የኦሮምያ ፕሬዘዳንት እና የኦህዴድ ሊቀመበር አረፉ

(EMF) የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንትና የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ሊቀመንበር አቶ አለማየሁ አቶምሳ አረፉ፡፡ አቶ አለማየሁ በአንድ ወቅት የተመረዘ ምግብ ከበሉ በኋላ ከህመም ማገገም አቅቷቸው… የአልጋ ላይ ቁራኛ ሆነው መሰንበታቸው ይታወሳል:: ባለፈው አቶ መለስ ዜናዊ በሞቱበት ወቅት ጭምር እንደምንም ከአልጋ ተነስተው ለቀብር መገኘታቸውን በዚሁ ኢ.ኤም.ኤፍ ድረ ገጻችን ላይ መዘገባችን የሚታወስ ነው::

አቶ አለማየሁ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት ከሁለት ሳምንት በፊት ሥልጣናቸውን እንዲለቁ ተደርገው ህክምናቸውን በባንኮክ ሲያደርጉ ቆይተዋል:: ይህ በንዲህ እንዳለ… አቶ ዓለማየሁ፣ የካቲት 26 ቀን 2006 ዓ.ም. ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ላይ ይታከሙበት በነበረው ታይላንድ ባንኮክ ከተማ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡

Alemayehu Atomsa

Alemayehu Atomsa


በ2002 ዓ.ም. የኦሕዴድ ሊቀመንበር፣ በዚያው ዓመት ወርሀ ጳጉሜን ላይ የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት አቶ ዓለማየሁ፣ ባጋጠማቸው ሕመም ምክንያት በአገር ውስጥና በውጭ አገር ሕክምና የተከታተሉ ሲሆን፣ ከሁለቱም ሥልጣናቸው በፈቃዳቸው የካቲት 10 ቀን እስከለቀቁ ድረስ ሠርተዋል፡፡

በቀድሞው አጠራር በወለጋ ጠቅላይ ግዛት ቢሎ ቦሼ ወረዳ ከአባታቸው ከአቶ አቶምሳ ሚጃና ከእናታቸው ከወይዘሮ አየለች ብሩ በ1961 ዓ.ም. የተወለዱት አቶ ዓለማየሁ፣
ባለትዳርና የአንድ ወንድና የሁለት ሴቶች ልጆች አባት ነበሩ።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on March 6, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.