ፊፋ አወዛጋቢውን ጎል አፀደቀ (ደብዳቤውን ይዘናል)

(ኢ.ኤም.ኤፍ) ለ20ኛው የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ እና ናይጄርያ፤ ኦክቶበር 13፣ 2013 አዲስ አበባ ውስጥ ግጥሚያ ማድረጋቸው ይታወሳል። በዚህ ግጥሚያ ላይ በ24ኛው ደቂቃ ሳላዲን ሰኢድ ናይጄርያ ላይ ግብ አስቆጥሯል። ሆኖም ካሜሪናውያኑ ዳኛም ሆኑ የመስመር ዳኛው ግቧን አላጸደቋትም። ኢትዮጵያውያኑ የተነጠቁት የመጀመሪያ ግብ ነበር።

የጎሉ መስመር እንዲህ ቢሆን ኖሮ፤ የካሜሩኑ ዳኛ ውሳኔ ትክክል ይሆን ነበር።

የጎሉ መስመር እንዲህ ቢሆን ኖሮ፤ የካሜሩኑ ዳኛ ውሳኔ ትክክል ይሆን ነበር።

ጨዋታው ሲጠናቀቅ ናይጄርያ 2-1 አሸንፋለች። ከዚህ በኋላ በኖቬምበር የመጀመሪያ ሳምንት ላይ፤ ናይጄሪያ ላይ የሚያደርጉት ፍልሚያ፤ የኢትዮጵያን ወደ ብራዚል የመሄድ እና ያለመሄድ እድል ይወስነዋል። በዚህም መሰረት ወደሚቀጥለው ዙር ለማለፍ ኢትዮጵያ – ናይጄርያን 2-0 ወይም 3-1 ማሸነፍ አለባት። ናይጄርያ በሚደረገው ጨዋታ ኢትዮጵያ 2-1 ብታሸንፍ 30 ደቂቃ ተጨማሪ ሆኖ ይፋለማሉ፤ ማለት ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ ኢትዮጵያ ላይ የገባው አወዛጋቢ ጎል… ተቃውሞ አጋጥሞታል። ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት፤ ለፊፋ ደብዳቤ ጽፎ ነበር። ለተጻፈው ደብዳቤ የተሰጠው ምላሽ በግልጽ እንደሚያመለክተው ከሆነ፤ ፊፋ በተሰጠው ውሳኔ ላይ ምንም ማድረግ እንደማይችል ይገልጻል። ይህም በተዘዋዋሪ መንገድ ገብታ እንዳልገባች የተቆጠረችውን ጎል ፊፋ አጽድቋታል ማለት።

Letter from FIFA

Letter from FIFA

ከዚህ በኋላ የሚያዋጣው ናይጄርያ ላይ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ነው። ናይጄሪያዎች ኢትዮጵያ መጥተው በጨዋታ ተበልጠው፤ ግን አሸንፈው ተመልሰዋል። ኢትዮጵያውያኑም ናይጄርያ ሄደው ሊያሸንፉ የማይችሉበት ምንም ምክንያት የለም። በርግጥ አንድ ጎል ስናገባ፤ አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው መከላከል ላይ ለማተኮር ይመስላል፤ ያደረገው የመሃል ተጫዋች እና የአጥቂ ተጫዋች ቅያሪ ትልቅ ዋጋ አስከፍሏል። በሚቀጥለው ጨዋታ መሃል እና አጥቂው ተጠናክሮ ወደ ናይጄሪያ ካመሩ የማናሸንፍበት ምን ምክንያት አይኖርም።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on October 16, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

3 Responses to ፊፋ አወዛጋቢውን ጎል አፀደቀ (ደብዳቤውን ይዘናል)

 1. dawit

  October 17, 2013 at 4:54 AM

  selam lenante yehun!!!
  i don’t understand how you read fifa’s response to ethiopian football federation, simply u have read it in your own wishful version, we are all sorry about the referee’s blindness but to reach to this kind of conclusion is not good.”fifa golun atsedeqew” is the title very bizzare.
  amesegnalehu

 2. Ethiopia

  October 17, 2013 at 5:20 AM

  What is the FIFA responsiblity, I know that “there is not fair decsion in this world” but this is more than unfair and we will not accept easily the decsion. The government has to interfair, if it would be political issue the gov’t doesn’t need pushing.

 3. Negussie

  October 17, 2013 at 9:56 PM

  የእግር ኳስ መሪዎቻችን የተጠቀሰውን ሕግ አያውቁትም? በእርግጠነት ለመናገር ሕጉን ያውቁታል:: እኔን የማይግባኝ የእግር ኳስ አፍቃሪው በአጉል ተስፋ እንዲዋልልና የተስፋ ዳቦ እንዲገምጥ ማድረግ ለምን እንደምርጡ ነው:: ሕጉንና በዚህ ሕግ መሰረት የተዳኙ መሰል አውዛጋቢ ክስተቶችን ካላውቁ ቦታውን የፊፋን ሕግ ጠንቅቀው ልሚያውቁ መተው አለባቸው:: በሁለት ቢጫ ምክንያት ማረፍ የሚገባው ተጫዋች በፌድረእሽኑ ቸል ባይነት ምክንያት ተጫውቶ አንድ እርምጃ ወደኋላ እንድንመለስና አስጊ ሁነታ ላይ እንድንደርስ መድረጉ አይዘነጋም:: በዚህ ሁነታ ለሚደርሰው የገንዝብና የሞራል ኪሳራ ተጠያቂነት ያለባችው መሆኑ መዘንጋት የለብትም:: የስፖርት ቤተስቡም ካጉል ተስፋ ብሎም ለሌላ መረጃ ፍለጋ ማዋል የሚገባውን ጊዘና ገንዘብ እንዳያባክን ጥበቃ ሊድርግለት ይገባል ይህ ደግሞ ክፌድረሽኑ አበይት ተግባራት የሚፈረጅ ጉዳይ ነውና ይታስብበት:: ቡድናችን ባልፈው እሁድ ለራሱ ትልቅ ተራራ ሰርቷል ይህንን አቅብት በድል ለመውጣት ሁሉን አቅፍ መሰናዶ ይጠብቅዋል ክኛም ከቡድኑም የሚጠበቅ ድርሻ ስላለ ተግተን ምስራት አልብን ባይ ነኝ:: ልጆቻችን በእግር ኳስ ታሪካችን ላይ ማስመዝገብ የጀመሩትን ድንቅ ድሎች ብምቅጠል ታላቅ ምእራፍ እንዲያሽጋግሩት እግዚአብሐር ይርዳን::