የእነ “… ወይም ሞት” ፖለቲካ (ያሬድ ኃይለማሪያም)

ከብራስልስ፣ የካቲት 1፣ 2006

ከ1960ዎቹ የተማሪዎች ንቅናቄ ጀምሮ የአገራችንን ፖለቲካ የተጠናወተው የ“…. ወይም ሞት” አስተሳሰብ ከአስርት አመታት በኋላም አለቅ ብሎን ዛሬም እኔ ከምደግፈው ፓርቲ ወይም የፖለቲካ ቡድን ወይም አስተሳሰብ ውጭ ያለው መንገድ ወይም አማራጭ ሁሉ ገደልና ሞት ነው ብለው የሚያስቡ ፖለቲከኞችና ዓጃቢዎችን ቁጥር በብዙ እጥፍ አባዝቶ ቀጥሏል። በ‘ደርግ ወይም ሞት’ የጀመረው የኼው የተወላገደ እና ጸረ-ዲሞክራቲክ የሆነው አስተሳሰብ ሳንወጣ ዛሬም ‘ወያኔ ወይም ሞት’፣ ‘ግንቦት 7 ወይም ሞት’፣ ‘ኦነግ ወይም ሞት’፣ ‘… ወይም ሞት’ በሚሉ ካድሬዎችና ስሜታዊ የድርጅት አምላኪዎች ተተክቶ እያደናበረን ይገኛል። ለአንድ የፖለቲካ ማኀበረሰብ በዲሞክራሲያዊ ጎዳና ለማቅናትም ሆነ እራሱን ከፍ ወዳለ የሥልጣኔ ባህል ለማደግ ትልቁ መሣሪያ ነጻ አስተሳሰብ እና ግልጽ ውይይት ነው። ባጭሩ በነጻነት የማሰብ (freedom of thought)እና ያሰቡትን በነጻነት የመግለጽ (freedom of expression) በዚያ ማኅበረሰብ ውስጥ በአግባቡ ሲተረጎሙ ነው ያ ማኅበረሰብ ወደ ጤናማ የፖለቲካ ባህል የሚሸጋገረው። ይህ ማለት ግን አንድ ሰው ያሻውን የማሰብ ነጻነት ቢኖረውም ሃሳቡን በተለይም አገራዊና ሕዝባዊ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ አውጥቶ ከሌሎች ጋር ሲወያይ ሊያከብራቸው የሚገቡ የሥነ-ምግባር እና የሕግ ገደቦች አይኖሩም ማለት አይደለም። ለጋራ ጥቅም ተብለው ከተቀመጡት የሕግና የሞራል ወሰኖች መለስ ግን ፍጹም ስልጡን በሆነ መልኩ ሃሳብን ማፍለቅ እና መወያየት የጭዋነት መለኪያ ብቻ ሳይሆን ሊሚናገሩትም ነገር ኃላፊነት የመውሰድን ግዴታንም አብሮ የያዘ የእያንዳንዱ ዜጋ ኃላፊነት ስለሆነ ሰዎች ባደባባይ ወጥተው ያሰቡትን ከመናገራቸው በፊት በቅጡ እንዲያስቡ ያደርጋል። ያለመታደል ሆኖ ከሃገር መሪዎች አንስቶ የፖለቲካ ተሿሚዎች፣ ካድሬዎችና ደጋፊዎች ለዚህ አይነቱ ኃላፊተት ብዙም ሳይጨነቁ ባደባባይ ያሻቸውን ይናገራሉ፣ የዘላብዳሉ፣ ይሳደባሉ፤ የሚጠይቃቸውም የለም።

