ድንገት ካመጽን፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚነሳው አመጽ፡ የቅድመ-ጥንቃቄ ምክሮች፤

ባይሆንም፤ ባይሳካም በ66ቱ አብዮት “ያለምንም ደም ኢትዮጵያ ትቅደም” እንደተባለው፡ በኛም ዘመን፡ እነዚህ የሕወሀት/ኢህአዴግ ሀይሎች፡ ያለምንም ደም ለውጥ የሚያመጡበት መንገድ ቢፈጠር ምኞቴ ነው። ነገር ግን ስለተመኘን ብቻ የሚሆን ነገር የለም። ከልምድ እንዳየነው፤ እንደ ልምድ ደግሞ ጥሩ ድግሪ የለም፤ ያለምንም ደም የሚሆን ነገር ያለ አይመስልም። እነሆ ሊነሳ ለሚችል አመጽና ሰፊ የሕዝብ እንቅስቃሴ ያገለግል ዘንድ፡ ከኛ ኢትዮጵያ በኔ አጭር እድሜ ካየሁት፤ ሰሞኑን ደግሞ ሁላችሁም እንደምትታዘቡት በዓረቡ ዓለም ከሚፈጠረው ተነስቼ፡ አንዳንድ ጠቃሚ የአመጽ ምክሮችን ልለግስ ወደድኩ።ምክር ቁጥር አንድ፡- አመጽ ቢነሳም ባይነሳም ሚዲያ ቁልፍ ነው። ርስ በርስ የምንግባባበት፡ ከውጭው ዓለምም ጋር የምንገናኝበት፡ አስተማማኝ የሚዲያ ተቋም የለንም። ስለዚህ በኢትዮጵያ፡ በአዲስ አበባ፡ በናዝሬት፡ በባህርዳር፡ በአዋሳ፡ አመጽ ከተነሳ፡ በምንም መልኩ በተለምዶ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ወይንም የኢትዮጵያ ሬድዮ የሚባለውን መገናኛ ብዙሀን ወሬ አትመኑ።

ትልቅ የአምባገነኖች አመጽ ማክሸፊያ ዘዴ ህዝብን የሚከፋፍልና የሚያጋጭ እንዲሁም የሚያዘናጋ ሀሰተኛ ወሬ መንዛት ነው።[1] ስለዚህ በምንም መልኩ የሚያዘናጋ፣ የሚከፋፍል፣ ጥርጣሬን የሚፈጥር የ”አገዛዙን” ወሬ እንዳናምን። ይልቅስ ሁልጊዜም ምክር ቁጥር ሁለትን እናስብ።ምክር ቁጥር ሁለት፡- ከዚህ በኋላ የሚነሳው አመጽ መንግስትን ለመጣል፣ ፖለቲካዊ ለውጥ ለማምጣትና በምንም መልኩ የተነሳንበት ጥያቄ ግብ ካልመታ ወደ ቤት ላለመመለስ ተቆርጦ መሆን አለበት። በዚህ ባሳለፍነው 20 አመት ውስጥ፡ በኢትዮጵያ ውስጥ የመንግስት ለውጥ ለማምጣት የተደረገ ሕዝባዊ አመጽ የለም። ብዙዎቹ ህዝባዊ አመጾች ቁጣን ለመግለጽ እንጂ “መለስ ይውረድ፤ ካልወረደ ግን ወደቤት አንገባም” ተብለው የተደረጉ አይደሉም። የሚቀጥለው አመጽ ውጤታማ ሊሆን የሚችልበት ብቸኛ መንገድ የመጨረሻው የጽድቅ መፈክራችን “እንበለ-ውጤት አንገባም ከቤት” (ያለውጤት አንገባም እቤት) ከሆነ ብቻ ነው። ሁሉም ተስማምቶ ሳይከፋፈል እስከመጨረሻው ሊጸና የሚችልበት ግብ የመንግስት ለውጥ ብቻ ነው። መንግስት ሲፈርስ፤ ወደ ቤት መልስ። አከተመ። ስለዚህ በመጀመሪያዎቹ የአመጽ ሰዓታት ወይንም ቀናት የተወሰኑ ሰዎች ቢገደሉ ወይንም ቢታሰሩ ወይንም ቢቆስሉ “እንበለ ውጤት አንገባም ከቤት” በሚለው መርህ መሰረት ምክር ቁጥር 9ን እያሰቡ ወደፊት መግፋት ነው።ምክር ሶስት፡- ማናቸውም የአመጽ እንቅስቃሴ ቀን ቀን ብቻ ቢደረጉ መልካም ነው። ምክንያቱም መንግስት ሊወስዳቸው የሚችላቸውን እርምጃዎች ሁሉ ማወቅና ማየት ይቻላል። የሞተውን የቆሰለውን የታሰረውን የታፈነውመን መቁጠር ይቻላል። ስለሳተላይት ቴክኖሎጂ እውቀቴ ኢምንት ቢሆንም ከሰማይ ለመመልከት፣ ቪዲዮ ለማንሳት፣ ፎቶ ለማንሳት የሚመቸው እንቅስቃሴው ቀን ቀን ቢሆን ነው። ከዚህ ቀደም እንዳየነው፡ ማታ ማታ መንግስት መኪኖችን በግድ እያቀረበ እስረኞችን ወደማጎሪያ ካምፕ ሊያግዝ ይችላል። በተጨማሪም ቀን ቀን ጠላቶቻችንን እናያቸዋለን።

