ደሴን ልክ እንደ ጦር አውድማ ! ደካማዎች ሴቶችና ህፃናት ተጎድተዋል

(ይህ ከደሴ የደረሰን ዘገባ ነው)
ንፁሀን በደላቸውን ለማሰማት በዳዮችም የግፍ ሴራዎችን ሲያጤኑ ከርመው ኢድ ቀን የተወሰነው ፍጥጫ በሙሊሙና በመስጂድ ነጣቂዎች በአሳሪ አሳሳሪዎች በደብዳቢ አስደብዳቢዎቹ ካድሬዎች ዛሬ ቀኑ ደርሶ መንግስታዊ እስልምና አራማጆችና ካድሬዎች ፈጥነው የሰላቱን የመጀመሪ ሶፍች በለሊት ተቆጣጠሩ፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ ልክ ከዚህ በፊት እንደሚደረገው የከረጉቱ ሜዳን ሞልቶ ተቀመጠ እዚህ ጋር ነው የተሸረበው ሴራ ፡፡
Dessei_Eid_aug8_2013
የአንድ ሰፈር ሙስሊም ሊያሰግድ የማይችል ሰማይ ቢደፋ የደሴን ሙስሊም ሊይዝ እንደማይችል እየታወቀ ሙስሊሙን ለሁለት ለመክፈልና ካድሬና አህባሾችን ከጥቃጡ ለመጠበቅ ብሎም ከጠባቧ ሜዳ መውጫ እንዳያገኛ ከመስጊዱ ጎን ተደርጎ በማይታወቅ ሁኔታ በአጥር የተከለው ጠባብ ሜዳ ላይ ህዝቡን በፖሊስና ልዩ ሀይል እየፈተሹ ማስገባት ጀመሩ፡፡ ያቺ ጠባብ ሜዳ ሞልታ ህዝቡ በአግራሞት ይመለከት ጀመር፡፡ ከኢድ ሰላት በፊት የሰላተል ጀናዛ ስግደት ነበር፡፡ የተከለለችው ሜዳ ውስጥ ያሉት ወንድሞች ብቻ ሰላቱን ቆሙ ወዲያው የኢዱን ሰላት ኢማሙ ሲጀምሩ ሰፊውና ነባሩ ሜዳ ላይ የተሰበሰበው ህዝብ ተክቢራ ጀመረ በዛች ጠባብ መሬት ላይ ከፊሉ የኢዱን ሰላት ጀምሯል ከፊሉ የወንድሞቹን የእህቱን ቁጣን ያዘለ የተቃውሞ ድምፅ ሰምቶ ከጠባቧ በአጥር የተከበበች ሜዳ መውጣት ጀመረ፡፡

ኢማሙ ሰላቱን ቀጥለዋል ሙስሊሙም ልዩ ልዩ የተቃውሞ መልዕክቱን እያሰማ ቆይቶ ለዲናችን እንሞታለን የሚለው ለሙስሊም ጥላቶች መሪር ቃል ሲሰሙ የጭምብል ለባሾች ልዩ ሀይል ወዲያው ከየት እንደመጡ ሳይታወቅ ሙስሊሙን መክበብ ጀመሩ ከመጡት ቁጥር አንፃር ሙስሊሙን መክበብ አይደለም ከምንም አይገቡም አንዳንድ ወንድሞች በድንጋጤ መሮጥ ጀመሩ….. አስለቃሽ ጭስ መተኮስ ተጀመረ…. ሁሉም ነፍሴ…… ነፍሴ……. ሰው በሰው ላይ መረማመድ ጀመረ፡፡

የሴቶች እና የህፃናት ጮኸት ምድሪቱን አናወጧት ወንዶች በተክቢራ…. ወደ ተራራው ….ወደ ተራራው ሩጫ ….ያንን ቀጥ ያለ ተራራ ጉልበት ያለው ወጣ፡፡ ደካማዎች ሴቶችና ህፃናት ይንከባለሉ ጀመር መርዘኞቹ ጭንብል ለባሾች ልዩ ሀይሎች ያገኙትን ጨፈጨፉ፡፡ በሚገር ሁኔታ በአንደኛው አቅጣጫ ከጥቃት የሚሸሸው ህዝብ ያንን ተራራ ሸለቆ ሲታገል በታጠረ ትንሽ ሜዳ የነበሩ ወንድሞች ኢማሙ እንዳሰላመቱ የቀለተ ተቃውሞቸውን እያሰሙ ከአጥሩ ወጡ ህዝቡን እንደ ውሻ የሚያሳዱ ጭንብል ለባሽ ተኩላዎች አስለቃሽ ጭሰ አድክሞት የጣለውን ሰው መደብደብ ትተው ወደ ቀለጠው ሁለተኛ ተቃውሞ አመሩ በዕርግጥ ከዚህ በኃላ ምን እንደተፈጠረ ይህ የሚፅፍላቹ ወንድም አያውቅም ብዙ ተራራና ሸለቆዎችን አቆራርጦ አብረውት ከነበሩ ወንድም እህቶቹ ጋር ወደ ቤቱ አምርቷል፡፡

