ድምጻችን ይሰማ በሁሉም ከተማ

የዛሬው የድምጻችን ይሰማ መል ዕክት በተለያዩ ከተሞች ተከናውኗል። በየከተማው የነበረውን ሁኔታ እየተከታተሉ ይዘግቡ የነበሩ የፌስ ቡክ ዜናዎች ይህን ይመስሉ ነበር። እንዳለ አቅበነዋል።

 

በዛሬው ዕለትም ፀረ ሠላም የሆኑት የመንግስት ሀይሎች ዛሬም ያለምክንያት በወልቂጤ ከተማ ሠዎችንበማሠር ላይ ይገኛሉ:: በጃሚዕ መስጂድ ለጁመዓ ሠላት በመዘጋጀት ላይ የነበረ አንድ አህመድ የተባለ ሙስሊም ወጣትን ሠዎችን አነሳሽ የሆነ ወረቀት ለጥፈሀል በሚል ከንቱ ጥርጣሬ ወደ ፖሊስ ጣቢያ

ይዘውት ሂደዋል በተጨማሪም ልዩ ሀይሎች በከተማዋ ሠውን ለማሸበር እየተንቀሳቀሱ በመሆኑ ሁላችንም አጅግ በጣም ጥንቃቄ ልናደርግና ሠላማዊ መሆናችንን ልናሣይ ይገባል!

ከማለዳው 10:20 ከፍተኛ የቅንጅት ስራ እንደተሰራበት የሚገለፀዉ “ድምጻችን ይሰማ በሁሉም ከተማ”  በብዙ ቦታውች ላይ የተቃውሞ መርሀግብሩ በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ ነው:: ብዙ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ወደ ተቃውሞ ቦታ እያመሩ ነው ::ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የመቀሌ እና የጅጅጋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ወደ ተቃውሞ ማድረጊያ መስጂዶች በማምራት ላይ እንደሚገኙ ከ ቦታው የደረሰን መረጃ ያሳያል::

 

ዛሬም አገር አቀፉን ተቃውሞ ሰላምን ዘምረንበት አንድነታችንን አሳይተንበት ድምጻችን አሰምተንበት በሰላም ይጠናቀቃል፡፡

በድሬዳዋ ሰባተኛ ሰፈር መስጊድ ደማቅ ተቃውሞ ለማካሄድ ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡

 

በአሁን ሰአት አዲስ በአባ ወደ አንዋር መስጊድ ህዝቡ እየጎረፈ ነው ከፒያሳ ከአውቶቢስ ተራ ከአብነት ከተክለሀይማኖት ባጠቃላይ ከሁሉም አቅጠቀጫ ህዝቡ ወደ አንዋር እየተመመ ነው

 

አዲስ አበባ አንዋር ኹጥባ ተጀምሯል፡፡ በብዙ አካባቢዎች ሰአቱ የኹጥባ ነው፡፡ ሰዉ ጉዞውን ወደ ተቃውሞ አደባባዮች አድርጓል፡፡

 

የጋምቤላ ሙስሊሞች በግፍ ታስረው ከነበሩትና አሁን ከተፈቱት ወንድሞቻን ጋር የምናደርገው የመሰባሰብ ተቃውሞ በመሆኑ ደስተኞች ነን ብለዋል፡

 

በአባጂፋር አገር ጅማ የዛሬ የተቃውሞ ማዕከል የሆነው ፈትህ መስጊድ በከተማዋ ሙስሊም እየተጥለቀለቀ ነው፡፡

 

በወልዲያ ሰላም መስጂድ እና በመርሳ ኡመሩል ፋሩቅ መስጂድ የዱአ ተቃውሞ ተጀምሯል፡፡ በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ተገኝቶል፡፡

 

በመቀሌ በካሊድ መስጂድ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የከተማይቱ እና የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተገኙ ሲሆን የዱአና የተቃውሞ መርሐ ግብር በሰላም እና በስኬት ተጠናቋል፡፡

 

እኛ የመቱ ሙስሊሞች መቼም ቢሆን ለወረኛ ቦታ የለንም!!

በመቱ ነጃሺ መስጂድ የነበረው ተቃውሞ በሰላም ተጠናቐል ምንም እንኩዋን አንዳንድ ግለሰቦች ተቃውሞው እንዳይካሄድ በማሠብ የተሳሳተ መረጃ ለህዝበ ሙስሊሙ ቢያናፍሱም የመቱ ሙስሊም ከምንም ባለመቁጠር ተቃውሞውን በአላህ ፍቃድ በሰላም አካሄዷል! ሁሉም ሙስሊም በሰላም ወደየቤቱ ተመልሷል!

