የግንቦት 7 የግፍ ተግባር እና የመገናኛ ብዙሃን ዝምታ – ያሬድ ኃይለማርያም

በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ፤ የወያኔ ሳያንስ የነፃ አውጪዎቻችን (የግንቦት 7) የግፍ ተግባር እና የመገናኛ ብዙሃን ዝምታ

ያሬድ ኃይለማርያም

ከብራስልስ

ጥር 29 ቀን 2006 ዓ.ም.

yared_hailemariam

Yared Hailemariam worked for seven years for the Ethiopian Human Rights Council (EHRCO) as a human rights investigator before he was forced to live in exile following the massacre on November 1 and 2, 2005 in Addis Ababa.. Click here t read his testimonies at the EU.

ከተወሰኑ ወራቶች በፊት “ወያኔ የሚፈጽማቸውን ስህተቶችና ወንጀሎች ሌሎች ሲፈጽሙት ትክክል ወይም ሕጋዊ ሊሆን አይችልም” በሚል ርዕስ አጠር ያለ ጽሑፍ ለአንባቢያን አቅርቤ ነበር። መልዕክቱም የኢትዮጵያን ሕዝብ የመከራ እድሜ እናሳጥራለን፣ ከዛሬዎቹ ጨካኞችና አፋኞች እጅ ነጻ እናወጣለን ብለው፣ ምለውና ተገዝተው እራሳቸውን በፖለቲካ ድርጅት ዙሪያ ያደራጁ ቡድኖች የአገርንና የሕዝብን ዘላቂ ጥቅም እና ደህንነት ሲጎዱም ሆነ አደጋ ላይ የሚጥሉ ተግባራቶችን ሲፈጽሙ እየያየ ዝም ልንላቸው አይገባም፤ ‘ሳይቃጠል በቅጠል’ እንዲሉ ዛሬ በእንጭጩ ከጥፋትና ከሕገ ወጥ ተግባራቸው እንዲታቀቡ ሕዝብ ሊገስፃቸው ይገባል የሚል ነበር። በዚሁ ርዕስ ላይ በድጋሚ እንድመለስበት ያስገደደኝ ሰሞኑን በተከታታይ ከወደ ኤርትራ የሚሰማውና እጅግ አሳዛኝም አሳፋሪም የሆነው የኢትዮጵያዊያን እሮሮና ሰሚ ያጣው የድረሱልን ጥሪያቸው ነው።

ኢትዮጵያዊያን በየተሰደዱበት አገራት ከሰው ተራ ወጥተውና ተዋርደው የሚያሳልፉትን የስደት ሕይወት፣ የሚደርስባቸውን በደልና የሰብአዊ መብት ረገጣ በተለይም ከሳውዲ፣ ከየመን፣ ከሱዳን፣ ከቤሩትና ሌሎች የአረብና አፍሪቃ አገራት ሆነው በየቀኑ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃይ የሚያሰሙትን የድረሱልን ድምጽ፣ የመንግስት ያለህ፣ የወገን ያለህ፣ የፍትህ ያለህ እያሉ የሚያቀርቡትን ጥሪ እየሰማን ነው። ለእነዚህ ወገኖቻችን  በቂ የሆነ ምላሽ ሳንሰጥ በጭንቀት በተዋጥንበት በዚህ ወቅት ለኢትዮጵያ ነፃነት እንታገላለን የሚሉ ባለ ነፍጥ ድርጅቶች የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት ከሆነው ሻቢያ ጋር በማበር በኤርትራ በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ላይ ተመሳሳይ በደልን እያደረሱ መሆኑ ሲሰማ ከማሳዘኑም ባሻገር ግራ የሚያገባ ሆኗል። የበለጠ ግራ የሚያገባውም በሳውዲ፣ በሱዳን፣ በሊቢያ፣ በየመንና ሌሎች አገሮች በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን እየተከታተሉ ይዘግቡ የነበሩ በውጭ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን ከወደ ኤርትራ ለሚሰማው የወገን ስቃይ ‘አይናችንን ግንባር ያድርገው’ በሚል ድምፃቸውን አለማሰማታቸው ነው። ለነገሩ ይህን የመገናኛ ብዙሃን ለፍትህ፣ ለዴሞክራሲ፣ ለሰብአዊ መብቶች እና ለሕግ የበላይነት ያላቸውን የተዛባ ምልከታ በቅርቡ ‘የግንቦት ሰባት ሁለገብ ጋዜጠኞች ክሽፈት’ በሚል ርዕስ አንዳንድ ማጣቀሻዎችን በማንሳት ገልጬ ነበር።

ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነኝ ዋናው ፍሬ ነገር የእነዚህን የመገናኛና ብዙሃን መድረኮችን ትኩረት ሊያገኝ ስላልቻለውና በኤርትራ ውስጥና ከኤርትራ መንግስት ጥቃት ሸሽተው በሱዳን ስላሉት ወገኖች የድረሱልን ጥሪ ድምጽ ነው። በቅርቡ እራሱን ከግንቦት 7 ድርጅት በመነጠል ‘የግንቦት 7 ዲሞክራቲክ’ በሚል የተቋቋመው ቡድን በተከታታይ በድርጅቱ ድህረ-ገጽ (http://www.ginbot7d.org/) በድምጽና በምስል አስደግፎ ያወጣቸውን የተበዳዮች እሮሮ የሚመለከት ነው። ጉዳዩን በአጭሩ እንዲህ ነው። ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ ጊዜያት በዶ/ር ብርሃኑ እና በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በሚመራው ግንቦት 7 የቀረበላቸውን የትግል ጥሪ በመቀበል እና በድርጅቱና በአመራሮቹ ላይም እምነት ያደረባቸውና አገራቸው ነፃ እንድትወጣ የሚፈልጉ ኢትዮጵያዊያን ከኢትዮጵያ፣ ከተለያዩ የአፍሪቃ አገራትና ከአውሮፓ ተመልምለው በኢሳያስ አፎርቄ መንግሥት ትብብር ወደ ኤርትራ ከተወሰዱ በኋላ ለከፋ የሰብአዊ መብት እረገጣ የተዳረጉ መሆኑን ተበዳዮቹ በአንደበታቸ የደረሰባቸውን ስቃይና እንግልት እያነቡ ገልጸዋል። እነኚህ ግለሰቦች ወደ ኤርትራ ከመጓዛቸው በፊት በግንቦት 7 አመራር አባላት ተደጋግሞ በኤርትራ ስላለው ሁኔታ እና ስለድርጅቱ አቋም ብዙ ነገር እንደተነገራቸው፤ ይሁንና የተነገራቸ ነገር ሁሉ ሥፍራው ላይ ሲደርሱ ሃሰት ሆኖ ማግኘታቸው፤ እንዲሁም የድርጅቱን ዝርክርክ አሰራርና ብልሹ አመራር አስመልክተው ጥያቄዎች በማንሳታቸው የተነሳ በግንቦት 7 አመራሮች ከተፈጸመባቸ በደል ባሻገር በቅጣት መልክ ተላልፈው ለኤርትራ የፀጥታ ኃይል መሰጠታቸውን ገልጸዋል። በኤርትራ መንግስት ቁጥጥር ስር ሆነውም እጅግ ለከፋ የእስር ሁኔታ፣ ለድብደባና የማሰቃየት ተግባር፣ ለበሽታና ለርሃብ የተዳረጉ መሆኑን፤ እንዲሁም ከመካከላቸው የተገደሉ ሰዎች መኖራቸውን ነው ዝርዝር ማስረጃቾችን በመጥቀስ ገልጸዋል። በአሁን ወቅት በእስር ላይ ከሚገኙትም መካከል የአ.አ. ዩንቨርሲቲ ምሩቅ የሆነው አቶ ትእግስቱ ብርሃኑ እና አብረውት የሚገኙ ሌሎች እስረኞች በማናቸውም ጊዜ በኤርትራ መንግሥት ሊገደሉ እንደሚችሉ የወጡት ዘገባዎች ይጠቁማሉ።

በግንቦት 7 እና በኤርትራ መንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ጥቃት ሰለባ የሆኑት አብዛኛዎቹ ግለሰቦች በቅርቡ ‘የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል’ በሚል ለአንድ አመት ያህል በበርካታ ድኅረ-ገጾች፤ በተለይም የኢሳት ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ ‘ሁለገብ’ ጋዜጠኞች አማካኝነት በርካታ ፕሮግራሞችን እየተዘጋጁ ያስተዋውቁን የነበረው ቡድን አባላት ናቸው። እንደውም አንዳንዶቹ በነዚህ የመገናኛ ብዙሃን በስልክ እንዲቀርቡ እየተደረገ የወሬ ዘመቻውን ነጋሪት ጎሣሚዎች ነበሩ። ዛሬ እነዚህ ወገኖች ህይወታቸው በአደጋ ላይ ሲወድቅ እና ‘የከፋ የመብት እረገጣ ተፈጽሞብናል፣ ተሰቃይተናል፣ ነፍሳችንን አድኑን፣ ግንቦት 7 ከኤርትራ መንግሥት ጋር በመሆን የሚፈጽመውን ሕገ ወጥ ተግባራትና በገዛ አባላቱ ላይ የሚያደርሰውን አፈናና ወከባ ሕዝብ ይወቅልን፣ ሌሎች ወገኖቻችንም እውነተኛ ትግል ያለ መስሏቸው ተታለው ወደ ኤርትራ ምድር እንዳይሄዱና እኛን የገጠመን አይነት መከራ እንዳይደርስባቸው ታደጉዋቸው’ በሚል ጥሪ ሲያቀርቡ የሰማቸ ያለ አይመስለኝም። እርግጥ ነው የግንቦት 7 ልሳን የሆነው ‘ኢሳት’ እንዲህ ያሉ የሕዝብ ብሶቶችን በካድሬ መነጽር ስለሆነ የሚመነዝረው ምንም እንኳን ጉዳዩ ኢትዮጵያዊያንን እና ኢትዮጵያን የሚመለከት ቢሆንም የግንቦት 7ን አካሄድ የሚያደናቀፍ ወይም የሚገታ መስሎ የታየውን ማንኛውንም ጉዳይ ለማስተናገድ ተፈጥሮው ስለማይፈቅድለት በድርጅት ልሳንነቱ ልንተወው እንችላለን። ይሁንና በውስጡ የሚሰሩት ‘ጋዜጠኞች’ ለእንዲህ አይነቱ ጉዳይ የሚራራ ልቦና እና እውነቱን ለሕዝብ እንዲታወቅ ለማድረግ የሚያስችል መንፈሳዊ ብርታት ማጣታቸው ግን ትንሽ ያስገርማል። ይህ አይነቱ ክሽፈት በኢሳትና በኢሳት ጋዜጠኞች ብቻ ሳይሆን በሌሎች በእዚሁ ሙያ የተሰማሩ የሕዝብ የመረጃ ምንጭ ለመሆን ለራሳቸው ቃል ገብተው የተለያዩ የመገናኛ መድረኮችን የተቆጣጠሩ ባለሙያዎች ተመሳሳይ ግርዶሽ ውስጥ መሆናቸው ከማስገረም አልፎ የሚያሳስብ ነው።