ጦርነቱ አንዱ በመሳሪያ…. አሽባሪ የተባለው ህዝብም በቃሉ …የነበረው የኢድ ተቃውሞ በአንድ በኩል ይህን ይመስላል፡፡ይህን ታሪካዊ ተቃውሞና ጭፍጨፋ በቪዲዮ በአላህ ፍቃድ ሰሞኑን ይቀርባል :: ይህ ፎቶው ላይ የምታዩት በቀይ የተከበበት አካባቢ የመኪና ጭስ አይደለም መኪናዎቹ የቆሙ ናቸው አረመኔዎቹ ህዝቡ ላይ የተኮሱት አስለቃሽ ጭስ ነው::
አላህ እርዳታውን ይስጠን! ኢንሻአላህ ነገ እነዚህ ሰዎች እግራችን ስራ የሚወድቁበት ቀን ቅርብ ነው

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on August 8, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

2 Responses to ደሴን ልክ እንደ ጦር አውድማ ! ደካማዎች ሴቶችና ህፃናት ተጎድተዋል

 1. muste

  August 9, 2013 at 7:26 AM

  gana mach tajamar!Ashabariwoch, talikalachu ba igirachihu sir Dadabi.

 2. ሰለሞን

  August 10, 2013 at 6:00 AM

  የሆነው እየሆነ ያለው ገና ወደፊትም የሚሆነው ይህን መሰል ግፍ ወያኒ እስካለ ድረስ እንደማይቆም ነው። እንዲያውም ሰላማዊ ሰልፉ በተካሂደባቸው ከተሞች ሁሉ የወያኒ የበቀል በትር መነሳቱ እንደማይቀር ነው። 22 አመት ያየነው ይህንኑ መሰል የግፍ በትር ነውና።

  ስለዚህ የወያኒ ብቀላ የማይቆም ከሆነ እኛም ሰላማዊ ትግሉን አጠናክረን መቀጠል ግድ ይለናል። እስከመቺ ድረስ ወያኒ እላያችን ላይ እየኮሰ ግፉን የቀጥላል።

  በቃህ ማለት ይጠበቅብናል ለማይቀረው የነጻነት ትግል እራሳችንን አዘጋጅተን ትግሉን እንቀላቀል ነጻነታችንን በ እግዚአብሂር ከተማመንን እራሳችን ታግለን ልናስመልስ እንችላለን። ከውጭ መንግስታት ምንም አንጠብቅ እነሱ ምንጊዚም ቢሆን ከኛ ጎን አይቆሙም ምክንያቱም ጥቁር ሆነን ንጭን ቅኝ ገዥ የጣሊያንን ጦር ስለአሸነፍን ወይም በዚሁ ድል ሳቢያ ቅኝ ያለመገዛታችን ብቻ አይደለም ዋናው ነጥብ የኛ አለኝታ የኛ መከታ እንድ አምላክ ብቻ ስለሆነ ነው።

  በታላቁ መጽሀፍ በመጽሀፍ ቅዱስ ስለ እኛ ስለ ኢትዮጵያውያን ተደጋግሞ የተነገረ ነገር ቢኖርም 3 መሰረታዊ ነገሮች ወይም ለሊሎች ህዝቦች ያልተነገረ ነገር ላኛ ስለትባለ ነው።እነሱም
  1ኛ. ህዝቢ ከሚላቸው እስራኢላውያን አብልጦ እንደሚያቅርበን ሲገልጽ {እናንተ የ እስራኢል ልጆች ለኒ እንደ ኢትዮጵያውያን አይደላችሁምን } ማለቱ
  2ኛ ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብር ዥንጉርጉርነቱን ሊለውጥ ይችላልን መባሉ
  3ኛ በችግራችን ጊዚ ከምድራዊ ገዢዎች ምንም መፍትሂ እንደማናገኝ የሚነግረን እንዲያውም በተግባር ያየነው መሆኑን ነጋሪ የማያስፈልገን ዛሪም በአሚሪካ በአውሮፓ ከተሞች ምድር አንቀጥቅጥ ሰላመዊ ሰልፍ ብናደርግ የማይሰሙን ነገሩ ወዲህ ስለሆነ ነው።መጽሀፉ እንዲህ ይላልና
  {ኢትዮጵያ እጆቻን ወደ እግዚአብሂር ትዘረጋለች} በማለት የኛ መፍትሂ ሰጭ አምላክ እንጂ ምድራዊ ገዢዎች አለመሆናቸውን በማያሻማ መልኩ ተነግሮናል በመሆኑም በአምላካችንን ተማምነን በአንድነት ሆነን የጀመርነውን ሰላማዊ ትግል እንቀጥል በአጭር ጊዚ ውስጥ ለውጥ ማየት ብቻ ሳይሆን ማምጣት እንችላላን።
  እግዚአብሂር ኢትዮጵያን በምህረቱ ይጎብኝልን አሚን