ብዙ ጊዜ በእንዲህ ያለው ማኅበረስብ ውስጥ ኅብረተሰቡን በማንቃት፤ እንዲሁም ፖለቲከኞችን በማረቅና ለሚናገሩትም ሆነ ለሚሰሩት ነገር ተጠያቂ በማድረግ የፖለቲካው ባቡር ሃዲዱን ስቶ ሕዝቡንም ይዞ ቁልቁል መቀመቅ እንዳይወርድ ትልቁን ድርሻ የሚጫወቱት ነጻ የመገናኛ ብዙሃን እና ገለልተኛና ደፋር የአደባባይ ምሁራን ናቸው። ነጻ ሚዲያ በሌለበት ወይም በተዳከመበት እና የከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና ምሁራን ነጻ ባልሆኑበትና በማይከበሩበት አገር ሁሉ ጨለምተኝነት፣ አክራሪነት፣ ጽንፈኝነት፣ ጎጠኝነት እና አንባገነናዊነት ይነግሳሉ። በእንዲህ አይነቱ ማኅበረሰብ ውስጥ በጠመኝጃ አፈሙዝ ሥልጣን የተቆናጠጠ የወያኔ አይነት አምባገን ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች ትናንሽ አምባገነን ድርጅቶችና ግለሰቦችም እንደ አሸን ይፈላሉ። ምክንያቱም የሚፈሩት ሕዝብ የለማ። ትንሹ አምባገነን ትልቁን፤ ትልቁም ትንሹን ይፈራል እንጂ ሕዝብን አይፈሩም። የሰሉና የተደራጁ ነጻ የመገናኛ መድረኮችና ብቃት ያላቸውና ለሕሊናቸው ያደሩ ጋዜጠኞች ባሉበት አገር አንድ ግለሰብ በሕዝብና በአገር አናት ላይ ቆሞ ያሻውን መናገርና መዘባረቅ ይቅርና ገና የፖለቲካ ጎራውን ሲቀላቀል ከልጅነት እስከ አዋቂነት የሄደበትን ጉዞና የሕይወት ታሪኩን በማጥናት ያ ሰው በሕዝብና በአገር ጉዳይ እጁን የማስገባት ሞራላዊም ሆነ ፖለቲካዊ ብቃት ያለው መሆኑን ሕዝቡ እንዲመዝን ያደርጋሉ። ይህ የፖለቲከኞቻችንን ሥነ-ልቦናዊም መሰረትም ሆነ ምሁራዊ ብቃት እንድናውቅ ከማገዙም ባሻገር የተጠያቂነትንም ባህል ያጎለብታል። በአንድ ወቅት በሕዝብና በአገር ጥቅም ላይ ጉዳት ያደረሰ፣ ወይም በመጥፎ ሥነ-ምግባር ውስጥ ያለፈ፣ ወይም ከቤተሰቡ አንስቶ በሚኖርበት አካባቢ በመልካም ተግባሩ የማይታወቅ ሰው በምንም መንገድ አገራዊ ኃላፊነት እንዳይጣልበት ያደርገዋል። እስኪ ዛሬ አገሪቷን ተቆጣጥረው የኢትዮጵያን ሕዝብ ደም እንባ እያስለቀሱ ካሉት የወያኔ ባለሥልጣናት እና በተቃዋሚ ጎራ ተሰልፈው ካሉት የፖለቲካ ተዋናዮች መካከል ስንቶችን በቅጡ እናውቃቸዋለን? በሁሉም ጎራ ስለተሰለፉት ፖለቲከኞቻችን ያለን መረጃ ምን ያህል ነው? እንዴነ እጅግ ውሱን ነው፤ ስም፣ የትምህርት ድረጃ፣ የፖለቲካ ተሳትፎ፣ የአንዳንዱን እድሜና ጥቂት ነገሮች። የእያንዳንዳቸውን ጀርባ እናጥና ከተባለ ጉዱ ብዙ ነው። በቅርቡ እንኳን ከሟቹ መለስ ዜናዊ እኩል ወይም በተወሰነ ደረጃ ባላፉት ሃያ መታት ውስጥ በኢትዮጵያ ውስጥ የወያኔ አገዛዝ ሥርዓት ለፈጸማቸው አስከፊ የሰብአዊ መብቶች እረገጣዎች በሕግ ተጠያቂ ሊሆኑ የሚገባቸው እንደ እነ አቶ ስዮ አብረሃ (የጦር ሚኒስትር እና የሥርዓቱ ቁልፍ ሰው የነበሩ) አይነት ሰዎች ከወያኔ ጋር ስለጠጣሉ ብቻ በሕግ ይቅርና በፖለቲካ መድረክ እንኳን ያለመጠየቅ ከለላ ተሰጥቷቸውና ወቃሽ ሳያገኙ የዲሞክራሲ ኃይሉ አካል ተደርገው ትግሉን እንዲቀላቀሉ ተደርጓል።

