ፈይሳ ጃታ… ብሄራዊ ውርደትን ያልተቀበለ ጀግና!!

ተራኪ – ተስፋ ጥ ዑመ-ልሣን

ጸሃፊ – ዳዊት ከበደ ወየሳ

ሰሞኑን ስለብሄራዊ ውርደት ብዙ ይባላል። ብዙ ስለሚባለው ነገር መልሼ ከማውራት ይልቅ፤ አንድ ሰው ላስተዋውቃቹሁ። ፈይሳ ጃታ ይባላሉ። ሀረር ውስጥ ለብዙ አመታት የኖሩ ናቸው። ጣልያን የጫነብንን ብሄራዊ ውርደት ያልተቀበሉ፤ የሱማሌ ወረራን ተከትሎ የመጣውን ሽንፈት፤ “እምቢኝ” ያሉ ጀግና ነበሩ።

የሀረሩን ፈይሳ ጃታ ያለ ምክንያት አላነሳሁዋቸውም። “ብሄራዊ ውርደት” ብለን በምንጠራቸው ዘመኖች፤ እንደሳቸው አይነት ያለተዘመረላቸውና ምንም ያልተባለላቸው ሰዎች መኖራቸውን ለማስታወስ፤ ከዚያም አልፎ ሁሌ ብሄራዊ ውርደትን ያሸነፉ፤ ጀግኖች መኖራቸውን ማውሳት አስፈላጊ ስለሆነ ነው።

ethio flag

ለነገሩ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በበርካታ የታሪክ ምዕራፎች ብሄራዊ ውርደትን አስተናግደናል። አንደኛውና ሁላችንም የምናውቀው በጣልያን ወረራ ወቅት፤ በራሳችን ባንዳዎች የተፈጸመብን ውርደት ነው። ሁለተኛውን ውርደት የተከናነብነው በቀይ ሽብር ዘመን ወንድም ወንድሙን ገድሎ የፎከረበት ወቅት ሲሆን፤ ሶስተኛው ብሄራዊ ውርደት ደግሞ፤ አሁን በአገራችን ያለው ስርአት ያከናነበን የቅሌት ቡሉኮ ነው። በመግቢያዬ ላይ እንደገለጽኩት ስለያንዳንዱ ዘመን ብሄራዊ ውርደት ለመተንተን አይደለም – የዛሬ መነሻዬ። ይልቁንም በእንደዚህ አይነት የውርደት ዘመናት አንገታቸውን ቀና አድርገው፤ ሰንደቅ አላማችንን ከፍ ስላደረጉ አንድ ግለሰብ ጥቂት ለማለት ፈልጌ ነው። (Click here to Read on PDF)

 

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on December 2, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to ፈይሳ ጃታ… ብሄራዊ ውርደትን ያልተቀበለ ጀግና!!

  1. Abera Gebre

    December 6, 2013 at 3:01 PM

    ዻዊት ከድም ስሊ ስአ ባልቻ አባ ንፍሶ የሳፍክዉ ታሪክ በታም የወደድኩት ስሆን አሁን ድገሞ ስለዘህ ጀግና ስለ ፈዪሳ ያክረብክው እጂግ ማራኪ ነው በታም አመስግናለሁ ወደፊትም ብዙ እንደምታስነብበን አምናለሁ በርታ .አመስግናለሁ