የእስር ቤት ግድግዳዎች

የሰው ልጅ ጠላቱ የገዛ ከንቱ ምኞቱ ነው፡፡ አንዳነድ ጊዜ ፍላጎታችን ወደ ምኞት ሲያዘነብል ያለው አደጋ አይታየንም፡፡ መጠን ያጣ ምኞት ደግሞ ሁሌም ቢሆን ከውድቀት በሰተቀር ሌላ የሚፈይደልን ምነም ዓይነት ነገር የለም፡፡ ከፉ ምኞት ወንጀለኛ ያደርጋል ወንጀል ደግሞ በወዳጅ ላይ አልያም በሌልም ሰው ላይ የሚፈጠር ድርጊት ነው፡፡

በጠላትነት የሚፈጠር ማንኛውም ድረጊት ደግሞ ውጤቱ ውርደት ነው፡፡ ወንጀል በአንድም በሌላም መልኩ ሊፈጸም ይችላል፡፡ ወንጀለኛ ደግሞ የሚቀጣበት ሕግ በመኖሩ ምክኒያት ማንም ቢሆን ከወንጀል ነጻ ሆኖ መኖር አይችልም፡፡ እስር ቤትን በአንድም በሌላም አጋጣሚ የማይት እድሉ እንዲኖርህ ምንም ዓይነት ምክር አልሰጥም፡፡

ነገር ግን በአንድ አጋጣሚ ወደ እስር ቤት ወረጄ ያየሁትን ነገር ላጫውታችሁ፡፡ በእርግጥ በጣም ከባድና ሞራልን ሁሉ የሚያደቅና ስሜትን የሚጎዳ ቦታ ቢኖር እንደ እስር ቤት ያለ ቦታ ይኖራል ብዬ አላስብም፡፡ እናላችሁ ወደ እስራት በወረድኩ ጊዜ በጣም ነበር የከፋኝ እንዲሁም ሆድ የባሰኝ፡፡ በመጀመሪያ ስገባ በእስር ቤት ውስጥ የነበሩት ታሳሪዎች ሁሉ ማንንም ታሳሪ በደማቅ አቀባበል አይቀበሉም፡፡ የደንቡን በሚባል የሰላምታ አይሉት የልመና ግራ በሚያጋባ ሁኔታ ብር እንደትሰጥ ትጠየቃለህ፡፡ በእርግጥ ካለህ ትሰጣለህ ከሌለህ ግን አትገደድም፡፡

ወገኖች እንደ እስር ቤት ያለ ታላቅ የሚስጥርና የወግ ቦታ የትም አይገኝም፡፡ በእኛ አገር ማንኛውም ወንጀለኛ ወንጀሉን ለማሳመን ምንም ዓይነት የስነ ልቦና እርዳታ አይደረግለትም በመርማሪውና በተረኛው ፖሊስ አሳሩንና የተወለደበትን ቀን እሰኪረግም ድረስ ይደበደባል፡፡ በጣም የሚገርመው ነገር እዚህ ላይ ነው እኔ በታሰርኩበት ወቅት አንድ ሰውነቱ በዱላ ብዛት የተላላጠ እስረኛ ነበር፡፡ እንዲሁም እኔ በገባው ማግስት አንድ እስረኛ እያነከሰ ሲገባ ተመለከትኩኝ ምን አድርገህ ነው ሲባል ለፖሊሶቹ ያ ሁሉ ዱላ ሲወርድበት ያላመነውን ለኛ በነጻነት ተረከልን፡፡ በኋላ አመንክ ታዲያ ሲባል እንዴት ነው የማምነው አለን፡፡ ወይ ጉድ አንዲህም ዓይነት ነገር አል እንዴ ያስብላል፡፡
እውነት ተናጋሪዎች ሁሉ ያሉት እስር ቤት ውስጥ እንኪመስል ድረስ እስረኛው ሁሉ የሚናገርው በጣም የሚገርም ነገር ነው፡፡ መርማሪ ፊትና ደብዳቢው ፊት ያልታመነ በደል ሁሉ ለእስረኛው ይተረክለታል፡፡ እኔ ግን አንድ ነገር ደስ አለኝ በታሰርኩበት ወቅት የነበሩ እስረኞች ወንጌልን እንድነግራቸው የጠየቁኝ ነገር በጣም አስደስቶኛል በሚገርም ሁኔታ ፈጣሪ ከእኔ ጋር በመሆኑ ታላቅ ነገር ተሰራ፡፡ ሌላውና አስገራሚው ቁም ነገር በእስር ቤት ግድግዳዎች ላይ ተጽፈው ያነበብኳቸው ነገሮች ናቸው፡፡ ይህንን ላካፍላችሁ እስቲ በእውነት የሚያጽናኑና የሚያዝናኑም ነበሩ

1….‹‹በሕግ ፊት ጉልበት ያለው ገንዘብ ብቻ ነው››
2….‹‹ኦ አምላኬ ሰው አድርገኝና ሰውን ይግረመው››
3….‹‹ወንድ ልጅ እግር እንጂ አገር የለውም››
4….‹‹አንድ ፍየል ነበር እንደኔ የከፋው የሆዴን ብነግረው የአፉን ቅጠል ተፋው››
5….‹‹የቀን እንጂ የሰው ጀግና የለም››
6….‹‹ታሰረክ ማለት ሞትክ ማለት አይደለም ለጊዜው ከምትሰራው ከፉ ነገር ለጥቂት ጊዜ አረፍክ ማለት ነው፡ አንጂ አበቃልህ ማለት አይደለም፡፡ ከዚህ ስትወጣ ሕይወትህም ሌላውም ነገር እንዳለ ይጠብቅሀል››

በጣም ሚገርሙ ነገሮች አሉ እስኪ ለአሁኑ ይህቺን ታህል ካወራን ይበቃናል
ፈጣሪ እስረኞችን በኃይሉ ያውጣልን፡፡
አሜን ኦ አሜን ለይኩን ለይኩን

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on November 28, 2010. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.