥላቻን ባንድ ህዝብ ላይ ያነጣጥራል የሚል ሃሳብ ስላሳደረብኝ፣ ይህንን የተሳሳተ ግምት በጊዜው ለማስተካከልና ወያኔም የትግራይን ህዝብ የማይወክልና የትግራይ ሰፊ ህዝብም ከወያኔ አንዳችም ዓይነት ልዩ ጥቅም ያላገኘ፣ ሰብዓዊ መብቱም ከሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች እኩል የተረገጠና እነደ ቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ በግለሰብ ደረጃ ጥሩም መጥፎም ሰዎች ያሉበት ማህበረሰብ  መሆኑን  በተቻለኝ  መጠን  ለማስረዳት  ነው።  መሰረታዊው  እምነቴ፣  በማንኛውም ህብረተሰብ ውስጥ የግለሰብ እንጂ የህዝብ ጥሩ ወይም መጥፎ የለም የሚለው ነው። [ PDF ]

ሙሉውን በ PDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

 

Share Button