የደሴው ሰላማዊ ሰልፍ በድምቀት ተካሄደ! (ከተጨማሪ ፎቶዎች ጋር)

(EMF) ዛሬ መጋቢት 28 ቀን በደሴ የሚደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ ያስተባበረው አንድነት ፓርቲ ነው:: የፓርቲው ከፍተኛ አመራር አባላት በትላንትናው እለት ቅስቀሳ እያደረጉ በነበረበት ወቅት ፖሊስ እና ደህንነቶች ቅስቀሳውን ለማስቆም ጥረት አድርገው ነበር:: በተለለይም የከተማው የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ ነው የተባለው ሰው የቅስቀሳ መሳሪያዎችን ጭምር ለመንጠቅ ሙከራ አድርጎ ነበር – ባይሳካለትም::

ይህ ሁሉ አልፎ ዛሬ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ በአስተዳደሩ ላይ በተለይም በመሬት ይዞታ ባለቤትነት ጉዳይ እና አላግባብ ስለታሰሩት ኢትዮጵያውያን ድምጹን ከፍ አድርጎ እያሰማ ይገኛል:: ሰላማዊ ሰልፉ እንደተጀመረ ፖሊስ መንገዱን በመዝጋት ሰልፈኛውን ለማወክ ጥረት አድርጎ ነበር:: ህዝቡ ግን ፖሊስን እየጣሰ ሰልፉን በሰላማዊ መንገድ እያደረገ ነው::
dessei11


በሰልፉ ላይ…
-ዜጎችን ከቀያቸው ማፈናቀል ይቁም
– መሬት ለህዝብ ይመለስ
– ጭቆና በቃን
– ድል የህዝብ ነው
– በግፍ የታሰሩ ይፈቱ
– መሬት ከካድሬው ወደ ህዝቡ ይመለስ
– አንድነት ኃይል ነው
– የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ… የሚሉ መፈክሮች ሲስተጋቡ ነበር::
ለተሰበሰበውም ህዝብ በደሴ የአንድነት ተወካይ በቅድሚያ ንግግር አድርገዋል:: ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ እና የአንድነት ፓርቲ ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ ተክሌ በቀለ ንግግር አድርገው ሰላማዊ ሰልፉ በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ተጠናቋል:: የደሴም ህዝብ ብሶቱን የሚያሰማበት መድረክ በመፈጠሩ ምስጋናውን ለፓርቲው አመራሮች አቅርቧል::

ተጨማሪ ፎቶዎችን ከፓርቲው ምንጮች ስናገኝ በርከት አድርገን እናቀርባለን!

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 6, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

5 Responses to የደሴው ሰላማዊ ሰልፍ በድምቀት ተካሄደ! (ከተጨማሪ ፎቶዎች ጋር)

 1. TERUBE

  April 6, 2014 at 12:34 PM

  DESIE GOGOGO BERAVO

 2. AleQa Biru

  April 6, 2014 at 3:12 PM

  ቂሎች !!

  የመሬት ፖሊሲ በሰላማዊ ሰልፍ ይቀየራል?

  የመሬቱን ፖሊሲ ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ፖሊሲዎች ከህዝብ ጋር ተወያይተህ አሳምነህ በምርጫ ስታሸንፍ ነው እንዲህ አይነት ነገሮችን የምትቀይረው:: አሁን የደሴ ከተማ የአንድነትን የመሬት ፖሊሲ ደገፈ እንኳ ቢባል ሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ስለመደገፉ እንዴት ይታወቃል?

