የወያኔ አባል ወጣቶችን ልኮ ያስሞላውን ፎርም ሰበሰበ

TPLF election ploy[PDF]   ከግንቦት 7 ድምጽ ሬዲዮ February 13, 2010 — ወያኔ በቅርቡ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የወያኔ አባል ወጣቶችን ልኮ ያስሞላውን ፎርም መሰብሰቡ ታወቀ። ወጣቶቹ ትናንት ተሰብስበው ያስሞልቱን ፎርም ለወያኔ ባለስልጣናት መልሰዋል። ዘጋቢአችን ከአዲስ አበባ እንደገለጸው ወጣቶቹ ህብረተሰቡን ለማየት ስለከበዳቸው የቤተሰቦቻቸውን ስም እያስሞሉ ለወያኔ ባለስልጣናት አስረክበዋል። ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ወያኔ ከአሁኑ የሚመርጡትንና የማይመርጡትን ሰዎች በመለየት፣ በማይመርጡት ግለሰቦች ላይ የማስፈራራት እርምጃ ለመውሰድ ወይም በረብሻ አነሳሽነት ለመክሰስ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ያደረገው መሆኑ ተገልጿል።የዝግጅት ክፍላችን ወጣቶቹ እንዲያስሞሉ የተሰጣቸውን “የአዲስ አበባ ወጣቶች ፎረም በ2002 ዓም ሀገራዊ ምርጫ የአባላት እና አመራሮች የስራ እንቅስቀሴ መመዘኛ ቅጽ” የሚለውን ቅጽ ያገኘ ሲሆን ፣ በአጠቃላይ ሰባት ጥያቄዎች እንዳሉበት ለማረጋገጥ ችሎአል። የመጀመሪያዎቹ ጥያቄዎች “የአባሉ ስም፣ ያለበት ክፍለ ከተማ፣ ያለበት ቀበሌ፣ በፎረሙ ውስጥ ያለው ሀላፊነት” የሚሉ ሲሆን፣ ከእነዚህ መጠይቆች ስር “ ቢያንስ 10 ሰዎች በመራጭነት እንዲመዘገቡ ማድረግ የሚል ትእዛዝ ተቀምጦበታል።

“የቤተሰቦቹና የዘመዶቹ” በሚለው ጥያቄ ስር ደግሞ ሥራ እና  አድራሻ የተጠቀሰ ሲሆን፣ ከጓደኞቻቸው፣ ከጎረቤታቸው ና ሌሎች ከማውቃቸው አብረውኝ ከተደራጁ አባለት ውስጥ በሚለው መጠይቅ ስር ደግሞ አሁንም  ስምና አድራሻ ተጠቅሷል። በተራ ቁጥር ሶስት ደግሞ “ በሚካሄዱ ስብሰባዎችና በሚካሄዱ ቅስቀሳዎች የሚሳተፉ ሰዎች አድራሻና ስም እንዲጠቀስ ትእዛዝ ይሰጣል። በተራቁጥር አምስት ላይ ደግሞ ወጣቶቹ ምርጫውን ለማደናቀፍ የሚጥሩ ሀይሎችን እንዲያጋልጡ የስለላ ስራ እንዲሰሩ ትእዛዝ የሚሰጥ ሲሆን፣ በተራቁጥር ስድስትና ሰባት ላይ ደግሞ አባላትን ስለማብዛትና እና ከሌሎች የወያኔ አባላት ጋር ተቀናጅተው ስለሚሰሩበት ሁኔታ ያትታል።

ወያኔ ይህን የይስሙላ ምርጫ እውነተኛ ምርጫ ለማስመሰል የማያደርገው ጥረት የሌለ ሲሆን ህዝቡ ግን አሁንም ለወያኔ የምርጫ  ተንኮል  ያለው አመለካከት አለመቀየሩን ለማወቅ ተችሎአል። የአዲስ አበባው ሪፖርተራችን በላከልን ተጨማሪ ዜና ደግሞ ወያኔ የነዋሪዎች ፎረም በሚል ስም የአዲስ አበባን ነዋሪዎች ሰብስቦ በምርጫው እንዲሳተፉለት ተማጽኖ አቅርቧል። ስብሰባዎችን የተሳተፉት ሪፖርተሮቻችን ለማረጋገጥ እንደቻሉት በስብሰባዎች በአብዛኛው የትግራይ ተወላጅ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ካልሆኑ በስተቀር የሌሎች ክልል ህዝቦች በስፋት አልተሳተፉም።

የተለያ  የግንቦት7 ሰዎች የተመዝጋቢውን ሁኔታ ለማረጋገጥ በአብዛኛው የምዝገባ ጣቢያዎች ተገኝተው እንዲመዘገቡ የተደረገ ሲሆን፣ እጅግ በሚገርም ሁኔታ አብዛኞቹ የተሰጣቸው የምዝገባ ቁጥር ከ100 በታች መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሎአል። አባሎቻችን እንደተናገሩት ከአንድ ወር በሁዋላም እንኳ በአዲስ አበባ ያለው የተመዝጋቢው ቁጥር በእያንዳንዱ ቀበሌ ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠር ሲሆን፣ የወያኔ ደጋፊ የሚባሉት እንኳን በነቂስ ወጥተው እስካሁን አለመመዝገባቸውን ለማረጋገጥ ችለዋል። ሁኔታው ከምን የመጣ ሊሆን ይችላል ተብለው ሲጠየቁም “ የወያኔ ደጋፊዎች በየጣቢያው ተገኝተው ለመመዝገብ ህብረተሰቡን ይፈራሉ፣ ሌላው ህዝብም ምርጫ እንዳለም እንኳ በውል የሚያውቅ አይመስልም፣ አውቆ እንዳላወቀ በመሆን ተቃውሞውን እየገለጸ ነው፡ የሚል መልስ ሰጥተዋል።

ወየኔ ቁጥሮችን በማምረት በርካታ የአዲስ አበባ መራጮች ለመምረጥ እንደተመዘገቡ እያደረገ በማስዋራት ህዝቡን ለማደናገርና ለማምታታት እየሞከረ እንደሚገኝ ይታወቃል። ወያኔ ለወጣቶቹ ያሰራጨው ፎርም እዚህ ጋር ይመልከቱ — PDF

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 13, 2010. Filed under NEWS. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.