“የፈረሱ ግንቦችና አጥሮቻችን እንጠግን!” ዳኛ ብርቱካን

ጁላይ 7 ቀን፣ 2011 ዓ.ም. ለዳኛ ብርቱካን አትላንታ ላይ የእራት ግብዣ ተደርጎ ነበር። አዘጋጆቹ የአትላንታ አንድነት ፓርቲ ድጋፍ ሰጪዎች ይሁኑ እንጂ፤ ከልዩ ልዩ የአሜሪካ ክፍለ ግዛት የመጡ የድርጅት ተወካዮችና ታዋቂ ሰዎች ተገኝተው ነበር።

July 7, 2011 Dinner with Judge Birtukan Midekesa - Atlanta

July 7, 2011 Dinner with Judge Birtukan Midekesa - Atlanta

አቶ ግርማየ ግዛው የአትላንታ ድጋፍ ሰጪና የፍሪ ብርቱካን ሊቀ መንበር ዳኛ ብርቱካንን “እንኳን ደህና መጣሽ” በማለት የወ/ት ብርቱካንን ጥንካሬ አድንቀዋል። በእስር በነበሩበት ወቅት ያሳለፉትን ጊዜ እንዲሁም ወላጅ እናቷና ታዋቂ ሰዎች ስለ ዳኛ ብርቱካን ሚዴቅሳ የተናገሩትን አስታውሰዋል።

July 7, 2011 Dinner with Judge Birtukan Midekesa - (ኣቶ ግርማዬ ግዛው) Atlanta

July 7, 2011 Dinner with Judge Birtukan Midekesa - Atlanta

በመቀጠል ንግግር ያደረጉት የሰሜን አሜሪካ የአንድነት ሊቀ መንበር አቶ አክሎግ ልመንህ ነበሩ። አቶ አክሎግ ልመንህ በበኩላቸው ለወ/ት ብርቱካን ያላቸውን አድናቆት ገልጠዋል። በንግግራቸውም መጨረሻ “የነብርን ጅራት አይዙም፤ ከያዙም አይለቁም። አሁንም የነብሩን ጅራት ይዘሽዋል፤ እንዳትለቂው። አትለይን… አሁንም ምሪን።” በማለት ሲናገር በአዳራሹ ውስጥ የነበረው ህዝብ ሃሳቡን በጭብጨባ ነበር የገለጠው።

July 7, 2011 Dinner with Judge Birtukan Midekesa - (አቶ አክሎግ ልመንህ) Atlanta

የመንፈሳዊ ሃይማኖት መምህር የሆኑት ዶ/ር ተጋ በበኩላቸው፤ “ሁሉ ነገር የእግዚአብሔር እጅ አለበት። ሁሉም ነገር በአምላክ ፈቃድ ይሆናል።” ካሉ በኋላ በማጠቃለያቸው፤ “እውነትን የሚናገሩ ይሰደዳሉ፤ ይጠላሉ። ወ/ት ብርቱካን የዚህ ክስተት ውጤት ናት። ሆኖም እውንነት ተናግሮ የመሸበት ማደር ይሻላል።” ብለዋል።

July 7, 2011 Dinner with Judge Birtukan Midekesa - (ዶ/ር ተጋ) Atlanta

July 7, 2011 Dinner with Judge Birtukan Midekesa - (ዶ/ር ተጋ) Atlanta

ቀጣዩ ተናጋሪ የዋሺንግተን የአንድነት ድጋፍ ሰጪ አካልን ወክለው የተገኙት አቶ አለማየሁ ነበሩ። “ወ/ት ብርቱካን የበኩሏን አድርጋለች። ‘እኛ ምን አደረግን?’ ብለን ራሳችንን መጠየቅ አለብን። ስንቶቻችን ነን ለሰላማዊ ሰልፍ የምንገኝ? ለወገኖቻችን በሚዘጋጅ የሻማ ማብራት ምሽቶች ላይ የምንሳተፍ?” ህዝቡ ለአገሩና ለወገኑ እንዲነሳሳ ጥሪ አቅርበዋል።

አቶ ግርማዬ ግዛው እና አቶ ዮናታን አመዘነ

ዳኛ ብርቱካን በእስር ላይ በነበረችበት ወቅት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ካደረጉት መካከል አቶ ግርማዬ ግዛው እና አቶ ዮናታን አመዘነ በዳኛ ብርቱካን አማካይነት የመታሰቢያ ምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል።
በመቀጠል አቶ ዳዊት ከበደ በዚህ ምሽት ላይ የተገኙትን ጋዜጠኞች አመስግነው፤ ለወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ በተለይ ለዚህ ምሽት የተዘጋጀውን የገጣሚ ንጉሤ ስመወርቅን ግጥም በንባብ አሰምተዋል።

አቶ ዳዊት ከበደ

አቶ ዳዊት ከበደ

በመቀጠልም ከኖርዝ ካሮላይና ዶ/ር ሰለሞን እና ሌሎች ተናጋሪዎች ለወ/ት ብርቱካን ያላቸውን አድናቆት በንግግር አሰምተዋል።
ወ/ት ብርቱካን ባደረገችው ንግግር፤ የተሰማትን ጥልቅ የሆነ ደስታ ገልጻ፤ ‘ጅምሩ አለ። መሰረቱም አልተናጋም’ በሚል ስሜት ንግግሯን በመጀመር፤ “ከዚህ በኋላ የፈረሱትን ግንቦችና አጥሮቻችንን እንጠግን” በማለት ልብ የሚነካ ንግግር አድርጋለች። በአዳራሹ የተገኘውም ህዝብ ከመቀመጫው በመነሳት ድጋፉን በጭብጨባ ገልጾላታል።

ዳኛ ብርቱካን ሚዴቅሳ

ዳኛ ብርቱካን ሚዴቅሳ

በመጨረሻም ዳኛ ብርቱካን በእስር ላይ በነበረችበት ወቅት የተሰጧትን ልዩ ልዩ ሽልማቶች በአቶ አክሎግ እና በአቶ አለማየሁ አማካኝነት ተሰጥተዋል። በተጨማሪም የዋሺንግተን ዲሲ፣ የሲያትል፣ የዳላስ፣ የአትላንታ እና የኖርዝ ካሮላይና ተወካዮች ልዩ ልዩ የመታሰቢያ ሽልማቶችን ለዳኛ ብርቱካን አበርክተዋል።

የሲያትል ተወካዮች

የሲያትል ተወካዮች

 

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on July 8, 2011. Filed under NEWS. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.