የፌዴሬሽኖቻችን ሁኔታ – በመጨረሻዎቹ ቀናት!

(EMF) [ዳዊት ከበደ ወየሳ እንደጻፈው]
ወደ ዝግጅቱ ማብቂያ ላይ ደርሰናል። የዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው ቆይታችንም ማብቃቱ ነው። ጁላይ 5 ቀን፣ 2013 ዓ.ም. “የኢትዮጵያ ቀን!” ተብሎ ይከበራል። የሜሪላንድ ስቴዲየም አንደኛው ወገን ጥም ብሎ ሞልቷል። ከውጭ ወደ ውስጥ ተጨማሪ ሰው እንዳይገባም ህዝቡ በመታገዱ ብዙ ሺህ ህዝብ ወደ ቤቱ ተመልሷል።

በዚህ ቀን የስፖርት ብቻ ሳይሆን፤ ባህላዊ ዝግጅትም ይደረጋል። መድረኩ ይሰናዳል። አገራዊ መልዕክት ይደመጣል፣ ህዝቡ በዚህ ቀን የአገር ባህል ለብሶ ወይም በኢትዮጵያ ባንዲራ ልብሶች አሸብርቆ ነው – ከቤቱ የሚወጣው። ከመድረኩ አካባቢም ባህላዊ ጨዋታ እና ዘፈኑ ሲደምቅ፤ በስቴዲየም የተገኘው ህዝብ ከሚያሰማው ሆታ በተጨማሪ፤ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ከፍ አድርጎ ያውለበልባል – እነሆ በዚያን ጊዜ የሁሉም ልብ በደስታ ይደምቃል።
ጋዜጠኞች ስቴዲየሙ ውስጥ ሆነን የህዝቡን እና የመድረክ ዝግጅቱን እንከታተላለን፤ ታሪካዊውንም ቀን በካሜራችን እንቀርጻለን። ማሪቱ ለገሰ “እንዲያው ዘራፌዋ” ብላ የጀመረችው የመድረክ ዝግጅት… በባህል ጨዋታ ረቅቆ፣ በብርሃኑ ተዘራ ደምቆ፣ በጃሉድ ደቆ እንደማያልቅ የለም – ሁሉም ነገር ለዚህ አመት አብቅቷል።

Disoriented Jalud on 30th ESFNA festival

Disoriented Jalud on 30th ESFNA festival

የጃሉድን ነገር ካነሳን አይቀር… አስቂኝ ነገርም ስላለበት፤ ባለፈው ያልኩትን በመድገም ጨዋታዬን ልቀጥል። ምናልባት ጃሉድ የተጠራ የመሰለው እዚያኛው ዝግጅት ላይ ነው። መዝፈን ጀመረና ቀና ብሎ ሲመለከት ስቴዲየሙ ጢም ብሏል። ዘፈኑን አላቋረጠም። በዚያው ዜማ… “እኔ እኮ የተጠራሁት እዚያ ነበር” ሲል ሰዉም ጋዜጠኞቹም፤ ከመሳቅ ይልቅ ተሳቀው ዝም አሉ። ጭራሽ ጃሉድ ወደኋላ ተመልሶ ሊያቆም አይነት ሆነ። ባንዱ ሙዚቃው በረድ አደረገው። ፈራ ተባ እያለ፤ መድረኩ ጫፍ ቀረብ ብሎ ምናልባትም የማይዘፍን መሆኑን ሊናገር ሲል፤ አንደኛው ጋዜጠኛ… “ለመለስ ዜናዊ ስትዘፍን ያልፈራህ፤ አሁን ምን አስፈራህ?” ሲለው ደንግጦ ወደ ሙዚቀኞቹ ተመለሰ። እነሱ ሙዚቃውን ሳያቋርጡ ቀጠለበት። እሱም ግራ እንደተጋባ… “ነይ እርግብ አሞራ” ብሎ የጀመረውን ጨርሶ ከመድረክ ወረደ።ጋዜጠኞች1
እኛ (ጋዜጠኞች ማለቴ ነው) በሚቀጥለው ቀን፤ ለቁርጥ እና ለጥብስ የሚሆን ብዙ ፓውንድ ስጋ ከስካይ ላይን ገዝተን፤ በቅርብ ርቀት ላይ ከሚገኘው ከሲሳይ አጌና ቤት ተገናኝተን፤ ከስጋው ጋር ገጠመኛችንን እያወራን ተሳሳቅን። ጃሉድ በመድረክ ላይ የሰራው ድራማ ለሁላችንም አስቂኝ ነበርና እሱንም ሌላውንም ነገር እያወራን ቀኑ ተጋመሰ።

(ቀሪውን በPDFያንብቡ) ESFNA and final days

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on July 8, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.