 

በጅጅጋ ቢላል መስጂድ የተደረገው የመጀመሪያው የዱዓ ተቃውሞ በስኬት ተጠናቋል፡፡ ሰላት እንደጠናቀቀም የመስጂዱ ኢማም ሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ አላህ እንዲያስቆምልን ከፍተኛ ዱዓ ማድረግ እንዳለብን አስታውሰዋል፡፡ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችም በተቃውሞው ላይ ተገኝትዋል፡

 

በአፋር ክልል አሳኢታና ዱብቲ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ በተገኘበት የተደረገው የመጀመሪያው ተቃውሞ በስኬት ተጠናቋል፡፡ በርካታ ሙስሊሞች እጃቸውን ከፍ አድርገው የመጣብንን መከራ አላህ እንዲያነሳልን ዱዓ አድርገዋል፡፡ ሁላችንም በዱዓ እንበርታ የሚል መልዕክትም አስተላልፈዋል፡፡

 

ዜና ወልቂጤ

በወልቂጤ ጀሚእ መስጂድ የተደረገው ከባድ ተቃውሞ በሰላም ተጠናቀቀ፡፤

መስጂዱን ከበውት የነበሩት አድማ በታኝ ፖሊሶች ያሰቡት ሳይሳካ ወደ መጡበት እየተመለሱ ነው፡:

 

በጎንደር ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የተገኘብት ታላቅ ተቃውሞ ተካሂዷል፡፡ በቀጣይም ተቃውሞውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል፡፡

 

በሲዳማ ዞን ሸበዲኖ ወረዳ በለኩ ከተማ ረህማ መስኪድ በተደረገው የዝምታ ተቃውሞ የተደረገ ሲሆን ኢማሙ ባደረጉት ኡጥባ ሰለ ሳህቦች የቢላልን የአማርን የሱሚያን እና የያሲንን ታሪክ አንስተው…የደረሰውን ስቃይ እና ሞት አክለው አሁንም በሃገራችን መንግስት ተመሳሳይ የሆነ ችግር እየፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል:; ሲል ሱልጣን የተባለ ሙስሊም የላከልን መረጃ ያስረዳል::

 

አዲስ አበባ አንዋር ዋናው መስጊድ ሞልቶ ሰዉ ወደ ሐብተጊዮርጊስ፣ ተክለሃይማኖት እና ጎጃምበረንዳ ደርሷል፡፡ ወደጣና የሚወስደው መንገድም በሰው ተሸፍኗል፡፡

አፋር ክልል ኹጥባው ስለ ዙልም (በደል) እና የተዞለመ (የተበደለ) ሰው ዱአ አላህ እንደሚቀበል የሚገልጽ ነው፡፡ ተበድለናልና አላህ ዱአችንን ይቀበለን፡፡ በአዲስ አበባ አንዋር መስጂድ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ የተገኘበት ታላቅ የተቃውሞ ሥነስርዐት በሰላም ተጠናቋል፡፡

 

አፋር ሎጊያ ሀምዛ መስጂድ

ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ በተገኘበት የዱአ ፕሮግራሙም በሰላም ተጠናቋል፡፡ ትግሉን አጠናክረው ለመቀጠልም ቃል ገብተዋል፡፡

በትግራይ ክልል አላማጣ ከተማ በሚገኘው አንዋር መስጂድ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገው የዱዓ ተቃውሞ በስኬት ተጠናቋል፡፡

===============

በትላንትናው እለት ወጥቶ የነበረው የተቃውሞ መርሃ ግብር ከዚህ የሚከተለው ነበር።

13ኛ ወሩን የያዘው ሰላማዊ ተቃውሞአችን ዳግም በለውጥ እና እድገት ውስጥ እየተንደረደረ ነው፡፡ በአላህ ፈቃድ ገና የተቃውሞ እንቅስቃሴያችን እስከ ድላችን ዋዜማ ድረስ እያበበ ይሄዳል፡፡ ባለፉት ጥቂት ወራት በጥቂት ከተሞች ታጥሮ የነበረው የ‹‹ድምጻችን ይሰማ›› ተቃውሞ በአይነትም በይዘትም እንዲለይ እና እንዲገዝፍ በማሰብ አዳዲስ ከተሞችን ባካተተ ሁኔታ በመጪው ጁምአ ይካሄዳል፡፡ የጁምአ ተቃውሞአችን ‹‹ድምጻችን ይሰማ በሁሉም ከተማ›› በሚል አቢይ ርእስ የሚካሄድ ሲሆን በከተማም በገጠርም በርካታ ሙስሊሞች እንዲገኙበትና ድምጻቸውን እንዲያሰሙበት የታለመ ነው፡፡
የዚህ ጁምአ ተቃውሞአችን ለየት የሚለው በሰላማዊው ተቃውሞተሳትፎ ለማድረግ ዝግጅት ሲያደርጉ የነበሩ አዳዲስ ከተሞች ተሳትፎ የሚያደርጉበትና በሁሉም የአገሪቱ አቅጣጫዎች በተናበበ መልኩ የሚካሄድ መሆኑ ነው፡፡ በአጠቃላይ በዚህ ሳምንት ተቃውሞ 36 ከተሞች ተሳታፌ እንዲሆኑ የተወሰነ ሲሆን የተቃውሞ ሂደቱም በሶስት እርከኖች እንዲከፈል ተደርጓል፡፡
በዚህም መሰረት በብዛት አዳዲስ ከተሞች የሚገኙበት የመጀመሪያው የከተሞች ምድብ ተቃውሞው የሚካሂደው በአንድ መስጊድ በመሰባሰብ ብቻ ነው፡፡ ከታች የተገለጹት የዚህ ከተማ ነዋሪዎች በከተማቸው በሚገኝ ትልቁ መስጊድ በብዛት ተሰባስቦ በመሄድ እና ጁምአን በጋራ በመስገድና ዱአእ ለሙስሊሙ ኡምማና በእስር ለሚሰቃዩ ወንድሞችና እህቶቻችን ዱአእ በማድረግ የሚያበቃት ይሆናል፡፡ ይህ የመጀመሪያ እርከን ወይንም የመሰባሰብ ተቃውሞ የሚደረግባቸው ክልሎች እና ከተሞች ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው፡፡

