ፌዴራል ፖሊስ ብዙ ሰው ገደለ

(EMF) ባህር ዳር – በባህር ዳር ከተማ ውስጥ አንድ የፌዴራል ፖሊስ ከ12 ሰዎችን በጥይት ደብድቦ መግደሉን ከስፍራው የደረሰን ዘገባ ገልጿል። ስሙ ገና ያልተገለጸው የፌዴራል ፖሊስ ትላንት ምሽት ልዩ ስሙ አባይ ማዶ ቀበሌ 11 ውስጥ ነው ይህንን አሰቃቂ ድርጊት የፈጸመው። በአሁኑ ወቅት ገዳዩ የት እንደደረሰ ለማወቅ አልተቻለም። ይታሰር ወይም ያምልጥ በፖሊስ በኩል የተሰጠ መግለጫ አልነበረም። አሁን ዘግይቶ የደረሰን ዜና እንደሚያስረዳው ግን፤ ፖሊሱ ግድያውን ከፈጸመ በኋላ፤ ከድልድይ ዘሎ ወንዝ ውስጥ በመግባት ተሰውሯል። ይህ ዜና በተዘጋጀበት ወቅት ገዳዩ ገና አልተያዘም ነበር። ንጹሃን ዜጎች የሞቱባቸው ቤተሰቦች ግን በሆስፒታል እና ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ በብዛት የታዩ ሲሆን፤ የብዙዎቹ የቀብር ስነ ስርአት ዛሬ እና ነገ ይፈጸማል። ዛሬ ባህር ዳር ትልቅ ሃዘን ውስጥ ገብታለች።

ethiopia1

ግለሰቡ ይህንን አሰቃቂ ድርጊት የፈጸመው፤ ከጥላቻ በመነሳት ወይም በመጠጥ ሃይል አልያም የአእምሮ መታወክ ደርሶበት ይሁን አይሁን ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም። ነገር ግን ቀድሞውኑም የፌዴራል ፖሊሶች ከህግ በላይ የሚፈጽሟቸው ድርጊቶች እየተበራከቱ ለመምጣታቸው ይህ ጥሩ አመላካች ነው – ይላሉ ታዛቢዎች።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on May 13, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to ፌዴራል ፖሊስ ብዙ ሰው ገደለ

  1. koster

    May 14, 2013 at 9:58 AM

    A Police whether federal or not was meant to protect civilians and implement rule of law. But in lawless Ethiopia under woyane ethnic fascists, federal Police or agazi means a license to kill. It is really unfortunate that thousands if not millions of Tigrians and others died to bring the home grown fascists into power so that they loot and terrorize us. Even the sons of Asgede Gebre Selassie who paid high Price thinking that the aim was to liberate Tigrai is now paying a high Price because he is having different poitical opinion than the home grown fascists. His two sons are languishing under the worst Fascist torture chamber.