ባጭሩ ያጎለበትነው የፖለቲካ ባህል ቁጥራቸው ቀላል ለማይባሉ እጃቸው በንጹሃን ደም ለጨቀየ፣ በርሃብና በድህነት በሚሰቃየው ሕዝባችን ውድቀት ሞስነው ለጠበደሉ፣ በግል ህይወታቸውም ሆነ በሙያቸው ላልተሳካላቸው አዳዲስ እና ነባር ፖለቲከኞች መደበቂያ ጫካ ሆኗል። በቅርቡ “የፍርሃት ባህልን እያነገሰ ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ” (http://humanrightsinethiopia.wordpress.com/) በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ጽሑፍ ላይ እንደገለጽኩትም የገዢዎቹንም ሆነ የነጻ አውጪዎቹን፤ በጥቅሉ የፖለቲካ መዘውሩ ዙሪያ ያሉ ግለሰቦችን ማንነትና ጀርባ በቅጥ ማወቅ አለመቻል አንዱ ኅብረተሰብን ለፍርሃትና ከፖለቲካ ተሳትፎ እንዲቆጠቡ የሚዳርግ ምክንያት ነው። እነዚህን መሰረታዊ ነገሮች ከግምት በማስገባት ከዋናው ርዕስ ጋር የተያያዙ አንዳንድ ነጥቦችን ላንሳ።

በዚህ ርዕስ እንድጽፍ ምክንያት የሆነኝ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ “በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ፤ የወያኔ ሳያንስ የነፃ አውጪዎቻችን (የግንቦት 7) የግፍ ተግባር እና የመገናኛ ብዙሃን ዝምታ” በሚል ርዕስ ከአንባቢዎች የተሰነዘሩ አስተያየቶች ናቸው። ሦስት አይነት ነቀፌታ አዘል አስተያየቶች ጽሑፌን አትመው ባወጡ ድኅረ-ገጾችና በማኅበረሰብ የመወያያ መድረኮች ላይ ተነበዋል። ለእያንዳንዱ አስተያየት ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ለኔም አመቺ ሆኖ ስላገኘሁት በሦስቱ ጎራ ላሉት አስተያየቶች ምላሽ ልስጥ። የመጀመሪያው አስተያየት ባነሳሁት ፍሬ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ሳይሆን ብስጭትና ንዴት በተቀላቀለበት ስሜት ዝልፊያና ‘ዋናው የአገር ጠላት ወያኔ እያለ እንዴት ግንቦት 7ን ትተቻለ’፣ ግንቦት 7ን የነቀፈ ሁሉ ‘ወያኔ’ ነው፣ ተቃዋሚዎችን መተቸት ‘ትግሉን’ ያዳክማል፣ ተቃዋሚዎች ከነሃጢያታቸው መደገፍ ብቻ ነው ያለባቸው፣ ገፋ ብሎም ወንጀልም ቢሰሩ እንኳን ሊጠየቁ አይገባም ወያኔን እስከታገሉልን ድረስ የሚሉ ሃሳቦች የታጨቁበት ነው። እውነት ለመናገር ከእንደነዚህ አይነት ግራ ከተጋቡ ሰዎች ጋር ለመወያየት ያስቸግራል። ስለፖለቲካም ያላቸው ግንዛቤ ጥያቄ ውስጥ ይወድቃል። ከዚህ በፊት በሌሎች ጽሑፎቼም እንዳልኩት እነኚህ ሰዎች ገሚሱ በቅን ልቦና ለውጥን ብቻ ከመናፈቅ፣ ገሚሱም አዕምሯቸው በቂምና በበቀል ስሜት ተወጥሮ ፖለቲካውን መሳሪያ ያደረጉ፣ ገሚሶቹም ስለ ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ባህል ያላቸው ግንዛቤ ውሱን ወይም የተዛባ በመሆኑ መፈክራቸው ሁሉ ‘ግንቦት 7 ወይም ሞት’፣ ‘ኢሳት ወይም ሞት’፣ ወዘተ የሚል ነው። እነዚህ ሰዎች አዕምሮዋቸውን ከፈት አድርገው በፃነት እንዲያስቡ እና ከካድሬነትና ጭፍን ድጋፍ ወደ ሰላና በእውቀት ላይ ወደተመሰረተ የፖለቲካ ደጋፊነት እራሳቸውን እንዲያሳድጉ እመክራለሁ።

