«ገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን» ምንድን ነው?

«በሰላም ተሳስራችሁ ከመንፈስ ቅዱስ የሚገኘውን ለመጠበቅ ትጉ። በተጠራችሁ ጊዜ ለአንድ ተስፋ እንደተጠራችሁ ሁሉ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ። እንዲሁም አንድ ጌታ አንድ እምነት እና አንድ ጥምቀት አለ። ደግሞም ከሁሉ በላይ የሆነ በሁሉም የሚሠራ፤ በሁሉም የሚኖር የሁሉም አባት የሆነ አንድ አምላክ አለ።» ኤፌ4፤3-7

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በዘመናችን የደረሰባት የመለያየት እና የመከፋፈል ዘመን፤ አንዱ ሌላውን ለማጥቃት ቀን ቆርጦ፣ቦታ መርጦ፣ ዘገር ነቅንቆ፣ ጦር ሰብቆ፣ ዝናር ታጥቆ፤ነፍጥ ቀስሮ ወረድ እንውረድ ተባብሎ በጦር መሳሪያ መዋጋት እና በሀገር፣ በሰው ኃይል፣ በማህበራዊ ግኑኝነትና ማህበራዊ ኑሮ፣በኢኮኖሚ ጥፋት ሀገሪቱን ከአንድነት ወደ መበታተን፣ ከማዕከላዊ የንጉሳዊ አስተዳደር የክፍፍሎሽ ሰለባ በማደረግ እድገትዋን እና ሥልጣኔዋን አንቆ ይዞ ለሰባ ስምንት ዓመታት ሲያንገላታት የቆየውን የዘመነ መሳፍንት ታሪካዊ የጥፋት ክስተት ወይም አገዛዝ ጋር የሚዛመድ ነው። Read the story in PDF: «ገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን»….

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on December 4, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

9 Responses to «ገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን» ምንድን ነው?

 1. Belachew Aredo

  December 6, 2013 at 10:05 PM

  መ?ጥ መንገሻ መልኬ በገለልተኛነት አርፈዉ የተቀመጡትን የቤተክርስቲያ አገልጋዮችንና ምአመናንን ተሳድበዋል፥፥
  ይህ መከፋፊል እንዴት እደተከሰተ በቂ ጥናት ሳያደርጉ ያወረዱት ስድብ ያለአፈሳጊና ሌላ አጀንዳ እንዳለዎት ያመላካታል፥፥
  ሃይኖታችንን የወረስነው ክቤተቦቻችን እንጂ ከርስዎ ዓይነቱ ተሳዳቢ አይደለም ከበረቱ ቤተክርስቲያን የማይደሱትን ወገንዎች እንዲመጡ ያስተምሩ፥፥
  የቅዱስ ሴኖዶስ ሕግ በተከበረ ጊዜ ሁሉም አንድ ይሆናል፥፥
  እግዚአብሔር ይመስገን ነፃ ሐገር ነዉ የምንኖረዉና የማንም ደብተራ አፍ መክፈቻ አንሆንም፥፥ የወያኔው ሚሊዮሮቹ ጳጳሳትም ሥራቸዉን እደዘነጉት ምነዉ አልተቿቸዉም? ወደማን እንዳዘበሉም ገብቶኛል፥፥ ንቃተ ሕሊናችን ከፍ ያለ ስለሆነ በስድብ ጋጋታ አንሸበርም፥፥ የኢትዮዽን ቤተክርስቲያን እግዚአብሔ ይጠብቃት ሞት ለነጋዴ ዻዻሳትና ካህናት፥(ሆቴልና ፎቅ ቤትዎች አከራይዎች )

