ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ሞቱ [Ethiopian Patriarch dies at 76]

(EMF) Patriarch of the Ethiopian Orthodox Church dies at 76. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አምስተኛ ፓትርያርክ የነበሩት አቡነ ጳውሎስ በተወለዱ በ76 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። በዛሬው እለት ዜናችን ሌሎች ምንጮችን እየጠቀስን ይህንኑ ዜና ስናቀርብ መቆየታችን የሚታወስ ሲሆን፤ አሁን እንደደረሰን የተረጋጋጠ ዘገባ ከሆነ ግን አቡነ ጳውሎስ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።
የፓትርያርኩን ሞት በተመለከተ ከዋልድባ ገዳም መነኮሳት ለቅሶ ጀምሮ ልዩ ልዩ ምክንያቶች ይሰጣሉ። “እግዚአብሄር ፍርድ እየሰጠ ነው” ከሚሉት ጀምሮ “ነፍሳቸውን ይማር” እስከሚሉት ድረስ የግለሰብ አስተያየቶች እየተሰሙ ነው።

Patriarch of the Ethiopian Orthodox Church dies at 76


ፓትርያርኩ የሹመታቸውን 20ኛ አመት ካለፈው ወር ጀምሮ ሲያከብሩ ቆይተው፤ አሁን በፍልሰታ ጾም ነው ከዚህ አለም በሞት የተለዩት። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ አወዛጋቢ የነበሩት ፓትርያርክ ህይወታቸው ያለፈው በደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ሲረዱ ከቆዩ በኋላ ሲሆን፤ አስከሬናቸው ወደ መንበረ ፀባዖት ግቢ መወሰዱን የኢ.ኤም.ኤፍ. ምንጮች ገልጸዋል።
አቡነ ጳውሎስ በህይወት በነበሩበት ወቅት፤ አወዛጋቢ ከነበሩባቸው በርካታ ጉዳዮች መካከል የሚከተሉት ጥቂቶቹ ናቸው።
1ኛ- ከፍትሃ ነገስቱ ህግ ውጪ፤ ፓትርያርክ በህይወት እያለ እሳቸው መሾማቸውና ሹመቱን መቀበላቸው፤
2ኛ – የኦርቶዶክስ ተዋህዶን የ እምነት መሰረት የሚያፋልሱ ህጸጾችን በመፍጠራቸው፤ በመጽሃፍም በማሳተማቸው፤
3ኛ – ራሳቸውን ከቅዱስ ሲኖዶስ በላይ ራሳቸውን መሾማቸው፤
4ኛ – በህይወት ሳሉ ለራሳቸው ሃውልት ማቆማቸው፤
5ኛ – በኢትዮጵያ ውስጥ ላለው የግፍ አገዛዝ እና ባለስልጣናቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ድጋፍ መስጠታቸው የሚሉት ይገኙበታል። ከዚህም መካከል በተለያዩ ጊዜያት በኢህአዴግ አመራር በህዝቡ ላይ ግፍ ሲፈጸም አለማውገዛቸው፤ በቅርቡም በዋልድባ ገዳም እየተከናወነ ያለውን ተግባር ከማውገዝ ይልቅ ዝምታን መምረጣቸው… ከሚያስወቅሷቸው በርካታ ምክንያቶች ጥቂቶቹ ነበሩ።

ከዚህ በኋላ እንደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት የቀብር ስነ ስርአታቸው ይፈጸማል። በዚህ የቀብር ስነ ስርአት አምና አብረዋቸው የነበሩት ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ አይገኙም፤ የሃዘን መግለጫም አይልኩም።
ሆኖም ቀጣዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ምርጫ በቅዱስ ሲኖዶሱ አማካኝነት ይከናወናል። ምዕመናኑም ቀጣዩ ፓትርያርክ ለኢትዮጵያ እና ለህዝቡ የሚበጅ፤ ለሰላም እና ለፍቅር የሚዋጅ እንዲሆን በዚህ የፍልሰታ ሶም ወቅት በጸሎት ይተጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ኢ.ኤም.ኤፍ. ተጨማሪ ዘገባዎችን እየተከታተለ ያቀርባል።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on August 16, 2012. Filed under FEATURED. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.