ያ’ገሬና የኔ! (አትክልት አሰፋ – ከቫንኩቨር)

እናቴና አገሬ ሙግት ገጠሙና፣
ሚስቴና እናት አለም ተወዳደሩና፣
ልጄ እና እማምዬ ፉክክር ገቡና፣
አንዱን ምረጥ ብለው ድርቅ ሲሉብኝ፤
እናቴም ውዴ ናት፣
ሚስቴም የኔ ፍቅር፤
ልጄም ንጉሴ ነው፤
የሚጣፍጥ ከማር፤

የግሌ የራሴ የማ’ለውጣቸው፣ በሰላሳ ዲናር የማልቀይራቸው፤

እናት፣ ሚስት፣ ልጄ፤ ሁሉም የኔ ናቸው።
እኔ ግን ያገሬ፤ እኔስ የ ‘ማምዬ…
የግል ንብረት ነኝ ብዬ መለስኳቸው።

ዲ ሴ ም በ ር 1 5 /2 0 1 3 – ቫ ን ኩ ቨ ር ( በ ርናቢ )

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on December 16, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.