በዘመነ ወያኔ የትግሬ የበላይነት የለም! የሚለው ማነው?

በዘመነ ወያኔ “የትግሬ የበላይነት የለም!” የምትሉ ወገኖች በማያወላዳ ሁኔታ መኖሩን የሚያረጋግጡላቹህ “ወያኔ የትግራይን ሕዝብ ፈጠረ ወይስ የትግራይ ሕዝብ ወያኔን?” የሚለውን እና “አዎ! ትግሬ ማለት ወያኔ ነው ወያኔም ማለት ትግሬ ነው!” በሚሉ ርእሶች ከዓመታት በፊት የጻፍኳቸውን የሁለት ጽሑፎችን ይዞች (ሊንኮች) ከታች አያይዠላቹሀለሁ ከፍታቹህ አንብቡና ያለባቹህን የግንዛቤና የመረዳት ክፍተት አሟሉ፡፡ አንድ ነገር ግን አትርሱ “የትግሬ የበላይነት የለም!” ስትሉ እንዲያው በድርቅና ሳይሆን “የለም!” ማለት የምትችሉት “የለም!” ስትሉ አለመኖሩን ለማሳየት ለማረጋገጥ የግድ እነኝህ ሁለት ጽሑፎች የያዟቸውን መሬት ላይ ያሉ ተጨባጭ ሃቆች ማስተባበል ይጠበቅባቹሀል!

ወያኔ የፈጠረውን የትግሬ የበላይነት “የለም!” የሚሉ ሰዎች ወይ ጥያቄው ምን ማለት እንደሆነ ጨርሶ አልገባቸውም ወይ ምን እየተኪያሔደ እንዳለ ምንም የሚያውቁት ነገር የለም ወይ የወያኔ ቅጥረኞች ናቸው ወይ እውነታውን አምኖና ተቀብሎ ሰብአዊና የዜግነት መብታቸውን ለማስከበር እውነታው የግድ የሚጠይቀውን ትግል መታገል የማይፈልጉ ፈሪና የዜግነት ግዴታ የማይሰማቸው ናቸው ወይ ደግሞ የሚፈጸመውን ግፍ እንደ ግፍ የማይቆጥሩ የባሪያ ሥነልቡና ያለባቸው ሰዎች ናቸው፡፡ በመሆኑም ዓይናቸው የሚያየውን ጆሯቸው የሚሰማውን ማመን አይፈልጉም፡፡ ምን ግፍ ምን በደል ቢፈጸምባቸው እንደ ግፍ እንደ በደል የሚቆጥር ልብ፣ ስሜትና ወኔ የላቸውም፡፡ እራሳቸውን እየሸነገሉ የመኖር ልክፍት የተጠናወታቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ከነኝህ ከአምስቱ ምክንያቶች አይወጣም፡፡

እነኝህ ሁለት ጽሑፎች ወያኔ ቅድሚያ ለትግሬ ብቻ እንዲጠበቅ ያደረገው የመንግሥት የሥራ ቦታዎች አልበቃ ብሎት ባለሀብቶችን በወረዳ አመራሮቹ በኩል እየቀረበ “እኛ የምንልክላቹህን ሠራተኛ ነው መቅጠር የምትችሉት!” እያለ ባለሃብቶች ቀጥረው ያሠሯቸው የነበሩ የገዛ ዘመዶቻቸውን ሳይቀር እንዲያባርሩ እየተደረጉ ሳይወዱ በግዳቸው እንቅስቃሴዎቻቸውን የሚከታተሉ የሚቆጣጠሩ የአንድ ለአምስት ጠርናፊ የትግሬ ሰላዮችን ለመቅጠር እንደተገደዱ ያሳያሉ፡፡

በተጨማሪም ይሄ “ብቻየን ልብላ፣ ብቻየን ልበልጽግ ሌላው የራሱ ጉዳይ ሲፈልግ አራት እግሩን ይንቀል!” የሚለው አስተሳሰብ ወያኔ ያመጣው የፈጠረው አስተሳሰብ ሳይሆን ወያኔ ከትግሬ ሕዝብ በመውጣቱ የያዘው አስተሳሰብ መሆኑን ወያኔ እና ትግሬ ማለት ፈጽሞ ሊነጣጠሉ የማይችሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች መሆናቸውን እነኝህ መጽሔት ላይና ድረ ገጾች ላይ ባስነበብኳቸው በእነኝሁ ጽሑፎች ላይ አመክንዮአዊ በሆነ መንገድ ሁሉም ሊረዳ በሚችለው አገላለጽ በሚገባ ተገልጿል ይዞቹን (ሊንኮቹን) ክፈቱና አንብቡ፦

ሌላኛው ደግሞ ፦

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

Share Button