ጋዜጠኛ ነብዩና የአንድነት ሊቀመንበር ታሰሩ፤ ሌሎችም ታገቱ፤ ቅስቀሳው በበራሪ ወረቀት እና በሸገር ሬድዮ ቀጥሏል

ጋዜጠኛ ነብዩ ሃይሉ የቀስቃሾቹን እንቅስቃሴ ለመዘገብ በወጣበት ለእስር ተዳርጓል፡፡በካዛንቺስ ፖሊስ ጣብያ ከነብዩ ጋር የአዲስ አበባ የአንድነት ሊቀመንበር ዘካሪያስ የማነብርሃንና ዘላለም ደበበ ይገኙበታል፡፡የጣብያው ኃላፊዎች ‹‹ቤተ መንግስት አካባቢ ቀስቅሳችኋል›› የሚል ውንጀላ አቅርበውባቸዋል፡፡
Nebiyu Hailu
በሌላ በኩል ብሮሸርና ፍላየር የሚያሰራጩ ወደ ቦሌ የተጓዙ አባላት መሳይ ትኩ፣ ማቲዎስ አርጉና አያሌው ዳርምያለውን ጃፓን ኤምባሲ (ጤና ጣቢያው) አካባቢ ባለው ፖሊስ ጣቢያ ታግተዋል፡፡
10
እስራቱ እና እንገልቱ ቢጠናከርም ቅስቀሳው ከጽ/ቤት ተነስቶ በ4ኪሎ አሚሪካ አምባሲ፣ መነን ት/ቤት፣ አፍንጮ በር፣ ፒያሣ፣ ቸርቸር ጎዳና፣ ጥቁር አንበሳ፣ ፍልውሃ፣ ቤተመንግስት፣ ሣሪስ፣ አደይ አበባ፣ ላንቻ፣ ጎተራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ቅስቀሳው ከጽ/ቤት ተነስቶ በ4ኪሎ አሚሪካ አምባሲ፣ መነን ት/ቤት፣ አፍንጮ በር፣ ፒያሣ፣ ቸርቸር ጎዳና፣ ጥቁር አንበሳ፣ ፍልውሃ፣ ቤተመንግስት፣ ሣሪስ፣ አደይ አበባ፣ ላንቻ፣ ጎተራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ የአዲስ አበባ ነዋሪም እሁድ እንወጣለን አይዟችሁ በርቱ በማለት ቀስቃሾቹን እያበረታቱ ሲሆን በተለይ መርካቶዎች ዛሬ ሰልፉን ጀመሩ በማለት የሕዝቡ የከፋ እሮሮ በማሰማት በጩሀት እየገለጹ ነው፡፡

ፖሊስ በመኪና፣ወረቀት በመበተንና ፖስተር በመለጠፍ መቀስቀስ አይቻልም በማለት እስር ይፈጽማል፡፡ቀዳዳዎቹን በሙሉ በመጠቀም አዲስ አበቤን ድምጽህን አሰማ የሚለው አንድነት በሸገር ኤፍ ኢም 102.1 ሬዲዮ ጣቢያ ማስታወቂያ እንዲነገርለት ተገቢውን ክፍያ በመፈጸም የመጀመሪያው ጥሪ ዛሬ እንዲተላለፍ አስደርጓል፡

ምንጭ፡ አቡጊዳ

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on May 2, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to ጋዜጠኛ ነብዩና የአንድነት ሊቀመንበር ታሰሩ፤ ሌሎችም ታገቱ፤ ቅስቀሳው በበራሪ ወረቀት እና በሸገር ሬድዮ ቀጥሏል

  1. andnet berhane

    May 2, 2014 at 10:49 AM

    ወያኔ ጆሮ የሌለው ከተግባሩ መማር የማይችል በትምክህት በጠመንጃ የሚተማመን የ20ኛው ክፍለ ዘመን ኋላ ቀር አስተሳሰብ ያለው የዓለማችን መሳቂያና መሳለቂያ የሆነ የተኮላሸ የማፍያ ተግባርን ለመመለስ የሚጥር ደካማ ለመሆኑ በተግባሩና ይጥፋት መሪውን ተከትሎ ቆፍሮ ባዘጋጀው በገባበት እያስገባቸው መሆኑን ያላወቁ የዋህነት ሳይሆን ሆድ አደርነት ያጠቃቸው ፍጹም ሕሊና ቢሶች ለመሆናቸው ራሳቸውን መመርመር ያልቻሉ በወገንና ቤተሰቦቻቸው ያለውን በነሱም ጭምር ያለውን የኑሮ ውድነት አይናቸውን ጨፍነው በተሰጣቸው እርካን ብቻ የሚኩራሩ የነገ ተጠይቂዎች ለመሆናቸው ፍጹም ያላስተዋሉ የዚህ ጨቋኝ አስተዳደር ወድቆ ትንሳኤ ኢትዮጵያም እንደሚሆን ተሳናቸው በጸጥታ በፖሊስ በሃገርመከላከያ በተለያዩ የመንግስት መስሪያበቶች ካድሬዎች በንጹሃን ዜጎች የሚደርሰው እስራት እንግልት ግድያ ኃላፊነት ተጠያቂነታችሁን በመዘንጋት በስልጣን ለተቀመጡ ለሃገር ሸክሞች እንጂ ሃገርና ሕዝባችሁን ላማገልገል እንዳልሆን ላላፉት 22ዓመታት ታይተዋል አሁንም የእሬታ ቀን እናንተንም ጨምሮ የሚጠየቅ ጥያቄ በመሆኑ ለህሊናችሁ በመገዛት ከወገን በመቀላቀል ግዴታችሁን መወጣት የታሰሩትን ንጹሃን ዜጎች መፍታትና የሕዝብን ፍላጎትና ጥያቄ ተገቢው መልስ እንዲያገኝ ማድረግ ይጠበቅባችኋል፡ ኢትዮጵያ የሁሉም ኢትዮጵያውያን እንጂ በጎጥ ከፋፍለው በሃገር ሃብት ለሚፍነሸነሹ ሙሰኞች ጎጠኞች እንዳልሆነች መረዳት እናንተም እኩል ሃገራዊ ጥቅም ተካፋይነታችሁን አይምሮ በማስፋት አይንና ጆሮቻችሁን በማንቃት ተከታዮች ብቻ ሳይሆን አስከታዮች ለመሆን ያላነሰ እውቀትና ችሎታ እንዳላችሁ በብቃት ማሳየትና የሃገርንና የሕዝብና ለልና የማረጋገጥ የተሸከማችሁት ነፍጥ ሃገርና ሕዝብን ለመከላከል ስላምና መረጋጋት ለማስፈን እንጂ ዜጎችን ለመግደልና ለማፈን እንድል ሆነ ራቅ ሳትሉ ማየት የሚገባችሁ እናት አባት እሕትና ወንድም አክስትና አጎት ያላችሁ እንጂ ከግንድ (ከምንም) የመጣችሁ እንድልሆነ በማጤን ህሊናችሁን መርምሩ