የገዢዎቻችን መጨረሻና የተከተላቸው ሀቅ – አንዱ ዓለም ተፈራ

የካቲት ፳፫ ቀን ፳፻፮ ዓመተ ምህረት

የመጨረሻውን በማያውቁት ያዘቀዘቀ ጨለማ መንገድ እየተውዘረዘጉ መሪዉን በማስተካከል ከመጨረሻው ለመድረስ  የሚጣድፉ መሪዎች፤ የድንቁርና ኒሻን ይገባቸዋል። በፈጠሩት የራሳቸው የመኖሪያ የገዢነት መኮፈሻ “ሀቅ” ተጀንነው  በመቀመጥ፤ ፈንጠር ብሎ ርቆ ሌላውን ማየት ባለመቻላቸው፤ የተከተላቸውውን ሳይውቁት እጃቸውን ሠጥተዋል። የተለዬ  የመሰለ የራስ “ሀቅ” የብዥታ ጭጋግ፤ ሩቅ ማየትን ነፈጋቸው። ማስተዋልን ከአእምሮ መዝገባቸ ሰወረው። መደናበርን  አነገሠባቸው። ካይናቸው ፈት በተገተረው የእብሪታቸው መነፅር ዓለምን ግቢ ውጪ እያሉ በማስገደድ፤ ያለው የሌለ ሆኖ፣  ከተጨባጩ ይልቅ በምኞታቸው ዓለም ሲዳክሩ፤ የቆሙበት መሬት ከዳቸው። ከሕዝቡ መሆናቸው ቀርቶ ሕዝቡ የነሱ አገልጋይ ሎሌ ሆነና፤ የነሱ መኖሪያና የሕዝቡ መኖሪያ በአጥር ተለያዬ። መኖሪያቸው ዓለማቸው ሆነና ከሕዝቡ ዓለም ወጡ። ረጋ ብለው ያሉበትን ለመመርመር ጊዜ አጠራቸው። ያጠራቸው ጊዜ ጥሏቸው ሄደ። እናም ባሉበት ቆመው ቀሩ። Read full story in PDF:እብሪትና የመሪዎቻችን መጨረሻ …

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on March 4, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

2 Responses to የገዢዎቻችን መጨረሻና የተከተላቸው ሀቅ – አንዱ ዓለም ተፈራ

 1. Yigermal

  March 4, 2014 at 3:31 PM

  መጀመሪያ እግሩ ይገኝ
  ብዙ ጊዜ ከእሳት ጋር የተቀራረበ ስራ የሚሰሩ ማለት እንጀራ ጋጋሪወች: ወጥ ሰሪወች: ደረቆት የሚቆሉ: አብሽሎ የሚጋግሩ— ሰዎች ከቅልጥማቸውና ከጭናቸው አካባቢ የሚታይ ደም የሰረበ ገላ ግመን ይባላል:: ግመን ባብዛኛው በቅልጥምና በጭን አካባቢ የሚታይ የሳምባ መልክ ያለው በእሳት የተቆጣ የሰውነት ክፍል ነው:: ከእሳት ዳር ቁጭ ብለው እሳት ሲሞቁ የሚውሉ ሰዎችም ግመን ይበላቸዋል::

  ታዲያ አንድ ቀን አንድ ጎልማሳ አንዲት ሴት ከጠዋት እስከማታ ድረስ ከእሳት ዳር ቁጭ ብላ ስትሞቅ ያያታል:: ጠዋት ወደስራ ሲሄድ: በምሳ ሰአት ወደቤት ሲመጣና አመሻሽ ላይ ከውሎ ሲመለስ ሴትዮዋ ለአፍታ ከተቀመጠችበት ሳትነሳ ቁጭ ብላ በእሳት ትንቃቃለች:: ጎልማሳው የሴትዮዋን ጉዳት የሚፈልግ አይደለምና በመቆርቆር ስሜት “እህቴ ኧረ እባክሽ ግመን ይበላሻል! ባይሆን ለጥቂት ጊዜ እንኳ ከእሳቱ ዞር በይ” ይላታል:: ሴትዮዋ ፊቷን ከስክሳ በቀዘቀዘ ስሜት “መጀመሪያ እግሩ ይገኝ: ከዚያ ግመን ይብላው” ስትል መለሰችለት:: ለካስ ሴትዮዋ እግር የላትም ኖሯል::

  ወንድሜ አንዷለም ኢህአዴግ ከወደቀ በኋላ የከፋ መንግስት እንዳይመጣ በተወሰኑ አላማወች ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ ይዘን አላማወቻችንን ለማስፈጸም እንሰባሰብ ሲል እየመከረን ነው:: ነገሩ ባልከፋ:: ግን በመጀመሪያ አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት እንዴት ነው የሚወድቀው? መጀመሪያ እግሩ ይገኝ ይሏል ይኸኔ ነው:: እንደኔ እንደኔስ መሰባሰቡ ወያኔ ከወደቀ በኋላ ልንተገብራቸው የምንፈልጋቸውን መርሆወች ለማስፈጸም ቅድሚያ ታሳቢ በማድረግ ሳይሆን ወያኔን ለማስወገድ ቅድሚያ ታሳቢ ባደረገ መልኩ መሆን ይኖርበታል:: ወያኔ ሊወድቅ ነው እያልን ስለለፈፍን ብቻ ወያኔ አይወድቅም:: ወያኔ ለመውደቅ እየተንገዳገደ እንደሆነ የሚያሳዩ ምልክቶችም እየታዩ አይደለም:: ካልተገፋስ እንዴት ይወድቃል! እና ተሰባስበን እንዲወድቅ እንግፋው እንጅ ከወደቀ በኋላ አላማችንን ለማስፈጸም ስንል ብቻ አንሰብሰብ::

 2. Tom

  March 5, 2014 at 4:09 PM

  that is true. the problem lies on how to remove the burden off our shoulders.