1) በትግራይ ክልል:- መቀሌ፣ አላማጣ እና አድዋ ከተማ
2) በአፋር- ዱብቲ፣ ሎገያ እና አሳኢታ ከተማ
3) በአማራ:- ጎንደር፣ ባህርዳር፣ መካነሰላም እና ጃማ ከተማ
4) በኦሮሚያ:-አወዳይ፣ ጭሮ እና ሮቤ ከተማ
5) በደቡብ:- አዋሳ እና ዲላ ከተማ
6) በሱማሌ:- ጅጅጋ ከተማ
7) በበኒሻንጉል ጉሙዝ: – አሶሳ ከተማ እና
በጋምቤላ: -ጋምቤላ ከተማ ናቸው፡
በሁለተኛው ምድብ የሚካተቱበትና ሁለተኛውን እርከን ተቃውሞ ወይም የዝምታ ተቃውሞ የሚያደርጉ ከተሞች በከፊል መቀዛቀዝ የታየባቸው ከተሞች ናቸው፡፡ በእነዚህ ከተሞች የሚገኙ ሙስሊም ነዋሪዎች በማዕከላዊ የከተማቸው መስጊድ በቁጥር በርክተው በመሰባሰብ እና አብሮ በመስገድ እነዲሁም ከጁምአ ሰላት በኋላ ለአምስት ደቂቃ ያህል እጅ ለእጅ ተያይዞ በዝምታ በመቆየት እና ቀጥሎም በግል ለሙስሊሙ ኡምማና በእስር ለሚሰቃዩ ወንድሞችና እህቶቻችን ዱአእ በማድረግዱ የመርሀ ግብሩ ፍጻሜ ይሆናል፡፡ ይህ የዝምታ ተቃውሞ እንደየአካባቢው ጸባይና ሁኔታ የሚለዋወጥ እንደሆነም ለማስታወስ እንወዳለን፡፡ እነዚህ የዝምታ ተቃውሞ የሚደረግባቸው ከተሞች ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው፡፡ ቦታዎቹም የሚከተሉት ናቸው
1) በአማራ:- ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ መርሳ፣ ወልዲያ ፣ወረባቦ እና ቢስቲማ ከተማ
2) በኦሮሚያ:- ጅማ እና አጋሮ ከተማ
3) በደቡብ:- ወራቤ እና አላባ ከተማ
4) በሃረሪ:- ሃረር ከተማ ናቸው፡፡
በሶስተኛው እርከን የተካተቱትና ከፍተኛ ተቃውሞ በድምጽ የሚደረግባቸው ከተሞች ተከታዮቹ ሲሆኑ በእነዚህ ከተሞች የሚኖረው ጠንከር ያለ ተቃውሞ ዝርዝር የአፈጻጸም መርሐ ግብር የሚገለጽ ይሆናል፡፡
1) በአማራ:- ባቲ
2) በኦሮሚያ:- ሻሸመኔ፣ በደሌ፣ መቱ እና ዶዶላ ከተማ
3) በደቡብ:- ወልቂጤ ከተማ
4) በድሬደዋ: -ድሬደዋ ከተማ እና
5) በአዲስ አበባ ከተማ ናቸው፡፡
ይህን በአይነቱ ለየት ያለውን የ‹‹ድምጻችን ይሰማ በሁሉም ከተማ›› መርሀግብር በተጠቀሱት ከተሞች የሚኖሩ ሙስሊሞች ሁሉ አስፈላጊውን እንቅስቃሴ እና ዝግጅት በማድረግ የተሳካ እነዲያደርጉት ጥሪያችን ነው፡፡
አላሁ አክበር!

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on March 1, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

2 Responses to ድምጻችን ይሰማ በሁሉም ከተማ

  1. Daniel

    March 1, 2013 at 5:59 PM

    The geam is over. The time is now you Chrstian and Muslems we are brouthers standup together.God bles you.

  2. ይጥር5

    March 3, 2013 at 6:47 AM

    IT WOULDN’T SURPRISE ME AS THE DEMONSTRATION ALWAYS HELD IN FRIDAY ? WHY NOT MONDAY TO THURSDAY, ?