ድምጻዊት ሚካያ ኃይሉ ከዚህ አለም በሞት ተለየች

(ኢ.ኤም.ኤፍ) እውቅ ድምጻዊ ነበረች። የመጀመሪያ አልበሟ መጠሪያ፤ “ሸማመተው” በሚል ይታወቃል – አመቱም 2007 ነበር። እዚያ ውስጥ ከነበሩት 11 ስራዎች ውስጥ 8ቱ የራሷ ስራዎች ሲሆኑ የተቀሩት የታዋቂው ሙዚቃ ቀማሪ የኤልያስ መልካ ስራዎች ነበሩ።
ከዚህ የመጀመሪያ አልበሟ በኋላ፤ በ2010 ላይ በተደረገው የአፍሪካው “ኮራ አዋርድ” ላይ እጩ ሆና እስከፍጻሜው የደረሰች ድምጻዊም ነበረች። “ሰበብ” የሚለው ዜማዋም በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ የነበረ ሲሆን፤ ባራክ ኦባማ ፕሬዘዳንት ሆኖ ሲመረጥ “ሆነልኝ” በሚል የተጫወተችው ዘፈኗም በአድናቂዎቿ ዘንድ የሚታወሱ ናቸው።

Mikaya Behailu (R.I.P.)

Mikaya Behailu (R.I.P.)


ሚካያ ተወልዳ ያደገችው በአዲስ አበባ ሲሆን፤ ከመዋዕለ ህጻናት ጀምሮ የአንደኛ ደረጃ ትምህርቷን የጨረሰችው በቤተልሄም 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነበር። ስለሙዚቃ ስታስብ፤ ሁሌም የምታስታውሰው ነገር ገና በልጅነቷ አባቷ ገዝቶ የሰጣትን ጊታር ነው። በ1994 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በአብዮት ቅርስ (ጂ.ሲ.ኤ) አጠናቃለች። ታዲያ አብረዋት የተማሩት ጓደኞቿ በሁለት ነገር ያስታውሷታል። አንድም በጣም ጎበዝ ተማሪ በመሆኗ እና የሌሎች ድምጻውያንን ዘፈን እያስመሰለች በመጫወት ትታወሳለች። ትምህርቷን ከጨረሰች በኋላ፤ በ1995 የራሷን የሙዚቃ ድርሰቶች አዘጋጅታ ለማሳተም እቅድ ነበራት። ሆኖም የገንዘብ እና የልምድ ማጣት ፍላጎቷ በፈለገችው ጊዜ ከዳር አልደረሰም ነበር።
ሚካያ ለትምህርት ከፍተኛ ግምት ስለምትሰጥ፤ ቀን እየሰራች ማታ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለሰባት አመታት ትምህርቷን ተከታትላ ዲግሪዋን አግኝታለች። የማስተርስ ትምህርቷን አጠናቃ የመመረቂያ ስራዋን እያዘጋጀት በነበረበት ወቅት ግን ታመመች። ላለፉት ሶስት ወራትም በህመም ላይ ሆና ነበር የቆየችው። በመጨረሻ ህመሟ ጸንቶባት ለድንገተኛ ህክምና ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተወሰደች። ሆኖም አልዳነችም። የፈረንጆች ገና በሚከበርበት ዋዜማ፤ ዲሴምበር 24 ለሊት ላይ 2013 ዓ.ም. … በተወለደች በ37 አመቷ ከዚህ አለም በሞት ተለየች። የቀብር ስነ ስርአቷ ዛሬ ከሰአት በኋላ በ’ለቡ’ መካነ መቃብር ይከናወናል።
ሚካያ የአንዲት ሴት ልጅ እናት ነበረች። ለመላው ቤተሰብ፣ ወዳጅ እና ዘመዶቿ መጽናናትን እንመኛለን።
“ሰበብ” በሚል የሚታወቀውን ዘፈኗን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የቪዲዮ መስኮት ይክፈቱ።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on December 25, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.