የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እናት አረፉ

ከመጀመሪያዎቹ የሴት ሃኪሞች መካከል የሚጠቀሱት፣ የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እናት፤ ወ/ሮ በላይነሽ አወቀ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።

በቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግስት ወደ ቤሩት ተልከው የህክምና ትምህርት ተከታትለው ከተመለሱት ወጣቶች መካከል ወ/ሮ በላይነሽ አወቀ የሚጠቀሱ ናቸው።

ወ/ሮ በላይነሽ አወቀ ልጃቸው በጋዜጠኝነት ሙያው ምክንያት ለእስር በተዳረገበት ወቅት በሙሉ ከጎኑ ያልተለዩ፤ በእስር ቤትና በፍርድ ቤት ይደርስበት የነበረውን እንግልት በቀጥታ ለእስር ቤት አስተዳዳሪዎችና ለዳኞች በድፍረት ይናገሩ እንደነበር የሚታወስ ነው።

በተለይም ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በመጀመሪያዎቹ የፕሬስ ውጤቶች፤ “ኢትኦጲስ” እና “ሐበሻ” ጋዜጣዎቹ ምክንያት ታስሮ በነበረበት ወቅት ወደ ሌሎች የነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች ቢሮ በመሄድ፤ “ዛሬ ካልተባበራችሁ፤ ነገ የእናንተም እጣ ፈንታ መታሰር ነው። ተባበሩ፣ ዝም አትበሉ!” በማለት ይቀሰቅሱ እንደነበር በተለይ የEMF ጋዜጠኞች የሚያስታውሱት ነው። ለሁሉም “አምላክ ነፍሳቸውን ይማር፤” ለእስክንድርና ለቤተሰቡም “ፅናቱን ይስጣችሁ” እንላለን።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 15, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.