ጎንደር ታምሷል፤ አዲሳባ ተነሳስቷል!

EMF – በመተማ ገንዳውሃ ከተማ ግንቦት 20 ቀን 2005 ዓ. ም የእርሻ መሬታቸው የተነጠቁ በርካታ ሰዎች በተገኙበት ስብሰባ ተካሄደ፡፡ በስብሰባው የ‹ክልሉ› ም/ አስተዳደር እንደሚገኝ ቢነገርም የተገኙት የሰ/ ጎንደር አስተዳደር ሀላፊ አቶ ግዛት አብዩ ናቸው፡፡

Blue party logo

Blue party logo

ስብሰባው የእርሻ መሬታቸውን በተነጠቁት አርሶ አደሮች ጉዳይ ሲሆን ከፍተኛ ክርክር ተካሂዶ ስምምነት ያልተደረሰ ሲሆን አቶ ግዛት ‹‹ መሬቱን መልቀቅ አለባችሁ..›› ሲሉ ተሰብሳቢዎች ተቃውሞ አድርገዋል፡፡
አያይዘውም አቶ ግዛት ‹‹…እስከ አፍንጫው የታጠቀ መከላከያ ሰራዊት ነው ያለን ሜዳው ያውላችሁ….›› በማለት ዛቻ አሰምተዋል፡፡ አርሶ አደሮችም ‹‹ መሬቱን አንለቅም መከላከያ እገላለሁ ካለም ይግደለን፡፡›› በሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ከስብሰባው በኋላ የኢህአዴግ አባላትን ይዘው እስከ ምሽቱ 6፡00 በመሰብሰብ ችግር ይፈጥራሉ ባሏቸው ሰዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ዶልተው ሂደዋል፡፡

በተመሳሳይ በጎንደር ከተማ የሚገኙ ባለኀብቶችና ነጋዴዎችን የቀበሌ ሹማምንት ‹‹የመለስ ራእይ›› የሚለው ‹‹መፃህፍን›› ከ2000.00- 5000.00 ብር ግዙ በማለት ከፍተኛ ጫና እየፈጠሩ መሆኑን ነጋዴዎች በምሬት ገለፁ፡፡ እያንዳንዱ ቀበሌ ‹‹መፅሀፉን›› ሽጦ ከ400.000.00- 500.000.00 ብር ገቢ እንዲያደርግ ታዟል፡፡

በሌላ መልኩ ቁጥቸው 500 የሚደርሱ ሚሊሻዎች ከደባርቅ ወረዳ በመሰብሰብ ለልዩ ስልጠና ከ21/ 09/ 2005 ዓ. ም ጀምሮ በድብ ባህር ልምምድ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ የስልጠናው ምክንያት በአካባቢው ባሉ የታጠቁ ኃይሎች ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይነገራል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰማያዊ ፓርቲ አዲስ አበባ ላይ የጠራው ህዝባዊ ስብሰባ የሰሞኑ የአገር ቤት አቢይ ዜና መሆኑ ተገልጿል። ከዚሁ ጋር የደረሰን መእክት እንዳስተላለፈው፤ የህዝባዊ ስብሰባው አጀንዳ ሀገራዊ በመሆኑ ቀደም ሲል ሁሉም ኅብረተሰብ ‹‹ተቃዋሚ የለም፣ ማን ያስተባብረን፣ ሚጠራን የለም፣…ወዘተ. ›› ጉንጭ አልፋ ወሬዎችን የሰበረ ነው፡፡ ይኸው ‹‹ና›› ተነስ ተቃውሞህን ግለጽ ተብለናል፡፡ በየጓዳው፣ በየካፌው፣ በየባንኮኒው፣ በየወረቀቱ፣ በየ…፣በየ…፣ መትመክመክ ዋጋ የለውም፡፡

ስለዚህ በዚህ ምቹ አጋጣሚ ሁላችንም ተነስተን ‹‹ሆ›› ብለን ተቃውሟችን እንግለፅ፡፡
በስብሰባው መገኘት የግድ የሰማያዊ ፓርቲ አባል መሆን አይደለም፣
ስብሰባው ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ይጋብዛል፣
ሁሉንም ተቃዋሚዎች ይጋብዛል፣
ሁሉንም እምነቶች ያካትታል፣
ከቤት ውጭ በመሆኑ በጣም አመችና ገላጭ ነው፣
መፈክር ይዞ ለመውጣት ያመቻል፣
ለረዥም ቀናት/ድል ለመጨበጥ/ ያመቻል፣
ከሁሉም በላይ ወሩ ግንቦት ነው፣
ጥንካሬ፣ ድፍረት፣ ቆራጥነት፣ ፅናት፣ ….ከሁላችንም ይጠበቃል፡፡

የዘገባው መጨረሻ፤ ራሳችን ነፃ ወጥተን ሀገራችንን ነፃ እናውጣ!!!
…..ቱኒዝያ፣ ግብፅ፣ ሊብያ፣ የመኒያ፣……ኢትዮጵያ፣……” ብሏል ርእየ- ሁለንተና – አዲስ አበባ- ኢትዮጵያ

 

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on May 30, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

3 Responses to ጎንደር ታምሷል፤ አዲሳባ ተነሳስቷል!

 1. BAYESHE ANDARGE

  May 30, 2013 at 9:47 AM

  ERE MIN GUD NEW MISEMAW TADIYA BESDET YALENS MIN HAGER ALENNA LEHAGERACIN ABKAN EYALN LEFETARI MINALEKSEW?YALUT KIYACIWN EYELEKEKU ERE EZBI ZIM ATBEL///

 2. ሀጎስ

  May 30, 2013 at 3:35 PM

  አረ ተው አባካችሁ ቀዝቀዝ አንበል

 3. ሃና

  May 31, 2013 at 10:17 AM

  እኔ ግን ሃገሬ እነሱን እንድትመስል አልፈልግም።ደም አትጠሙ።