ፍቃድ የማያሻውን ተቃውሞ ማን ይጥራው (ዳዊት ዳባ)

በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ተቃውሞ ለማድረግ ሲያስቡ ህጉ ማሳወቅ ቢልም አሳውቀናል ብቻ ብለው ለመቀጠል ያለው ተጽኖ ቀላል አይደለም። ሆን ብሎ ወደ ግጭት [confrontation] የሚገፋቸውን አገዛዝ መብለጥ አለባቸው። ስለዚህም ለማስፈቀድ የሚያልፉበት ውጣ ውረድና ዝቅ ማለት ይኖራል። ባሰቡት ቦታና ጊዜ ተቃውሟቸውን ማሰማቱ ደግሞ ሌላ ሆን ብሎ ባገዛዙ የሚቀናበር ጋሬጣ ማለፍን ይሻል።ስለተቃውሞው ህዝብን ማሳወቁም እንዲሁ።

በዚህ አፈና ውስጥ ሲንቀሳቀሱ አንዳንዴ በውሳኔ አለመፅናት፤ መላዘብ፤ አልፎ አልፎም ተሸንፎ ለጊዜውም ቢሆን መተው፤ ለህግ መከበር ደንታ የሌለው ስረአት መሆኑ ግልጽ ሆኖ እያለ ጥንቃቄ በበዛበትና በህግ አግባብ ለመንቀሳቀስ መሞከራቸውና በሌሎችም የዚህ አይነት እውነቶች ላይ ተነተርሶ በተወሰኑ ዜጎችና ድርጅቶች ዘንድ ጥረታቸው ጥያቄ ሚያስነሳባቸውና የሚያስወቅሳቸው ሆኗል።

አስፈቅዶ በሚደረግ ተቃውሞ ነጻነት አይመጣም ከሚል ጀምሮ ተቃወማችሁ ከዛስ?። እሱ በፈቀደው ቦታና ጊዜ የሚደረግ ተቃውሞ ምን የሚሉት ተቃውሞ ነው። የናንተን የመጀመርያ እቅድና ምርጫ ባስለወጣችሁ ቁጥር ይህ ሁኔታ የህዝብን አመኔታና የመታገል መንፈስ አይሸረሽረ ነው። የሚመስሉሉ ጥያቄዎች እና ወቀሳዎች እንዲነሱ አድርጓል። Continue reading ማን ቢጠራው ይሻላል

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 20, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

2 Responses to ፍቃድ የማያሻውን ተቃውሞ ማን ይጥራው (ዳዊት ዳባ)

 1. sherif,

  April 21, 2014 at 7:54 AM

  Mr Dawit Fuzo ,,,wishfull thinker

 2. andnet berhane

  April 21, 2014 at 5:25 PM

  የትግልሉ ፊትወራሪኦች የሚያደርጉት ሁለንተና ተግባር የሚደነቅና ድጋፍም የሚገባቸው ናቸው ነገርግን የተነሱበትን ሰላማዊና ፍትሃዊ የሕዝብ ምሬት ለማሰማት የሚወስዱት ማንኛውም እርምጃ ሕገ መንግስቱ የሚያዘውን አሟልተው እስከተገኙ ሰልፉን በሃገሪቱ ባሉ አደባባዮች ያለ ድርድር ማካሄድ ይገባቸዋል ምክንያቱም ይህ እምባገነን አስተዳዳደር በነፍጥ ማስፈራራትና አላስፈላጊ እርምጃ ለመውሰድ ወደኅውላ አይመለስም ይህ ለማንኛችንም የበራና ምስክርነት አያሻውም ነገርግን የሰልፉን ጥሪ ከማስታወቅ ባለፈ ቦታ መወሰን ሕገ መንግስታዊ ጥሰት ነው: በሌላ በኩል በአንድ ወቅት ሁለት ድርጀቶች ሰላማዊ ሰልፍ መጥራት ለወያኔ(ኢሓዴግ)ፍለጎት እንቅፋት አማቺ እንድማድረግ እወስደዋለሁ መልክቱ የመብትና የነጻነት ጥያቄ ከሆነ የሚጠይቁትን ጥያቄዎች በቦርድ ላይ በመጻፍ ሕዝቡም ተበራ ክቶና በዝቶ ስለሚወጣ ለሰልፉ ድምቀት ለገዥው ፍርሃት እንድሚፈጥር ጥርጥር የለኝም
  አላማችሁ የሃገርና የሕዝብ መብትና እየደረስበት ያለው ችግርና ሶቆቃ ለመቅረፍ እስከሆነ ሁሉም ተቃዋሚ ድርጅቶች ሰልፉን የጠራው ምን ይሁን ማን ለሰልፉ መቀላቀል ግዴታ አለባቸው:ሕዝቡም አታጋይ ሳይሆን የሚጠብቀው ራሱን ታጋይ አድርጎ ለመብቱና ለህላዊነቱ መቆም ይኖርበታል: በየበእቱ ተቀምጦ መቆዘም ችግሩን ያባብሰዋል እንጂ መፍትሄ የለውም:መፍትሄው በጁ በመሆኑ ነጻ ለመውጣት ነጻአውጪ መጠበቅ ሳይሆን ራስህ ነጻአውጭ መሆን ነው: