ጥሪ: የትብብርና የቤተሰብ ቀን

march4freedom.org  – ዛሬ በዓለማችን ዙሪያ ለነፃነት፣ ለእኩልነት፣ ለሰብኣዊ መብትና ለዲሞክሲ ስርዓት መከበር ህዝቦች እጅ ለእጅ ተያይዞው፣ መድፍና ታንኪ ሳይበግራቸው እምቢ ለነፃነቴ፣ እምቢ ለመብቴ፣ እምቢ ለሰብኣዊ ክብሬ ብለው አደባባይ በመውጣት ለዘመናት ሲጨቁኑዋቸው የነበሩ አምባገነናዊ ስርዓቶች በህዝባዊ ዓመፅና በተባበረ ክንድ ከዙፋናቸው በሀይል መንግለው ሲጥሉዋቸው በዓይናችን እያየን ነው።

በሀገራችን ውስጥ እየታየ ያለው ሁኔታም ለሁላችን ግልፅ ነው። በአንድ በኩል በረሃብ የሚገረፍ፣ ለባዕድ ምፅዋትና ልመና ተጋልጦ ንሮውን መሸነፍ ያቃተው ህዝብ አለን። ህፃናት በቆሻሻ ቦታ የተጣለና የበሰበሰ አጥንት እየለቀሙ ከውሾች ጋር እየተሻሙ የሚበሉበት፣ በችግር ላይ ችግር የወደቀችና የደቀቀች ሀገር ነው የምናየው። በአንፃሩ በሙሱና የናጠጡ ጥቂት ጉልበተኛ ቡድኖች ክብረ ልዕልናዋን ደፍረው፣ አንጡራ ሃብትዋን እየዘረፉ፣ ለም መሬትዋን እየሸነሸኑ ለባዕዳን በመቸብቸብ ህዝባችንን የበይ ተመልካች በማድረግ ረግጠውና አፍነው የሚገዙ አምባ ገነኖች የበቀሉባት ምድር ሆና ትገኛለች።

እኛ በዲያስፓራ የምንገኘው ኢትዮጵያውያን ያለንን መለስተኛ የአመለካትና የእምነት ልዩነት ወደ ጎን ትተን በቅድሚያ ሀገርንንና ህዝብን ከመበታተንና ከጭቆና ማዳን ዋል እደር የማይባልበት ወቅቱ የሚጠይቀው ጉዳይ ነው። ስለሆነም ጎሳ፣ ሀይማኖት፣ ፆታ፣ ህፃን፣ ሽማግሌ ሳይለይ እንደ አንድ ቤተሰብ ሁላችንም ተሰባስበን ለህዝባችን ያለንን የትግል አጋርነታችንን በጋራ የምንገልፅበትና ከጎኑ መሰለፋችንን በተግባር የምናሳይበት የትብብርና የቤተሰብ ቀን (people to people Solidarity day) በተቀናጀ መልኩ ተዘጋጅቷል። በመሆኑም ይህ በልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ታጅቦ የሚከናወን የወንድማማቾች ቀን ከወዳጅ ዘመዶቻችሁ ጋር አብራችሁ እንድትገኙልን የአክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን።

በዋሽንግተንና አካባቢዋ የሚገኙ የኢትዮጵያ ማሕበረሰቦች በመተባበር
Info. 202 656 8070 Email – joinus@march4freedom.org
በዋሽንግተን ዲሲ White House ፊት ለፊት ነው።
ዕለተ ሰንበት February 27/2011ዓ.ም 2፡00pm ይጀምራል

======= //////// =======
ከህዝባችን ጋር ያለንን አጋርነት ስደትና ርቀት አይከልለውም

ስንተባበር እናሸንፋለን !!

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 22, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.