 3. ሳምሶን አምባዬ

  April 6, 2014 at 10:17 PM

  እግዚአብሔር አንድነት ፓርቲን ይባርክ
  አንድነት ፓርቲ ኢትዮጵያውያንን ይወክላል

 4. ትዝብት

  April 7, 2014 at 5:34 AM

  ብሩ :- “አለቃ” የሚለው ለታላላቅ ሊቆችና አዋቂ ተመራማሪዎች የሚሰጥ “የማዕረግ” ስም እንጅ: እንደአንተ ያለ ባዶና ቀፎ ራስ ሆድ አደር ዝም ብሎ የሚለጥፈው አይደለም::
  የባህር ዳር ህዝብ ምን ነበር ያለው ‘ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል” ነበር ያሉት!! ቀፎ ራስ ይዘህ ወይም ጠባብነት ወጥሮህ ክሆነ የደሴን ህዝብ ሰላምዊ ሰልፍ የምታናንቅ: ለጌቶችህ አርዳቸው መቃብራቸው የተማሰ መሆኑን: እድሜአቸው በጣም አጭር መሆኑን ም ግለጽላቸው!!
  ወደ ጽሁፍህ ስመለስ የመሬት ፖሊሲ በሰላማዊ ሰልፍ መቀየር ይቻላልን? ላልከው መልሴ እንዴታ!!! በደንብ እንጅ!!!! ነው መልሴ:: የሌሎች አሁግራትን ለውጥ እንዴት አመጡ የሚለውን አንብበህ ተረዳ ብዬ አልፈዋለሁ::
  ሆኖም ግን የ-1966ዓ.ም/እንደ ኢትዮ.አቆ./ የማይደፈረውንና የማይገረሰሰውን ዘልዓለማዊ ነኝ ብሎ ሃገሪቱን የዘውዱን መንግሥት ብል እንደበላው ትልቅ ዛፍ የተደረመሰው በጦር መሳሪያ አይደለም::
  “መሬት ላራሹ” የሚለውን መፈክር አንግበው አዲስ አበባን ባጥለቀለቁት የተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ መሆኑን መካድ ትፈልጋለህ??
  ህዝብ አሳምነህ በምርጫ ስታሸንፍ ነው ላልከው የ-1997ቱና የ-2002ምርጫዎች በቂ ምስክር ናቸው:: ከማስፈራራት እስከ ኮሮጆ ሰረቃና ከነፍስ ግድያ እስከ እስር የወሰደውን እርምጃ መካድ አየቻልም::
  ስለዚህ ህዝቡ በጣም መሮታል:: ባህርዳር በደሴ ተደግሞአል: ገና በሁሉም ይቀጥላል::
  እባካችሁ!!! አንተና የሆድ ጉዋደኞችህ ወደ ህዝቡና ወድ ቀልባችሁ ተመለሱ!!!
  እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ያስባት!!!!!! አሜን!!!!!!

 5. AleQa Biru

  April 7, 2014 at 10:54 AM

  ትዝብት:-)

  አንድነት እኮ እታገላለሁ የሚለው ሰላማዊ በሆነ መንገድ ነው እንጂ አንተ እንዳልከው አብዮት በማካሄድ አይደለም:: የ1966ቱ የተማሪዎች ንቅናቄ “መሬት ላራሹ” የሚለውን መፈክር ይዞ ያካሂድ የነበረው የምርጫ ቅስቀሳ አልነበረም አብዮት አንጅ!!

  አሁን አንድነቶች እና ሰላማዊ ምናምን የሚባሉት ቅራቅንቦዎች የበነነ የተነነውን ምክንያት እያደረጉ በየሳምንቱ ሰላማዊ ሰልፍ ይጠራሉ:: እነሱ ስልጣን ቢይዙ ግን አሁን ኢህአዴግን የሚከሱበትን ሁሉ ችግር እንዴት መፍታት እንደሚቻል አማራጭ ዘዴአቸውን አሳማኝ በሆነ መንገድ ሲገልጹ አይታዩም::

  ማንም ቀፎ-ራስ እየተነሳ ችግር መዘርዘር ይችላል: መፍትሄውን ማቅረብ ነው እንጂ የማይችለው::

  እኔ የኢህአዴግ ደጋፊ አይደለሁም:: ኢህአዴግን የምትችበት ብዙ ጉዳዮች አሉኝ:: ነገር ግን ተቃዋሚዎችንም ቢሆን አልምራቸውም:: የግድ ስልጣን ይዘው ሌላ ኢህአዴግ ወይም ደርግ እስኪሆኑ ድረስ መጠበቅ ያለብኝ አይመስለኝም::