“ስደተኛዎችን አትርሱዋቸው…” አንጀሊና ጆሊ

ዳንኤል ገዛኸኝ ከአትላንታ –

ዛሬ በ አለማችን እስከ 40 ሚሊዮን የሚደርሱ ስድተኛዎች በየ አህጉሩ ተሰደው ይገኛሉ።ከ አርባ ሚሊዮኑ ውስጥ 10ሺህ የሚደርሱት የተባበሩት መንግስታት የስደተኛዎች መርጃ ቢሮን ጥብቅ የደህንነት ክትትል የሚሹ እንደሆኑ በዘንድሮው የ አለም ስድተተኛዎች ቀን በአል አከባበርን አስመልክቶ ቢሮው ያወጣው መግለጫ ያመለክታል።የ አለም የስደተኛዎች መርጃ ቢሮ ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር.ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉታሬዝ ጁን 20/2011 የሚከበረውን የ አለም የስደተኛዎችን ቀን አስመልክተው ባስተላለፉት መል ዕክት ስድተኛዎችን እንዳንዘነጋ ችግራቸውንም ለማጋደድ የሚያስፈልጋቸውን በማድረግ እና በመርዳት በሚሊዮን ለሚቆጠሩት በ አለም ለተበተኑት ስደተኛዎች የምትችሉትን ሁሉ በማድረግ ሂወታቸውን መስመር በማስያዙ ረገድ አለም እንዲተባበር ተማጽነዋል።በተመሳሳይ እውቅዋ የፊልም ተዋናይ የ ዩ.ኤን. ኤች.ሲ.አር የበጎ ፈቃድ አምባሳደር አንጀሊና ጆሊ በበኩልዋ ለዘንድሮው የስደተኛዎች ቀን በቪድዮ ባስተላለፈችው መል ዕክት በ አሳዛኝ ድምጸት”ስድተኛዎችን አትርሱዋቸው” ስትል አደራዋን ተናግራለች።ጆሊ የምትችለውን ሁሉ ለ አለም ስደተኛዎች ማድረግ ብቻ አይደለም ከ አፍሪካዊትዋ ኢትዮጲያ ወላጅ አልባ ህጻናትን ወስዳ በማሳደግ የበኩልዋን ለመወጣት የቻለች የ አለም እንቁ ናት።ምንም እንኩዋን ይሃገራችን ብርቅዬ ተብዬ የኪነጥበብ ሰዎች ከዚህ አይነቱ አርኪ ተግባር ይልቅ አቅማቸውን የግል ሃብት በማጋበስ እና ለ አምባገነን ፖለቲከኛዎች ኪስ ማድለቢያ ከማቀንቀን የዘለለ አንዳችም በጎ ተግባራቸውን አይተን ባናውቅም …እንደ ጆሊ አይነቶቹ ሲያስደንቁን እነሆ አሉት።