ግንቦት 7ን በተመለከተ እና በተለይም የድርጅቱ አመራ አባላት ከላይ የተጠቀሱትን ንጹሐን ዜጎችን ‘በነፃነት ትግል’ ስም ወደ ኤርትራ እየወሰዱ እያደረሱባቸው ስላለው በደል እና ግፍ ወደፊት በዝርዝር እመለስበታለሁ። በዝርዝር ስል የተበዳዮችን ማንነት፣ የደረሰባቸን የመብት እረገጣ፣ በማን እና እንዴት፣ የግንቦት 7 አመራሮች ያላቸውን ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ ተሳትፎ፣ ስንት ሰዎች በእስር እንደተጉላሉ፣ ስንቶች ሕይወታቸው እንዳለፈ፣ ስንቶች ከኬንያ ተመልምለው ወደ ኤርትራ ከተወሰዱ በኋላ ይህ ነው ያማይባል ስቃይና መከራ አይተው በድጋሚ ከኤርትራ ተወስደው በኡጋንዳና በኬንያ ከተሞች እንደተበተኑ እና ሌሎች ዝርዝር መረጃዎችን ወደፊት ሁኔታው እንዳመቸ ለሕዝብ ይፋ አደርጋለሁ። ለነገሩ ይህ አይነቱ በዜጎች ሕይወትና ተስፋ የመቀለዱ ተግባር የተጀመረው ዛሬ ሳይሆን ገና ግንቦት 7ን ለማቋቋም ሸርጉድ ከሚባልበት ጊዜ ጀምሮ ስለሆነ ታሪኩ ብዙ ነው። የብዙ ወጣት ኢትዮጵያዊያኖችም ሕይወት በዚህ መያዣና መጨበጫ በሌለው የግንቦት 7 ቅዥት ተደናቅፏል፣ በርካቶችም ለወያኔ የደህንነት ኃይሎች ሲሳይ ሆነውና በሽብርተኝነት ተወንጅለው በሃሰት የበርካታ አመታት እሥራትን ተከናንበው በየማጎሪያ ቤቱ ፍዳቸውን እይቆጠሩ የገኛሉ፤ ከታሳሪዎቹ መካከል የተወሰኑት ቤተሰቦቻቸውም ተበትነዋል።

እንግዲህ ነፃነትን የማያውቁት ገዢዎቻችን ብቻ ሳይሆኑ ‘ነፃ አውጪዎቻችንም’ ጭምር እንደሆኑ ልብ ልንል የገባል። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በመጽሐፋቸው ርዕስ ‘ነፃነትን የማያውቁ ነፃ አውጪዎች’ በሚል የገለጹት የገዢው መንግሥት ባህሪ እርሳቸውንና ድርጅታቸውንም የተጠናወተው መሆኑ ልብ ሊሉ ይገባል። ለዚህም እርቀን መሄድ ሳያሻ በቅርቡ ከወደ አስመራ ብቅ ብለው የራሱን ሕዝብ በማፈን፣ በማሰቃየት፣ ጋዜጠኞችንና የፖለቲካ ተቀናቃኞቹን በማዋከብ፣ በመግደልና ለአመታት አስሮ በማሰቃየት፤ በጥቅሉ ሰብአዊ መብቶችን በከፋ ሁኔታ በመጣስ አለም ያወቀውን አንባገነናዊ የአቶ ኢሳያስን አስተዳደር ሲያሞካሹና ዲሞክራት አድርገ ሲያቀርቡ ሰምተናል። ለዚህ ምስክርነታቸው ከበርካታ ኤርትራዊያን እና ለሰብአዊ መብቶች መከበር ከቆሙ ኢትዮጵያዊያን በቂ ምላሽ ስለተሰጣቸው በዚህ ጉዳይ ብዙ ከማለት እቆጥባለው። ነገር ግን እሳቸውንም ሆነ ድርጅታቸውን ለማሳሰብ የምወደው የኤርትራ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ባለው ግፍ እና መከር በዚ መልኩ መሳለቅ፤ እንዲሁም የአቶ ኢሳያስ መንግስት በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊያን ላይ እየፈጸመ ያለውን ደባና የመብት እረገጣ ችላ በማለት አብሮ መቆም ወደፊት በታሪክም ሆነ በሕግ እሳቸውን፣ ድርጅታቸውን እና የአመራር አባላቱን የሚያሰጠይቃቸው መሆኑን ነው። ለነገሩ ይህ ሂደት ባጭሩ ታሪክ እራሱን እየደገመ እንደሆነ ነው የሚያሳየው። የአንባገነኑን የደርግን ሥፍራ ወያኔ ከነ ጎሰኝነት መርዙ፣ የወያኔን በሻቢያ ጉያ ስር ተወሽቆ ኢትዮጵያን የማተራመሱን ተግባር የዛሬው ታጣቂ ግንቦት 7፣ ሻቢያ ያንኑ ቦታውን ሳይለቅ ገዢም፣ ነጻ አውጭም፣ ተባባሪው ሻቢያም አንድም ሦስትም ሆነው ቀጥለዋል። ሰብአዊ መብቶችን፣ ዲሞክራሲን፣ ፍትሕንና የሕግ የበላይነትን በተመለከተ በነዚህ አካላት መካከል ምንም አይነት ልዩነት አይታይም። አንድ አይነት ባህሪይ ነው የሚታይባቸው። ልዩነታቸው የሚገኙበት ሥርፍራና ድርጅታው ተልኳቸው ነው። ተልኳቸም የሚያስፈጽሙበት መንገድ ግን ከሞላ ጎደል አንድ ነው።

ጽሑፌን በሦስት መልዕክቶች ላጠቃልል፦

 • በውጭ የምትገኙ የመረጃ መድረኮች፣ ድኅረ-ገጾች፣ የዜና ማሰራጫ ጣቢያዎች (ኢሳትም ቢሆን)፣ የመገናኛ ብዙሃን (ጀርመን ድምጽና ቬኦኤንም ጨምሮ)፤ በእርግጥም ለሰብአዊ መብቶች፣ ለፍትሕ እና ለዲሞክራሲ እኩል ከልባችሁ ትወግኑና ትቆሙ እንደሆነ እና ሙያዊ የሥነ-ምግባር ግዴታችሁ በአግባቡ ትወጡ እንደሆነ የኢትዮጵያዊያን (የሰው ልጆች በጠቅላላ ማለት ይቻላል) መብት በማንም ይሁን በየትም ሥፍራ ሲጣስ ድምጻችሁን በማሰማት ሕዝቡ ማወቅ የሚገባውን መረጃ አድርሱ። በሰብአዊ መብቶች ጥሰት ዙሪያ መደራደርም ሆነ የአንዱ ገበና እየከለሉ የሌላው እያሳጡ መቀጠል ሙያው የሚፈቅደው ተግባር አይመስለኝም። የተበዳዮችን ድምጽና የናተን ዘገባ ዛሬ የሚሰማ ሥልጣን ያለው አካል ባይኖር እና አፋጣኝ መፍትሔ ባይገኝም እንኳን የሰብአዊ መብት ጥሰት ተግባሮች በወንጀልም ሊያስጠይቁ የሚችሉ ሰለሆነ ጊዜና ሁኔታዎች ሲፈቅዱ በደል አድራሾቹ ከፍርድ አደባባይ ይቆማሉ። የእናንተም ዘገባዎችና ማስረጃዎች በአስረጅነት ይጠቅማሉ።
 • ለኢትዮጵያ ወጣቶች በሙሉ እርግጥ ነው ፍትሕና ነፃነት ዋጋ የሚያስከፍሉ ነገሮች ናቸው። በፍርሃት፣ በስደትና በሽሽት ነፃነት አትገኝም። ይሁንና እራስህን ነፃ ለማውጣት የምትመርጠውን መንገድ ‘ሀ’ ብለህ ከመጀመርህ በፊት አቅምህ የቻልውን ያህል የመንገድህን አዝላቂነት፣ ካሰብከውና ከተመኘኸው የነፃነት ድንበር ማድረስ አለማድረሱን በጽኑ መርምር። እንደኔ እንደኔ ከፍ ያለ መንፈሳዊ ወኔን የሚጠይቀውም ሆነ ከፍ ወዳላ የነጻነት ማማ የሚያዘልቀው ፍጹም ሰላማዊ የሆነው የፖለቲካ ትግል ነውና የአገርህን ድንበር ሳትለቅ በአገር ውስጥ ለፍትሕ፣ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ ከሚታገሉት የፖለቲካ ኃይሎች ጎን በመቆም እራስህንም ሆነ አገርህን ከወያኔ አንባገነናዊ ሥርዓት መንጋጋ ለማውጣት ታገል። ለነጻነት ትግል ብለው ኤርትራና ሌሎች ጎረቤት አገሮች ገብተው የሥልጣን ጥመኝነትና ቂም ባረገዙ ቡድኖችና የኢትዮጵያ ጠላቶች ከሆኑት እንደ ሻቢያ ያሉ ኃይሎች መንጋጋ ውስጥ ገብተው በየሜዳው ከቀሩና ከስቃይ ተርፈው ምስክርነት እየሰጡ ካሉ ወንድምና እህቶችህ ተማር።
 • የመጨረሻው መልዕክቴ በተለያዩ ጊዜያት በግንቦት 7ም ሆነ በሌሎች ድርጅቶች ጉትጎታ ኤርትራና ሌሎች ጎረቤት አገሮች በመሄድ በቀቢጠ ተስፋ በተደገሱ የነፃነት ትግል ድርጅቶች በደል የደረሰባችው፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት የተፈጸመባችሁ ወገኖች ሌሎች ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ ከእናንተ እንዲማሩና በሰላማዊ ትግል ላይ ጊዜና ሕይወታቸን እንዲያጥፉ በአደባባይ ወጥታችሁ ምስክርነታሁን ስጡ።

