የFBI መርማሪዎች አበበ ገላውን ለመግደል የታቀደ ሴራ አከሸፉ – በሴራው የተሳተፉ የህወሃት ሰላዮች ምርመራ እየተደረገባቸው ነው

ታህሳስ ፴(ሰላሳ ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ሰሞኑን አንድ የአሜሪካ የፌዴራል ወንጀል ምርመራ (FBI) ግበረሃል ባለፈው ወር መባቻ ላይ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ወደ ቦስተን ለኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በተጓዘበት ወቅት የግድያ ወንጀል ለመፈጸም በመዶለትና በማስተባበር ተግባር ላይ ተሰማርቶ የነበረና ለህወሃት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት እንደሚሰልል የሚጠረጠር ግለሰብ እና በግብረአበሮቹ ላይ ከፍተኛ ምርመራ መክፈቱን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጡ።

በአሜሪካ ሀገር የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቆ የሚኖረውና እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ብሎ የሚጠራው ጽንፈኛ የዘር ድርጅት አባል እና ሰላይ እንደሆነ የሚታመነው ግኡሽ አበራ በመባል የሚጠራው ይሄው ግለሰብ ጋዜጠኛውን ለመግደል በማሴር ሶስት የወንጀሉ ተባባሪ የሚሆኑ ግለሰቦችን መመልመሉ ንና ድርጊቱን ለመፈጸም መሰናዶ ማድረጉን የFBI መሪማሪዎች ደርሰውበት ሴራውን በግዜ ማክሸፋቸው ተረጋግጧል።

Source: ethsat.com

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on January 9, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.