ማን ወሬኛ ነው፣ ማን አቃጣሪ፡ ማን ትግሬ ነው? ማን አማራ፣ ማንስ ኦሮሞ ነው ማንስ ጋምቤላ? የሚለውን ለማወቅም ይረዳናል። ትግሉ የቀን መሆኑ ለኛ ብቻ ሳይሆን ለእግዜርም አመቺ ነው። እግዚአብሄር በጨለማ የሚመላለሱትን አይመለከትም።ምክር አራት፡- በሁሉም አካባቢዎች ተመሳሳይና ተቀራራቢ የትግል ሰዓት ቢታወጅ መልካም ነው። አንድም ጠላትን ለመከፋፈል ይረዳል። ሁለተኛም ህዝቡ የተለያየና የሚጋጭ መረጃ እንዳይኖረው ያደርጋል። ለምሳሌ ከጠዋቱ 9 እስከ 10 ሰዓት ወይንም ከምሳ ሰዓት በፊት ሁሉም ሰው ወደ አደባባይ እንዲወጣ ቢባል መልካም ነው። የታሰረም ታስሮ፣ የሞተም ሞቶ የተረፈው የሚገናኝበትን አንድ ወጥ ሰዓት ቢመርጥ መልካም ነው።ምክር አምስት፡- ወታደሮቹንና ታጣቂዎችን ቢቻል መከፋፈል። ባይቻል ጉዳዩን እንደግል ጥቃት እንዳያዩት ግብግብ አለመግጠም። ከወታደሮች ጋር በሚደረግ ግብግብ በተቻለ መጠን ወታደሮቹን ማርኮ ከጎን ማሰለፍ። የህልውና ጉዳይ ካልሆነና ወታደሮቹን ማጥቃት ብቸኛ መንገድ ካለሆነ በስተቀር በተቻለ መጠን ወታደሮችን አለመንካት።

ሲሆን ሲሆን ማቀፍ፣ ማስጠጋት፣ የኛና የኢትዮጵያ ህዝብ ናችሁ ማለት። ሳይሆንም መማጠን፡ ማስጠንቀቅ። ነገር ግን አለማስቆጣት።ምክር ስድስት፡- የተደገለውን ገድለው አመጹን ለማስቆም ከመሞከር ወደኋላ አይሉም። ይገድላሉ። ምንግዜም ቢሆን ይገድላሉ። ይሄንን አውቀን ነው መግባት ያለብን። ይሄንን ግዜ ትንሽ የተሻለ የሚያደርገው ዓለም ይመለከታል። ቢያንስ ተገድለንም ቢሆን ወደስልጣን ለመምጣት አረቦቹ አሳይተውናልና የአረቦቹን ያህል ሳንገፋ አንዳናቆም ያ ይረዳናል ለማት ነው እንጂ፤ ወደአመጽ ሲገባ ሊገደል የሚችለውን ሰው ቁጥር አውቀን መሆን አለበት።[2]