 2. Megabi Tibebe

  December 7, 2013 at 6:50 AM

  ለውድ ወንድሜ/ እህቴ
  ስለ አስተያየቱ አመሰግናለሁ ሚዲያ ሁሉንም አስተሳሰብ በእኩልነት እንዳለብት ሁሉ የመሰለወትን መናገረዎ መልካም ነው። ነገር ግን ሀገሩ ነጻ ሀገር ነው ተብሎ ልጓም የሌለው ፈረስ ሆኖ እንደፈለጉ መጋለብ አይቻልም፤ አዎን! የሚያጠፉ ሰዎችን የቤተ ክርስቲያን ሕግን የሚጥሱ ሰዎችን መገሰጽ የመጽሐፍ ትእዛዝ ነው። ሰዎችን መበደል ግን አግባብ አይደለም። «ተቆጡ ፈጽማችሁ ግን አትበድሉ» ገለልተኞች ሊወቀሱ ሊገሰጹ የሚገባ አፈንጋጮች ናችው። ምክንያቱም የቤተ ክርስቲያን ሕግን ጥሰዋልና።
  ሃይማኖት ምርጫ ሁሉት ብቻ ናቸው። እነሱም እሳትና ውሃ ወይም ጽድቅና ኩነኔ በመሆኑም መጽሕፍ ቅዱስን አጥንቶ፣ሊቃውንትን ጥይቆ፣ሕገ ቤተክርስቲያንን መርምሮ የሚያዋጣውን መንገድ መምረጥ የአምኙ/የካህኑ ምርጫ ነው። አቅረብኩ ለከ እሳት ወማየ እ ዴከ ሀበ ዘፈቀድከ እሳት እና ውሃ አቀረብኩላችሁ እጃችሁን ከፈለጋችሁት ስደዱ። በማለት መጽሐፍ ይመክረናል ስለሆነም የዘመን እና የታሪክ ባለዕዳወች በመሆናችን በእኛ ዘመን አንድዋ ቤተ ክርስቲያን ለሁለት ተከፍላለች የተከፈለችውም በቤተ ክርስቲያንዋ የመጨራሻው አካላት በቅዱስ ሲኖዶስ አማካኝነት ነው። ቅዱስ ሲኖዶስ በእኔና በእርሰዎ ፈቃድ የሚመራ ሳይሆን በመንፈ ስቅዱስ ፈቃድ የሚመራ ነው ብለን እናምናለን። አባላቱም ብጹአን ናቸው ብለን እንረዳለጅን። እዚህ ላይ ግለሰባዊ የግል ታሪክ ውስጥ አልገባም መግባትም አያስፈለገኝም። ሕጉን ብቻ።
  ክህነት የሚሰጡ እነሱ ናቸው፣ ጽላት የሚባርኩ እነሱ ናቸው፣ ሕግ የሚያወጡ እነሱ ናቸው። እነሱ ለሁለት ሲከፈሉ ከሁለት አንዱ ትክክል ነው ወይም ከሁለት አንዱ ተሳስትዋል። ስለዚህ ህሊና ያለን ሰዎች በመሆናችን ከሁለቱ አንዱን መምረጥ ተገቢ ነው።ገለልተኛ መሆን ወይም ከሁለቱም የወጣ «ፕሮቴስት» ማድረግ መስመሩን የለቀቀ ነው። ግለሰባዊ አስተሳሰብ ነው። ክህነቱን እና ጽላቱን ከቅዱስ ሲኖዶስ የተቀብሉ ከዳተኞችና ጥቅመኞች ካህናት « ገለልተኛ» ነኝ ብለው እራሳቸውን ማደራጀት ከተዋህዶ እምነት የወጣ ነው።

  አግዚያብሔር የስጥልኝ
  መ/ጥ መንገሻ
  ሎንደን

 3. Megabi Tibebe

  December 7, 2013 at 8:38 PM

  ለውድ ወንድሜ በላቸው፤

  ስለ አስተያየቱ አመሰግናለሁ ሚዲያ ሁሉንም አስተሳሰብ በእኩልነት ማስተናገድ እንዳለብት ሁሉ የመሰለወትን መናገረዎ መልካም ነው።

  ነገር ግን ሀገሩ ነጻ ሀገር ነው ተብሎ ልጓም የሌለው ፈረስ ሆኖ እንደፈለጉ መጋለብ አይቻልም።አዎን! የሚያጠፉ ሰዎችን የቤተ ክርስቲያን ሕግን የሚጥሱ ሰዎችን መገሰጽ የመጽሐፍ ትእዛዝ ነው። ሰዎችን መበደል ግን አግባብ አይደለም። «ተቆጡ ፈጽማችሁ ግን አትበድሉ» ገለልተኞች ሊወቀሱ ሊገሰጹ የሚገባ አፈንጋጮች ናችው። ምክንያቱም የቤተ ክርስቲያን ሕግን ጥሰዋልና።