ሁለተኛው አስተያየት ሰጪዎች “ከግንቦት 7 ወይም ሞት’ የወጡ ቢሆንም አሁንም በተነሳው ፍሬ ነገር ላይ ያተኮሩ ሳይሆኑ በጸሃፊው (በእኔ) ማንነትና በአስረጂነት በጽሁፌ ላይ ባጣቀስኩት ድኅረ-ገጽ ባለቤቶች ማንነት ላይ ያተኮሩ ናቸው። ይህም አስተያየት ቢሆን ያው ‘ፍሬውን ትቶ ገለባውን’ የመውቀጥና ከአስተሳሰብ መዛነፍ የመነጨ ነው። ገሚሶቹ ድብቅ ተልዕኮ ከሌለህ ግንቦት 7ን በአደባባይ መተቸት አልነበረብህም፣ ችግሩ ተከስቶም ቢሆን ባደባባይ ሳይሆን ውስጥ ለውስጥ ነው ጉዳዩን መግለጽ ያለብህ የሚል ነው (ወያኔ እንዳይሰማ መሆኑ ነው)። ሌሎቹ ደግሞ ‘የወያኔ’ መልዕክተኛ ነህ በሚል ፈርጀውኛል። እኔን ብቻ ሳይሆን የመረጃው ምንጭ ተደርገው የተጠቀሱትንም አካላት ወያኔዎች ናቸው ብለው ደምድመዋል። ለነገሩ እንዲህ ያለው ፍረጃ በተሰነካከለው የፖለቲካ ባህላችን ውስጥ ትችቶችን ለማፈን፤ ለማስቆምና የሰላ ትችት የሚሰነዝሩ ሰዎችን ዝም ለማስባል እንደ ስልት ገዢው ወያኔም ሆነ አንዳንድ ተቃዋሚዎች የሚጠቀሙበት ስልት ስለሆነ አያስገርምም። በፖለቲካችንም ውስጥ ይህ አካሄድ የቆየ እድሜ አለው። ይሁንና እኔንም ዝም አያሰኘኝም፤ እውነታውንም የመሸፈንም ሆን የመቀየር አቅም የለውም። እውነት ደግሞ ጊዜን እየጠበቀች የምትፈካና ከተገለጠችበት የምትወጣበት አንዳች ተፈጥሯዊ ኃይል ያላት ስለሆነች እንዲህ ያሉ ፍረጃም ሆነ ማደናገሪያ ጭርሱኑ አያጠፏትም። ይልቅ እንደ ሰለጠነ ማኅበረሰብ ችግሩን መመርመረሃ ምፍትሄ መሻት ይበጃል፤ ለአገርም ለድርጅቶቹም ቢሆን።

ሦስተኛው አስተያየት ኃላፊነት ከሚሰማቸውና የጉዳዩን ክብደት በቅጡ ከተረዱ ወገኖች የተሰነዘረ ነው። ይህውም ጉዳዩ የሰብአዊ መብትን የሚለለከት ስለሆነ በተበዳዮቹ ላይ ደረሱ ለተባሉት ጥቃቶች በቂ ማስረጃ አለህ ወይ? የሚል ነው። በመጀመሪያ እንኳን ለፍትሕ፣ ለዲሞክራሲና ለነጻነት እንታገላለን ያሉትን የፖለቲካ ኃይሎች ይቅርና አለም በሰብአዊ መብቶች እረጋጭነት ያወቀወን አንባገነናዊ የወያኔ ሥርዓት ለመተቸትም ሆነ ለመንቀፍ የሁል ጊዜ መነሻዬ ማስረጃዎች ናቸው። እንደ አንድ የሰብአዊ መብት ተሟጋች መረጃና ማስረጃዎች ያላቸውን ልዩነትም ሆነ ጠቀሜታ ጠንቅቄ ስለማውቅ ያለመረጃም ሆን ያለ ማስረጃ ማንንም ባደባባይ ለመውቀስም ሆነ ለመተቸት አልደፍርም። በተነሳው ጉዳይ ላይም በቂ ብቻ ሳይሆን ከበቂ በላይም ማስረጃዎችን መዘርዘር ይቻላል።