እንግዲህ የወያኔ የሰብአዊ መብቶች ጥሰትና አፈና አንገፍግፎን እያሰማን ያለነው ጩኸት ሳያበቃ ዛሬ ደግሞ ‘ነፃ አውጪዎቻችንንም’ በዚሁ እረድፍ ተሰልፈው ስናይ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል ከድጡ ወደ ማጡ እየሄደ ለመሆኑ አንድ ምልክት ሊሆነን ይችላል። የኢትዮጵያ ሕዝብ አምባገነን ገዢም ሆነ የመብቱ እረጋጭችን በታሪኩ አጥቶ አያውቅምና ነገንም ልታጨልሙብን እንቅልፍ አጥታቸው ከሻቢያም ሆነ ከወያኔ የአፈና ልምድ እየቀሰማችሁ ያላቸሁ ‘ነፃ አውጪዎቻችን’ ከዚህ እኩይ ተግባራችው ትታቀቡ ዘንድ እንደ አንድ የሰብአዊ መብት ተሟጋች እማፀናለሁ። የአለም መሳቂያም አታድርጉን። እንኳን ገዢዎቻቸው ነጻ አወጪዎቻቸውን መኑኑም ስያዙት አንባገነኖችና የሰብአዊ መብት እረጋጮች ናቸው አታስብሉን። ምድራችሁም ሆነ የሕዝባቸው ባህል ዲሞክራሲ፣ የሕግ ለዕልና እና ፍትሕ የማያበቅል፣ ቢያበቅልም ፍሬ ሳያፈራ የሚያክስም በርሃ ነው ለሚለው የምዕራቡ ዓለም ትችት ማጠናከሪያ አትሁኑ።

‘ሁሉም ሰብአዊ መብቶች ለሁሉም’

በቸር እንሰንብት

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 6, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

32 Responses to የግንቦት 7 የግፍ ተግባር እና የመገናኛ ብዙሃን ዝምታ – ያሬድ ኃይለማርያም

 1. Pingback: የግንቦት 7 የግፍ ተግባር እና የመገናኛ ብዙሃን ዝምታ – ያሬድ ኃይለማርያም - EthioExplorer.com | EthioExplorer.com

 2. Nesanet

  February 6, 2014 at 1:07 PM

  Well written. The truth is offically coming out. Down with killer and courrapt party.

  IP Address: 174.236.200.144
  Hostname: 144.sub-174-236-200.myvzw.com
  IP Country: United States
  IP Country Code: USA
  IP Continent: North America
  IP Region: Virginia
  IP City: Rockville
  IP Latitude: 37.7232
  IP Longitude: -77.7125
  Organization: Verizon Wireless
  ISP Provider: Verizon Wireless

 3. Abegaz

  February 6, 2014 at 1:26 PM

  EMF, I do not think entertaining this piece is useful for the cause of the struggle. If not contributing to the struggle, better to avoid name calling. In any guerilla fighting there are military disciplines to follow. The punishment usually are severe. Otherwise the struggle will not meet the result needed. EPLF and TPLF passed through this military exercise. Guerilla fighting is not discussion in round table. Echoing the splinter Ginbot 7D which is supported by Aiga is hameful to EMF.

 4. Sam

  February 6, 2014 at 2:06 PM

  yared is right. Only peaceful political struggle is the only way to go in Ethiopian politics. Almost all opposition party politicians attest the reason that EPDRF has a hard time embracing democracy emanates from its political culture embedded in armed struggle. Those who seize power, they say, using weapons would not be the one to implement democracy. They have a point to some degree. But some politicians among them discredit their own argument by resorting to armed struggle. Namely Ginbot 7. The leaders of Ginbot 7 are political illiterates. Not only they tossed away their belief when the going got tough, but also failed to acknowledge in today’s Ethiopia such misguided political strategy is fruitless. We have heard about Ginbot 7 armed struggle for some time now, but I have never heard a single armed struggle they have done so far. They could not. Ethiopians have no appetite for another Ethiopians killing Ethiopians adventure. Besides EPDRF is well-suited to strangle such effort from its outset. So then why some wonder the Ginbot 7 leaders chose such a dead-end politics? My belief is the leaders share Isayes’s fantasy. Isayes at least in his mind believes he has a power to reshape Ethiopian politics. They embraced that delusion. But the fact is Isayes is a dictator whose political survival depends on political oppression of his own people. Is that a secret for Ginbot 7 leaders that Isayes is a dictator? If it is the Ginbot 7 leaders are not what Ethiopians want as leaders. It is an organization they wish to disarm. pretty soon Ginbot 7 will evaporate.That is for sure. An organization parked in North America which has no following here let alone in Ethiopia cannot survive long. I take that back. In today’s politics to exist as a political party what you need is a web site. They have that. Well, Isayes’ delusion and money might help to prolong their delusion as well. The real losers are those who believed in Ginbot 7 and went to Eritrea to take orders from Eritreans. That is really sad. I hope that will come to an end pretty soon as the more people learn Ginbot 7 exists because Isayes want it to exist.

 5. GETACHEW REDA

  February 6, 2014 at 2:40 PM

  ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ)
  ክቡር ወንድሜ አቶ ያሬድ ሃይለማርያም፡

  ይህ ድረገጽ ከጐበኘሁ ብዙ ጌዜ ሆኖኛል። ጎብኝቼም ከሆነ “የግንቦት 7 የግፍ ተግባር እና የመገናኛ ብዙሃን ዝምታ” የሚለው ጽሑፍህ አጋጣሚ ሆኖ ልብ አላልኩትም ማለት ነው። መቸም ይህ የጻፍከው በማንም ስብአዊነት የሚሰማው ኢትዮጵያዊ ዜጋ የሚደገፍ እና የሚያስመሰግንህ ነው። እዚህ የጻፍከው የግንቦት 7 ሰለባዎች እሮሮ በሙሉ የተቃዋሚ ድረገፆች አንዲዘግቡት በተደጋጋሚ ብቻዬን ስጮህበት የነበረ እና “የብዙሃን አገልጋዮች” ነን የሚሉን እኔ እና አንተ እያወገዝናቸው ያሉት የተቃዋሚ ድረገፆች የኔን ጩኸት እንዳበደ ሰው በመቁጠር፤ ይህ የሰው ልጅ ሰቆቃ እና አስደንጋጭ ዜና ጀሮ ዳባ ብለው የሰው ልጅ ስቃይ ከመጠፍ ያልቆጠሩ በጣም አሳፋሪዎች፤፤ቡድናዊ ወገንተኞች መሆናቸው በዚህ ድረገጽ አንድ ምስክር አንተን ማግኘቴ በጣም ነው ደስ ያለኝ። ለዚህም ከልቤ አመሰግናሃለሁ። እውነት የሰው ልጅ ስቃይ በማንም ይሁን በማን ሲደርስ ለፍትህ ቆመናል፤ የሰፊው ሕዝብ ጆሮ እና ምላስ ነን የሚሉን በውሸት የተለወሱት የግንቦት 7 ጋዜጠኞች፤ የቪ.ኦ.ኤ፤ የጀርምን እና ሌላ ቀርቶ የእነ “መንግስቱ ሃይለማርያም” ስልክ አንኳ ሳይቀር ማግኘት የማይቸግራቸው የቋጠሮ እና የግንቦት 7 ጋዜጠኞች፤ የእነዚህ ሰዎች እሮሮ መዘገብ የለገሙበት ምክንያት አንተ አንዳልከው “ግንቦት 7” የሚባለው ቡድን በእነዚህ ሚዲያዎች ውስጥ ሰርጎ ገብቶ አባሎቹ አንዲቆጣጠሩት በማድረጉ ጥር ር የለውም።

  አብዛኛዎቹ ተቃዋሚ ሚዲያዎች በግንቦት 7 መሪዎች በተለይም በብርሃኑ ነጋ የተሰለቡ አሳፋሪዎች በመሆናቸው፤ የብርሃኑን ስም በመጥፎ እንዳይነሳ እና እነሱም አብረው የግንቦት 7ን አደናጋሪ ፖለቲካ አብረው በሚዲያቸው ሲያጫፍሩ እና ብርሃኑም ሆነ ጃዋር መሐመድ ኢትዮጵያን ከወያኔ የሚታደጓት ናቸው እያሉ ሕዝባችንን ሲያሳስቱ ስለነበር አባሪ ተባባሪ ገመናቸው አንዳይጋለጥባቸው በመሸማቅ ነው። ይህ አድላዊ ቡድናዊ አገልግሎታቸውም፤ የሰው ልሆች ስቃይ እያዩ፤ እያነበቡ፤ እየሰሙ እና እየተነገራቸው እንዳልሰሙ እነዳላወቁ መሆን፤ ከወንጀለኞቹ ምንም አልለያቸውም፤፡ ለዚህም ነው ፤ደጋግሜ በቃለ መጠይቄ “ፍትሃዊ፤ሕዝባዊ የተቃዋሚ ሚዲያ የሚባል የለም፡ እያልኩ ስሞግት የነበርኩት። አሁን ሙግቴ ትክክለኛ መሆኑን ይኸው እያሳዩን ነው።

  በጣም የሚያሰዝነው ደግሞ መከራውን ያልቀመሱት ውጭ አገር በሞቀ ቤት እየኖሩ በእነ በርሃኑ ነጋ እና አንዳርጋቸው የውሸት ቅስቀሳ በስሜት ሰክረው የምናያቸው አንዳንድ የግንቦት 7 ተኰልኳዮች/ፑፔትሰ ኢንተርኔት ውስጥ ሰለባዎችን “የወያኔ ሰላዮች” በማለት አንኔንም የሰለባዎቹ ስቃይ ለሕዘብ በማስተጋባቴና በመዘገቤ ተነመሳሳይ ስም በመስጠት የወንድሞቻቸው ስቃይ ደመከልብ ሆኖ አንዲቀር የወንጀለኞዩ ተባባሪዎች የሆኑትንም እዚህ ላይ ሳልጠቅስ አላልፍም።
  እንዲህ ያለው የሚዲያዎች እውርነት ሆን ብለው ካሁን በፊትም በኦነግ እና በመሳሰሉ ጸረ አማራ ድርጅቶች እና ወንጀለኞችንም አሽሞንሙነው በማቅረብ ሕዝባችንን ለማደናገር ሞክረዋል። ለእነ ተስፋየ ገብራብ ለነ ጃዋር፤ለነ ሌንጮ፤ለነ ስብሓት ነጋ፤ ለመሳሰሉ ጸረ ሕዘብኦች የለገሱላቸው መድረኮቻቸው በእነዚህ ወገኖች ላይ ሲደርሱ ጀሮ ዳባ ብለው ለብርሃኑ ነጋ እና ለአንዳርጋቸው ጽጌ፤ለሻዕቢያ ወንጀል ድርግት ሲቆሙ ከማየት ወንጀል ሌላ ምን አሳፋሪ ተግባር ሊኖር ይችላል?

