ግልጽ ደብዳቤ ለሃይሌ ገብረሥላሴ (ከአበበ ገላው)

ውድ አትሌት ሃይሌ፣ ከነመላው ቤተሰብህ እንደምን ከርመሃል? ልጆቹ እንዴት ናቸው፣ አለምስ እንዴት ሰንብታለች? ሰሞኑን የወዳጅ የዘመድ ምክር አላዳምጥ ብለህ እንደነ ጋሼ ግርማና ጋሼ ሃይለማርያም ደሳለኝ የህወሃቶች አሻንጉሊት መሆን እንዳማረህ ስሰማ በጣም ተገረምኩ። በመላው አለም ዝና ያተረፍክበትን እሩጫ ትተህ “ቤተመንግስት” ወይንም “ፓርላማ” ቁጭ ብለህ ዝንብ ማባረር ምን ይጠቅመኛል ብለህ ነው? አንተም እንደነጋሼ ግርማና ሀይለማሪያም በቁምህ ከመሞትህ በፊት ምክሬን ባትሰማ እንኳን ለማንኛውም ይቺን አጠር ያለች ጦማር ልጽፍልህ ወሰንኩ። Read full story in PDF.

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on July 17, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

2 Responses to ግልጽ ደብዳቤ ለሃይሌ ገብረሥላሴ (ከአበበ ገላው)

 1. አቢይ ኢትዮጵያዊ+ሥጋዊ-ወመንፈሳዊ

  July 18, 2013 at 6:25 PM

  ይህ የአበበ ገላው ግልፅ ደብዳቤ በ”ላም እሳት ወለደች”ኃይሌ ገብረ-ሥላሴ ያቆሰለውን ልቤን በብዕሩ ፈንቅሎ አፈረጠልኝ::

  ደም የቋጠረ ቁስል ሲፈርጥ እንዴት ደስፈቅ እንደሚያደርግ የደረሰበት ብቻ ነው ሊረዳው የሚችለው:-እናም አበበ ገላው አውቆልኛል::ወንድማችን አቶ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በጥልቀት ሊያውቀውና ሌሎቹም ኢትዮጵያን ወክለው በረከት የሚያገኙ ሁሉ አጥብቀው ሊገነዘቡት የሚገባው:-እንኳን ካኒቴራቸው ይቅርና እነሱ እራሳቸው እንደኢትዮጵያ ሕዝብ ሀብት ተለይተው የሚቆጠሩት ዋናው ምክንያት በኢትዮጵያ ሕዝብ ሥም ያደረጉት እና የፈጸሙት ማናቸውም ተግባር ነው::

  እናም ያቺ የኢትዮጵያ ሕዝብ ካኒቴራ እጁ በደም ለተጨማለቀ አምባገነን በኃይሌ ገ/ሥላሴ የተሰጠች ቀን”ላም እሳት ወለደች”ሆነና በድርጊቱ እንዳፈርኩበት*ኃይሌም አለቀሰ*ብዬ ያወጣኋት ግጥም የነበረኝን ቅሬታ ለመግለፅ ሲሆን:-ከዛሬ ነገ ሐቁ ይወጣል ስንል ለታሪክ ምሥክርነቱ ይኸው በጀግናው አበበ ገላው መድፉ ተተኮሰ::
  ነገሩም ሐቅ ስለሆነ ከኃይሌ ገብረ-ሥላሴ እኔም የግልፅ ደብዳቤ ምላሹን ላነብ እወዳለሁ::ይህ ካልሆነ ክብር ለማይወድለት እና ሕዝብን ለሚንቅ የሥልጣን ጥመኛ ከሚወረወረው ፍላፃ አይድንም::በጊዜ ጉዳዩን ሳያለባብስ ሕዝቡን ይቅርታ ጠይቆ ግንባር ቀደም ተፀጻች ብልህ እንጂ ብልጥ ሰው ለመሆን እንዳይሞክር:-ምክንያቱም ብዙ ወንጀለኞች(ኣጋዚ “ኮላቦሬተርሶች”)ገና ለይቅርታ ይሰለፋሉና::

  አበበ ገላው ብዕርህ ይባረክ !!!

 2. white Nile

  July 19, 2013 at 3:50 PM

  ማንኛችዉም ሩጫ የሚሮጥ ሰዉ የኢቶፕያ ፕሬዜዛንት ልሁን ካለ አገሪቱ 100 አመት ቀርታአለች ማለት ንው እርግጥ አይሌ መጀመሪያ እራሱን ማወቅ አለበት እሱ እስፖርተኛ እንደመሆኑ መጠን አዲስ አበባ ቦሌ ያውጠዉን የጆኒ ዋከር አደቭርታዝመንት ማየት አለብት ሊትዮፕያ ሃይሌ ምንም ነገር አላደርገም የተወለደብትን አገር ያልረዳ ለኢትዮፓ ፕሪዜዳንት ሊሆን አይችልም እንደሱ ያለ ገንዘብ ወዳጅ ለኢትዮፕያ ፕርዜንድት ቀርቶ ለተወለደብት አገር ከንትባ ሊሆን አይችልም