ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬን ወደ ዝዋይ ሊወስዱት ነው

(ኢ.ኤም.ኤፍ) ከአዲስ አበባ የደረሰን ዜና እንዳመለከተው ከሆነ፤ የቀድሞ አውራምባ ታይምስ ምክትል አዘጋጅ የነበረው እና፤ የኢህአዴግ አስተዳደር በአሸባሪነት ያሰረው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ አሁን ካለበት የቃሊቲ እስር ቤት ወደ ዝዋይ ሊያዛውሩት መሆኑን በተለይ ለኢ.ኤም.ኤፍ የደረሰው ዘገባ አመልክቷል። የዝዋይ እስር ቤት የሚታወቀው እስረኞች የሚንገላቱበት፤ ኢህአዴግም “እናንተን ለመግደል ጥይት አንጨርስም!” በማለት እስረኞች በወባ እና በተስቦ በሽታ እንዲሞቱ የሚደረግበት እስር ቤት መሆኑ ይታወቃል። ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ወደ ዝዋይ የሚወሰድ ከሆነ፤ ቤተሰቡም እንደልብ እየተመላለሰ መጠየቅ የማይችልበት ደረጃ ላይ ይደርሳል።

Ethiopian Journalist arrested

Ethiopian Journalist arrested


በህገ መንግሥቱ መሰረት ማንኛውም እስረኛ ቤተሰቡ ባለበት አካባቢ መታሰር እንዳለበት ተደንግጓል። ከዚህ ቀደም ጋዜጠኛውን በአሸባሪነት መክሰስ ሳያንስ፤ አሁን ደግሞ ህገ መንግስታዊ መብቱ ተጥሶ ባለቤቱ፣ ልጁ እና ቤተሰቡ ካሉበት ዋና ከተማ ርቆ፤ ከአዲስ አበባ 250 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንዲታሰር መደረጉ አግባብ አለመሆኑን የህግ አዋቂዎች ገልጸዋል። ከቤተሰቡ አካባቢ የተላከው አጭር የአደራ መልዕክት እንዲህ የሚል ነው… “የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች እና ሌሎች ሚዲያዎች በጉዳዩ ላይ ትኩረት ሰጥተው አቤት ይበሉልን” ብለዋል።
በሚቀጥሉት ቀናት ሁኔታውን እየተከታተልን የምናቀርብ መሆኑን እንገልጻለን።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 18, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.