የዓረና ማእከላዊ ኮሚቴ አባል በዓዲግራት ታሰረ! (አብርሃ ደስታ ከትግራይ እንደዘገበው)

መምህር ፍፁም ግርሙ የተባለ የዓረና ፓርቲ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል ዛሬ በዓዲግራት ከተማ በፖሊስ ታስረዋል። መምህር ፍፁም የታሰረው ባለፉት ሁለት ቀናት በዓረና አባላት ላይ የተፈፀመው ደብዳብ አስተባባሪ የነበረች ትርሓስ የተባለች የህወሓት ካድሬ “እሱ ካልታሰረ ለራሴና ለልጆቼ ደህንነት እሰጋለሁ” የሚል አቤቱታ ለፖሊስ በማሰማቷ ነው።

ትናንት ህወሓት ባደራጃቸው ዱርዬዎች፣ ሲቪል የለበሱ የፖሊስ አባላት፣ የከተማ አስተዳደር ባለስልጣናትና ሰላዮች መደብደባችን ይታወሳል። አቶ አስገደ ገብረስላሴ ሲታሰር ሌሎቻችን ደግሞ በፖሊስ ጣብያ ታግተን አምሽተናል። አቶ አስገደ ሌሊት ከእስር በዋስ ቢለቀቅም ፖሊስ በእሁዱ ስብሰባ ጥበቃ እንደማያደርግልን ስላሳወቀን የጠራነው ስብሰባ ሰርዘን ጉዳዩ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ለማሳወቅ ዛሬ ጠዋት መቀሌ ገብተናል።

የዓዲግራት ተወላጆች የሆኑ አባላቶቻችን ግን ከሌላ ወረዳ በመጡ ቅጥረኞች “ከዓዲግራት ዉጥሉን” እያሉ ወደ ቤታችን ድንጋይ ሲወረዉሩ ዉለዋል። ድንጋይ ወርዋሪዎቹ የዓዲግራት ተወላጆች ሳይሆኑ በህወሓት አማካኝነት ከሌላ አከባቢ የመጡና የአከባቢው ሕብረተሰብ እያሰቃዩ ያሉ ናቸው። ቅጥረኞቹ ደብዳቢዎች ከዓዲግራት ህዝብ ጋር ሲጋጩ ነበር። የህወሓት ማፍያ ቡድን በሰለማዊ ዜጎች ላይ ድንጋይ በመወርወር የአምባገነንነት ሪከርድ ሰብሯል። ከዚህ በፊት አቶ አረጋዊ ገብረዮሃንስ የተባለ የዓረና አባል በባንዳዎቹ የህወሓት ቅጥረኞች መገደሉ ይታወሳል።

የዓዲግራት ህዝብ ላደረገልን መልካም ትብብር እናመሰግናለን።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on January 26, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to የዓረና ማእከላዊ ኮሚቴ አባል በዓዲግራት ታሰረ! (አብርሃ ደስታ ከትግራይ እንደዘገበው)

  1. ታድ

    January 27, 2014 at 1:54 PM

    god bless all ethiopians