  የሆኖ ሆኖ በዚህ ጉዳይ ስላደረግከው አስመስጋኝ እርምጃና ሰብአዊነት ከፍተኛ አክበሮት ላንተ አለኝ። በዚህ ላይ የኔ እና ያንተው ትችት ሰምተው ወደ ልቦናቸው እንዲመለሱ አሁንም አንመክራቸዋለን። ሆኖም ጅብ ከሄደ ውሻ ይጮሃል ፤ምን ይረባል። በሰፊው ለመነጋጋር እባክህን በዚህ ኢመይል አግኘኝ። ይህ ጽሁፍ ለሚመለከታቸው ልኬላቸዋለሁ።getachre@aol.com
  ጌታቸው ረዳ
  ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ

 6. አጅረ

  February 6, 2014 at 5:52 PM

  ኣመፍ. ምነው የወያነ መቀለጃ ሆናችህ? እነዚህ ግ7ዲ የሚባሉት የወያነ ሰርጎገቦች መሆናቸውን ረሳችሁ?
  ወያነ የሚፈራው ከሁሉም በላይ ግ7 መሆኑን እያወቃችሁ, ወያነን እየተባበራችሁ ነው እኮ!!
  እንደት ነው በዚህ አይነት የነጻነት ትግሉ ወደፊት የሚሂደው? እነዚህ የወያነ ሰርጎገቦች ግ7ን ለማፍርስ ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም አሁን ሲነቃባቸው ተበደልን ይላሉ? እንደ ህዝብ ጠላትነታቸው እዚያው የትግሉ መዳ ላይ እርምጃ መውሰድ ይገባ ነበር. ኣይጋ ፎረምና አውራምባ ላይ ሲቀባጥሩና የወያነ ጥሩምባ ሆነው ከርመው ደግሞ እዚህ ይስተናገዱ?? ኢመፈ. አፈርኩ!

 7. GETACHEW REDA

  February 6, 2014 at 8:16 PM

  GETACHEW REDA

  ሕዝብ ጆሮ እና ምላስ ነን የሚሉን በውሸት የተለወሱት የግንቦት 7 ጋዜጠኞች የሚለው “የኢሳት ጋዜጠኞች” ተብሎ ይነበብ።
  ጌታቸው ረዳ

 8. T.Goshu

  February 6, 2014 at 8:31 PM

  Well, I do not really know the very ulterior motive of the writer of this piece which sounds highly sensational and hypocritically disinformation. I am not saying it is wrong to be critical toward G-7 or any other opposition political movement for that matter. What I am saying is that the writer has clearly showed all his unhealthy or unconstructive intention right from his topic of discussion. I do not know why people come up with kind of critical but rational comments at least with their very first piece of writings. the writer complain that those who dissented from G-7 are suffering under the Eritrean government. I strongly believe that any Ethiopian with his or her right mind would be negligent enough about this kind of mistreatment on any Ethiopian . Whoever, I sincerely believe that the question of know why and how ( well-investigated information) is required. It is fine to dissent oneself and from another faction calling it ” G-7 Democratic” . But I do not think to be a genuine dissent mean to glorify one’s own way by blackmailing and condemning others. Let us try to get out from this kind of very clumsy political mentality and terribly dirty political game.

 9. ሳተናው

  February 6, 2014 at 10:50 PM

  What a surprise?

 10. ሳተናው

  February 6, 2014 at 11:07 PM

  በጣም ስለ ሳቅሁ የልብ ድካም ይዞኝ 911 እየደወልኩ ነው ይህንን ኣስተያየት የምሰጠው:: ቂቂቂቂቂቂቂቂቂ! ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ! ቁቁቁቁቁቁቁቁቁ!

  ያረድና ጌታቸው ይህን እብድ እንቁላል እንዴት ኣምጠው ወለዱት ጃል!

 11. Nesanet

  February 6, 2014 at 11:27 PM

  Kinfu is a Tigreu undercover who work hard to divide the opposition and very recently tryed hard to divide the Oromo and Amhara for his support of divide and rule weyane regime now he show his naked body of him self by posting weyane garbage .emf and kinfu were tried hard to sell thier weyane propaganda by his cousin newspaper aweramb times of dawit kebede.now Kinfe is the way to follow him to back home to save tplf.

  IP Address: 174.236.226.191
  Hostname: 191.sub-174-236-226.myvzw.com
  IP Country: United States
  IP Country Code: USA
  IP Continent: North America
  IP Region: Virginia
  IP City: Springfield
  IP Latitude: 38.7893
  IP Longitude: -77.1872
  Organization: Verizon Wireless
  ISP Provider: Verizon Wireless

 12. ሳተናው

  February 7, 2014 at 12:21 AM

  Save Shewa 1 hour ago

  አንዳንድ አማራዎች ይገርሙኛል። ትግሬን አጠገባቸው ያቀርቡና ራሳቸውን ሆነ ሌሎችን አደጋ ላይ ይጥላሉ። ይህንን ብታነቡ ይገርማችኋል። =================================== = ስልክ ጠላፊው ሰላይ “ጋዜጠኛ”

  FEBRUARY 6, 2014 LEAVE A COMMENT በማህሌት ነጋ (ሲያትል) ከሁሉ የእኔን ቀልብ የሳበው የቀጂው ማንነት ነበር። ለማጣራት ያደረኩት ጥረት ብዙም ግዜ አልፈጀብኝም። አበበ ገላው በዚሁ “ሊክድ” በተባለው ቅጂ “እኔ ከሞትኩም እንደ ሃየሎም መጠጥ ቤት በከንቱ መሞት አልፈልግም። መሞት የምፈልገው ለአላማ ነው ይላል።” በዚህ ግዜ አንድ ሳቅ ይሰማል። የኢያጎ ሳቅ። ዳዊት ከበደ ስለመሆኑ ብዙም አልተጠራጠርኩም።

