ፍኖተ ነፃነት ቁጥር 7

“ሰላማዊ ትግል ሲባል ሞት፣ እስራትና እንግልት የለም ማለት አይደለም፡” አቶ አንዱአለም አራጌ (ከመታሰሩ በፊት የተናገረው)

የአንድነት ፓርቲ ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ አንዱአለም አራጌ ከመታሰሩ በፊት፤ የሚከተለውን ብሎ ነበር። “ በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድም ሆነ በተቃውሞው ጎራ አንድ ሊታወቅ የሚገባው ጉዳይ ዝም ብሎ በሆይ ሆይታ ሰላማዊ ትግል ማድረግ ብሎም ለውጥ ማምጣት እንደማይቻል ነው፡፡ በቆራጠነት፣ በፅናትና አርቆ በማየት ነው ለድል መብቃት የሚቻለው፡፡ ሰላማዊ ትግል ሲባል ሞት፣ እስራትና እንግልት የለም ማለት አይደለም፡፡ ልዩነቱ ሰላማዊ ታጋዩ አይገድልም፡፡ ሠላምን አያደፈርስም፡፡ ነገር ግን በፀናና በተደራጀ ሁኔታ መብቱን ይጠይቃል፡፡ ሉዓላዊ ስልጣኑን ዕውን ሳያደርግ አይመለስም፡፡ በሠላማዊ ትግል ውጤታማ እንዲሆን የሕዝብ አንድነትና የዓላማ አንድነት ወሳኝ ቅድመ-ሁኔታዎች ናቸው፡፡ ትግሉ የራሱ ስነ-ምግባር አለው፣ መደጋገፍን ይጠይቃል፡፡ አንዱ ሲወድቅ እሱን አንስቶ ከፍ ባለ የሞራልና የዓላማ ልዕልና ትግሉን እየተቀባበሉ ወደፊት መሄድ ይጠይቃል፡፡” ይህንን ቃል ያስተላለፈው በፍኖተ ነፃነት ቁጥር 7 እትም ነበር። የጋዜጣውን ሙሉ እትም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ።

Finote_Nesanet_7_091411

Finote_Nesanet_7_091411

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on September 14, 2011. Filed under PRINT MEDIA. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.