የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እስር (ኤዶም ካሳዬም ታሰረች)

(ኢ.ኤም.ኤፍ) አርብ ሚያዝያ 17 ቀን 2006 አመሻሹ ላይ 11፡20 ገደማ ነበር ስድስት የዞን ዘጠኝ ጦማርያን በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ከያሉበት ተይዘው የተወሰዱት። እነርሱም ናትናኤል ፈለቀ፣ በፍቃዱ ሀይሉ፣ አጥናፍ ብረሀነ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ ዘላለም ክብረት እና አቤል ዋበላ ናቸው፡፡ ጦማርያኑን ያሰሯቸው አካላት የማሰሪያና የመፈተሻ የፍርድ ቤት ፈቃድ የያዙ መሆናቸውን የ“ዞን 9” ብሎግ በመግለጫው አሳውቆ ጦማርያኑ በምንም አይነት ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው እነዳልነበር ካረጋገጠ በኋላ የታሰሩ የዞኑ አባላትና ወዳጆች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጠይቋል
ዞን ዘጠኝ ጦማርያን
ማምሻውን በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር ዋሉት 6 የዞን 9 አባላትና ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ማእከላዊ ምርመራ እንደሚገኙ ተረጋግጧል፡፡ ታሳሪዎቹን ቤተሰብ ማየት የማይችል ሲሆን ስንቅ በማቀበል ብቻ ተመልሰዋል፡፡ በተያዙበት ሰአት ቤታቸውና ቢሯቸው የተፈተሸ ሲሆን መጽሃፍት ጋዜጦች እና ላፕቶፖቻቸውም ጭምር እንደተወሰዱ ለማወቅ ችለናል፡፡ 
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሌላኛዋ የዞን ዘጠኝ ጦማሪት ኤዶም ካሳዬ በዛሬው እለት ቤቷ ተበርብሮ፤ እሷም ወደ እስር ቤት ተወስዳለች።

“‘ዞን 9’ ምንድነው?” ብላችሁ ለምትጠይቁ…

“… የዞን 9 የሚለው ስያሜ የመጣው ጋዜጠኛ ርእዮት አለሙን ቃሊቲ እስር ቤት ሊጠይቁ በሄዱበት ሰአት ርእዮት አለሙ ዞን 9 ደህና ነው ? ብላ ስትጠይቃቸው ነበር።
ቃሊቲ እስር ቤት ያለው እስከ ዞን 8 ድረስ ነው ከየት አመጣሽው ? አይ ዞን 9 ማለት ከእስር ቤት ውጪ ያለው የኢትዮጵያ ትልቁ እስር ቤትን ነው ብላ መለሰችላቸው።”

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 27, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እስር (ኤዶም ካሳዬም ታሰረች)

  1. Kassaye Yosef

    April 27, 2014 at 10:59 AM

    የትግል ወጤት

    ከጠመንጃ ይልቅ የተሻለ የጦር ሜዳ ማለት ይህ ነው፡አንደም ሰው አልቆሰለም፧አንደ ሰወ አልሞተም፡ ይህን አይነት ትግል ነው የሚያሰፈልገን። በእረግጥ ይህ ትግል በቀላሉ አልመጣም፡ ለምሳሌ በሳህን የተቀመጠን እንጀራ ወደ አፍ ለማሰገባት እጀ ወደ ሳህኑ መዘርጋት አለበት ከዚያም መቁረሰ፧ከዚያም ወደ አፍ መወሰደ አለበት ይህ ሲሆን ብዙ ሴሎች ይሞታሉ ይህ የዛሬው የተገኝው ውጤት ከዚህ የተለየ አይደለም።በሀገራችን ይህ አይነት አሰራረ አልተለመደም አዱሱ ትወልድ ከአሮጌው ትውልድ የተሻለ መሆኑን የሚያሳየው ከደም መፈሰስ ነፃ የሆነ ትግል ነው ማደረግ ያለበት። ይህም ለገዝው ፖርቲ ትልቅ ትምህርት እንደሜሆን አምናለሁ፡ ምክንያቱም የሜሰራ ሰው ይሳሳታል ሀገር በመምራት ላይ ነው ያሉት የተሳሳቱትን በመልካም መንገደ ይህ ሰህተት ነው፡ መልካም የሆነውን ደግሞ ይህ መልካም ነው ለማለት መለማመደ አለብን። ይች ሀገረ ያሳለፈችውን የአገዛዝ ሥራዓቶች በታሪክ በዝገብ እንደተቀመጠ ከኋላ የሜመጣው ሥርዓት ከፊቱ የነበሩትን የአሰራር መሰረቶችንና የተጀመሩ ልማቶች ሆነ ሌሎችንም ከተጀመሩበት መሰረት በማጥፋት ተመሳሳይ የሆነ የአሰራረ መንገዳቸውን ይጀምራሉ። እንደ ሌሎች ሀገራት አንደ ልማት ሲጀመረ ለሀገረ ልማት ለወገን ጥቅም ይውላል ተብሎ ነው የሜጀመረው፡ በአሁኑ ሰዓት በአባይ ላይ የተጀመረው ግድብ ለትውልድና ለሀገረ የሜውል ሥራ ሰለሆን በዚህ በኩል ሁላችንም አብረን በመሰለፍ መልካም ይሆነው ለውጤ እንዲበቃና ከሰደት፧ከሥራ አጥነት ለመውጣት እንደንችል አብረን እንሰለፍ፡ አሁን የተጀመረው ግድብ በሥራ ላይ ከዋለ(ለ300 ዓመት የሜሆን የልማት ጅምረ ነው ይላሉ) ታደያ ከዚህ የተሻለ ሥራ ኢህአድግ ምን ይሰራ? ከውጭ ያላችሁ የተቃውሞ ፓርቱ አባላት ከዚህ በመማረ የታጠቃችሁት ትጥቅ በማውረደ ይህን ወደመሰለው ትግል ተመለሱ እንላለን፡ ህብረታችን ለጠላቶቻችን ሞታቸው ሰለሆነ አብረን እንዳንቆም በጠላቶቻችን በተሰፋ ማሊያ ተለያይተን ሀገሪቱ የጀመረችውን ልማት ወደ ግብ እንዳይደረሰ ጠላቶቻችን ሳይሆን እኛው እረሰ በራሳችን ከማልማት ወደ ጥፋት በመታገል ላይ እንገኛለን፡ ሌሎችም የሰማያዌ ፓርቲን በመከተል ወደ ሰላም ትግል ተመለሱ በማልት መልዕክቴን አሰተላልፋለሁ።።