ዛሬ ዛሬ ወገኖቻችን ኢትዮጲያውያን በሃገራችን ከተንሰራፋው ብልሹ አስተዳደር በተወለደው የፖለቲካ የጎሳ…የሃይማኖት የዘር…የኢኮኖሚ እና ልዩ ልዩ ቀውስ ምክንያት ሃገር ለቆ በመሰደድ የ አንበሳውን ድርሻ በመያዝ በአለም በሰደተኝነት ሪኮርድ የያዙ ናቸው።ዜጎቻችን ኢትዮጲያውያን በሰው ሃገር ተሰደው ቁጥራቸው የት እየለሌ ከመሆኑም በላይ ኢትዮጲያዊያን በብቸኝነት ያልተደፈሩ የስደት ድንበሮችን ሳይወዱ በግድ እየደፈሩ ለሞት እና ለስቃይ ለረሃብ እና ለቸነፈር እየተዳረጉ ይገኛሉ።በኢትዮ ሱዳን በሊቢያ ቤንጋዚ በረሃ በሶማሊያ ጠረፎች ባህር በማቁዋረጥ በሚደረገው የስደት መንገድ ባለፉት ሁለት አስርት አመታት ያለቁት ኢትዮጲያውያን ቁጥር ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም።በተለይም እኔ ባለፍኩበት የ ኢትዮ-ሶማሊያ ወደ የመን የመሻገሪያ የስደት መንገድ በለስ ቀንቶዋቸው በሂወት የተረፉ ወገኖቼ ለ አመታት በየመን እንደታየው ከሆነ ለሶማሊያውያን ብቻ ይሰራል በሚባለው ፍሪማ ፌሲ በተሰኘው ለመንግስት አልባ ዜጎች የተቃራኒዋን ሃገር መሬት እንደረገጡ የስደተንነት መብት በሚያጎናጽፈው አድሎአዊ ህግ ምክንያት ሶማሊያውያን የ የመንን መሬት እንደተቆናጠጡ በየመን የባህር ድንበር ጠባቂያን እና በ እርዳታ ሰራተኛዎች እንክብካቤ ወደ ስደተኛ ጣቢያ ሲወሰዱ ኢትዮጲያውያን ግን በ አስቸኩዋይ ለቀናት በሚያጉዋጉዝ መንገድ ወደ እስር ቤት ይጋዛሉ ከዚያም የየመን መንግስት ህገ-ወጥ ስደተኛዎችን ካገሩ ለማባረር ከ ሳውዲ አረቢያ መንግስት እና ከ አለም አቀፉ የስደት ድርጅት አይ.ኦ.ኤም.በሚበጀትለት በጀት አማካኝነት ያለምንም እንክብካቤ ያለምንም ተቀያሪ ልብስ እና የኪስ ገንዘብ ከወራት የየመን ሲኦል እስር ቤት ቆይታ በሁዋላ እነዚያን ስደተኛ ኢትዮጲያውያን በ ወያኔ ኢምባሲ የይለፍ ወረቀት ሊሴፓሴ ወደ ኢትዮጲያ ይጠርዙዋቸዋል። የወያኔው መንግስትም ከየመን መንግስት እና ከአለም አቀፉ የስደት ድርጅት ጋር በመተባበር ስደት በቃኝ ያሉ በየመን የሚገኙ ኢትዮጲያውያንን ሃገር ማስገባቱን በህሊና ቢስ ሆዳም ጋዜጠኛ ተብዬዎቹ ያነበንብልናል።ይህ ብቻም አይደለም በየመንም ይሁን በሌሎች ጎረቤት ሃገሮች ባሉ የስደተኛ መርጃ ቢሮ ተመዝግቦ መፍትሄ ከሚጠባበቁ የተለያዩ ሃገራት ዜጋ ስደተኛዎች መካከል በ ኢትዮጲያውያን ስደተኛዎች ላይ የሚደረገው የሃማኖት እና የቀለም ልዩነት በተደጋጋሚ የታየ እየታየ ያለ ጉዳይ ነው።በተለይ በተለይ እኔም እንደ አንድ ኢትዮጲያዊ አብዝቼ መናገር የምችለው ከሰማሁት ይልቅ በግንባር የተመለከትኩትን ነው እና በየመን ሰነአ እና የመን ኤደን የስደተኛ መርጃ ቢሮዎች ተመዝግበው ከ ሃያ አመታት በላይ መፍትሄ የሚናፍቁ ስደተኛዎች አሁንም መብታቸው እየተገሰሰ በግድ ሃይማኖታቸውን እንዲለውጡ እየተገደዱ እንደሃገሬው ህዝብ አይነት ሃይማኖት ያላቸው ደግሞ በጥቁርነታቸው እየተረገጡ እና እየተገለሉ ቢሮውም ይህንን እያየ እና እያወቀ ለ ኢትዮጲያውያን መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ ሌሌላ ሃገር ዜጎች በላይ በላዩ ድጋፍ እያደረገ ኢትዮጲያውያን ስደተኛዎች በየመን የመን በፈረመችው ኮንቬንሽን መድሎ እየተደረገባቸው ይገኛሉ።እንደሚታወቀው በየመን በተነሳው ቀውስ ሳቢያ ዜጎቻችን ሞተዋል ቤታቸው የፈረሰባቸው በ አሰሪዎቻቸው ጦርነት ውስጥ መግባት እና ልዩ ልዩ የከባድ መሳሪያ አደጋ ሽሽት ስደተኛዎች የመንግስታቱን የስደተኛዎች መርጃ የ የመን ሰነአውን ቢሮ ከበው መፍትሄ ፍለጋ ደጅጥናት ከጀመሩ ወር ሊሞላቸው ነው። ነገር ግን ሁኔታውን አስመልክቶ በሚድያ ከተዘገበ በሁዋላ እንኩዋን ማንም ኢትዮጲያዊ ሊያስታውሳቸው እና አለኝታነቱን ሊያሳያቸው አልደፈረም…ስደተኛዎቹም እንደሚገልጡት ጊዜያዊ የገንዘብ እና የቁሳቁስ ስጦታ እንደማይረባቸው ገልጠዋል ሆኖም ግን አቅም ያላቸው በስራቸው ምክንያት ከታላላቅ የዲፕሎማሲ እና የመንግስታቱን ድርጅት መድረስ የሚችሉ ሁሉ ድምጻቸውን እንዲያሰማላቸው ጉዳያቸው ለ አመታት ተዘግቶ ነው እና ያለው ታይቶ እልባት ማግኘት ይችል ዘንድ እየተማጸኑ ነው።ይህ ብቻም አይደለም ይህ እየሆነ ያለው የየመን መንግስት በፈቀደው መሬት በተከፈተ ቢሮ ነው እና በአለም ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጲያውያን ለግማሽ ሰአታትም ቢሆን የየመን ኢምባሲ ባለበት ሻማ በማብራት የ አመታት ስቃያቸውን እንዲያስረዳላቸው ስድተኛዎቹ ይማጸናሉ።

እናም ዛሬ የስደተኛዎች ቀን በ አለም በሚከበርበት ቀን በማህበራዊ የመገናኛ ድልድዮችም ቢሆን ቴክኖሎጂውን በመጠቀም ውድ ኢትዮጲያውያን በየመን የሚገኙ ስደተኛዎችን የተመለከተ አንድ ቃል እንኩዋን ለሚመለከተው ክፍል ታስተላልፉ ዘንድ የስደተኛዎቹ መል ዕክት ነው።”ስደተኛዎችን አትርሱዋቸው”…።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on June 20, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.