የውሃው ይሁዳ – ግጥም

አባይ ስም ነው እንጂ ምን ጠቅሟል ለሀገሩ
ትርፉ ለሌላ ነው ሄዶ መገበሩ

እንዲህ ነበር ከያኒው ያለው
በአንተ ላይ ክሱን ያዜመው
አቤት አባይ አቤት አባይ
 ጥንትም ዛሬ ሁሌም አባይ

ተንኮታኩቶ ላበቃለት
የብዙ ሰው ደም ላለበት
የክፉ ቀን ደራሽ ልትሆን
እድሜ ልትሰጥ ለፈርኦን

ጌዜ መርጠህ ጌዜ ቆርጠህ
ከመልቲዎች ተመሳጥረህ
ፀንቶ ለማይቆም ለሰባራ
እኮ እንዴት አንተ ከዘራ

እንዴት አባይ ለምን አባይ
አንተ የወገን ያገር ሲሳይ
መብትን ባንተ ደስታ ለማሰቀየር
ወገንን እግርከወርች ለማስጠፈር
ነፃነት ተጠምቶ በጥይት የተቆላውን
ፍትህ ይከበር ባለ ሜዳላይ የተደፋውን
ለዲሞክራሲ ብሎ በእስር የማቀቀውን

እኮ ይሄን ሁሉ ረስተህ
ከወገኖችህ ተለይተህ
እልፍ ዓመት የነፈገውን
ያን የሚያጓጓ ጥቅምህን
ዛሬ እንካ የምትለው
ምን መቀበያ እጅ አለው
እንዴት አባይ ለምን አባይ
አንት የወገን የአገር ሲሳይ
አባይ አንተማ ነበርክ እኮ መካሻ
እኮ እንዴት ዛሬ ለማስረሻ
ለብልጥ ተባዮች መታገሻ
እድሜ አራዛሚ ማድረሻ
ከቻልክበትማ እድሜ ማርዘም
ለምሲኪኖች ነበር መቆዘም
በፍሰትህ ቅኔ መወድስ
የወገንህ አንጀት እንዲርስ

የእስከዛሬው ሳያንሰኝ ዳግም አልሳሳትም
ነገሩ ሁሉ ገብቶኛል ስሜን አላበላሽም
ከጥሙ ይረካብኛል እንጂ ወገኔ በኔ አያፍርም

ይልቅስ ብለህ ተነሳ
ወገንህ ቂሙን ቢያነሳ
ዛሬም ለወገን የማይረባ
እኔ አልፈፅምም ደባ
ጌዜዬ ዛሬ አይደለም
በጭራሽ አልገደብም
ይሁዳነቴን እያወቅሁት
እስከዛሬ እንዳቆየሁት

በጭራሽ በፍፁም አልገደብም
ማንም ሰው በኔ አይነግድም
በፍሰትህ ቅኔ መወድስ
የወገንህ አንጀት እንዲርስ
የቃል ያሻራዬን ተወጥቼ
የመንፃት ንስሀዬን ገብቼ
እኔም እንደ ይሁዳ የምሰዋው
አምላክ ነኝ ባዩን ጠቁሜ ነው

ቦንዱም ሀብቱም ይቅርብኝ
ወገኖቼ ይቅር እንዲሉኝ

ነሀሴ 1ቀን 2003
ዶኑ ከላስቬጋስ

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on August 11, 2011. Filed under COMMENTARY. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.