ጽሑፌን ለመደምደም በመጀመሪያ ወደ እዚህ ውይይት ያመራንን ጽሑፍ በማተም የጋዜጠኝነትና የመረጃ መድረክነታችውን ባግባቡ ለተወጣችሁ ድኅረ-ገጾችና የመወያያ መድረኮች ምስጋናዬ የላቀ ነው። የኔን ጽሑፍ በማስተናገዳችሁ የተነሳ ‘ወያኔ’ ተብላቸሁ የተሰደባችሁም ለእውነት መቆም የሚያስከፍለውን ዋጋ ነው እና እየከፈላችው ያላችሁት ግፉበት። ጽሑፌን አሉ ለተባሉት ድኅረ-ገጾች ሁሉ ነው የላኩት፤ መልእክቱም የደረሳቸው መሆኑን ከራሳቸው በተላከ ኢሜል አረጋግጫለሁ ይሁንና በሥራ ብዛት ይሁን በሌላ ያላስተናገዳችሁንት ወደፊት እንደምታትሙት እየጠበኩኝ የፍረጃ ፖለቲካውን ፈርታችሁ ወይም እናንተም የ’… ወይም ሞት’ የፖለቲካ አዙሪት ውስጥ ገብታችሁ አቋም ለያዛችሁትም ሁሉ እግዚያብሄር ለእውነት የምትቆሙበትን ልቦና እና መንፈሳዊ ወኔ ይስጣቸሁ በሚል ልሰናበት።

እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል።

በቸር እንሰንብት።

www.humanrightsinethiopia.wordpress.com

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 8, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

8 Responses to የእነ “… ወይም ሞት” ፖለቲካ (ያሬድ ኃይለማሪያም)

 1. Ancient Ethiopia

  February 8, 2014 at 6:35 PM

  yared, lemayawukesh tagni belual. we know you very well. you are like water that no one can catch you.the time will come when each and every individual will be accountable his or her single word.
  ethiopians have more than enough about you from day one untill now, no wonder if you defend TPLf at this crucial time to safe that terrorists group because TPLF assigned you and others to help it as this time.
  your divisble weyane’s work disaarayed ethiopians from their belgium community because some self appointed civil activists have used the community as their own personal propery and the means to milk belgium’s government.
  g7 has no time to respond for such a useless accusation from the useless and workless man.your stand was clear long ago when you defended TPLF for it’s genocidials crimes in different parts of ethiopia and accused of innocents as the cause of the genocide. that file will come out one day when the time ripes untill that time you can get any article from TPLF’s camp , sell your name and psot it. you can work day and night, but you can not safe TPLF any more because real lions are in the ground action from ethiopia’s soil, not from europe. if you are man, you could not run from ethiopa to europe, you could join ethiopia’s jungle and became the threat to TPLF.we know TPLF has planted so many odd individuals in different places and sent to the westren world to ack as refuggees like dawit kebede from journalists, like gashaw from ” politicians”. all dogs from different directions try to spray their bullets against the nightnare of TPLF like ESAT and g7, but you can not safe. TPLF know very well no single hidden agent will safe TPLF.

 2. Abegaz

  February 8, 2014 at 7:35 PM

  Yared,

  I think you confuse yourself deliberately.

  1) You yourself put G7D as your source of information. We know G7D works closely with Aiga and Awrambatimes, both operatives of TPLF.

  2)There is no such thing human right issue for every little things in gorilla fighting business. If you are a member of a gorilla team, you got to respect the charter. All liberation movements including TPLF have passed through this process. You would have brought TPLF to justice for what it did in 17 years fighting. Have you seen TPLF being accused for that? You writings are rubbish. You simply wanted to discredit Ginbot 7 and get a reward from TPLF. We know you are in distress in exile and want pardon from TPLF to go back to Ethiopia like Dawit.

  3) You know how the 1981 coup in Ethiopia failed? The organizers wanted it to be free of any causality. That failure resulted in far worst results we see then and today. You try to avoid little things and burden us with a mountain of problems. You are worried about some one in Sudan for unconfirmed reasons and forgot the day to day suffering of our people.

  4) Why don’t you form an model gorilla group and liberate your people in a manner you wanted? You may be treated well in history books as the first man of this task. As far as I know every gorilla teams have some problems.

  5)The people behind G7 are respected people. I do not think anybody will suffer beyond punishments per the charters of military engagements. That is normal even for government forces.

  7) Also understand the difference between G7 and G7 Popular Force. Do you really know that? Your criticism should be to that force, if at all.

