ፖለቲካዊ ተቃውሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Addis Ababa UniversityAccording to reports, Addis Ababa University is surrounded by Zenawi’s heavily weaponed vehicles and guards, following politically motivated clashes among students last weekend.

Awramba.com, 03 May 2010 – አውራምባ ታይምስ (አዲስ አበባ) በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ ተማሪዎች ከምርጫው ትኩሳት ጋር በተያያዘ ከገዢው ፓርቲ አባት ጋር መጋጨታቸውን የአይን ምስክሮች ገለጹ፡፡

ሰሞኑን በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በተከታታይ ሲተላለፍ በነበረው የቴሌቭዥን ክርክር ገዢው ፓርቲ ‹‹ተቃዋሚዎች አገር መምራት አይችሉም›› ሲል በተደጋጋሚ መግለጹ የሚታወስ ሲሆን በዩኒቨርስቲው ያሉ የገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች የመድረክ ደጋፊ ለሆኑ ተማሪዎች ይህንኑ አባባል በመድገማቸው ትናንት ምሽት ከባድ ግጭት መቀስቀሱና ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ተማሪዎችም ለጉዳት መዳረጋቸው ታውቋል፡፡ ግጭቱን ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ ወደ ቅጥር ግቢው በመግባቱ ሁኔታዎች ሊረጋጉ መቻላቸውን የገለጹት የአይን ምስክሮች በርካታ ተማሪዎች ከካምፓሱ በመሸሽ በአካባቢው በሚገኙ መኖሪያ ቤቶች ተጠግተው ለማደር መገደዳቸውን የደረሰን መረጃ ይጠቁማል፡፡

በተለያዩ ጊዜያት በአገሪቱ የተከሰቱ መጠነሰፊ ተቃውሞዎች መነሻቸው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሲሆን በ1997 ዓ.ም ምርጫም በአገሪቱ የተቀጣጠሉ መጠነ ሰፊ ተቃውሞዎች በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እንደተጀመሩ ይታወሳል፡፡ ይህ ዜና እስከተዘጋጀበት ሰዓት ድረስ ዩኒቨርስቲው በከባድ ጥበቃ ላይ መሆኑን የአውራምባ ታይምስ ዘጋቢ እቦታው ድረስ በመሄድ አረጋግጧል፡፡

Source: http://awramba.com/?p=45

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on May 3, 2010. Filed under NEWS. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.