የጎሣ ፖለቲካ፣ የጎሣ ግጭቶች እና መዘዛቸው በኢትዮጵያ (ከያሬድ ኃይለማርያም)

(በዘመነ ወያኔ)
(ክፍል አንድ)
ብራስልስ፣ ቤልጂየም፤ መጋቢት 1 ቀን 2006 ዓ.ም.

መግቢያ
ይህ ጽሑፍ በኢትዮጵያ ላለፉት አስርት አመታት ጎሣና ኃይማኖትን መሰረት አድርገው በተደጋጋሚ ጊዜያት በተከሰቱት ግጭቶች ዙሪያ እና ግጭቶቹ ባስከተሉት ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳት ላይ የሚያተኩር ነው። በተለይም ከ1983 ዓ.ም. ወዲህ ጎሣን መሰረት ያደረገውን የኢሕአዴግ ፌዴራላዊ የመንግስት አወቃቀር ተከትሎ በአገሪቱ የተለያዩ ክልሎች ውስጥ የተከሰቱ ዋና ዋና ግጭቶችን ይዳስሣል። ለግጭቶቹ መንስዔ ተደርገው የሚጠቀሱትን ጉዳዮች፣ በግጭቶቹ ሳቢያ በሰው ሕይወትና በሕዝብ ንብረት ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠን፣ ግጭቶቹ እንዳይከሰቱ ለመከላከልም ሆነ ከተከሰቱ በኋላም ለማብረድ እና ዘላቂ በሆነ መልኩ ለመፍታት በመንግስት የተወሰዱ እርምጃዎች፣ የመንግስት የግጭቶች አፈታት ስልት፣ እና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮችን ይህ ጽሑፍ በመጠኑ ይዳስሳል።

የጽሑፉም ዋነኛ ዓላማ ጎሣን እና ኃይማኖትን መሠረት አድርገው የሚቀሰቀሱ ግጭቶች፤ ሰብአዊ መብቶች በገፍ በሚጣሱበት፣ ዴሞክራሲያዊ መብቶችና ነፃነቶች በማይከበሩበት እና የሕግ ልዕልና ባልተረጋገጠበት፤ እንዲሁም ነፃና ገለልተኛ የፍትሕ ተቋማት በሌሉበት እንደ ኢትዮጵያ ባለ አገር ውስጥ የሚኖራቸውን መጥፎ ገጽታ ማሳየት ነው። በተለይም የኢሕአዴግን የጎሣ ፖለቲካ አወቃቀር ተከትሎ በአገራችን ተደጋግመው በመከሰት ላይ ያሉት የጎሣ ግጭቶች በአገሪቱ የልማት እንቅስቃሴዎችና በሕዝቡ ሰላምና ደኅንነት ላይ የሚያስከትሉትን ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ ቀውሶች ማመላከት ነው። Read in PDF: የጎሣ ግጭቶጭ – ክፍል አንድ

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on March 11, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.