ምክር ቁጥር ሰባት፡- የምንፈልገው ነገር በግልጽ መታወቅ አለበት። ያም ብቻ አይደለም በተቻለ መጠን የማያጋጭና የማይከፋፍለን መሆን አለበት። ለምሳሌ አንቀጽ 39 ይወገድ ከምንል የሽግግር መንግስት ይቋቋም ብንል ይሻልል። የሚሰማኝ አጣሁ እንጂ አንዳንድ ሰፊ የህብረተሰብ ክፍሎች ከሕወሀት ኢህአድግ የማይናቅ ሰፊ ለውጥ አግኝተዋልና፡ ይሄንን ስርአት ለመጠበቅ እስከሞት ሁሉ ሊሄዱ ስለሚችሉ እነሱ ያገኙትን ለውጥ የሚነጥቅ አመጽ እንዳልሆነ ማስመስከር እንዲሁም ማረጋገጥ አለብን። ስለዚህ ስርአቱ፡ በተለይ በአናሳና ተበደልናል በሚሉ ብሄረሰቦች ዘንድ የሚያስከብረውን ነገር በምንም መልኩ እንቀለብሳለን ብለን መናገር የለብንም። እሱን ወደፊት የምንመክርበት ቢሆንም፡ መቀልበስም የለብንም።ምክር ስምንት፡- በተቻለ መጠን “ግዛቸው፣ ሀይላቸው፡ በላቸው፣ አምባቸው: ተክላቸው” የሚሉ አማራ ቀመስ ስሞች ከመሪዎች ተርታ መወገድ አለባቸው። ይልቅስ አብርሀ፣ አጽብሀ፣ ጉዲና፣ ጊዳዳ፣ አረጋሽ ምናም የሚሉት ስሞች መብዛት አለባቸው። ይሄ በተወሰነ መልኩ በሌሎች ብሄሮች ዘንድ ያለውን የአንድነት ሀይሉ የቀድሞውን የአማራ የበላይነት ሊመልስብን ነው የሚለውን ስጋት ይቀንሳል። በርግጥም ለዚህ ስርአት ህልውና መስዋእትነት ሊከፍሉ የተዘጋጁትን ከኢህአዴግም በኋላ ሕይወት እንዳለ ያሳያል (በላይኞቹ አማራ-ቀመስ ስሞች የምትጠሩ የማውቃችሁም የማላውቃችሁም ሰዎች ወፍራም ይቅርታ)።

ምክር ዘጠኝ፡- ትግሉ ቀናት፣ ሳምንታት፣ ወራትም ሊፈጅ እንደሚችልና ባንድ ቀን ሰልፍ መንግስት ሊወድቅ እንደማይችል መገንዘብ ያስፈልጋል። ለምሳሌ የግብጽን ብንመለከት 15 ቀን፤ የቱኒዚያ ከወር በላይ፣ የየመን ከ12 ቀን በላይ፣ የሊቢያ ከስድስት ቀን በላይ፣ የባህሬንም እንዲሁ ከሳምንት በላይ እየፈጀ ነው። ስለዚህ አምባገነናትም ነፍሳቸው ቶሎ እንደማትወጣ ተገንዝበን ከላይ በምክር ቁጥር ሁለት እንደገለጽኩት ብቸኛው የትግሉ መደምደሚያ የቀኑ ብዛት ሳይሆን የስርአቱ መደምሰስ መሆኑን አውቀን እስከዚያ ቀን መግፋት ነው።ምክር አስር፡ እናንተ ጨምሩበት።

እስከዚያው ግን አንድ ሁለት ነጥቦችን ለፖለቲካ ድርጅቶችና ለሲቪክ ማህበራት በተለይም በውጭ ላለነው ማከል እፈቅዳለሁ።አንደኛ፡- በውጭ ያሉ አንጋፋና የተደራጁ የፖለቲካ ድርጅቶች ከህዝቡ አስቀድመው ትግሉን ቅርጽ የሚያስይዙ አጫጭር፡ ቶሎ ወደ ህዝቡ ሊዳረሱ የሚችሉ ዓላማዎችን ማሰራጨት አለባቸው።

