የጃኪ ጎሲ ዝግጅት በዲሲ እንዲቀጥል ፍርድ ቤት ወሰነ!

(ኢ.ኤ.ኤፍ) ወጣቱ ከያኒ ጃኪ ጎሲ፤ ከኤፕሪል 26 2014 ጀምሮ በአሜሪካ የሚያደርገውን የሙዚቃ ዝግጅት ለማድረግ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን የዝግጅቱ አቅራቢዎች በተለይ ለEMF ገለጸዋል:: ሆኖም ዝግጅቱን ከማቅረባቸው አንድ ቀን ቀደም ብሎ የጃኪ ጎሲ እና የሙዚቃው አዘጋጆች ውሎ በዋሺንግተን ዲሲ ፍርድ ቤት ነበር::

የክሱ ጭብጥ እንደሚያስረዳው ከሆነ “ሸዋ ኢንተርቴይመንት ከዚህ ቀደም ከጃኪ ጎሲ ጋር የስራ ውል ካደረገ በኋላ በማፍረሱ፤ ጃኪ ሌላ የሙዚቃ ዝግጅት በዋሺንግተን ዲሲ ማድረግ አይችልም” የሚል ነበር:: በጉዳዩ ላይ ከሳሽ ሸዋ ኢንተርቴመንት ሲሆን ተከሳሽ ደግሞ ኢቫንጋዲ ፕሮሞሽን ሆነው በዋሺንግተን ዲሲ ፍርድ ቤት ቀርበዋል::

sela belu3

በፍርዱ ሂደት ወቅት… ገና ከመጀመሪያው የክሱ ጭብጥ ለዳኛው ሲቀርብላቸው ሁኔታው ግራ መጋባትን ፈጥሮ ነበር:: ዳኛው “ለምንድነው ዝግጅቱ የሚቋረጠው?” ለሚሉትና ተያያዥ ጥያቄዎች በሸዋ ኢንተርቴመንት ጠበቃ በኩል በቂ እና አሳማኝ ምላሽ አልተሰጠም:: በዚህም ምክንያት ዳኛው በተከሳሾች ማለትም በነጃኪ ጎሲ በኩል ያለውን ጉዳይ እንኳን ለመስማት ሳይፈልጉ ቅዳሜ ኤፕሪል 26፤ 2014 የሚደረገው ዝግጅት መቋረጥ አይችልም::” ሲሉ ውሳኔ ሰጥተዋል::

በሸዋ ኢንተርቴመንት በኩል “ጃኪ ጎሲ ውል አፍርሶብኛል::” በሚል ለተሰነዘረው የመቃወሚያ ሃሳብ ዳኛው ሲመልሱ “እንደዚያ ከሆነ ጉዳዩ በፍትሃብሔር ወይም በCivil code የሚታይ ነው:: በዚያ በኩል ክስ መመስረት ትቻላላችሁ” የሚል ምላሽ ለሸዋ ኢንተርቴመንት ሰጥተዋል::

ከፍርድ ውሳኔው በኋላ የጃኪ የአሜሪካ ጉዳይ ዋና ሃላፊ የሆነውን ሄኖክ መኮንንን አግኝተን አናግረነው ነበር:: እንደሄኖክ ገለጻ ከሆነ “ዝግጅቱ በዋሺንግተን ዲሲ ይጀመራል፤ በላስ ቬጋስ: በሎስ አንጀለስ: በሲያትል: በአትላንታ: በሜኒሶታ እና ሌሎች ከተሞች ይካሄዳል:: ምንም ነገር አያቆመውም::” ብሎናል:: የክሱን ጉዳይ አስመልክተን ለጠየቅነው ጥያቄ ዝርዝር ሁኔታዎችን ከመናገር ተቆጥቦ… “ያው በክሱ ምክንያት ለጠበቃ እና ለሌሎች ጉዳዮች ወጪ አድርገናል:: ያወጣነውን ወጪ መልሰን ለማግኘት በሸዋ ኢንተርቴመንት ላይ ሌላ ክስ እንመሰርታለን:: ይህ ደግሞ በሁሉም የክስ ውዝግብ ወቅት የሚደረግ ነው:: አሁን የኛ ትኩረት ዝግጅታችንን በድምቀት ለማቅረብ ነው:: ዝርዝር ጉዳዮችን ወደፊት እንነጋገራለን::” ብሎናል – ሄኖክ መኮንን::
Click here to watch promoters comment after the court. (Video by – EthioTube)

sela belu2

 

sela belu1

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 25, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to የጃኪ ጎሲ ዝግጅት በዲሲ እንዲቀጥል ፍርድ ቤት ወሰነ!

  1. ገረመው

    April 26, 2014 at 12:08 AM

    ማን ነበር “ይገርማል”ን የዘፈነው?