  ሃይማኖት ምርጫ ሁሉት ብቻ ናቸው። እነሱም እሳትና ውሃ ወይም ጽድቅና ኩነኔ በመሆኑም መጽሕፍ ቅዱስን አጥንቶ፣ሊቃውንትን ጥይቆ፣ሕገ ቤተክርስቲያንን መርምሮ የሚያዋጣውን መንገድ መምረጥ የአምኙ/የካህኑ ምርጫ ነው።

  «አቅረብኩ ለከ እሳት ወማየ ደእዴከ ሀበ ዘፈቀድከ» እሳት እና ውሃ አቀረብኩላችሁ እጃችሁን ከፈለጋችሁት ስደዱ። በማለት መጽሐፍ ይመክረናል ስለሆነም የዘመን እና የታሪክ ባለዕዳወች በመሆናችን በእኛ ዘመን አንድዋ ቤተ ክርስቲያን ለሁለት ተከፍላለች የተከፈለችውም በቤተ ክርስቲያንዋ የመጨራሻው አካላት በቅዱስ ሲኖዶስ አማካኝነት ነው። ቅዱስ ሲኖዶስ በእኔና በእርሰዎ ፈቃድ የሚመራ ሳይሆን በመንፈ ስቅዱስ ፈቃድ የሚመራ ነው ብለን እናምናለን። አባላቱም ብጹአን ናቸው ብለን እንረዳለን።

  እዚህ ላይ ግለሰባዊ የግል ታሪክ ውስጥ አልገባም መግባትም አያስፈለገኝም። ሕጉን ብቻ ማየት ግዴታ ነው። ተገዥነታችን ለሕግ ነው እንጂ ለግለሰብ አደለም።

  ክህነት የሚሰጡ እነሱ ናቸው፣ ጽላት የሚባርኩ እነሱ ናቸው፣ ሕግ የሚያወጡ እነሱ ናቸው። እነሱ ለሁለት ሲከፈሉ ከሁለት አንዱ ትክክል ነው ወይም ከሁለት አንዱ ተሳስትዋል።
  ስለዚህ ህሊና ያለን ሰዎች በመሆናችን ከሁለቱ አንዱን ትክክለኛ ነው ብለን ያመንበትን መምረጥ ተገቢ ነው።«ገለልተኛ» መሆን ወይም ከሁለቱም የወጣ «ፕሮቴስት» ማድረግ መስመሩን የለቀቀ ነው። ግለሰባዊ አስተሳሰብ ነው። ክህነቱን እና ጽላቱን ከቅዱስ ሲኖዶስ የተቀብሉ ከዳተኞችና ጥቅመኞች ካህናት « ገለልተኛ» ነኝ ብለው እራሳቸውን ማደራጀት ከተዋህዶ እምነት የወጣ ነው።ጽሁፉ ገለልተኛ ቤተ ክርስቲያንን ለመተቸት ከበቂ በላይ ነው ካስፈለገ የበለጠ መጽሐፍ ቅድይሳዊ መረጃ መስጠት ይቻላል።

  እግዚአብሔር ይስጥልኝ

  መ/ጥ መንገሻ መልኬ
  ሎንደን

 4. በላችው አረዶ

  December 7, 2013 at 11:16 PM

  የማክበር ሰላምታዬ ይድረስዎ
  የመጣንበት ሕብረተሰብና አስተዳደግ ሆነና ነው እንጂ አሁኅም ሰዉ ያመነበትን ሀሳብ መስጠት ልጏም የሌለው ፈረስ አያስብለውም የሚኖሩበት ሃገር ለዚህ ምስክር ነው፥ሰው የመሰለውን መናገር ይችላል።
  ቤተክርስቲናችን እረኞች ካጣች ዓመታት ተቆጥረዋል ቤተክርስቲያናችንን ያፈረሱት እናስተዳድራታለን የሚሉት ነጋዴዎቹ ዻዻሳትና ካህናት መሆናቹው በግልጽ እየታየ ከነዚህ ጋር ከመጨማለቅ እግዚአብሔር እዉነተኛ እረኛ እስከሚሠጠን በገለልተኛነት እንቆይ ማለት ምንም ችግር የለውም፤ እደጌቶቻቸው (የራሳቸዉን ሕገ መንግስት እደማያከብሩት) የሴኖዱሱን ሕግ የሚጥሱት ዻዻሳቱ ናቹው። እርስዎ ፈርተዋቸዉም እንደሆነ አላቅዉም አልወቅስዋቸውም።
  ጳጳሳት እና ካሕናት እግዚአብሔር ፊት እኩል ናቸወ፣ እደመግሥት መዋቅር ፓትራያርክ፣ ዻዻስ ተብለዉ ቢሾሙ ቤቱን የሙስናና ለግል መበልጸጊያ አደረጉት
  ደሕን ሁሉ እያዪ አህያዉን ፈርቶ እንዳሆንብዎት አላለሁ፣
  አመሰግናሁ።

