ገዳዩ ሞቶ ተገኘ (ማንነቱ እያነጋገረ ነው!)

(ኢ.ኤም.ኤፍ) ከትላንት በስትያ፤ ምሽት ላይ ከ12 ሰዎች በላይ የገደለው የፌዴራል ፖሊስ አባል አባይ ወንዝ ውስጥ ሞቶ ተገኝቷል። የፖሊሱ ማንነት በውል ባይታወቅም በባህር ዳር ከተማ በሰፊው እየተነገረ ያለው፤ ግለሰቡ የህወሃት አባል እንደሆነና ድርጊቱን የፈጸመው፤ ሆን ብሎ በአማራ ህዝብ ላይ ያለውን ጥላቻ ለመግለጽ ነው፤ የሚለው ወሬ በሰፊው እየተናፈሰ ይገኛል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በፌዴራል ፖሊስ ሰበብ በከተማው በሚገኙት የሌላ ብሄር ተወላጆች ላይ ህዝቡ ቁጣውን እየገለጸ ነው። ይህንን የህዝብ ስሜት ለማብረድ እና ለማባበል በሚመስል መልኩም የፌዴራል ፖሊስ በተደጋጋሚ ይቅርታ እየጠየቀ ነው።

ገዳዩ የፌዴራል ፖሊስ ከአባይ ወንዝ ውስጥ ሞቶ ተገኝቷል

ገዳዩ የፌዴራል ፖሊስ ከአባይ ወንዝ ውስጥ ሞቶ ተገኝቷል


ከትላንት በስትያ ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ በተፈፀመው ድርጊት ከሞቱት መካከል ሴቶች ፣ ህፃናትና  አዛውንቶች ይገኙበታል ። ከተገደሉት ግለሰቦች መካከልም የሰባቱ የቀብር ስነ ስርዓት በደብረ አባይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን በጋራ  ተፈፅሟል ።
በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ  የተገኙት የአማራ  ክልል  ርእሰ መስተዳድር  አቶ አያሌው ጎበዜ የክልሉ መንግስት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለፅ ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝተዋል ።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን  በበኩሉ በግለሰቡ ድርጊት ህይወታቸውን ባጡ ዜጎች  ህልፈት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል ፡፡

በእንዲዚህ አይነቱ  ወንጀልም በህብረተሰቡና በፖሊስ መካከል ለዓመታት የቆየው መልካም ግንኙነትም አይሻክርም ብሏል በመግለጫው፡፡

የፖሊስነት ሙያዊ ዲስፕሊን  በጎደላቸው መሰል ፖሊሶችም ይህ አይነት ክስተት ደግም እንዳይፈጠር ጥረት እንደሚያደርግ ገልጿል። ይህ ሁሉ የፌዴራል ፖሊስ ልመና ግን ለህዝቡ እምብዛም የተዋጠለት አይመስልም። ይልቁንም ሰሞኑን በህወሃት ውስጥ የተፈጠረው ሽኩቻ ያበሳጨው ሰው መሆኑ ነው በሰፊው የሚወራው። ፖሊስም ይህንን የህዝቡን ቁጣ ላለማባባስ ሲል፤ የገዳዩን ስም እና ማንነት ከመግለጽ ተቆጥቧል፡፡

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on May 14, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

4 Responses to ገዳዩ ሞቶ ተገኘ (ማንነቱ እያነጋገረ ነው!)

 1. Kassa

  May 14, 2013 at 11:40 AM

  The so called political writer do not understand what is happening in the real world. They are day-dreamers, filled with illusion. The blood of 2.75 million Amharas disappeared through the hidden genocide and still counting more shall not be forgotten and be stopped immediately.

 2. አባ ጦብያ

  May 14, 2013 at 5:04 PM

  የኢሕአድግ ቃጥራዎችን ገድሎ የሞተ ይመስለኛል.

 3. dubale

  May 15, 2013 at 5:47 AM

  ዝም ብለህ አታካብድ ባከህ ሹጣም!! በግፍ ለተጨፈጨፉት ወገኖች ከማዘን ይልቅ ተራ ለሆነ የውንብድና ስራ አቃቂር ለማውጣት ትሞክራለህ? እኔ እንደው ምን የሚሉት ልክፍት ነው?? ፖሊቲካ ጊዜ እና ሰአት አለው. አንተ ራስህ በዛ ቦታ አርገህ እስኪ አስበው ምን ያህል እንደሚዘገንን:: ለነገሩ መሃይም ነህ ምኑም አይገባህ:: አመሪካ ባለፈው በአንድ ትምህርትቤት ጭፍጨፋ ነበረ….ፖሊትከኞችም ህዝቡም ሰዎችን ለመርዳት ሲራራጡ ነበረ…ስለ ወደፊት ተመሳሳይ ወንጀል እንዴት ማስቀረት እንደሚቻል በጣም ብዙ debate ነበረ:: አንተ ቁጭ ብለህ ምንም ዉሃ የማይቁጥር ትዘላብዳለህ:: እንደው ሃበሻ ምን ድግምት ተዶርጎብን ይሆን?
  ፈታሪ ይቅር ይበለህ ጮማ ራስ!

 4. አንድነት በርሃነ

  May 17, 2013 at 10:01 PM

  ዱባለ እውነትም ጥሩ ስም መርጠዃል የምትጠቀምባቸውን ቃላቶች በውነቱ ታስተውላለህ “አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል” ይባላል በእውነት ሕሊና የሚባል የፈጠረብህ አትመስልም አዋቂ አዋቂነኝ አይልም አላዋቂን አታውቅም የሚል ከሆን እሱ ነቱን አያውቅም ማለት ነው:: አሜሪካ ውስጥ የሚፈጸሙት ወንጀሎች ይሁን ግድያዎች በዘርና በጎጠኝነት የሚፈጸም ስላልሆነ መነሻዎቹም ከሚደርስበት የኑሮ ጫና ያይምሮ ሕመም በሕክምና የተረጋገጠ በመሆኑ ያንተ አዋቂነት እሚታየው እዚህ ላይ ነው አንተ ማነህና አዮ አበሻ ብለህ የምትዘብት ለመሆኑ ፖለቲካ ማለት ወገንተኛነት ሆዳምነት ሳይሆን በጭፍን መፍረድና ያለውን አሳፋሪና ዘግናኝ ግድያ ደጋፊ በመሆን የሰዎችን ነጻ አስተያየት ማንቛሸሽ አዋቂነት እንድልሆነና ሆድ አደርና እበላ ባይነት ሁልግዚ እይታቸው የሚታወቅባቸው የተደረገውን ለምን በዝምታ አይታለፍም ለማለት ይሞክራሉ: ውይይት እሚባለው በመልካምና ቅንነት ባለው መንግስትና ሕዝብ መካከል እንጂ በሕዝብ ጫንቃ ለተቀመጠ እምባገነኖችና በጭፍን ደጋፊዎች ስር ባለ ሳይሆን ቀኑ ቢረዝም እውነቱ ማንነቱ ስለሚገለጥ ወንድመእ በድህረ ጋጻችን ገብተህ ያልታረመ ቃላትና አስጽያፊ ስድብ ለዚህ አፍህ ሉግውም አብጅለት የሰፋ ሀሳብና ራስክን በመተማመን ያለህን አስተያየት በጭዋነት ማስፈር እንጂ የውያኔን አጀንዳና እኩይ ተግባር ተቀባይነት የለውም