 3. andnet berhane

  February 8, 2014 at 7:38 PM

  አቶ ያሬድ ኃይለማርያም ያስቀመጥካቸው ዝርዝር የህብረተሰባችን ነጻ የፖለቲካ ተሳትፎ በግልጽና በመድረክ ለመወያየት የሚያስችለው ልምድ የራሱንም ግንዛቤ የለውም ይህ የሚታወቅ ነው ሆኖም ሁሉም በስሜት የሚጓዝ ሳይሆን በደረጃ እንዳስቀመጥካቸው አይነት ልመሆኑ አይታበልም:
  አሁንም ይህን አስረጅ ካለ እንደ ዜጋ የሚመለከተን በመሆኑ የግንቦት ሰባት አመራሮች ወም የኤሪትራ መንግስት በዓልም ሕብረተሰብ ደንብና መመርያ መጠየቅ ያስችላል: በምንም መልኩ በወገኖቻችን የሚደርሰው ኢስባዊ ድርጊት ሁላችንም የምናምንበትና የምናቃውመው በመሆኑ ጉዳዩን አጥቂዎቹ ወደፍርድ ለሕግ እንዲቀርቡ መደረግ ይኖርበታል:
  እርግጥ እሕብረተሳችን አንድን ወገን ካመነ ተቃውሞ የሚባል የመጠየቅ ልምድም ብቃትም የለውም ይህም በፖለቲካ ላይ ሳይሆን በማንኛውም የህብረተሰቡ ስብስብ የሚታይ ደካማ ራስን አለማመን በስልጣን ይሁን በኑሮ የተሻለ ውይም ሙሁር ከተባለ ማሸርጎድና የሚለው ሁሉ እውነት ብሎ ይከተላል እነኝህን ግለሰቦች የሚጠይቅና የሚቃወም ካለ አፍረሽ እንድሚባል እያየነው ያለ በመሆኑ: መልካምና አስተማሪ የሆነውን ጽሑፍህን ግፋበት: እንዲሁም የራሳችሁን ውሳነእ የሰጣችሁ ወገኖች ጉዳዩን በጥሞና በማየት ያለውን እውነተኛ የተፈጸመ ተግባር ለማየት ትግስት አድርጉ:

 4. Abegaz

  February 9, 2014 at 12:22 AM

  It is a pity EMF entertaining this shoddy human right activist.

  For all intention and purpose one can go into Ginbot 7D website (indicated below this comment) and make personal judgment. Ginbot 7D is obsessed denouncing ESAT, Ginbot 7 and other progressive forces. ESAT for example is listened by 31 million Ethiopian people. Does this new outlet deserve hate propaganda? Absolutely not. Ginbot 7D ha no accomplishments to speak of. It has no credible leaders of known personality. Why is it obsessed bringing down freedom fighters like G7 and ESAT? I suspect it is in collision with TPLF. Here comes Yared Hailemariam showing solidarity with Ginbot 7D and in doing so helping TPLF. Lets wait for his reward.

  G7D even went as far as making contacts with Ginbot 7 popular force freedom fighters in Eritrea illegally. A gorilla fighter making contacts with an outsider body out of command line is automatically consider illegal and criminal according to military rules, and is severely punishable act. Yet, here comes the shoddy human right activist, Yared in crocodile tears about G7D and TPLF spies.

  Let us not forget that G7 leaders are people who could get a great personal gain should they elect to serve woyanies. These are people who did not choose to dance with TPLF,rather wanted to see Ethiopian people exercise their God given freedom. That is how we evaluate G7 people.

  We have insider information that the Ethiopian security apparatus has strategized media war against inside and outside prominent oppositions. Yared’s attempt is one little part of that grand plan. No amount of fake accusation by people like Yared can discourage G7 and ESAT from exercising their duties.

  http://www.ginbot7d.org/

 5. ሳተናው

  February 9, 2014 at 1:27 AM

  እ የደላው ሙቅ ያኝካል አሉ:: እኛ መሰረታዊ ነጻነት አሮብን ለነጻነት ስንታገል ያሬድና መሰሎቹ ዲሞክራሲ. ኣሁኑኑ እያሉ ሙቅ ያኝካሉ:: ዳቦ ያጣ ረሃብተኛ ኬክ ካልሰጣችሁኝ ብሎ ሲነዘንዝ ማለት ነው:: እስኪ ግንቦት 7ንም ሆነ ኢሳትን ከማሳደድ በፊት ወያኔን እናስውግድና መጀመሪያ ነጻ እንውጣ:: ከዚያ በኋላ ግንቦት 7ንም ሆነ ኢሳት ላይ እንዘምታለን::