 5. tazabi

  December 8, 2013 at 4:19 PM

  over all any religious institution in Ethiopia or abroad is run by bible holding sharks….none of them can be trusted anymore.

 6. terunesh seyoum

  December 9, 2013 at 3:32 AM

  It is a little exagruated there is no yeshewa yegonder church in the states that is really a big lie …correction pls. As we know most ppl dont accept the tplf popes who work depeding on tplf and tribe and we already have a pope who isnot yet dead He has to be placed in his place that is all …u dont need to lie saying geleltgna church is amhara wollo gonder church menamen which is a big lie stop it we dont want the dead pope aba paulos so aba mathias who are from tigre tribe these ppl work only for tplf they have less to do with the orothdox church .I want to say someting to daniel kiberet who is tplf cadre who says the california pope and all those who are outside of ethiopia orthdox church ppl are tehadeso pente that is lie stop it daniel newer new mewashet asertu hig lay atewash yelal pls keep the commandemnts .tx

 7. Megabi Tibebe

  December 9, 2013 at 6:28 AM

  ወንድም በላቸው

  በድጋሜ ምስጋናየ ይድረሰዎ!

  አሁን እየተነጋገርን ያለነው ስለሕጉ ነው። ስለ ግለሰቦች አይደለም፤ ከማህበረ መልአክት ሳጥናኤል ተሳሳተ ከአንድነት ማህበሩ ተለየ፤ ይሁዳ ተሳሳተ ከማህበረ ሐዋርያት ተለየ፤ አሪወስ ተሳሳተ ከማህበረ ሊቃውንት ተለየ። የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደሚያስረዳን ገለልተኛ ነኝ ብለው የተለዩት በሙሉ የተሳሳቱት ናቸው።

  እዚህ ላይ ያስተውሉ መክፈል እና «ገለልተኛ» መሆን የተለዩ ናቸው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ካህን፣ምዕመን፣ ክርስቲያን እና ኢትዮጵያዊ ሆኖ ከቤተ ክርስቲያን ጉዳይ አያገባኝም «ገለልተኛ ነኝ» ማለት ቅጥፈት ነው።

  ከውስጥ ሆኖ የተበላሸውን ሕግ ማስተካከል አጥፊውን አጋልጦ በማውጣት ያልተማረውን ማስተማር ማሳወቅ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ማስከበር የቤተ ክርስቲያንን ሐብት መጠበቅ ብልህነት ነው። ተለይቶ ወጥቶ ምንም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እርሾ የሌላቸውን ሰብስቦ በመካከላችው ያአማረ ቀሚስ ለብሶ በመንዘራፈፍ ያልነብረ፣ የሌለ፣ የማይታወቅ ሕግን ማወጣት «ገለልተኛነኝ» ከሌሎቹ በእምነት ላይ ክህደት ከፈጽሙት አማጽያን ተለይቶ አይታይም።

  «ገለልተኛ» በመሆን እራስን ብቻ ማዳንና መነገድ የሚቻል ቢሆንማ ኖሮ ነብያት፣ ሐዋርያት እና ቅዱሳን ሰማዕታት በሙሉ እንደ ሽንኩርት ባልተላጡ፣ እንደከብት በስለት ባልታረዱ፣ እንደጥዋፍ በእሳት ባልነደዱ ፤ እኛም ቅዱስ ብለን ባልተቀበልናቸው። እንደ አማሩ ገለልተኛ ሆነው በሞቱ ነበር። «ገለልተኛ» መሆን ቀላልና የደካሞች ሥራ ነው። ያለን የነበረን በአንድነት መጠበቅ አማኝነትን እና ታማኝነትን ፤ ጥንካሬን እና አዋቂነትን የሚጠይቅ መስዋትነት ነው።

