የዕርቀ ሰላም ውይይቱ ተጠናቋል (ደጀ ሰላም)

የዕርቀ ሰላም ውይይቱ ተጠናቋል – ዛሬ መግለጫ ይሰጣል፤ በአቡነ መርቆርዮስ ጉዳይ ተጨባጭ ስምምነት ላይ የተደረሰ አይመስልም

(ደጀ ሰላም ኅዳር 30/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 9/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ በአሜሪካዋ የቴክሳስ ግዛት ዳላስ ከተማ ከኅዳር 26/2005 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የሰነበተው የአባቶች ዕርቀ ሰላም ውይይት በመልካም ሁናቴ በመካሔድ ላይ ቆይቶ ቅዳሜ የተጠናቀቀ ሲሆን ዛሬ እሑድ መግለጫ በመስጠት ይፈጸማል ተብሎ ይጠበቃል።

በአጀንዳዎቹ ላይ በመግባባትና በመከባበር ውይይቱን ያደረገው ጉባኤው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ከሥልጣናቸው እንዴት ሊወርዱ እንደቻሉ በአገር ውስጥም በውጪው የሚገኙት አበው ልዑካን የታሪክ ምስክርነታቸውን ከሰጡ በኋላ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ አስመልክቶ ረቡዕ ዕለት ሰፊ ውይይት መደረጉንና ሳይጠቃለል በይደር መገታቱን መዘገባችን ይታወሳል።

በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ ባሉ አባቶች እና ምእመናን ዘንድ በጉጉት የሚጠበቀው የአራተኛው ፓትርያርክ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ጉዳይ ዋነኛው የመነጋገሪያ አጀንዳ በሆነበት በዚህ ጉባዔ ከሁለቱም ወገን የተለያየ ሐሳብ ከመቅረቡ አንጻር ለጊዜው ከስምምነት ላይ የተደረሰበት አይመስልም።

ከአገር ቤት የመጣው ልዑክ “ቅዱስነታቸው በመረጡት ቦታ በጸሎት ተወስነው ይቀመጡ” ሲሉ በውጪ የሚገኙት አበው ደግሞ “ከነሙሉ ማዕረጋቸው ወደ መንበራቸው ይመለሱ” የሚለውን ሐሳብ አቅርበዋል። በሁለቱም በኩል ሐሳቡ ዕልባት ሳይሰጠው ቀርቷል። ጉባዔው ዛሬ መግለጫውን ሲሰጥ በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ በሌላ ጊዜ ድጋሚ ተገናኝቶ ይወያይ እንደሆነ የደረሰበትን የውሳኔ ሐሳብ ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ስለ አቡነ መርቆርዮስ መመለስ ግልጽ ደብዳቤ የጻፉትን የፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስን ሐሳብ አስመልክተው ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ጣቢያ ቃለ ምልልስ የሰጡት ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ አቡነ ናትናኤል ከትናንት በስቲያ አርብ “ፓትርያርኩ በተወሰነላቸው ቦታ እንዲቀመጡና ለአገራቸው አፈር እንዲበቁ” እንጂ ሌላ ነገር እንደማይጠበቅና እንደማይወሰን መናገራቸው የዕርቅና የሰላም ውይይቱ ሳይጀመር የተፈጸመ አስመስሎት ሰንብቷል። ለሰላም ውይይት ምንም ዓይነት በር መዘጋት እንደሌለበት ከማመን አንጻር አሁንም ውይይቱ እንዲቀጥል የሁሉም ተስፋ ነው። የመግለጫውን ሙሉ ሐሳብና ዝርዝር ጉዳዩን እንደደረሰልን እናቀርባለን።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on December 10, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

2 Responses to የዕርቀ ሰላም ውይይቱ ተጠናቋል (ደጀ ሰላም)

 1. ኅጎስ

  December 10, 2012 at 9:51 AM

  ማፋርያዋች ናችው,ለላ ችግር እዳይማታ ነው.ሙስሊም ከዘ ቅዳም አሁን ክርስትይን

 2. መላበሉ

  December 10, 2012 at 11:55 AM

  በስማም ወ ወልድ ወመፈስ ቅዱስ
  ፈጣሪ አምላክ ይክበር ይመስገን ለዘላለሙ!!!!
  በመጀመሪያ ደረጃ በቤተክርስቲያን አባቶች መካከል የእርቀ ሰላም ዜናዉን ስሰማ ለቤተክርስቲያናችን እና ለሃገራችን ሰላምና ለህዝባችን ፍቅር ሊመጣነዉ ብዮ ተስፍ አርጌ ነበር። ነገርግን ሃገረ ኢትዮጵያን እያስተዳደርኩና እንዲሁም ሕግ እና ደብን እያስከበርኩ እያከበርኩ ነዉ የሚለዉ ቀጣፊዉ ወያኔ መንግስት እጁን አስገብቶ አባቶችን በራሳችዉ ውሳኔ እና መንገድ እንዳዪሄዱ እያረገ ስለሆነ ከባለፉት ስህተት ምንም አልተማሩም። እኔ ግን ሀገር ቤት ያሉ አባቶች ለእግዚአብሔር ነዉ የሚገዙት ወይስ ለፋሺስት ወያኔዎች ነዉ?አምላክ ግን መንገዱን ግን ከፍቶላቸዉ ነበር።ነገር ግን መልሰዉ ሊዘጉት እየሞከሩት ነው።አትርሱ ወያኔዎች የዛሬ 16 ዓመት ገደማ ባልሳሳት አዲስ አበባ ዉስጥ በሚገኘዉ በዑራኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ ትንቢት እኮ ተነግሮላቹሃል።ትንቢቱም የሃገራችን ጠላቶች ወያኔ እና ሻቢያኖች ይበላላሉ ከዚያም ወያኔ ትቀራለች እሷም ለሁለት ትከፈልና አንዶአ ትቀራለች ።መጨረሻ እርስበእራሱዓ ተበላልታ ትጠፋላቹ ።የኢትዮጲያም ህዝብም አንዲት ጥይት ሳይተኩስባት ብን ብላ ትጠፋለች ። በሃገራችን ዉስጥ ሰላም ፍቅር እና ብልጽግና ይሆናል።ስለዚህ የመለሰ እና የተጋደላይ ፓውሎስ ሞት አስቡት ።እናንተ ወያኔዎች የተከፈተዉን በር ብትዘጉት እንኩአን አምላካችን ግን የበሩን ቁልፍ ለዘላለሙ ሰብሮ ኢትዮጵያን ሊያድናት ተዘጋጅቶአል ። ይቅር ይበላቹ አምላክ!!!!
  ኢትዮጵያ እጆቻን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች
  እግዚአብሄር ለዘላለም ይክበር የመስገን !!!!! አሜን