  የቅራኔዎችን ደረጃና የአፈታታቸው ሳይንሳዊ አካሄድ ሳይገባን ፖለቲካ ውስጥ መፈትፈት አግባብ አይደለም:: መጻፍ ወይም መናገር እችላለሁ ብሎ የማያውቁት ነገር ውስጥ ዘው ብሎ መግባትና መዘላበድ የጠላት መሳሪያ መሆን ነው::

  Priorities of contradictions and their dialectical resolution የሚባለውን መሰረታዊ የፖለቲካ ሃሁ ስይረዱ ስለፖለቲካ መጻፍና ማውራት እንድ ህጻን ለጅ ውሃ ውስጥ ገብቶ እንደሚንቦራጭቀው ማለት ነው:: ለህጻኑ ግን ዋና የዋኘ መስሎት ልቡ ጠፍቷል::

  የያሬድ ሌላው ደካማ ጎኑ ደግሞ ሰለ ራሱ አስትያየት ያለው ጭፍንና ሙሉ ለሙሉ እርግጠኛ የሆነ አመለካከት ነው::እኔ ብቻ ሃቀኛ እኔ ብቻ እውነተኛ ነኝ የሚለው:: ለሚከሰው ኢሳት ትንሽ እንኳን ክሬዲት አይሰጥም:: እስከአሁን በኢትዮጵያ ላይ እንደተፈራረቁባት አምባገነኖች ከኔ ወዲያ እውነተኛ ለአሳር ነው አለን:: የራስ የራስ ይጣፍጣል ፈስ ሆነ የያሬድ ነገር::

 6. ዘገየ

  February 16, 2014 at 6:40 PM

  ቀስ በል ያሬድ
  መረጃ ካለህ አሁንም ማቅረብ አልቻልክም:: በተነሳው ጉዳይ ላይም በቂ ብቻ ሳይሆን ከበቂ በላይም ማስረጃዎችን መዘርዘር ይቻላል። ካልክ የታለ
  ሌላው ቢቀር ዘገባህን ሚዛናዊ ለማድረግ ከስልጠና የወጣውን የልጁን ወሬ ከ G7D / ‘ዲሞክራቲክ’ ወያኔው ሰምተህ እንደወሰከትክ ሁሉ ጉዳዩ በጣም የሚመለከታቸውን የግንቦት ሰባት መሪዎች ጠይቀህ ዛሬም አልቀረብክም
  ለመሆኑ የትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ አካሄዶችን አሉታዊና አዎንታዊ ታክቲኮች ሁሉ መልስ መስጠት ይገባል እንዴ?
  ማፈሪያ ነህ

 7. getachew gere

  March 8, 2014 at 3:37 AM

  በሰነዘርከው አጠቃላይ አስተያየት ከየትኛው የአስተሳሰብ ነፃነት እንደተነሳህ ለመገመት ቀላል ያደርጓል ያሬድ፡፡ በ60ዎቹ የነበረው የነፃነት ትግል እንዲሁ አንተ እንደፃፍከው የተወላገደ አስተሳሰብ ያዘለ ሳይሆን ቁርጠኝነትን፣ ጠንካራ ዓላማን እና የህዝቦች ችግርን በመለየት ወደ ትግል የገሰገሰ ሓይል ነው የነበረው፡፡ ይህ ደግሞ ትክክለኛና ሚዘናዊ ከሆኑ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ከፃፏቸው በርካታ መፃህፍቶች በሰፊው ለመረዳት ችለናል፡፡

  • getachew gere

   April 2, 2015 at 2:56 AM

   አያ ያሬደ ዘባረቂ እንዳንልዎት ኢትዮጵያዊ ባህል አይደለም እንደ አንተ ግን የሚመጠንህ ቃል ይመሰለኛል ወያነ አገሩን ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሸጋገር በትጋት ያለ እንጂ ወያነ ወይ ሞት ተብሎ የሚገለፅ አይደለም