ድምጻዊ እዮብ መኮንን በጠና ታሟል

(ጽዮን ግርማ እንደዘገበችው) ማክሰኞ ረፋዱ ላይ ሁሌም የሚያሽከረክራትን ብስክሌት ይዞ ከቤቱ የወጣው ድምጻዊ እዮብ መኮንን ወደቤቱ መመለስ እንደመሄድ ቀላል አልኾነለትም መኖሪያ ቤቱ መግቢያ ላይ ሲደርስ ‹‹አንድ እግሬ እንቢ አለኝ እስቲ ጫማ አውልቁልኝ›› አለና ተዝለፈለፈ ቤተሰቦቹ አፋፍሰው ወደ ሃያት ሆስፒታል ወሰዱት እዮብ ግን መናገር እየተሳነው ነበር፡፡ ሃያት ሆስፒታል ወደ ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ላካቸው እዮብ መናገርና ራሱን ማዘዝ እያቃተው ነበር፡፡ የቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል የሕክምና ባለሞያዎች እዮብን ተቀብለው ‹‹አዲስ ያስገባነው ነው›› ባሉት አየር መስጫ መሳይ ማሽን ላይ በማስተኛት እዮብን ለማንቃት ጥረታቸውን ጀመሩ ግን እስካሁን አልተቻላቸውም፡፡ እዮብ ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ሪከቨሪ ውስጥ ራሱን እንደሳተ በማሽን መተንፈሱን ቀጥሏል፡፡ አተኛኘቱ እጅግ አንጀት ይበላል፡፡ በሆስፒታሉ የሚገኝ እያንዳንዱ ሰው በደቂቃዎች ክፍልፋይ የመንቃቱን ዜና ይጠባበቃል፡፡ በአንዷ ደቂቃ ፈጣሪ በድንገት እንዲያነቃው ሁላችንም እንፀልይለት፡፡

ጽዮን ግርማ ጨምራ እንደዘገበችው፤ ልጠይቀው በሄድኩበት ሰዓት ቤተሰቦቹ እና ጓደኞቹ ከሐኪሞቹ ጋራ ሲመካከሩ ነበር አንተ እንዳልከው ኮርያ ሆስፒታልም ሄደው ሐኪም አማክረዋል የተሻለ ሕክምና ሊያገኝ ይችላል ወደተባለበት ባንኮክ እንዲወሰድም ከሃያ በላይ የሚኾኑ ወዳጆቹ ለመታከሚያ የሚኾነውን ገንዘብ ለማዋጣት ቃል ገብተው በቁጥር ደረጃ ብሩ ተገኝቷል…..እንደመሰለኝ ….ሐኪሞቹ ባለበት ሁኔታ መንቃቱን መጠባባቁ የተሻለ አማራጭ መኾኑን መክረዋል….ፈጣሪ ከእርሱ ጋር ይሁን!

Liasten to Eyob’s song

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on August 16, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

2 Responses to ድምጻዊ እዮብ መኮንን በጠና ታሟል

 1. weshet alewdem

  August 16, 2013 at 12:11 PM

  who is eyob mekonen ? does he have any song i can listen if i can know or rember him.

 2. Abiy Ethiopiawe+SegaweWemenfesawe+አቢይ+ኢትዮጵያዊ+ሥጋዊ-ወመንፈሳዊ.

  August 19, 2013 at 2:17 PM

  ሞትህ ውሸት ይሁን።

  እሱም እንዲያ ደግሞ፤
  ሞተብን ወይ ታሞ
  እዮቤ መኮንን፤
  ሞትህ ውሸት ይሁን።
  ያበቫው ሬጌ፣-
  ያልሆንከው ባለጌ፤
  ምነውሳ ወዳጄ እዮቤ ወጣቱ፤
  ገና ቀትር ሳይሆን ጠፋህ በጧቱ???…
  እኮ እስኪ ንገረኝ፤
  ከሙዚቃህ መሐል፣አለ የሚያስተምረኝ???…
  ሙታን ይሰሙኛል ምልክትህ የታል፤
  እባክህ በሙት ድምፅ ንገረኝ ያንተን ቃል።
  ሞቷል የሚሉኝን በፍፁም አልሰማም፤
  ሁላችን ስለሞትን ባንተስ አልስማማም።
  እናም፦
  አዮብ ባለቅላፄ፣ጎልማሳው ወጣቱ፤
  ገና አደግክ ስንል ጠፋህ በጧቱ???…
  ምንድነው ምክንያቱ፤
  የድንገትህ ሞቱ???…
  ያም ሆነ ይህ ቢባል፤
  በዚህ ትግል መሐል፤
  ኢትዮጵያን ሳትከዳ፤
  ሳትባል “ያ ባንዳ፤”
  በኢትዮጵያዊነትህ፤
  ትንሳኤ ነው ሞትህ። እዮቤ መኮንን፤
  ሞትህ ውሸት ይሁን።