ጄኔራል ፃድቃን፣ ኢሕአዴግና የሰሜን አፍሪካ አብዮት (ክፍል ሁለት)

እስክንድር ነጋ (አዲስ አበባ)

መግቢያ፦ ”ሻይ፤ በሎሚ፣ ያለስኳር” አልዃት፤ ትዕዛዝ ልትቀበለኝ ፊት ለፊቴ የቆመችውን ወጣት። ትላንት፤ ሰኞ፣ የካቲት 28 ቀን 2003 ዓ.ም፤ ከጠዋቱ 2 ሰዓት። ኢንተርኔት ካፌ እስከሚከፈት ሚጢጢ ሻይ ቤት ውስጥ ቁጭ ብያለኹ። በእጄ “OBAMAS” የሚ+ለውን ቢጫ እስክሪቢቶ ይዣለኹ። ጠረጴዛ ላይ ወረቀት አስፍሬያለኹ። የጀኔራል ፃድቃንን ክፍል ሁለት መጣጥፍ ለመጀመር እያቅማማኹ ነው። ቴሌቪዥኑ ትኩረቴን እየተሻማው ነው። የኒክ ኒልቴ የድሮ ፊልም በዐረብ ሳት እየተላለፈ ነው። ፊት ለፊቴ ሶስት ሰዎች ሞቅ ያለ ጨዋታ ይዘዋል። አንዱ ሽበት ጣል ጣል አድርጎባቸዋል። ሁለቱ ወጣቶች ናቸው። [Read on PDF]

”ዜና ላይ አድርጊው …” አለ ወጣቱ ወደ ባሬስታዋ ዞር ብሎ።
ባሬስታ ሆና የምትሰራው የሻይ ቤቷ ባለቤት ናት። ከደንበኞቿ ጋር ትግባባለች። ”ለምን? …”።
”ስለማንቼ ጨዋታ ይኖራል …” አላመነታችም። ሪሞቱን ብድግ አድርጋ ኢቲቪ ላይ አደረገችው።
”ዜና” የሚለው ምስል ብልጭ አለ። ዓይኔን ቶሎ ከቴሌቭዥኑ ላይ ነቀልኹ። አሁን ትኩረቴ ሳይሰረቅ መፃፍ ልጀምር ነው። እስከ ግማሽ ቀን ሁሉን ነገር መጨረስ አለብኝ።
“ጋዳፊ ወረደ እንዴ?” ብላ ባሬስታዋ ስትጠይቅ ቀና አልኩኝ። Read on PDF

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on March 9, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.