ደመቀ መኮንን – ከብአዴን ምክትል ሆኖ ተመረጠ

(ኢ.ኤም.ኤፍ.) ሰበር ዜና – አሁን ምሽቱን እየተደረገ ባለው ስብሰባ ኢህአዴግ የድርጅቱን ምክትል ሊቀመንበር መርጧል። ዜናው በሌሎች መገናኛ ብዙሃን ገና አልተሰራጨም፤ ሆኖም በተለይ ለኢ.ኤም.ኤፍ. የደረሰው ልዩ መረጃ እንዳመለከተው ከሆነ፤ በዛሬው የምክትል ሊቀመንበርነት ምርጫ ወቅት በተለይ የህወሃት ሰዎች ከነሱ በኩል ሰው እንዲመረጥ ቢፈልጉም ያልተሳካ መሆኑን ነው ለመረዳት ያልቻልነው። ስብሰባው ገና አልተጠናቀቀም። ዜናውም በአገሪቱ መገናኛ አልተገለጸም። በኛ በኩል ዋናውን ዜና እነሆ ብለናል። ዝርዝር ዘገባውን በቀጣዮቹ ቀናት እናሳውቃለን።

ተያይዞ የደረሰን ሌላ ዜና አለ። ይህ ምርጫ ኢህ አዴግ ድርጅቱን ለመምራት ሲሆን፤ ለምክትል ጠቅላይ ሚንስትርነት አምባሳደር ብርሃኔ ገብረክርስቶስ እንዲሆን፤ ህወሃት እየጠየቀ ሲሆን… ምርጫው ግን ወደፊት ፓርላማው የሚያጸድቀው ጠቅላይ ሚንስትር ይሆናል። በዚህም መሰረት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ምክትል ጠቅላዩን የመምረጥ ስልጣን ይኖረዋል። ምርጫውም ከብ አዴን (አማራ) ወይም ህወሃት (ትግራይ) ይሆናል። ኦህዴድ ይህን በተመለከተ እጩ በማቅረቡ ረገድ ብዙም ያልገፋበት መሆኑን ለመረዳት ችለናል። ለሰበር ዜና ያህል ምክትሉን አሳውቀናል። ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆኖ ተመርጧል።

ብአዴኑ ደመቀ መኮንን የብአዴን ድርጅት ሊቀመንበር እና የፌዴራሉ ትምህርት ሚንስትር ሆነው እየሰሩ መሆናቸው ይታወቃል።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on September 15, 2012. Filed under NEWS. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.