የ23 ግለሰቦችና የ15 ድርጅቶች ተንቀሳቃሽ ሒሳብ ታገደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ታህሣሥ 17 ቀን 2001 ዓ.ም. ለአቢሲኒያ ባንክ ፕሬዚዳንት በፃፈው ደብዳቤ የ23 ግለሰቦችና የ15 ድርጅቶች ተንቀሳቃሽ ሒሳባቸው እንዲታገድ አዘዘ፡፡

ብሔራዊ ባንክ ለአቢሲኒያ ባንክ ፕሬዚዳንት በደብዳቤ ባስተላለፈው ትዕዛዝ “በድርጅቶቹና በግለሰቦቹ ሥም በባንካችሁ የሚንቀሳቀስ ሂሣብ ካለ፣ ሌላ ተለዋጭ ትዕዛዝ እስከሚሰጥ ድረስ ከታህሣስ 17 ቀን 2001 ዓ.ም. ጀምሮ እንዳይንቀሳቀስ እንዲደረግ እናስታውቃለን” ብሏል፡፡

በብሔራዊ ባንክ በሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ናና ፊርማ የተላከው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው፣ ድርጅቶቹም ሆኑ ግለሰቦቹ ሒሣባቸው እንዲታገድ ብቻ ሳይሆን፣ በሂሣቡ ውስጥ በዕለቱ ያለው ገንዘብ መጠን ተጠቅሶ፣ የተከፈተ ሒሣብ ከሌለም አለመኖሩን በመግለፅ እስከ ታህሳስ 20 ቀን 2001 ዓ.ም. ለብሔራዊ ባንክ ገዢ በፖስታው ላይ “በገዢው ብቻ የሚከፈት” በሚል እንዲላክ አሳስቧል፡፡

ብሔራዊ ባንክ ለአቢሲኒያ ባንክ በፃፈው ደብዳቤ ሒሳባቸው እንዲታገድ ትዕዛዝ የሰጠባቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች በምን ምክንያት እርምጃውን ሊወስድ እንደቻለ አልገለፀም፡፡ ሆኖም ምንጮቻችን የሒሳቡ እገዳ የተላለፈው ሰሞኑን የናይል ኢንሹራንስ ዋስትና በማስያዝ ከፍተኛ የባንክ ብድር ወስደዋል ከተባሉ ተከሳሾች ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

የአቢሲኒያ ባንክ ህዝብ ግንኙነት ቢሮ ስለጉዳዩ ማብራሪያ ተጠይቆ፤ “ምንም የማውቀው ነገር የለም” የሚል ምላሹን ሰጥቷል፡፡

ሒሳባቸው እንዳይንቀሳቀስ ከብሔራዊ ባንክ ትዕዛዝ የተላለፈባቸው
1. ካሳ ቤል ኃ/የተ/የግል ማህበር
2. ጣና ትራንስፖርት ኃ/የተ/የግል ማህበር
3. ጢስ አባይ ኃ/የተ/የግል ማህበር
4. ጣና ኢንተርናሽናል ኃ/የተ/የግል ማህበር
5. ናይል ቡና ላኪ ኃ/የተ/የግል ማህበር
6. ናይል ትራንስፖርት ኃ/የተ/የግል ማህበር
7. ናይል ኢንተርናሽናል ኃ/የተ/የግል ማህበር
8. ዶልፊን ትራንዚትና ሺፒንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር
9. ሚና ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር
10. አበባው ደስታ አለሙ
11. ትዕግሥት ወንድይፍራው ታምራት
12. አቶ ተመስገን መሀሪ ቢተው
13. አቶ መሀሪ ቢተው
14. ወ/ሮ ብርሃን አሰፋ
15. ወ/ሪት ማስተዋል መሀሪ ቢተው
16. አቶ ዘላለም ተመስገን መሀሪ
17. አቶ ክበር ተመስገን መሀሪ
18. አቶ ሀብታሙ መሀሪ ቢተው
19. አቶ ምንውየለት አጥናፉ አበጠው
20. ወ/ሮ ላቀች መንግሥቴ መለስ
21. አቶ አብርሃም ምንውየለት አጥናፉ
22. ናይል የምግብ ማዘጋጃ (Nile Food Processing)
23. አዋሽ ትራንስፖርት
24. ዝሆን ትራንስፖርት
25. ጎጀብ ትራንስፖርት
26. ስታር ቢዝነስ ግሩፕ
27. ኢትዮ ኢንቨስትመንት ግሩፕ
28. ሚካኤል አበባው ደስታ
29. ጌታሁን አበባው ደስታ
30. ሰለሞን አበባው ደስታ
31. ታደለ አበባው ደስታ
32. ዮሐንስ አበባው ደስታ
33. አልማዝ ምንውየለት አጥናፉ
34. ዳንኤል ምንውየለት አጥናፉ
35. ሐብታሙ ምንውየለት አጥናፉ
36. ትእግሥት ምንውየለት አጥናፉ
37. ዘመናይ ምንውየለት አጥናፉ
38. አብርሃም ምንውየለት አጥናፉ

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on January 2, 2009. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.