  ሰሞኑን አንድ ሚስኪን ጋዜጠኛ ነኝ ባይ ከአንድ የከሰረ ፖለቲካኛ ጋር ቃለ ምልልስ ሲያደርግ በቪዲዮ ለቆ ስለነበር ለሶስት ደቂቃ ያህል ተምልክቼ ጭንቅላቴን በሃዘን እየነቀነኩ ዘጋሁት። እኔን ጨምሮ በርካቶች ድረ ገጾችን የምናስሰው መረጃ ፍለጋ እንጂ የከሰሩ ግለሰቦችን ደረቅ ወግ ለማዳመጥ እንዳልሆነ ለማንም ግልጽ ነው። በአንድ ወቅት ያዙን ልቀቁን ይሉ የነበሩት ሁለት ግለሰቦች የዛሬን አያድርገውና ኢትዮጵያዊያን እንደ ማንዴላ የነጻነት ታጋዮች አድርገው ያከብሯቸው ስለነበር ድምጻቸው የጎላ በራስ መተማመናቸው ከውስጣቸው ሞልቶ በአፋቸው ይገነፍል ነበር። ዛሬ ግን ድምጽ አጥሯቸው ቀልብ እርቋቸው ሲንሾካሾኩ ያየ ሁሉ እንደ እኔ ከንፈር መጦ የሁለቱን ምስኪኖች ወግ በግዜ ዘግቶ ወደ ስራው እንደሚመለስ ብዙም አያጠራጥርም። “ምስኪኖች እነማን ናቸው?” እንደማትሉኝ እርግጠኛ ነኝ:: የአውራምባው ዳዊት ከበደና የኢዴአፓው ልደቱ አያሌው ጉዳይ መቼም አንገት ያስደፋል። ሁለቱም ጠላታቸው ወያኔ እንዳልሆነ እነርሱ እንደሌሎች “ጽንፈኛ” እንዳልሆኑ ሌሎችን ከሰው እራሰቸውን ከፍ ለማድረግ ሲጥሩ ላስተዋለ ጠበል የሚወስዳቸው ያጡ በሽተኞች መሆናቸውን ድርጊታቸው ይመሰክራል። ዲያስፖራውና የግል ጋዜጦች በተለይ የጋራ ጠላቶቻቸው ይመስላሉ። እንደው ለመንደርደሪያ እንጂ የዚህ ጹሁፍ አላማ የሁለቱ ምስኪኖች ወግ ስላልሆነ ወደ ቁም ነገሩ ልመለስ:: ሾተላዩ ሰላይ ዳዊትን ለመጀምሪያ ግዜ በአካል ያገኘሁት ወደ ሲያትል የዛሬ ሶስት አመት በመጣ ግዜ ነበር። አስተባባሪዎች መርጠን፣ ገንዘብ አዋጥተን፣ ድግስ ደግሰን፣ ሽልማት አዘጋጅተን ነበር የጀግና አቀባበል ያደረግንለት። ወቅቱ የብርድ እና የበረዶ ግዜ ስለነበር እኔም እንደሌሎች ይህንን “ጀግና ጋዜጠኛ” ለመቀበል ብዙ መስዋእትነት ነበር የከፈልኩት። በተለይ የኢትዮሜድያው አብርሃ በላይና ሼክስፒር ፈይሳ እንግዳውን ተቀብለው ቤታቸው ከማሳደር አልፈው ለዝግጅቱ ስኬት ያበርከቱት አስተዋስኦ ቀላል አልነበረም። ሰላዩ ጋዜጠኛ ግን አብርሃ በላይን አራክሶ፣ ሼክስፒር ፈይሳን ደግሞ ስምህን አጠፋለሁ ብሎ በማስፈራራት ከንቱነቱን ብቻ ሳይሆን የኢያጎ ባህሪውን ፍንትው አድርጎ አጋልጧል። ይሁንና ኢያጎን (ዳዊትን) በቅርብ የሚያውቁት ሁሉ አትመኑት ማለታቸው አልቀረም። እውነት ለመናገር ዳዊት እነ ውብሸት ታዬ እና ርእዮት አለሙን በማሳሰሩ ድርጊት እጁ አለበት የሚል ሹክሹታ ከወደ አገር ቤት ሲናፈስ ማናችንም የዚህ ጎጠኛ “ጋዜጠኛ” ወዳጆች በቁም ነገር አልወሰድነውም። መቼም ሰው በምልካም ስራው ሲታወቅና ሲወደስ ምቀኛ እንደማይጠፋ ለማንም ግልጽ ነው። ስለዚህም ነበር ዳዊትን አትመኑት የሚለውን የአገርቤት መልእክት ማንም ትኩረት ያልሰጠው። አሁንም ስለዚያ ድርጊቱ ተጨባጭ መረጃ ስለሌለኝ ድርጊቱን ፈጽሟል አልፈጸም ለማለት ባልችልም ከጀርባ የመውጋት ጋህሪውን ለማስተዋል በመቻሌ አያደርግም ብዬ መከራከር አልችልም። ዳዊት ተራ የሆኑ ጉዳዮችን ሁሉ የመቅዳት ባህሪ አለው። ሰው ሲጎርስ፣ ሲጠጣ፣ ሲናገር፣ ሲቀልድ (ከተቻለውም ሽንት ቤት ሲጸዳዳ) ቪዲዮና ፎቶ ማንሳት ድምጽ መቅዳት ይወዳል። በስውር የሚቀዳበት ሪኮርደርም ይዞ እንደሚዞር ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ። ብዙ ሰው ግን የዳዊትን ድርጊት ከጋዜጠኝነት ስራው ጋር ስለሚያያይዘው ተንኮሉን አይጠረጥርም። ነገሩ ያልጠረጠረ ተመነጠረ መሆኑን ነው። አሁን እንደምንሰማው ነዋሪነቱ በአሪዞና ፊኒክስ የሆነው የዳዊት ከበደ ታላቅ ወንድም ብስራት ከበደ የሚታወቀው በተመሳሳይ የመቅዳት ባህሪው ነው። በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት ብስራት ምንም ጭንብል ሳያጠልቅ አይኑን በጨው አጥቦ ስለሚንቀሳቀስ የህወሃት ታማኝ ካድሬና ሰላይ መሆኑ በስፋት ይነገራል። እርሱም እንደ ወንድሙ የትርፍ ግዜ ስራው ስለሆነ እንኳን ፖለቲከኞችን እና ታጋዮችን በስካይፕም ይሁን በስልክ የሚያናግራቸው ሴቶች ምስልና ድምጽ ሳይቀር እንደሚቀዳ በጉራ ይናገራል፣ ለቅርብ ጓደኞቾም ያሳያል። እዚህ ላይ ግለሰቡን እምታውቁ ሴቶች ጠንቀቅ በሉ ማለት ሳያስፈልግ አይቀርም። የኢያጎ ጩቤ ወደ ዲሲ ደዋውዬ እንዳጣራሁት ዳዊት ወያኔ አባረረኝ ብሎ ወደ አሜሪካ ፈርጥጦ ሲመጣ የኢሳት ሰዎችም የተቀበሉት በመልካም አይን ነበር። በተለይ ከሲሳይ አጌና፣ ከመሳይ መኮንን እንዲሁም አበበ ገላው ጋር መልካም ወዳጅነት ለማፍራት፣ አብሮ ለመጠጣትና ለመብላት ግዜ አልወሰደበትም። ለጋዜጠኝነት ስነምግባር እጨነቃለሁ የሚለው ይሄው ግለሰብ ወያኔ ጠለፍኩ ያለውን የዶ/ር ብርሃኑን የስካይፕ ውይይት በድህረ ገጹ ላይ በማውጣት የራሱ አጸያፊ ድርጊት መነጋገሪያ ሆኖ እንደ ነበር ይታውሳል። ዳዊት ከበደ በኢሳት፣ ግንቦት ሰባትን እና ዶ/ር ብርሃኑ ላይ በተከታታይ የሰራውን አሳፋሪ ግን ደግሞ የከሸፈ ፕሮፓጋንዳ ሁሉም ስለሚያውቀቅ መድገም አያስፈልግም። ከሁሉ የገረመኝ ሰሞኑን ዳዊት ኢያጓዊ የስለላ ስራውን ለማራቀቅ መሞከሩ ነው። ሞኝ እራሱን ያታልላል ነው ነገሩ። ልክ እንደ ኢያጎ ዳዊትም ጩቤን በጀርባው ደብቆ ያመኑትን እና ያቀረቡት ሁሉ ላይ ከማሴር ቦዝኖ እንደማያውቅ ሙሉ በሙሉ ግልጽ ሆኗል። በቅርቡ ለመረዳት እንደቻልኩት በርግጥም የዛሬው ኢያጎ ዳዊት ከበደ መስዋእትነት ከፍሏል፣ መልካምነቱንም በስራው አስመስክሯል በማለት እንደ ትግል አጋር ያዩት ከነበሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያን አንዱ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ይገኝበታል። ለዚህም ምክንያት አንዱ ኢያጎ ከእስር ወጥቶ በሲፒጄ ሳይቀር ለፕሬስ ነጻነት ላበረከተው አስተዋጽኦ በታላላቅ የአለማችን ጋዜጠኞች ፊት በኒውዮርክ ቀርቦ ሽልማት ሁሉ መውሰዱ ነው። ይቺም ስኬት ለዳዊት ጥሩ ጭንብል ሆና ቆይታለች። በወቅቱም ወያኔ ይገለኛል ያስረኛል እንጂ አገር ለቅቄ አልሰደድም ብሎ በየመድረኩ ሲደነፋ በእውነትም የጎልያድ ጠላት ቅዱስ ዳዊትን ነበር የመሰለን። ያሁሉ ተረት ሆኖ ወያኔ ሊያስረኝ ነው ብሎ አገር ጥሎ ሲፈረጥጥ አሜሪካ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ክብርና ፍቅር አልነፈጉትም ነበር። የእኛው ኢያጎ ግን ያን ሁሉ ክብር ትቶ በእኩይ ተግባሩ የነጻንት ትግሉን የሚጎዳና የህወሃት አንባገነኖችን በሚጠቅም እኩይ ተግባራት ላይ ለመሰማራት ግዜ አልፈጀበትም። በቅርቡ ወያኔዎች ክፉውን ጎልያድ መለስ ዜናዊን በአለም መሪዎች ፊት አዋርዶና አስደንግጦ የመጨረሻና ወሳኝ ስንብት ላደረገለት ጋዜጠኛና አክቲቪስት አበበ ገላውን ለማስጠላት እንዲሁም ኢትዮጵያዊውን ለመከፋፈል በህገወጥ መንገድ የተቀዳ የግል የስልክ ንግግር አዛብተው፣ ቆርጠውና ቀጥለው በኢንተርኔት ላይ ለቀቁ። ይሄም የተለቀቀው በዳዊት ድርገጽ ሳይሆን በቀንዲል የወያኔ የፈስቡክ አቀንቃኝ ዳንኤል በርሄ አማካኝነት በሆድ አደሩ ሹምባሽ ከበደ ካሳ አቀናባሪነት ነው። ደግነቱ የተባለው ሁሉ ምንም ሚስጥር የሌለው ስለነበር እንዳሰቡት ሳይሳካላቸው እነርሱንው መሳለቂያ አድርጓቸዋል። ከሁሉ የእኔን ቀልብ የሳበው የቀጂው ማንነት ነበር። ለማጣራት ያደረኩት ጥረት ብዙም ግዜ አልፈጀብኝም። አበበ ገላው በዚሁ “ሊክድ” በተባለው ቅጂ “እኔ ከሞትኩም እንደ ሃየሎም መጠጥ ቤት በከንቱ መሞት አልፈልግም። መሞት የምፈልገው ለአላማ ነው ይላል።” በዚህ ግዜ አንድ ሳቅ ይሰማል። የኢያጎ ሳቅ። ዳዊት ከበደ ስለመሆኑ ብዙም አልተጠራጠርኩም። ሳቁ በጣም የተለየች ውስጧ ሸፍጥና ተንኮል ያዘለች ነች። ዳዊትን ለሚያውቁት ወዳጆቼ አስተያየት ሳልሰጥ ይቺን አምልጣ ስትቆረጥ የወጣች ወሳኝ መረጃ አድምጣችሁ የማን ሳቅ እንደሆነ ንገሩኝ ብዬ በኢሜይል አያይዤ ላኩላቸው። አራቱም መልሳቸው አንድ ነው፣ የኛው ኢያጎ ዳዊት ከበደ። ዳዊት በጣም አሳዘነኝ። ብዙ ተስፋ የጣልንበት “ጋዜጠኛና የነጻነት ታጋይ” እንዴት ከክብር ወንበሩ ወርዶ ቆሻሻ ትቦ ውስጥ ይወድቃል? ለነገሩ ከልብ ያልሆነ ነገር ሁሉ እራሱን መግለጡ አይቀርምና ዳዊትም ከልቡ ኢያጎ እንጂ ሌላ አልነበረም። በጣም ተምታቶበታል። እኛ ግን የበለጠ ነቃን። እነዳዊት ከበደ ግን ግራ እንደተጋቡ እንደሰካራም በየትቦው ውስጥ እየወደቁ ይገኛሉ። ተመስገን ደሳለኝ ከጥቂት ወራት በፊት “የፖለቲካ ስር ቁማርተኞች” በሚል የጻፈው አንጀት አርስ ጹሁፍ ትዝ አለኝ። ተመስጌን የጠየቀው መሰረታዊ ጥያቄ በእኔም አእምሮ ውስጥ ያቃጭላል። ለመሆኑ ወደ አገር ቤት ከአሜሪካ ልክ እንደ አመጣጡ ፈርጥጦ ያስመለሰው ጉዳይ የፕሬስ ነጻነት መሻሻሉና “የጽንፈኞችን” ፖለቲካ በመጸየፉ ነው ወይንስ ደግሞ ኢሳትን የማፍረስ እና በጸረ-ወያኔ ትግሉ ግንባር ቀደም ሚና ይሚጫወቱ ኢትዮጵያዊያንን ለማምታታትና ለመሰለል ስላላመቸው? መልሱ ግልጽ ነው። ወያኔዊ ኢያጎነት በቀላሉ እንደማይለቅ ከዳዊት መማር ይቻላል። ዲሲ አካባቢ በቅርብ የታዘቡት እንደነገሩኝ ዳዊት ሁለት ነገሮች አብዝቶ ይወዳል፣ መጠጥና ሴት ማባረር። ከአገር ቤት ፈርጥጦ ዲያስፖራ የተቀላቀለው ዳዊት ሲነቃበትና ይሄ የሱስ ጥማት ሲያስቸገረው ፈርጥጦ እነአቦይ ስብሃት እና ሽመልስ ከማል ጋር ብርጭቆ ማጋጨት መጀመሩን ሰማን። ተመሳሳይ ላባ ያላቸው ወፎች አብረው ግር ይላሉ አሉ ፈረንጆች። አበው ሲተርቱ ግም ለግም አብረህ አዝግም እንዳሉት መሆኑ ነው። መልካም እድል፣ መልካም ቅምቀማ ብለናል ከወደ ሲያትል!!