  «ገለልተኛ» ሆኖ መነገድ ቀላልና ያአማረ ነው። ነገር ግን ሃይማኖታዊ መሰረትነት የለውም፣ ይልቁንም ግለሰባዊ ጥቅመኝነት ነው። ሊቃነ ጳጳሳት ሰዎች ናቸው ያጠፋሉ፡ የቤተ ክርስቲያን ሕግ ግን የግላቸው አይደለም የቤተ ክርስቲያን ሆኖ ነው የኖረው እንደዚሁ ይቀጥላል።

  «ገለልተኞች» የተጣሉት ከቤተ ክርስቲያን ሕግና ከሃይማኖታዊ መንፈሳዊ አወቃቀር እንጅ ከግለሰቦች ጋር አይደለም። የእኔ ጽሑፍ ደግሞ ከቤተ ክርስቲያን ሕግ አንጻር የሚደረሰውን ጥፋት መጠቆም ነው።

  ጳጳሳትም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ገለልተኞች የየራሳቸው ያአማረ ፊታውራሪ እንዲኖራቸው አስተዋጻኦ እንዳደረጉ ጽሁፌን ደግመው በማንበብ ይበልጥ ይረዱት።

  «ገለልተኖች ካህናት» ክህነት የሰጣቸው ቅዱስ ሲኖዶስ ነው። ጽላት ባርኮ የሰጣቸው ቅዱስ ሲኖዶስ ነው። የቤተ ክርስቲያን አደራ ጠባቂወች ናቸው እንጅ አደራ የሰጣቸውን ቅዱስ ሲኖዶስ ክደው «ገለልተኛ» ሆነው ሸፍተው ያአማረ ትልቅ ደመወዝ እያገኙ የገለልተኛ ሐዋርያ መሆን አይቻሉም። ቅዱስ ሲኖዶስ ካልሰነፈ በስተቀር የሰጠውን ክህነትና ጽላት ከአደራ በላተኞችና ከዳተኞች «ገለልተኞች» መለሶ የመቀማት ሃይማኖታዊ ሥልጣን አለው።

  ቀጣዩ የእኔ ሥራ ይኸው ነው ጳጳሳት በውስጥም ሆነ በውጭ ያሉት የጋራ በሚያደርጋቸው ሀይማኖታዊ ክፍፈሎሽን «ገለልተኛን» የአንድነት ጠላት ከዳተኛ በሕብረት ማውገዝ አለባቸው። የሰጡትን ክህነትና ንዋየ ቅደሳት ከገለልተኛ ሽፍታ መቀማት እና ወደ ሕጋዊ ባለቤቱ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መመለስ መንፈሳዊ ግዴታ ነው።

  ቸር ይግጠመን

  መ/ጥ መንገሻ መልኬ

  ሎንደን

 8. Mt.Mengesha

  December 9, 2013 at 6:36 AM

  • Belachew Aredo

   December 10, 2013 at 2:11 AM

   አሁንም የማክበር ሰላታዬ ይደረሰዎ እያልኩ የሚቀጠልው ሥራዎ ገለልተኛ ቤተክርስቲያኖች ለማሳደድ ነውና ይሞክሩት።
   አዲሱ ፓትርያክም ይህን እንዳሉ ይነገራል፣ የተማከራችሁም ይመስላል። እስላሞች ወገኖቻችንን ይመልከቱ ያልመረጥነው ካድሬ አያስተዳድረንም ብለው ነው አስር ቤት ገብተው መስዋትነት እየከፈሉ ያሉት። የቅዱስ ሲኖዶስን ሕግ አፍርሰዉ የተሾሙትን የካቢኔ አባል አይነቱን ባትሪያሪክ ያልተቀበለ ወዎልህ ነው የሚሉት በጣም የሚያሣዝን ነው፣ ሚስማር ሲመታ ይጠብቃል ኢንዲሉ ታጥቀን እንጠብቅዎታለንና ብቅ ይበሉ። እግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይግባዉና በነፃ ሀገር ስለምንኖር የርስዎ ፉከራ ወንዝ ኣይሻገርም።
   ደህና ይሁኑ።