ለምሳሌ “የህወሀት/ኢህአዴግ አገዛዝ ተወግዶ በኢትዮጵያ ሁሉንም የፖለቲካ ሀይሎችና የህብረተሰብ ተቋማት ያሳተፈ የሽግግር መንግስት ይቋቋም” አይነት፡ ግልጽ፣ ወደነጥቡ ያተኮረ፣ ያልተድበሰበሰ አላማ መትከል አለባቸው። ትናንትም ዛሬም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሀይሎች ህዝቡን መምራት ሲኖርባቸው ህዝቡ ሊቀድማቸው አይገባም። አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የምንፈልገው ለውጥ ምንድር ነው? ምን ይምጣ? መታወቅና ጥቅል ስምምነት ላይ ለመድረስ፡ የፖለቲካ ድርጅቶች የሆነ ነገር ማለት አለባቸው። እንጂ ዝም ብሎ መንገላወድና መዘብዘብ አያስፈልግም።ሁለተኛ፡- በውጭ የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን በተለይም ኢትዮጵያዊያን በብዛት የሚገኙባቸው ከተሞች ለምሳሌ ዋሽንግተን ዲሲ፣ ለንደን፣ ቶሮንቶ፣ የሕወሀት/ኢህአዴግ ህልውና መገለጫ የሆኑትንና በተለምዶ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እየተባሉ የሚጠሩትን የህዝብ ሀብትና ቢሮዎች መክበብ፣ መቆጣጠር በሰላማዊ መንገድ ማወክና መበጥበጥ አለብን። አገር ቤት ያለው ህዝብ ትግል ወሳኝ ቢሆንም፡ አገር ቤት ያለው ህዝብ እንዲሞት ስንቀሰቅስ እኛም በተጓዻኝ፡ እንዲያውም ቀድመን እነዚህን ተቋማት ማጥቃትና መንጠቅ አለብን። ያ የአገር ቤቱን ህዝብ ሊያነሳሳው፡ አጋር አለን ሊያሰኘው ይችላል። እንጂ እርምጃችን በቴሌኮንፈረንስና በግማሽ ቀን፡ ለዚያውም ጥገኝነት ጠያቂዎች ብቻ በበዙበት ሰልፍ መወሰን የለበትም።

የኢትዮጵያ ህዝብ፡ ይቅናን።ጎልማሳውና ጎረምሳው ቾምቤ፡ የቀድሞ አመጸኛ። የካቲት፡ 2003/2011

[1] ለምሳሌ በቤንጋዚ ቀውጢ ሆኖ በትሪፖሊ ጋዳፊን የሚደግፉ ሰልፎችን ያሳያሉ። በ2001 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያሉ ተማሪዎች የትምህርት ማቆም አድማ አድርገው ሲበተኑ፤ በሶስተኛው ቀን 95 ከመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች ወደትምህርት ገበታቸው ተመለሱ ብሎ ከየዲፓርትመንቱ የተለቃቀሙ ተማሪዎችን በቴሌቪዥን ያሳያል። ተሜ ተበላሁ ብሎ አመጹን አቋርጦ ወደ ትምህርት ገበታው እንዲመለስ።[2] ከአጼ ኃይለስላሴ ስርአት በተለየ መልኩ፣ ልክ ደርግ የወታደር ዩኒፎርሙን በካኪ ለውጦ ስልጣን ላይ እንደቆየውና እስከመጨረሻው ግን ወታደራዊ ባህርይው እንዳልተለየው ሁሉ፡ ሕወሀት ኢህአዴግም ስልጣን ይዞ የሲቪል መንግስት ነኝ ቢልም፡ የ17 አመት የጫካ ትግሉን ዘመናዊና የከተማ አደረገው እንጂ፡ በባሕርይና በአስተሳሰብ በምግባርና በተፈጥሮ የጫካው መንፈስ አለቀቀውም። በትጥቅ ትግል ውስጥ መግደል ትክክለኛና ህጋዊ እርምጃ ነው። ወደሲቪል Share Button

Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 22, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.