 13. andnet berhane

  February 7, 2014 at 1:26 AM

  አቶ ያረእድ ሃይለማርያም ይህን ያቀረብከው በትክክል ለመፈጸሙ የተጨበጠ አስረጅ ካቀረብክ በ እውነትም ስለሰባዊ ጥሰቶች በቂና የማይወላውል ለመሆኑ ሁሉም ዜጋ ችቸል የማይለው ባግንቦት 7 አመራሮች ላይ ሆነ በድርጅቱ የሚወሰድ ሕዝባዊ እርምጃ እትጠራጠር: ነገርግን የወያኔ ቅጥረኞች ይህን የተዛባ ወሬ የድርጅቱን አቋምና ፍትኃዊነት ለማደፍረስ ትግሉን ለማንቀፍ የሚደረግ ተንኮል ዋጋው ቀላል አይደለም ለመሆኑ እነንህ ለትግል ሄደው ከትግል ሸተው ሆነ አምልጠው ሱዳን ኬኒያና ኡጋንዳ ያሉ ወጣቶች ሰጡኝ ለምትለው የወከባን የእስራት የግድያ የድረሱልን ጥሪ:
  1ኛ አምልጠው ለመውጣት እንዴት ቻሉ
  2ኛ ወደትግል ስትገባ ትግሉ ያለበት ሃገር ማን እንድሆነ ካወቁ ለምን ሄዱ
  3ኛ ትግልን ስትቀላቀል በተነገረህ ሳይሆን የራስህን ጥናትና የትግሉንም ሁለንተና ተግባሩን ጠንቅቀህ ማወቅና ብዙ አስቸጋሪ ውጣ ውረድድ እንዳለበት ማወቅ ያስፈልጋል
  4ኛ ወደሱዳን ሆነ ወደ ኢትዮጵያ ድምበር ጥሶ መወጣት አስቸጋሪና ገንዘብም መሻገርያ ያስፈልጋል እንዴት ወጢ?
  ሰባዊ ረገጣ ቅትለት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የማይቀበለው ወያነ ሀገር በመሸራረፍ ህዝብ በመለያየት የሚያደርሰው በደልና ሰቆቃ የምንቃወመው እሡን የሚተካ በዳይ ፍለጋ እንዳልሆነ እንተም ታምንበታለህ
  የጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማርያም አፈቀላጤ ጌታቸው ረዳ ትንሽ ቀዳዳ አገኘህ ህልም ነው ውን አይደለም ወያነ የሚሸርበው ትንኮል ሕዝቡ ያውቃል ሰላዮቻችሁ በየ ቦታው በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም የሚመጣው እርዳታ ብር የተገዙ ሎለእዎች የማያቦኩት የለም አንተም ይህችን አግኝተህ አታበራይ እውነቱ አንተው ታውቃልህ: ኢሳት ወደድክም አልወደድክም የኢትዮጵያ ሕዝብ አይን ጆሮ ነው በደሞዝ ሳይሆን ለውድ ሃገራቸው ህዝባቸው ተገቢውን መብትና ነጻነቱን ለማስከበር ቀን ከለሊት የሚጥሩ ብርቅ የኢትዮጵያ ልጆች የሞያው ባለቤች ናቸው እንዳንተ ለከርሳቸው ያደሩ ስላልሆኑ ያለሞያቸው ስም አትለጥፍ ከሆነ ማንነት ለማወቅ በድህረገጽ ሳይሆን በመድረክ ግጠማቸው:
  ያረእድ ሃይለማርያም በድህረገጽ ካማውጣትህ በፊት እውነት የሃገርና የወገን በደልና ሰቆቃ ከገባህ ልምንድነው በደብዳበእ ወይም ባካል ብርሃኑ ነጋን ወይንም እዳልካቸው ጽጌን ለማነጋገር የተፈጸመውን በደል ተበዳዮቹን ቦታና ስም ሳትሰጥ በድርጅቱና በኤሬትራ መንግስት የተፈጸመውን ነጥብ በነጥ መወያየት ያልቻልክ የኢሳት ጋዘእጠኞችን የጀርመን የአሜሪካ ድምጽ የምትኮንነው ከነሱስ ጋር በዚህ ጉዳይ ተወያይተሃል? ይህ ትንሽ ሊገባኝና የትግሉን መንፈስ ለማዳከም የተጠነሰሰ ሴራ መስሎ ይታየኛል:የሚገርመው ወደአንድ መጥተን የሕዝባችንን ስቃይና የሃገራችንን ችግር እንድመፍታት እርስ በርሳችን በመጠላለፍ ሌላ 40 አመት ለመጓዝ አይቻልም በቅቷል ወያነን ስራአቱንና ጥፋቱን ማስወገድ እንጂ ወደኅውላ ተመልሰን ሌላ ትግል አንጀምርም ሁሉም ኢትዮጵያዊ እውነቱን ለማግኘት ጥረት ያድርግ

  • sherif,

   February 7, 2014 at 4:23 AM

   ANDINET BEREHANE,,,JUST STOP YOUR THEORY THE WRITER IS NOT JOURNALIST,,WHAT EVIDENCE DO YOU NEED MORE THAN THIS LIKE YOUR MASTERS START TO LIE BY BLAMING TPLF THAN DEALING WITH FACT,,,,YOU ARE TO PATHETIC AND HYPOCRAT.

 14. Dechasa

  February 7, 2014 at 7:07 AM

  አቶ ያረድ
  አንተ ፈሳም ነህ. አውሮፓ ቁጭ ብልህ ወፍባልዋለብት ትፈራለህ.ፈሪ የወያነ ቀጥርኛ. ለባ

 15. Abegaz

  February 7, 2014 at 8:48 AM

  EMF, Sham! shame! big shame!

  Yared’source of information is Ginbot 7D, which claims a splinter group from Ginbot 7. Ginbot 7D until recently has been working with Aiga, Awrambatimes and TPLF. The former are operatives of TPLF.

  Yared did not bother to find out who Ginbot 7D people are. Nor he tried to find out the reason these people are in Sudan or around. He parroted G7D information. In the first place there is difference between Ginbot 7 and Ginbot 7 Popular force. There may a working relationship but it I essential to distinguish between the two. Even if the two are the same, a person working for gorilla fighting team need to follow those rule. human right is not an issue in those type of business. Military rule is different. A civil person and a military person’s punishment is different, even in the US army let alone in Ginbot 7 force that starts from scratch. I mean if it happens. But Yared’s shouting is based on Ginbot7D information. What a senseless article Yared provides us here. That is precisely what makes our struggle against TPLF makes it hard. I do not know if Yared is to follow Dawit Kebede’ foot print. Yemetelalef poletica beche newe yemiabekaw, senseless Yared!!!

  By the way Kiflu is not the person behind this website. He gives technical help to the site but article posting is not his role. I am responding to one opinion because some think Kiflu is the owner of this website and promoted Yared. He is not in charge of this website as far as I know.

 16. maru

  February 7, 2014 at 8:59 AM

  my comment was not posted since it touches the soft spot of kinfu and I will never visit this website any longer as I have been an active member and has been using emf my prior source and has been visting at least 5 times a day….no more emf…let emf dance with the worthless weyane undercover cadres of g7-democratic stomach headed arrogant worthless elements..

  bye bye

  • ጎራው

   February 7, 2014 at 4:49 PM

   @Maru, you must be the most stupied person. do u think you re the ionly visiting the site. እውነት ለምን ወጣ ብለህ አትንጨርጨሩ;;

