የፕሬስ ቀን በኢትዮዽያ

ዛሬ የአለም ዙሪያ የፕሬስ የነፃነት ታስቦ ውሏል። በርካታ ለፕሬስ ተሟጋች የሆኑ ድርጅቶች የኢትዮጵያን የፕሬስ ነፃነት፤ ጥያቄ ውስጥ ከተዋል።

በተለይም ቅርብ ጊዜ “Freedom Housse” የተባለው የፕረስ ተሟጋጅ ድርጅት፤ ኢትዮጵያ በፕረስ ነፃነት ከማያሰጉ አገሮች ወደ ሚያሰጉ አገሮች መመደቧን ማስታወቁ ይታወሳል። በትላንትናው ዕለት ደግሞ ዓለም ዓቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ሲፒጄ ኢትዮዽያ ኢንተርኔትን ከሚያቅቡ 10 ሀገሮች አንዷ ሲል የኮነነበትን መግለጪያ አውጥቷል። ዛሬ በአዲስ አበባ ሲደረግ የነበረው የዓለም የፕሬስ ቀን መታሰቢያ ስብሰባ ውዝግብ ገጥሞታል። ስብሰባው በመንግስት ሆን ተብሎ ተበጥብጧል ሲል የግሉ ፕሬስ አባላት ሲወቅሱ መንግስት በሰላም እየተካሄደ ነው ይላል። ልደት አበበ የኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ነፃ የመገናኛ ብዙኸን ቀኑን በምን አይነት ሁኔታ እብደሚያከብሩ ፤ የአውራምባ ታይምስ ዋና አዘጋጅ የሆኑትን አቶ ዳዊት ከበደን እንዲሁም ከመንግስት በኩል አቶ ሽመልስ ከማልን አነጋግራቸዋለች። የአውራምባ ታይምስ ሳምንታዊ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ዳዊት የዛሬው የፕሬስ ቀን ላይ የተፈጠረውን ውዝግብ በመግለጽ ይጀምራል።

ልደት አበበ-መሳይ መኮንን-ነጋሽ መሐመድ

የፕሬስ ቀን በኢትዮዽያ

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on May 4, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.