 17. አጅረ

  February 7, 2014 at 9:23 AM

  ጌታቸው ረዳ, ወያኔን የሚቃወም መስሎ ሁልጊዜ ከአማራው በላይ “አማራው ተበደለ, አማራ ተነሳ!” እያለ ተቆርቓሪ መሳይ አስመሳይ ዘረኛ, ጠንካራ ኢትዮጵያዊያን ወያኔ ወዳዘጋጀው ወደ ዘር ጉድጛድ እንዲገባ የሚገፋፋ; በአሁኑ ሰአት ህዝቡ አለኝታ ባጣበትና ታፍኖ ባለበት ጊዜ ይህችኑ ብልጭ ያለች የህዝብ ተስፋ መወያያ መተንፈሻ መደራጃ የሆነችውን የኢሳት ድምጽ ወያኔ ብሎ ብሎ ሲያቅተው ግ7ን ለመውቀስ አስታክኮ ይችኑ አለኝታችንን ኢሳት ላይ መጣህባት?? እረ ጎበዝ ነቃ እንበል!!
  አሁን እውነት የሚቃወሙት የሚያወግዙት ጠላት ጠፍቶ ነው እስኪ ኢሳት ላይ ውርጂብኝና ስድብ?
  ግ7 እንደ ፖለቲካ ድርጅት ሊወገዝ ሊነቀፍ ሊታረም ይችላል. እኔም መቼም ወያኔ በአሁኑ ሰአት ህዝቡን በማናለብኝነት ሲረግጥና አገሪቱአን አጥንቱአን ሲግጥ ትንሽ እንኩዋ “ዘራፍ አለሁልህ ነጻ አወጣሃለሁ አይዞህ ወገኔ” ብለው ከተነሱት ጥቂት ድርጅቶች ውስጥ አንዱ ግንቦት7 መሆኑን አምናለሁ:: እንዳለመታደል ሆኖ ያለንበት ጂኦ-ፖለቲካዊ ሁኔታ እንኩዋን ፈጣን ድል ማግኘት ይቅርና ትግሉን ወደፊት ለመግፋት አስቸጋሪ ቢሆንም እንኩዋ በምንም መንገድ ግ7 የህዝብ ጠላት ነው ለማለት አፌን አልከፍትም!! አዎ ግ7 የገቡትን ቃል ፈጥነው ለማሳካት አልቻሉም የውስጥም ይሁን የውጭ ችግር ይኖርባቸዋል:: ወያኔ የጦርና የስለላ ሃይሉን ለጥቃትም ሆነ ለመከላከል ያስተባበርው (ኤርትራ ድረስ ነፍሰ ገዳይ መላክን ጨምሮ) ካለው የግ7 ፍራቻ መሆኑን እያየን ነው; ወያኔ ከድሎት ከእንቅልፉ የሚባንነው በ ግ7 ነው! ታዲያ ግንቦት 7ን መርዳት ቢቀር ለምን እወቅሳለሁ? በዚህ ሰአት? እረ ጎበዝ እያየን እንጂ!! እስኪ የህዝቡን የየቀኑን እሮሮ እናዳምጥ! ችግሬ ግ7 ነው አለ? ችግሬ ኢሳት ነው አለ?? ኢትዮጵያ ፈተና ላይ ናት! መንታ መንገድ ላይ ሆና ወዳጅና ጠላትውን ለመለየት ተቸግራለች! ልጆቼ ያለቻቸው ሰሜንተኞች ሁሉ ስትስቃይ እያዩ እነሱም እየተበድሉ እንኩዋ ወይ አለንልሽ አላሉም; ዝም ብለው አጋጣሚ መጠበቅ እና ሚዛኑ ላይ አይናቸውን አፍጥጠው ይገኛሉ:: አይዞሽ ካሉት የሰሜን ሰዎች ውስጥ ደግሞ ይሄው ወያኔ መውደቂያው ሲቃረብና ወሳኝ ሰአት ላይ አይናቸውን ከሚዛኑ ላይ አንስተው ወያኔን የሚደግፍና ቀና የሚያደርግ ስራ ለመስራት ደፋ ቀና ይሉልናል!!
  ኢሳትን ለቀቅ አርጉት እባካችሁ!! ሁሉም የራሱን ትንታኔና ግምት ሲሰጥ በኔ ግምት የነጻነት ትግሉ የሚጠናቀቀው በጦር ሃይል ሳይሆን ከአገር ውስጥ በሚነሳው ትግል ነው:: ለዚህ ደግሞ ህዝቡን የመቀስቀስ የማሳወቅ የማደራጀት ሃላፊነቱን ሳይወድ በግዱ ኢሳት ተረክቡአል:: ታዲያ እነ ጌታቸው ረዳ ኢሳትን ምን አድርግ ነው የሚሉት?? ምን ጎደለባቸው?? ምን ጎዳቸው? እስኪ ከሃገር ቤት የሚሰማውን እሮሮ ቢሰሙት??
  ዶ/ር ጌታቸው ረዳ ስራ ካጣህ እስኪ የሚሰራ ስራ ላስታውስህ !! እስኪ አንተን የመሰሉ የተማሩ የትግራይ ልጆች በዚህ ወሳኝ ወቅት ዝም ብለው ድምጻቸውን አጥፍተው ከትግሉ የራቁ ወይም ከወያኔ ጎን የተሰለፉትን ወገኖች ወደህዝብ ወገን ለማምጣት ታገል!! ይሄ ነው ከባድ የወገን ፈተና የሆነው! እስኪ ጊዜህንና ሃይልህን ወገኖችን በማስተባበር ቁም ነገር ስራ! ወያኔን ስለተሳደብክ ብቻ ድል አይገኝም; ኢሳትንና ግንቦት7ን የሚወቅስና የሚወነጅል በቂ ሃይል በወያኔ በኩል አለ:: በተለይ ኢሳትን ቢያንስ በአሁኑ ሰአት ለቀቅ አድርገው!!

 18. Nesanet

  February 7, 2014 at 11:19 AM

  I live in the free land of the America not in the old socialist Soviet Union or the revolutionary weyane controlled Ethiopia where people go to jail because they speak their mind .i know why u are not posting my comment instead my ip that is to silence my voice and several other Ethiopians who speak for voiceless Ethiopians.finaly what I am telling u is that u can’t silence my voice and other Ethiopians by not posting our comment instead my ip with out asking or getting my permission which is in my opinion illegal .but one thing what I would tell you again is I would not stop until the Tigre/weyane corrupt killer regime come to justice and Ethiopia free.

 19. Abegaz

  February 7, 2014 at 12:19 PM

  Is Yared a member of G7D, a splinter from G7?

  G7D =Aiga=Awrambatimes=TPLF. Why bother about these guys, Abugida? By the way, I have never heard a gorilla fighters being criticized for human rights? Gorilla fighters have their own charters. Know their charters first. Also understand G7 does not mean G7 popular force. A working relationship can exist.They are two organization. So on any level, Yared has no legitimacy to accuse G7 nor this website should promote TPLF tools such as G7D. What has G7 to do for a person in exile in Sudan or Uganda? They got to talk to the United Nation Human Right organization for asylum, and not accuse G7. How does yared know a person in Sudan was once a member of G7 in the first place? Is it because G7D sent him their photos? How does he know it is not from TPLF operatives? He is a shoddy reporter at best putting himself as unreliable person of information.

 20. ጣሒር

  February 7, 2014 at 12:32 PM

  ያሬድ ተክለማርያምም ሆንክ ጌቾ
  መዋጋት ያለባቹ ከወያኔ እና ከወያኔ ጋር ብቻ ነው። ጸረ ግንቦት ሰባት ወይም ጸረ ኦነግ በሆናችሁ ቁጥር ህዝብ ይጠላችኋል። እርር ድብን ትላላች ሁ እንጂ እነሱ ለቅጥረኞች ለወረኞች ቦታ የላቸውም። ትኩረታቸው ወያኔን መጣል ላይ ብቻ ነው።

  እናንተም ወያኔን ለመጣል ብቻ ስሩ።

 21. Abegaz

  February 7, 2014 at 4:37 PM

  What is Ginbot 7 Democratic? Who are they in name? Are n’t they members of Agia forum? I always see them in Aiga forum writing a piece and praised by Aiga forum webmaster. They are playing the role of Awramba times who we know spying EAT, EMF, Ethiomedia and prodemocracy individuals of the diaspora. Why EMF is posting this crap here? You destroyed Kinijit supporting Bertukan and others over Hailu Shawel outside of party structure, and now you want to destroy Ginbot 7? When do you guys learn how to run a successful propaganda that promotes democracy in Ethiopia. Posting G7D ideas is not democratic because the end result is to destroy opposition of the TPLF.

 22. Abay

  February 7, 2014 at 4:42 PM

  Thank you for the news. Also i am one of the G7 victim. So how can i
  release about it?

  ******

 23. ጾል

  February 7, 2014 at 4:44 PM

  እናንት ግፍ የምትሰሩ የእውነት አምላክ ፍርዱን ይስጣችሁ;; እውነት ትደብቆ አይቀርም.

 24. Abegaz

  February 7, 2014 at 4:50 PM

  What is Ginbot 7 Democratic? Who are they in name? Are n’t they members of Agia forum? I always see them in Aiga forum writing a piece and praised by Aiga forum webmaster. They are playing the role of Awramba times who we know spying EAT, EMF, Ethiomedia and prodemocracy individuals of the diaspora. Why EMF is posting this crap here? You destroyed Kinijit supporting Bertukan and others over Hailu Shawel outside of party structure, and now you want to destroy Ginbot 7? When do you guys learn how to run a successful propaganda that promotes democracy in Ethiopia. Posting G7D ideas is not democratic because the end result is to destroy opposition to the TPLF.

  Even if the information is true, do you know the rules of gorilla fighting? When the going gets hard, a person cannot simply leave an organization except differences in ideology. People are not joining gorilla group to be leaders and get position without doing the hard work. This is dangerous to a political organization survival and there are disciplinary measures in any military engagement including the USA. Human right is not an issue. It is the gorilla group charter what matters. Also do you guys know G7 and G7 popular force are two different organization?

 25. kebede

  February 7, 2014 at 10:46 PM

  It is very sad to see people who do not know politics messing everything up.

  If you do not understand politics, please get out of the way. You are extending weyane’s life. Have you read what ato Gebremedhin Araya said.

  “Stop preaching peaceful struggle.By doing so, you are furthur extending weyane’s life.”

  Ato Gebremedhin knows TPLF better than any of us. We must listen to him.

 26. Musa Mohammed

  February 7, 2014 at 11:26 PM

  Look what Journalist Argaw Ashine and ginbot 7 public relation comments on his facebook page\
  https://www.facebook.com/argaw.ashine

  @Argaw Ashine Unknown number of Ginbot7 (armed wing) fighters have been detained inside #Eritrea, including the poster boys of the group. #Ethiopia @GTWTW_Now

  @Cosmos Michael @fasil I am abichu in my desert name,cosmos in the real world, the public relation of ginbot 7 now u know me who I am and Im telling u Ethiopians are loosing their life each day and they are tortured in hell prisons of Eritrea. actually we have nothing…See More
  17 January at 15:51 · Edited · Like · 3

 27. Ancient Ethiopia

  February 8, 2014 at 2:57 PM

  the standless and self appointed human right activist yared H’mariam wrote and posted as if he saw the acussation on his eyes. when shele got older, she came akatari. we know very well those who claim them selves as G7D and with whom they have been working from day one, even from ethiopia. so the self appointed human right activist uses gashaw’s web site as the source to blackmail the real TPLF’s nightmare [ G7], we have a right to put under question the self appointed human right’s activist yared’s stand. we know TPLF sent it’s hidden agents in different ways.we know that any one could not escape from TPLF unless or otherwise he or she is hidden agent of TPLF.For yared who uses ethiopia’s human right’s organization as his hidding place at this time which ethiopians are heading to take the right action against the enemies of ethiopia, the shameless and self appointed human right’s activist came out to blackmail the real nightmare of TPLF. yared my have one old house in addis ababa or need to visit addis ababa like his self appointed human right activist and holidayers, to get that access yared and other self appointed human rightactivists need to show their solidarity for the most posinious and terrorists group TPLF by attacking the ethiopia’s black lions who decided to use their fathers way to punish ethiopia’s enemies. yared and other self appointed , standless weyane’s backers, TPLF will be a history soon, but the crimes you and your advisors did will never over with out punishement. The standless getachew reda , the oldy EPRP opened his closed eyes when he hears yared’s non existed and baseless accusation of g7. the anti Amharas elements will not have place on ethiopia’s soil to hidde any more. we knpow who is who. who pretended as Amharas and who kisses weyane’s ass at this time. so go a head with your empty accusation, but you must know that you are lossers for ever.using g7d web site as an information source shows how the self appointed human right activist and looter of belguim’s communty works closely with TPLF. that was expected because such odd individuals can not be found in the jungle like belay zelek, gersu duke , abebe argai or any other ethiopia’s patriotes,to be like them one has be lucky enough and must free her or him self from selfishness. how can any one enjoy holiday in ethiopia every year and be against TPLF? The agreement between TPLF and such a standless and hidden agents is to work together and attack ESAT and g7 in different ways. but at the end of the day you all will be lossers. what is very interesting from yared’s shit is that his accusation of shabia. when shabians feel not good , they asked asylum their jungle and fought for 30 years and won the war, but when the self appointed human activists like yared found life is unbearable in ethiopia, the ran to europe ,became refuggees and claim them selves as an ethiopia’s lions, and bussy of producing fake documents in support of TPLF. the histryof ethiopia teaches us that when ethiopia ‘s unity and it’s people are indanger, the selfishes run to westren world where as the real lions returned from westren world to ethiopia’s jungle. the self appointed human right activist who defends TPLF for all genocidials crimes in gambella, arusi, harar and other parts of ethiopia, came out now to accuse the ethiopia’s lions in the jungle because their way will free ethiopia from TPLF and it’s hidden agents who defends TPLF in different ways including the self appointed human right activists. but we assure you that the ethiopia’s people will win the war against all odds including you and individuals like you

 28. Abegaz

  February 8, 2014 at 7:46 PM

  FYI,

  Yared has done great job exposing the TPLF’ crime against Agnuak people. The problem I have now with him is him quoting G7D a his source of information. G7D has been cooperating with TPLF operatives. I think he is more like Dawit kebede who initially showed determination againt TPLF but later gave in. When Dawit returned to Ethiopia his issue was the diaspora. Yared is in that process. He needed a sacrificial lamb and got G7 for that.

 29. ዮሰፈ

  February 9, 2014 at 1:32 PM

  የነጻነት ትግል መሰዋእትነት ብእርም ብቻ አይደለም ተግባርም እንጂ!
  የጽሁፌ መነሻ Ato ያሬድ ሃይለ ማርያም ወረድ ብሎ ደግሞ የማይቀረው ማእረግ ያለበት ለ ሰባት አመት በኢትዮጵያ የሰበአዊ መብት ምክርቤት የሰራ በወያኔ ግፍ ከሚወዳት ሀገሩ በ97 አም ጭፍጨፋ የተሰደደ ከፈለጋችሁ ደግሞ በአውሮፓ ህብረት የተናገረውን ምስክርነት ተመልከቱ ይላል። ይበጅ ብያለሁ! ከዚህ በፊት ለዳዊት ከበደ(አውራምባ ጋዜጠኛ) እልል በሉ ተብለን በኢሳት ቀርቦ እንዲሁም ሌሎች ሌሎች ተደርጎ አጨብጭበናል። ይህም ይሁን ዝናን የማይፈልግ ኢትዮጵያዊ ቁጥር በጣም ጥቂት ስለሆነ… ፕሮፌሰር…ዶክተር….ተመራማሪ…..ኢንጅነር…አንጋፋው ጋዜጠኛ…አንጋፋው አርቲስት… ወዘተ ብዙ ዝና አለን። ብዙ የነጻነት ታጋዮች፣ ወታደሮች የሉንም ቢኖሩም ጥቂትና እነሱንም ማጥፋት የተለመደ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ባህሪያችን ነው። ምክንያቱም እነዚህ የነጻነት ታጋዮች ከዶክተሮቹ ከሰበአዊ መብት ተሟጋቾቹ መብለጥ የለባቸውም በሚል አናሳ አስተሳሰብ ነው። ቆብ ሌላ ተግባር ሌላ።
  ወያኔ በሚሰጠን የቤት ስራ እየተዘናጋን ስራ ፈቶችን ሰብስቦ ትግሉ አንድ እርምጃ ወደፊት እንዳይራመድ እንባላ ዘንድ ማእረግ ባላቸው ሰዎች የምቀኝነትን መርዝ ማሰራጨት ይጀምራል። እኛ ደግሞ እንመቻቻለን። የነጻነት ትግል መንገዱን ወጣ ገባ ለማደረግ ያልተተባ፣ ያልተገራ ብእራችንን አንስተን “ግንቦት 7 ሆይ ፍረስ ወያኔ የጀመረን ይጨርሰን፣ ተዋርደን መገዛታችን እንቀጥል ዘንድ ወታደሮችህን ጋዜጠኞች አድርጋቸውና የዜና ሀተታ ይስሩልን” እንላለን።
  እኔ ግን ከቻልን ትግሉን መቀላቀል ካልቻልንና እውነተኛ የኢትዮጵያ ህልውና እንዳትፈራርስ የምንፈልግ ከሆንን እሲት ገለል እንበል። ለወያኔ ብቻ ሳይሆን ለግንቦት ሰባትም፡፡ ማናችንም ቢሆን ብእርን አንሰተን ዌብሳየት ፈጥረን የምንታገለውን መሰዋእት ሳይሆን፤ እንደ እየሱስ ክርስቶስ በሞታቸው ድነትን፣ በደማቸው ነጻነትን፣ በአጥንታቸው ክብርን ሊመልሱልን ከበርሃ ማዶ ድቅድቅ ባለ ጨለማ የኢትዮጵያን ኤሎሄ ሰምተው ዳር ሳይሆን እሳት ላይ ያሉትን ጀግኖች ከእነ ችግራቸው በርቱ ከማለት ፈራርሱ ብሎ ማለቱ ማን ነኝ እኔ ማን ነው እሱ? እንበል እኔ ማጨብጨብ ደክሞኛል።
  ስለዚህ ጸሃፊውና ብእሩ ምነው በዴሞክራቲክ በተባለው የወያኔ ግሩፕ ላይ አተኩሮ ሀገራችንን አደጋ ውስጥ የከተታትን ‘እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይበቅል’ ያለቸውን አህያ ነጭና ጥቁር አሊያም ቢጫ መሆኗን በካበቱት ልምዳቸው ለምን አላዩልንም ወይስ ይሄን አይጋ ፎረም ላይ አገኘዋለሁ?
  በአኬልዳማ ድራማ ወያኔ ይህንን ጸሃፊው አሁን ያሉንን “የብዙ ወጣት ኢትዮጵያዊያኖችም ሕይወት በዚህ መያዣና መጨበጫ በሌለው የግንቦት 7 ቅዥት ተደናቅፏል” የሚለውን ዜማ ደጋግመን ሰምተናል። አብዛኞቻችን አይ ወያኔ እና ኢቲቪ ብለን እሰየው ግንቦት 7 በርቱ ወያኔ እንቅልፍ አጥቶ ሌሊት እየተነሳ ድራማ መስራት ጀምሯል አልን፤ ደገፍናቸውም። ታዲያ ወያኔና አጫፋሪዎቹ በደነገጡ ቁጥር ስራ ሳይሰራ ይቅር? ኧረ ግንቦት ሰባቶች ይህን ሰምታችሁ ቅር እንዳትሰኙ። በአማራው ፕሬዝዳንት ለሃጫም አማራ፣ ማንነቱን የማያውቅ ጫማ የሌለው ህዝብ፣ በሶማሊያው ፕሬዝዳንት አማራው ና ኦሮሞው እንዳየተባበሩ ትግሬውን ውደዱ፣ ከደቡብ ደግሞ አማራውን አስወጡ፣ ዋልድባን አፍርሱ… ዜጎቻችን ህገ-ወጥ ናቸው በሳውዲ ይገደሉ… እኮ የትኛው ይሆን ግንቦት 7 ፈጽሞት እንታገለው የምንለው? ኧረ ጎበዝ ማንነው የምንታገለው? በዳዩን ወይስ ተበዳዩን?

  በርግጥ ነው ዝና የሚፈልጉ ሰዎች ወይም እኔ ያልኩት ካልሆነ የሚሉ ሰዎች ብእራቸውን አንሰተው አንዴ ስለ ግንቦት 7 የውጪ ፖሊሲ ሌላ ግዜ ደግሞ ስለ መከረኛው የህዝብ ልሳን “ኢሳት” ላይ መጎንተራቸው አልቀረም። ይህም ባልከፋ የአጻጻፉ ዘይቤ ወይም የትረካው አጨራረስ ግን ምን አለበት አንድ ሆነን እንደ ግንቦት 7 መረር ብለን “ታላቁን’ ህወሃት እንጥለው ዘንድ አመስግነው ቢዘጉት፤ ከፈቶ ከማበላሸት ይልቅ።

  ልጨርስ “ነፃነትን የማያውቁ ነፃ አውጪዎች’ መሆን ይከብዳል። ስለዚህ በእኔ እምነት ግንቦት ሰባት የሚባለውን ሁሉ እያዳመጠ ሙያ በልብ ብሎ እንደሚሰራ አልጠራጠርም። ዶክተሮችም፣ ፕሮፌሰሮቹም፣ ኢንጅነሮችም፣ ወታደሮቹም አሉት ለየት ከሌላው የሚያደርጋቸው ማእረጋቸው ሳይሆን ለተነሱለት አላማ መጠመዳቸው ለተግባራዊ ስራ መፍጨርጨራቸው ነውና ተግባርን እናስቀድም፤ ከዛ ደግሞ እንተቻቸው። ትችት ጥሩ ነው ግን ከቅንነት ጋር ሲሆን ይጠቅማል፡፡ ስለዚህ ጠላታችን ወያኔ ነው!!! ብእራችን፣ ገንዘባችን፣ ጉልበታችን ሁሉ ለነጻነት ለሚደረጉ እልህ አስጨራሽ ትግል የሚረዱ ጋሻዎች ይሁኑን እላለሁ።
  ህዝባዊ ሃይሉም በርታ! የማንችል ደግሞ አምላክ ጩኸታችን ሰምቶ ሀገራችንን የሰላም የደስታና የነጻነት ሃገር ያድርግልን ዘንድ እንጸልይ። የምንችል ደግሞ አንድ ሁነን ትግሉ ውስጥ እንግባና እንደህዝባዊ ሃይሉ እምቢ ለነጻነቴ፣ ለሀገሬ እንበል!!! ነገር ግን እምቢ ለወሬ……..
  ዮሴፍ ጸጋየ

 30. ማማሩ

  June 8, 2014 at 9:59 AM

  አረ ነገሩ ኣንዲት ነው ጎበዝ እሁን ግንቦት ነጻ የሚያወጣችሁ ይመስላችሁአል? ድንቂእም ነጻ ትውጣ:: ኣረ ባካችሁ ተስፋ ቁረጡ ለዚያውም ከሻቢያና ኣና ከግብጽ ጋር..ክክክክክክክክ